Logo
SeledaPost
ተራዝሟል!!

የጤና ሚኒስቴር እስከ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ የአገልግሎት ጊዜዉ ባለፈበት የሙያ ፍቃድ አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ጤና ባለሞያዎች ማሳደስ እንዳለባቸውና የሞያ ፍቃድ የሌላቸው ደግሞ አዲስ እንዲያወጡ ለሁሉም ክልሎች እና ለሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ሰርኩላር አውርዶ ነበር።

ነገር ግን በተባለው ጊዜ ለማደስ የIhris-HrI ስርዓት እያስቸገረ መሆኑን ጠቅሶ እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ ለ1 ወር ጤና ሚኒስቴር ያራዘመ መሆኑን የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አሳውቋል።

ከጥቅምት 30 ቀን 2018 ዓ/ም በኃላ " no license, no practice " በሚል መሪ ቃል የሙያ ፍቃድ ያላወጡ እና ያላሳደሰ ባለሞያዎች በሞያዉ መስራት እንደማይችሉ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

seledadotio
seledadotio
8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.