ጫካ ቡና | CHAKA COFFEE
ስምንተኛ ቅርንጫፍ - በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር መንገድ✈️
ተፈጥሯዊ የቡና ጣዕም ☕️
Taste as Nature Intended!
#ethiopia | ላለፉት አስር ዓመታት በኢትዮጵያ የቡና ገበያ ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ያለውን የጫካ ቡና በማቅረብ የሚታወቀው "ጫካ ቡና"፤ ስምንተኛ ቅርንጫፉን በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር መንገድ ቅጥር ግቢ ውስጥ በይፋ አስመረቀ።
ጫካ ቡና በኢትዮጵያ የቡና ኢንዱስትሪ ውስጥ ያለውን የ10 ዓመት ቆይታ ምክንያት በማድረግ በተከፈተው በዚህ አዲስ ቅርንጫፍ ምረቃ ላይ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የደንበኞች አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሳምሶን አረጋን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የኩባንያው አመራሮች ተገኝተዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የደንበኞች አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሳምሶን አረጋ ፤ " "የኢትዮጵያ አየር መንገድ በየቀኑ በርካታ መንገደኞችን ያስተናግዳል። እነዚህ መንገደኞች ወደ አገራችን ሲገቡም ሆነ ሲወጡ የኢትዮጵያን ትክክለኛ ጣዕም እንዲያገኙ እንፈልጋለን። ጫካ ቡና ይህንን ጥራቱን የጠበቀ የቡና አገልግሎት በአየር መንገዳችን ቅጥር ግቢ ውስጥ ለመስጠት መወሰኑ የደንበኞቻችንን እርካታ የሚያሳድግ ነው ያሉ ሲሆን ዛሬ እኛ ግቢ ውስጥ ጫካ ቡና ስምንተኛውን ቅርንጫፉን ሲከፍት ማየት የሚያኮራ እንደሆነ ገልጸዋል።
የጫካ ቡና መስራች እና ባለቤት አቶ ብስራት በላይ በምረቃው መርሃ- ግብር ላይ እንደገለጹት፤ አዲሱ ቅርንጫፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ስም ባለው እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ መንገደኞች በሚተላለፉበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግቢ ውስጥ መከፈቱ ለየት ያለ ትርጉም እንዳለው ተናግረዋል። "አየር መንገድ የኢትዮጵያ ትልቁ ብራንድ ነው፤ እዚያ ላይ መክፈታችን ለጫካ ቡና ትልቅ ስኬት ነው" ሲሉም አክለዋል።
ጫካ ቡና ከአገር ውስጥ አገልግሎት ባሻገር ወደ ውጭ ንግድ ለመግባት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አቶ ብስራት አስታውቀዋል። በተለይም ጥሬ ቡናን ከመላክ ይልቅ፤ እሴት የተጨመረበት (የተቆላ እና የታሸገ) ቡና ለዓለም ገበያ ለማቅረብ እየሰሩ እንደሚገኙ በስፍራው ለተገኙ ለሚዲያ ባለሙያዎች በሰጡት ማብራሪያ ላይ ገልጸዋል።
ለዚሁ ዓላማ የሚውል በ3,000 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ዘመናዊ መጋዘን መገንባቱን እና በቀጣይ ሁለት ወራት ውስጥ ምርት ወደ ውጭ መላክ እንደሚጀምሩ አቶ ብስራት በላይ ጨምረው ገልጸዋል።
በተጨማሪም ኩባንያው በቀጣይ ዓመታት ውስጥ የዶሮ እርባታ ዘርፍ ለመቀላቀል ዕቅድ የያዘ ሲሆን፤ በቀን እስከ 50,000 ዶሮዎችን እና እንቁላል በማምረት የገበያውን ውድነት ለማቃለል ማቀዱን አቶ ብስራት ጠቁመዋል።
ጫካ ቡና በአዲስ አበባ
📌 ሃያሁለት ፣
📌 ቦሌ - ሞርንግ ስታር ህንጻ ፣
📌 ቦሌ - አለም ሲኒማ ጀርባ ፣
📌 አዲስ አበባ ስታዲየም
📌 ብሔራዊ አካባቢ፣ ራስ ኦላ ማዲያ
📌 ለገሃር - አቢሲኒያ ባንክ ህንጻ ስር
📌 የተባበሩት - አዲስ ኮንቬንሽን
📌 ቦሌ - በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር መንገድ ተርሚናል
www.chakacoffee.com
infochakacoffee.com
#coffee #ethiopia ☕️
📷 ከበደ መክብብ

7 months ago