የመጀመሪያዉ የአፍሪካ የኢነርጂ ዉጤታማነት ኮንፍረንስ በኢትዮጵያ ሊካሄድ ነዉ!
#fastmereja I የአፍሪካ ህብረት ያዘጋጀው የመጀመሪያው የኢነርጂ ውጤታማነት ኮንፍረንስ (Energy Efficiency conference) ታህሳስ 2 እና 3 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል።
ኮንፍረንሱ የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ አመራሮች፣ ሚኒስትሮች፣ የኢንዱስትሪ መሪዎች፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት፣ ተመራማሪዎችና ባለሙያዎችን በአንድ መድረክ የሚያገናኝ እንደሆነም ተገልጿል።
ኮንፍረንሱ የኢነርጂ ውጤታማነትን በማረጋገጥ የአፍሪካ ኢኮኖሚ እድገት፣ ዘላቂ ልማትና ለአየር ንብረት ለውጥ የተግባር ምላሽ አቀጣጣይ ሞተር የማድረግ አላማ ያለው መሆኑ ተገልጿል።
የኮንፍረንሱ መሪ ሀሳብ “የአፍሪካ የኢነርጂ ውጤታማነት አጀንዳን በስትራቴጂካዊ አጋርነት ውጤታማ ማድረግ” መሆኑን የአፍሪካ ኢነርጂ ኮሚሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ራሺድ አሊ ገልፀዋል።
የኢነርጂ ውጤታማነት የኃይል ብክነት፣ የካርቦን ልቀት እና ወጪ ለመቀነስ እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ እድገት ማረጋገጥ እንደሚያስችል ገልጸዋል።
ከአፍሪካ የኢነርጂ ውጤታማነት ኮንፍረንስ ጎን ለጎን ሌሎች ሁነቶች ይኖራልም ተብሏል።
#ኹነት

8 months ago