1 month ago
ዳሸን ባንክ ሸሪክ ከደንበኞቹ በአደራ የሰበሰበውን ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች አበረከተ
#ethiopia | ዳሸን ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ዘርፉ በሆነው ሸሪክ አማካኝነት ከደንበኞቹ በአደራ መልክ የሰበሰበውን 16.9 ሚሊዮን ብር ለሀገር በቀል ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ድጋፍ አድርጓል።
ስምንተኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በማክበር ላይ የሚገኘው ሸሪክ ይህንን የገንዘብ ድጋፍ ያስረከበው የባንኩን 30ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው የዳሸን ኤክስፖ ማጠቃለያ መርሐ ግብር ላይ ነው።
በዕለቱ ማብራሪያ የሰጡት የዳሸን ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ቺፍ ኦፊሰር አቶ አምዱ ሰማን ሸሪክ ለደረሰበት ስኬት የደንበኞች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።
ባንኩ ጠንካራ የሸሪዓ አማካሪ ኮሚቴ በማቋቋም የማህበረሰቡን እሴቶች የጠበቁ አገልግሎቶችን እየሰጠ እንደሚገኝና ማህበራዊ ኃላፊነቱንም እየተወጣ መሆኑን አስረድተዋል።
ሸሪክ ባለፉት ስምንት ዓመታት ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን ማፍራት የቻለ ሲሆን የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑንም ከ25 ቢሊዮን ብር በላይ ማድረስ ችሏል።
የባንኩ ቺፍ ባኪንግ ኦፕሬሽን ኦፊሰር አቶ ጥበቡ ሰለሞን በበኩላቸው ሸሪክ በስምንት ዓመታት ውስጥ ያስመዘገበው ዕድገት አስደናቂ መሆኑን ጠቁመዋል።
ዳሸን ባንክ በኢትዮጵያ ጠንካራው ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ሰጭ በሚል ዓለም አቀፍ ሽልማት መቀበሉንና በአሁኑ ወቅት ከ90 በላይ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ አገልግሎት የሚሰጡ ቅርንጫፎች እንዳሉት ተገልጿል።
ዳሸን ባንክ ዓለም አቀፍ የኢስላሚክ ፋይናንስ መስፈርቶችን የሚያወጣው ተቋም (AAOIFI) ቋሚ አባል የሆነ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋም መሆኑም ተጠቅሷል።
#dashenbank #sharik #interestfreebanking #charity #ethiopianfinance #socialresponsibility #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

2 months ago
ዳሸን ባንክና ኤሌጋንስ አስመጪና ላኪ ለ50 የኤሌክትሪክ መኪናዎች ግዢ ተስማሙ
#ethiopia | ዳሸን ባንክ በ"ሸሪክ" ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቱ አማካኝነት፣ ከኤሌጋንስ አስመጪና ላኪ ድርጅት ጋር የመጀመሪያ ዙር የ50 ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪናዎች ግዢ የፋይናንስ ስምምነት ተፈራርሟል።
ዳሸን ባንክ ለኤሌጋንስ ድርጅት እስከ 50 የሚደርሱ የኤሌክትሪክ መኪናዎች ግዢ ከወለድ ነፃ በሆነ መንገድ ፋይናንስ ያቀርባል።
መኪናዎቹ "ያንጎ ባይ ኤሌጋንስ" (Yango by Elegance) ለሚሰጠው የሜትር ታክሲ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚውሉ ናቸው።
በሀገሪቱ የትራንስፖርት ዘርፍ ውጤታማ የሆነውን ሀገር በቀል ተቋም በቴክኖሎጂ በመደገፍ የዘርፉን ሽግግር ማፋጠን።
ስምምነቱ ሁለቱ ተቋማት በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን መደላድል የፈጠረ ታሪካዊ እርምጃ መሆኑ ተገልጿል።
ይህ ስምምነት የሀገሪቱን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ፖሊሲ በተግባር የሚያግዝና ለአካባቢ ጥበቃም ትልቅ ፋይዳ ያለው ነው።
#getu #dashenbank #eleganceimportexport #electricvehicles #yangobyelegance #interestfreebanking #ethiopia #transportsector #sharik #greenenergy #ዳሸንባንክ #የኤሌክትሪክመኪና #ከወለድነፃ #ኢትዮጵያ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

5 months ago
የዑምራ ጉዞ በእጅዎ ነው!
በእጅዎ የያዙት ካርድ የዳሽን ባንክ ሸሪክ አልያም አን-ኒሳእ ካርድ ከሆነ አብዝተው ይገበያዩ፡፡ ግብይትዎን መሰረት በማድረግ ዳሽን ባንክ በበኩሉ የዑምራ ጉዞ ስጦታ ተካፋይ ሊያደርግዎት ተዘጋጅቷል፡፡
ታዲያ ምን ይጠብቃሉ? ከኅዳር 12 እስከ ጥር 23፣2018 በሚቆየው መርኅ-ግብር የሸሪክ እና አን-ኒሳ ካርዶችን ተጠቅመው በዳሸን ኤቲኤም ማሽን ቢያንስ ሁለት ጊዜ፣ በፖስ ማሽን ከሆነ ደግሞ ቢያንስ አንድ ጊዜ ከ300 መቶ ብር በላይ ግብይቶችን በማደረጉ የተሸላሚነት ዕድልዎን ያስፉ።
ግብይት ባደረጉ ቁጥር፣ ይህንን ልዩ ሽልማት የማሸነፍ ዕድልዎ ይጨምራል። 10 ከፍተኛ ግብይት ያከናወኑ ተጠቃሚዎች የዑምራ ጉዞ ተሸላሚዎች ይሆናሉ።
ለበለጠ መረጃ አቅራቢያዎት ወደሚገኝ ቅርንጫፋችን ጎራ ይበሉ።
ደንብና ሁኔታዎች ተፈጻሚነት አላቸው።
#sharik #ifb #cards #ethiopia #ኢትዮጵያ #dashenbank