21 days ago
ከ500 በላይ ዜጎች ከልብ ህመም እፎይታን አግኝተዋል
*ልባም ኢትዮጵያዊያን ለወገኖቻቸው አዲስ ህይወት ሰጥተዋል
#ethiopia | በጤና ሚኒስቴር አነሳሽነትና በጎ ልብ ባለቸው ዲያስፖራ ኢትዮጵያዊያን ትብብር ከ500 በላይ ዜጎች ከልብ ህመም ስቃይ ተላቀው አዲስ ህይወት መኖር መጀመራቸውን ሚኒስትሯ ገልጸዋል።
እያገባደድነው ባለው 2018 አመት በበጎ ፍቃድ አገልግሎት ቢቻ ደጋግ ኢትዮጵያዊያን ባደረጉት ድጋፍ ከ500 በላይ ዜጎች የልብ ቀዶ ጥገና እንደተደረገላቸው ተገልጿል።
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ እንደገለፁት የልብ ህመም ሕክምናው ውድነቱ ሳይሆን በዜጎች ላይ የሚፈጥረውን እንግልት መሆኑን ተናግረዋል።
ዜጎች አሁን ያገኙት ዕድል ለብዙዎች የሕይወት እና የሞት ጉዳይ የነበረ ጉዳይ ነበረም ብለዋል።
በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር የሚኖሩ ልባም የሆኑ ኢትዮጵያውያን ዛሬ ለወገኖቻቸው ጤነኛ ልብን እየሰጡ መሆናቸውም መስክረዋል።
ይህ ሀገር ወዳድነታችን እና ለወገን ያለንን ጥልቅ ፍቅር ያሳያል በማለት ገልፀዋል።
ዶ/ር መቅደስ ዳባ አያይዘውም የዲያስፖራው ማህበረሰብ እና በበጎ ፈቃደኛ የህክምና ባለሙያዎች ቀና ልብ ከ500 በላይ ልቦች አሁን አዲስ ሆነዋል ብለዋል።
የዛሬው ስኬት ኢትዮጵያውያን በአንድነት ከቆሙ የማይችሉት ነገር እንደሌለ ማሳያ ነው በማለት ኢትዮጵያዊያን ላደርጉት በጎ ተግባር ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #summervolunteer #ministryofhealthethiopia #mohethiopia

የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ዋነኛ ሀገራዊ ግዴታችን ነው!
- ዶ/ ር መቅደስ ዳባ
#ethiopia | የጤና ሚኒስትር የክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት መርሀግብር ፕሮግራም በዛሬው እለት አስጀምሯል።
በጤና ሚኒስትር አስተባባሪነት የተጀመረው የክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት በዛሬው እለት በኦሮምያ ክልል በሸገር ከተማ አስተዳደር በዳለቲ ማረምያ ቤት አስጀምሯል።
የጤና ሚኒስትር በዚህ በአራተኛውን የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት መርሀ ግብር 20 ሚሊዮን ዜጎች ለማገለገል እንደሚሰራ ተናግሯል።
የጤና ሚኒስቴር በባለፉት ዓመታት የጤና ተቋማትን ጽዱና ጤናማ ለማድረግ በሀገር አቀፍ ደረጃ የክረምት በጎፍቃድ ተግባራትን በጤና ተቋማት ውስጥ በማስጀመር ይታወቃል።
ነፃ የክረምት የጤና ምርመራ የምክርና የሕክምና አገልግሎት የቤት እድሳት በማከናወን በርካታ የማህበረሰብ ክፍልን ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል።
የጤና ሚኒስቴር እንደ ሀገር የክረምት በጎ ፍቃድ ተግባራትን በጤና ተቋማት ውስጥ ሲየካሂድ የነበረ ሲሆን በዘንድሮ የክረምት በጎ ፍቃድና በሰብዓዊ ድጋፍ አገልግሎት ተግባራት ተደራሽ ያልሆኑ አካባቢዎች ተመርጠዋል።
የጤና ሚኒስትር በዛሬው ፕሮግራም ለዳለቲ ማረምያ ቤት የዋጋ ግምታቸው ከ17 ማሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የተለያዩ የህክምና ቁሳቁሶችን በስጦታ አበርክቷል።
በዘንድሮ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት በማረሚያ ቤቶች ለሚገኙ ዜጎች ነጻ የጤና አገልግሎትን እንዲያገኙ ከማድረግ ባሻገር የጤና አገልግሎት መስጫ ተቋሞቻቸውን የተሟሉና ደረጃቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ ለማድረግን አላማ ያደገረ ነው።
ዛሬ በተካሄደው መርሀግብር ላይ በበጎ ፍቃድ አገልግሎት ላቅ ያለ አፈጻጸም ለከወኑ ተቋማት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በችግኝ ተከላ መርሃግብሩ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሎሚ በዶ እና የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባን ጨምሮ የክልል ጤና ቢሮ ኃላፊዎች የጤና ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ኃላፊዎች እና የሆስፒታል አመራሮች ተሳትፈዋል።
የመርሃግብሩ ተሳታፊዎች ማረሚያ ቤቱን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን የምግብ ማብስያ የመፀዳጃ ቤት ግንባታ እንዲሁም ጤና ጣቢያ የማደራጀት ስራዎች በቀጣይ ይሰራሉ።
በማራሚያ ቤቱ ለሚገኙ ታራሚዎች ነጻ የጤና ምርመራ ሕክምና እና የምክር አገልግሎት ተሰጥቷል።

1 month ago
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የሀገራዊ አንድነታችን እና የማህበራዊ ትስስራችን መገለጫ ነው፡- ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ
*************
የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አገራዊ አንድነትን፣ አብሮነትንና ማህበራዊ ትስስርን በማጠናከር ረገድ ጉልህ ሚና እየተጫወተ መሆኑን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ገለጹ።
ርዕሰ መስተዳድሩ የአማራ ክልልን የ2018 ዓ.ም የክረምት ወራት የዜጎች በጎ ፈቃድ አገልግሎትን በባሕር ዳር ከተማ ዛሬ በይፋ አስጀምረዋል፡፡
አቶ አረጋ በመርሐ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ የመረዳዳት ባህልን በማጎልበት ለዜጎች ሁለንተናዊ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነትን እያስገኘ መሆኑን አስገንዝበዋል።
በዘንድሮው የክረምት ወቅትም በክልሉ በተለያዩ የስራ ዘርፎች በርካታ የዜጎች በጎ ፈቃድ ተግባራት እንደሚከናወኑ ጠቁመዋል።
የአረንጓዴ ዐሻራ ልማትን ጨምሮ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት የተጀመረውና በአሁኑ ወቅት ባህል እየሆነ የመጣው የማዕድ ማጋራት ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
የማህበረሰባችን የቆየ እሴት የሆነው የእርስ በርስ የመረዳዳትና የመጠያየቅ ባህል ይበልጥ እንዲጎለብት የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የክልሉ ሕዝብም ይህንን በጎ ተግባር ወደ መሬት ለማውረድ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ጥሪ አቅርበዋል።
የአማራ ክልል ሴቶች፣ ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ብርቱካን ሲሳይ በበኩላቸው፤ በዘንድሮው የክረምት ስምሪት በ17 ዋና ዋና የስራ ዘርፎች ላይ ከ9.8 ሚሊዮን በላይ በጎ ፈቃደኛ ዜጎችን በማሳተፍ፣ ከ15 ሚሊዮን በላይ ማህበረሰብን ተጠቃሚ ለማድረግ መታቀዱን ገልፀዋል፡፡
በተስፋሁን ደስታ
#amhararegion #volunteering #greenlegacy #summervolunteer #ethiopianbroadcastingcorporation

Comments