#እንኳን_ደሰ_አላችሁ !
#ethiopia | የኢትዮጵያ የባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን ለአህጉር አቀፉ የአፍሪካ የባህል ስፖርቶች እና ጨዋታዎች ኮንፌዴሬሽን (ATSGC) ያቀረበው የአባልነት ጥያቄ ተቀባይነት አገኘ።
የኢትዮጵያ የባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን ለአህጉር አቀፉ የአፍሪካ የባህል ስፖርቶች እና ጨዋታዎች ኮንፌዴሬሽን (African traditional sports and games confederation) ያቀረበው የአባልነት ጥያቄ በዛሬው ዕለት ተቀባይነት አገኝቷል።
በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው የኢትዮጵያ የባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ህይወት መሀመድ የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ በመግለፅ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
አክለውም በሀገራችን በአራቱም አቅጣጫ በኩል የሚገኙ የፍቅር፣ የአንድነት፣ የውበት፣ የማንነት፣ የኩራት እና የጀግንነት ተምሳሌታዊ መገለጫ የሆኑ ብርቅዬ ባህላዊ ስፖርቶቻችንን በሀገር አቀፍ፤ በአህጉር አቀፍ እና በአለም አቀፍ ደረጃ በስፋት ለማስተዋወቅ ብሎም ተዘውታሪ ለማድረግ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢትዮጵያ የባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን አመርቂ ውጤቶችን ያስመዘገቡ ከፍተኛ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
አያይዘውም ፌዴሬሽኑ በ2018 ዓ.ም ለመከወን ከያዛቸው እቅዶች መካከል አንዱ የሆነውን በአህጉር አቀፉ የአፍሪካ የባህል ስፖርቶች እና ጨዋታዎች ኮንፌዴሬሽን (African traditional sports and games confederation) አባል የመሆን እቅድ በአጭር ጊዜ ውስጥ በተደረገ ከፍተኛ እንቅስቃሴ በአመቱ የመጀመሪያ ወር ላይ ልናሳካ ችለናል ያሉ ሲሆን በቀጣይ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጋር ድንበር ተሻጋሪ የሆነ ግንኙነቶችን በመፍጠር ባህላዊ ስፖርቶቻችንን ለማስተዋወቅ እና የባህል ልውውጦችን ለማድረግ ጉልህ ሚናን ይጫወታል ብለዋል።
በተጨማሪም ፌዴሬሽኑ በአሁኑ ወቅት ልዩ የሆነ ትኩረትን በመስጠት ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደውን የ2026 African traditional sports and multi event festival ለማዘጋጀት መጠነ ሠፊ ስራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ ወ/ሮ ህይወት ጠቁመዋል።
በመጨረሻም በፌዴሬሽኑ በኩል ለሚሰሩ በርካታ ስራዎች ፈር የቀደደ ታሪካዊ ጅማሮ በመሆኑ ሁላችንም የዚህ ጅማሮ አካል በመሆን ባህላዊ ስፖርቶቻችንን በማሳደግ፣ በማስተዋውቅ፣ በመጠበቅ እና በማልማት ሀላፊነታችን ልንወጣ ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

8 months ago