Logo
Getu Temesgen
⚫ የዑራኤል ልጆች እንባ! 💔
#ethiopia | ​"ነፂ... ዛሬ ቤተሰቦችህን ከበን ተቀምጠናል፤ አንተ ግን የለህም!"

​እኛ የልጅነት ጓደኞችህ፣ አብሮ አደጎችህ... መላው የዑራኤል ልጆች ዛሬ ቤትህ ተገኝተን ሀዘናችንን እየገለጽን ነው። ግን ነፂ... ቤትህ ባዶ መሰለን!

​አንተ ለኛ የዑራኤል አካባቢ ሠንደቃችን፣ ምልክታችን እና አብሮ አደግ መጠሪያችንም ጭምር ነበርክ። ዛሬ በመኖሪያ ቤትህ ተሰብስበን ስናየው፤ ያ አንተ የዋህ፣ ደግና ምሥኪን ወንድማችን ከፈጣሪ ፈቃድ ተገኝቶ የሞተን በለቅሶ መመለሥ ቢቻል ኖሮ ዛሬውኑ በተነሣህ ነበር፤ ግና አይሆንም!

​ነፂ... ሀዘናችን የፀና ነው! ልባችን በሀዘን ተሠብሯል። ደግ ነበርክና ሰይፈ ዑራኤል ነፍሥህን በደጋጎቹ አጠገብ ያኑርልን።
​አንረሳህም! ደህና ሁን ወንድማችን! 🕯️

​ከሀዘን ቤት፡- መላው የዑራኤል አካባቢ አብሮ አደግ ወንድሞችህ

***
ከጠዋቱ 1:30 አስከሬን ከቤት ይወጣል
ከጠዋቱ 2:30 አሰከሬኑ መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይደረሳል

​#rip #netsanetworkneh #urael #childhoodfriends #tribute #addisababa

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.