ኢትዮጵያ በአፍሪካ የባህል ስፖርቶች ኮንፌደሬሽን አባልነት አገኘች
👉ፕሬዝደንቷ ምክትል ፕሬዝደንት ሆነው ተመረጡ
#ethiopia | የኢትዮጵያ የባህል ስፖርቶች ፌደሬሽን ለመናኸሪያ ሬዲዮ ባስታወቀው መሰረት፣ ኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት ስትጠይቀው የቆየው በአፍሪካ የባህል ስፖርቶችና ጨዋታዎች ኮንፌደሬሽን (ATSGC) የአባልነት ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቷል።
ጥያቄው ተቀባይነት ያገኘው ከኖቬምበር 6 ጀምሮ በዚምባቡዌ ሃረሬ እየተካሄደ ባለው የኮንፌደሬሽኑ ጉባኤ ላይ ሲሆን፣ አባልነቱ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጋር ልምድ በመለዋወጥ የሀገር ውስጥ ባህላዊ ስፖርቶችን ለማሳደግና ተወዳዳሪነትን ለመጨመር ትልቅ እድል ይፈጥራል።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ የባህል ስፖርቶች ፌደሬሽን ፕሬዝደንት ወ/ሮ ህይወት መሃመድ በትላንትናው እለት የኮንፌደሬሽኑ ምክትል ፕሬዝደንት ሆነው ተመርጠዋል። ይህ ምርጫ ለኢትዮጵያ ባህላዊ ስፖርቶች ማደግ ላቅ ያለ አስተዋፅኦና ተደማጭነትን እንደሚጨምር ተጠቁሟል። ከዚህ ባሻገር፣ ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ አቆጣጠር 2026 የሚካሄደውን አህጉራዊ የባህላዊ ስፖርቶች ፌስቲቫል እንድታዘጋጅም ስለመመረጧ የተሰማ ሲሆን፣ ይህም ለሀገሪቱ ተጨማሪ እድል ይዞ ይመጣል።
በሌላ በኩል፣ በአሁኑ ወቅት የውድድር ህግና ደንብ ወጥቶላቸው በፌደሬሽን ደረጃ ጥቅም ላይ እየዋሉ ያሉት 11 ያህል ባህላዊ ስፖርቶች ሲሆኑ፣ የአፋር ክልል ባህላዊ ጨዋታ የሆነው ኮይሶ ጥናቱ ተጠናቆ 12ኛ የባህል ስፖርት ሆኖ ለመቀላቀል ዝግጅት ላይ እንደሆነም ተገልጿል።

7 months ago