Logo
Getu Temesgen
ዳሸን ባንክና ኤሌጋንስ አስመጪና ላኪ ለ50 የኤሌክትሪክ መኪናዎች ግዢ ተስማሙ
#ethiopia | ​ዳሸን ባንክ በ"ሸሪክ" ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቱ አማካኝነት፣ ከኤሌጋንስ አስመጪና ላኪ ድርጅት ጋር የመጀመሪያ ዙር የ50 ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪናዎች ግዢ የፋይናንስ ስምምነት ተፈራርሟል።

​ዳሸን ባንክ ለኤሌጋንስ ድርጅት እስከ 50 የሚደርሱ የኤሌክትሪክ መኪናዎች ግዢ ከወለድ ነፃ በሆነ መንገድ ፋይናንስ ያቀርባል።

​መኪናዎቹ "ያንጎ ባይ ኤሌጋንስ" (Yango by Elegance) ለሚሰጠው የሜትር ታክሲ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚውሉ ናቸው።

​በሀገሪቱ የትራንስፖርት ዘርፍ ውጤታማ የሆነውን ሀገር በቀል ተቋም በቴክኖሎጂ በመደገፍ የዘርፉን ሽግግር ማፋጠን።

ስምምነቱ ሁለቱ ተቋማት በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን መደላድል የፈጠረ ታሪካዊ እርምጃ መሆኑ ተገልጿል።

​ይህ ስምምነት የሀገሪቱን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ፖሊሲ በተግባር የሚያግዝና ለአካባቢ ጥበቃም ትልቅ ፋይዳ ያለው ነው።

​#getu #dashenbank #eleganceimportexport #electricvehicles #yangobyelegance #interestfreebanking #ethiopia #transportsector #sharik #greenenergy #ዳሸንባንክ #የኤሌክትሪክመኪና #ከወለድነፃ #ኢትዮጵያ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.