የጤና ሚኒስቴር እስከ መስከረም 30/2018 ዓም የታደሰ የሙያ ፈቃድ ያልያዙ እና ያላወጡ የጤና ባለሙያዎች አገልግሎት መስጠት እንደማይችሉ አሳውቋል።
የጤና ባለሙያዎች የሙያ ፈቃድን በሚመለከት በጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፍሬህይወት አበበ ተፈርሞ በ 30/12/2017 ዓም ለሁሉም ክልሎች የተላከው ደብዳቤ " ሁሉም ክልሎች እስከ መስከረም 30/2018 ዓም ድረስ የንቅናቄ ስራ በመስራት ሁሉም ባለሙያ የሙያ ፍቃድ ይዞ እንዲሰራ እንዲደረግ አሳስባለሁ " ይላል።
"በመመሪያው መሰረት የጤና አገልግሎት የሚሰጡ ሁሉም ባለሙያዎች የታደስ የሙያ ፈቃድ እንዲኖራቸው ይጠበቃል "ያለው የጤና ሚ/ር ይህንንም ተከታትሎ ማስፈጸም በጤና ሚ/ር የጤናና ጤና ነክ ተቋማትና ባለሙያዎች ቁጥጥር መሪ ስራ አስፈጻሚ መሆኑን ይገልጻል።
በ2017 በጀት ዓመት የጤና ሚኒስቴር ባካሄደው የዳሰሳ ጥናት መሰረት የሙያ ፈቃድ ሳይኖራቸዉ እንዲሁም የአገልግሎት ጊዜው ባለፈበት የሙያ ፈቃድ አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ባለሙያዎችን መኖራቸዉን ማረጋገጡን ገልጿል።
በዚህ መሰረት "ሁሉም የጤና ባለሙያዎች በሙያቸው ለመስራት የታደሰ የሙያ ፈቃድ መያዝ እንደሚያስፈልጋቸው ታውቆ በክልላችሁ ስር በሚገኙ ጤና ተቋማት ላይ የሚሰሩ ጤና ባለሙያዎች እስከ መስከረም 30/2018 ዓ.ም ብቻ የሙያ ፈቃድ እንዲያወጡ" ሲል ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ አሳስቧል።
ከመስከረም 30/2018 ዓ.ም በኋላ ግን "No license,No practice" በሚል መሪ ቃል የሙያ ፈቃድ የሌላቸው ባለሙያዎች በሙያቸው መስራት እንደማይችሉ አሳውቋል።
የሙያ ፈቃድ ለማውጣትና ለማሳደስ የተሰጠው ጊዜ እስከሚያልቅ ክልሎች አስፈላጊው የንቅናቄ ስራ በመስራት ሁሉም ባለሙያ የሙያ ፍቃድ ይዞ እንዲሰራ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ መሰጠቱን ተገልጿል።
seledadotio

8 months ago