Logo
Getu Temesgen
ከ500 በላይ ዜጎች ከልብ ህመም እፎይታን አግኝተዋል

*ልባም ኢትዮጵያዊያን ለወገኖቻቸው አዲስ ህይወት ሰጥተዋል
#ethiopia | በጤና ሚኒስቴር አነሳሽነትና በጎ ልብ ባለቸው ዲያስፖራ ኢትዮጵያዊያን ትብብር ከ500 በላይ ዜጎች ከልብ ህመም ስቃይ ተላቀው አዲስ ህይወት መኖር መጀመራቸውን ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

እያገባደድነው ባለው 2018 አመት በበጎ ፍቃድ አገልግሎት ቢቻ ደጋግ ኢትዮጵያዊያን ባደረጉት ድጋፍ ከ500 በላይ ዜጎች የልብ ቀዶ ጥገና እንደተደረገላቸው ተገልጿል።

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ እንደገለፁት የልብ ህመም ሕክምናው ውድነቱ ሳይሆን በዜጎች ላይ የሚፈጥረውን እንግልት መሆኑን ተናግረዋል።

ዜጎች አሁን ያገኙት ዕድል ለብዙዎች የሕይወት እና የሞት ጉዳይ የነበረ ጉዳይ ነበረም ብለዋል።

በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር የሚኖሩ ልባም የሆኑ ኢትዮጵያውያን ዛሬ ለወገኖቻቸው ጤነኛ ልብን እየሰጡ መሆናቸውም መስክረዋል።

ይህ ሀገር ወዳድነታችን እና ለወገን ያለንን ጥልቅ ፍቅር ያሳያል በማለት ገልፀዋል።

ዶ/ር መቅደስ ዳባ አያይዘውም የዲያስፖራው ማህበረሰብ እና በበጎ ፈቃደኛ የህክምና ባለሙያዎች ቀና ልብ ከ500 በላይ ልቦች አሁን አዲስ ሆነዋል ብለዋል።

የዛሬው ስኬት ኢትዮጵያውያን በአንድነት ከቆሙ የማይችሉት ነገር እንደሌለ ማሳያ ነው በማለት ኢትዮጵያዊያን ላደርጉት በጎ ተግባር ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #summervolunteer #ministryofhealthethiopia #mohethiopia

21 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.