2 months ago
"የሦስቱ ሀገራት ጥምረት ለቀጠናው የደህንነት ከለላ ነው"
#ethiopia | የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሳዑዲ አረቢያ፣ ቱርክ እና ፓኪስታን በቅርቡ የፈጠሩት የመካ የጋራ መከላከያ ስምምነት በደስታ ተቀብለውታል።
ፕሬዝዳንቱ ጥምረቱ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት እራሳቸውን በብቃት የመጠበቅ አቅማቸውን የሚያሳይ ትልቅ እርምጃ ነው ሲሉ አድንቀውታል።
በስምምነቱ መሰረት በአንዱ ላይ የሚቃጣ ጥቃት በሁሉም ላይ እንደተፈጸመ የሚቆጠር ሲሆን ይህም የኔቶ አንቀጽ አምስት አይነት ቅርፅ እንዳለው ተነግሯል።
የፖለቲካ እና የደህንነት ተንታኞች እንደሚሉት ከሆነ ይህ ስምምነት ለአሜሪካ የደህንነት ጥበቃ ሙሉ በሙሉ ምትክ መሆን አይችልም ነገር ግን ተጨማሪ የደህንነት ከለላ ይሆናል ብለዋል።
እነዚህ ሰዎች በምክንያት የሚያነሱት ጉዳይ የባህረ ሰላጤ ሀገራት አሁንም ቢሆን በአሜሪካ የላቀ የጦር መሳሪያ የደህንነት እና የቴክኖሎጂ አቅም ላይ በእጅጉ የተደገፉ በመሆናቸው ነው።
በተጨማሪም የቀጣናው ሀገራት በአሜሪካ ላይ ብቻ ከመደገፍ ይልቅ የደህንነት ትስስራቸውን ለማጠናከር እና የራሳቸውን የመከላከል አቅም ለማጠናከር ይጠቀሙበታል ነው የሚሉት።
በአጠቃላይ የመካው ስምምነት የአሜሪካን ወታደራዊ ሚና ሙሉ በሙሉ የሚያስቀር ሳይሆን የቀጣናው ሀገራት የራሳቸውን መከላከያ ለማጠናከር እና በአሜሪካ ላይ የነበራቸውን ሙሉ ጥገኝነት ለመቀነስ የተወሰደ እርምጃ መሆኑን ተንታኞቹ የተናገሩት።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #defencepacts #mecca #military #agreement #usapresident #turkey #saudiarabia #pakistan

በሞትና በህይወት መካከል ናቸው
#ethiopia | የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ከካንሰር ህመም ጋር ትግል እያደረጉ መሆናቸው ተገለፀ።
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በደረጃ 4 የፕሮስቴት ካንሰር ጋር እያደረጉት ባለው ህክምና ላይ ባለቤታቸው ዶ/ር ጂል ባይደን ልብ የሚነካ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የቀድሞው ፕሬዚዳንት ከኋይት ሀውስ ከተለዩ በኋላ በ2025 ህመሙ እንደተገኘባቸው ይታወሳል።
በጊዜው ካንሰሩ ከፍተኛ የጉዳት ደረጃ ያለውና አጥንት ላይ የደረሰ እንደሆነ ተገልጾ ነበር።
ጂል ባይደን ከኬሊ ሪፓ ጋር በነበራቸው የፖድካስት ቆይታ ወቅት እንደገለጹት የካንሰሩ ህመም ወደ አጥንታቸው በመሰራጨቱ ሙሉ በሙሉ ማዳን የማይቻልበት ደረጃ ላይ ደርሷል ብለዋል።
ካንሰሩ ወደ አጥንት በመሰራጨቱ ምክንያት ሙሉ በሙሉ ሊድን እንደማይችል የተናገሩት ጂል ባይደን
ጆ ባይደን እስከ ህይወቱ ፍፃሜ ድረስ ከካንሰር ጋር ይኖራል ብለዋል።
አሁን ላይ በየሶስት ወሩ በሚደረጉ የህክምና ክትትሎች እና መድኃኒቶች ህመሙን የመቆጣጠር ስራ እየተሰራ ይገኛል ሲሉም አክለዋል።
ጂል ባይደን በኋይት ሀውስ በነበሩበት ወቅት የፕሬዚዳንቱን የጤና ሁኔታ ደብቀዋል በሚል ወቀሳ ደርሷቸው ነበር።
ካንሰሩ እድገቱን ለማዘገየት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑ እየተደረገ እንደሚገኝና አሁን ባለው ሁኔታ ባይደን በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #usapresident #cancer #joebiden #jilebiden

Comments