5 months ago
🌼 እንኳን ለ"ቲካሻ-ቤንጊ" (የሸኮ ብሔረሰብ የምስጋና በዓል) በሰላም አደረሳችሁ! 🌼
"Dacha íti Tikasha Bengikn Zhazha Sakuke!"
#ethiopia | "ቲካሻ-ቤንጊ" በሸኮ ብሔረሰብ ዘንድ "የምስጋና ዓመት" ማለት ሲሆን፤ ፈጣሪ ለሰው ልጆች የሰጠውን ቸርነትና በረከት የሚመሰገንበት ታላቅ የቱባ ባህል መገለጫ ዕለት ነው።
በዓሉ ለምን ይከበራል?
🌾 የተዘራው እህል በተፈጥሮ አደጋ እና በተባይ ሳይበላሽ ለምርት በመብቃቱ፣
🕊️ በሀገር ላይ ሰላምና ጤና በመስፈኑ፣
🍯 ቀፎው ማር በማስገኘቱ ለፈጣሪ ምስጋና ለማቅረብ ነው።
የበዓሉ ልዩ ክዋኔዎች፡
የምርት ጥምጣም:
ከአዲሱ እህል የተዘጋጁ ምግቦች በቅድሚያ በባላባቶች ከተቀመሱ በኋላ ለህዝቡ ይዳረሳሉ።
የዘር ምርቃት: የሀገር ሽማግሌዎች እና ባላባቶች ለቀጣይ ዓመት የሚሆን የእርሻ ዘር ተቀብለው ይመርቃሉ።
የጥጋብ በዓል: ቲካሻ ቤንጊ ከሃይማኖታዊው "ሚያንጉ" ስርዓት በተለየ መልኩ በአደባባይ በደስታ፣ በጭፈራ እና በፌሽታ የሚከበር የጥጋብ በዓል ነው።
ይህ በዓል የሸኮ ህዝብ ለተፈጥሮ ህግጋት ያለውን ጥልቅ ግንዛቤ እና ስነ-ምግባር የሚያሳይ ነው።
እንኳን ለ3ኛው "ቲካሻ-ቤንጊ" በዓል አደረሳችሁ!
ሙባረክ አበበ
#sheko #tikashabengi #culture #thanksgiving #ethiopia #harvestfestival #southwestethiopia

🌼 Hacamuc Begn Digam Nu Hatsmake!
(የዓመት ሰው ይበለን!)
#ethiopia | ታላቁ የቤንች ህዝብ በዓል - "ቢስት ባር"
ግራዋ (ዣምፕ)፣ አደይ አበባ፣ ጉብስቱ እና አዳል ኡሽክን ሲያብቡ፤ በቆሎ፣ ማሽላ፣ ጤፍ እና የግራዋ ማር ሲደርስ የሚከበረው ታላቁ የቤንች ህዝብ የምስጋና በዓል!
የ"ቢስት ባር" ገጽታዎች፡-
✅ ምስጋና:
የቤንች መሪዎች (ቲያትንድ) እና ህዝቡ አዲሱን ምርት ቀምሰው "Mv xsal saxs" በማለት ፈጣሪያቸውን በአደባባይ የሚያመሰግኑበት ነው።
✅ አንድነት:
ሀብታም ድሃ ሳይል ሁሉም በአንድ ላይ በነገሥታቱ ደጃፍ (ፖርት) ተሰብስቦ የሚጋራው ማዕድ ነው።
✅ በረከት:
ታላላቅ አባቶች መርቀው ለቀጣዩ ዘመን አዲስ የሥራ መንፈስ እንዲኖር አዋጅ ያውጁበታል።
ይህንን ታሪካዊ በዓል ከረዳት ፕሮፌሰር ዘመድኩን እና ከአንጋፋው ጋዜጠኛ ዘረዓይ ያቆብ ጋር በመሆን መታዘብ መቻሌ ልዩ ደስታን ፈጥሮብኛል።
ቢስት ባሪ ዲርት ባር ~ ፔትማኬ!
(እንኳን አደረሳችሁ!)
ጌታመሳይ ሙሉጌታ
#benchpeople #bistbar #culture #ethiopia #harvestfestival #thanksgiving #tradition

🎉 ጭጋጉ ተገፏል፤ ብራው ወጥቷል! እንኳን ለ"ቢስት ባር" በዓል አደረሳችሁ! 🎉
#ethiopia | ታላቁ የቤንች ብሔር የማንነት መገለጫ የሆነው የ “ቢስት ባር” በዓል የሰላም፣ የፍቅርና የበረከት እንዲሆንላችሁ ከልቤ እመኛለሁ!
🌼 ቢስት ባር ምንድን ነው?
ይህ በዓል ተፈጥሮ አዲስ ልብስ ለብሳ፣ ጭጋጉ ተገፎና ብራው ወጥቶ የሚከበር የድልና የምስጋና በዓል ነው። የክረምቱ ዳመና በብሩህ ፀሐይ ሲተካ፤ የቤንች ምድር በአረንጓዴ ምንጣፍ አጊጣ አዲሱን ዘመን ትቀበላለች።
በዚህች ታሪካዊ ዕለት፣ ጀግናውና ኩሩው የቤንች ሕዝብ የቤንችቴት፣ የሜሪቴት እና የሼይቴት አብራክ ክፋዮች ባህላቸውን አንግበው፣ በማንነታቸውን ደምቀው ያከብሩታል።
🌾 የላብና የጥረት በዓል
ቢስት ባር ዝም ብሎ በዓል አይደለም፤ የጥረት ውጤት፣ የላብ መፍሰስና የአዝመራ መሳካት በዓል ነው።
"ከድካሙና ከላቡ ውጭ ያልዘራውንና የጥረት ወጤቱን ያልሆነውን የሚበላ በቤንቾች ዘንድ እንደተረገመ ይቆጠራል።"
ስለዚህ አርሶ አደሩ ድካሙን በአንድነት የሚያጣጥምበት፣ እህሉን ሰብስቦ “የበኩሩን” ለፈጣሪና ለታላላቆች የሚያቀርብበት የምስጋና በዓል ነው።
👴🏽 የትውልድ ቅብብሎሽ
በማንነቱ እና በክብሩ የማይደራደረው የቤንች ሕዝብ፣ ይህንን በዓል ሲያከብር የታላላቆችን ምርቃት በመቀበል ነው።
የወጣቱ ጉልበት ከሽማግሌዎች ጥበብ ጋር የሚገናኝበት፣ ታሪክ ለትውልድ የሚተላለፍበት፣ የሰላም እና የአንድነት ቃል ኪዳን የሚታደስበት ልዩ በዓልም ነው።
አዲሱ ዓመት "ቢስት ባር" ለሁላችንም የደስታና የሰላም ይሁንልን!
✍️ ጌታቸው ባይባ (ሚዛን አማን)
#bistbar #benchpeople #newyear #harvestfestival #ethiopianculture #mizanaman #gratitude

Sponsored by
Surafel