" እገዳዎች እንዲነሱ ተወስኗል" - የዳሰነች ዘረዳ አስተዳደር
በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ አካባቢ በነበረው የማርበርግ ቫይረስ ስርጭት ስጋት ምክንያት በትምህርት ቤቶች፣ የሕዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት አገልግሎትና ሌሎችም ሕዝብ የሚሰበሰብባቸዉ ኩነቶች ላይ ተጥሎ የነበረው በከፊል እንደተነሳ የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ኡመር ኖኩዌ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቀዋል።
በዚሁ መሰረት ፦
- በትምህርት ቤቶች የተማሪዎችን ቁጥር በመቀነስ በፈረቃ ወይንም በማሸጋሸግ እንዲሁም የመከላከያ ዘዴዎችን በማስጠቀም የመማር ማስተማር ስራዉ እንዲቀጥል፤
- የህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት ባለንብረቶች ከመቼውም ጊዜ በላይ የተሽከርካሪዎችን ንፅህና በሳንታይዘር በመጠበቅ በወንበር ቁጥር ልክ ብቻ እንዲያሳፍሩ፤
- ባለ ሶስት እግር ባጃጆች ከሹፌሩ ውጪ ከሁለት ሰው በላይ መጫን እንደይችሉ፤
- DStv የስፖርት ማዘወትሪያ ስፍራዎች ተጠቃሚዎችን አራርቀው እና የመከላከያ ግባዓቶችን በማስጠቀም አገልግሎት መስጠት እንደሚችሉ ማሻሻያ የተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
ለቅሶ እና ሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮች በጥንቃቄ እንዲከወኑ ዉሳኔ ተላልፏል።
በሌላ በኩል የዳሰች አከባቢ ካለዉ ሰፋ ያለ መልክዓ ምድር እና በአንዳንድ ቦታዎች ካለዉ የዉሃ ሙላት መነሻ የማርበርግ ክትባት በድሮን ታግዞ እየተሰራጨ መሆኑን አቶ ኡመር ኖኩዌ ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#tikvahethiopiafamilyhawassa
tikvahethiopia

6 months ago