11 months ago
Intervision Song Contest 2025
#ethiopia | የፊታችን መስከረም 10/2018 ዓ.ም በሩስያ ዋና ከተማ ሞስኮ "Intervision Song Contest 2025" (ኢንተርቪዥን ሶንግ ኮንቴስት 2025) የተሰኘ አሜሪካንን ጨምሮ ከ21 በላይ ሃገሮች የሚሳተፉበት ታላቅ የድምፃዊያን ውድድር ይካሄዳል።
ይህን ውድድር የሚያስተባብረው የሩስያ መንግስት ሲሆን ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አስጀምረውት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ዲሚትሪ ቼርንየሽኮ በበላይነት እንዲቆጣጠሩት ሾመዋቸዋል።
የሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፤ ባህልን ለመጠበቅ እና የብሔራዊ እና የዓለም ባህልን ለማሻሻል የተቋቋመው ("Traditions of Art”)፤ ቻናል ዋን ሩሲያ (Channel One Russia)፤ እና ናሽናል ሚዲያ ግሩፕ (National Media Group) ከአዘጋጁ ጎን ተሰልፈዋል።
ይህንን ታላቅ ውድድር በተባባሪ አዘጋጅነት አብሮ እንዲሰራ ባላገሩ ቲም (Balageru Team) በመመረጡ ከፍተኛ ደስታ ይሰማናል።
ይህንንም ለወሰነው ለሩስያ አዘጋጅ ክፍል ያለንን አድናቆት ስንገልፅ በስራችን የምትኮሩትንና የምታበረታቱንን በመላው አለም የምትኖሩ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ በማሰብና ይህ ምርጫ የናንተም እንደሚሆን በመተማመን ነው።
ውድድሩ በእለቱ መስከረም 10/2018 ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ በባላገሩ ቴሌቪዥን በቀጥታ ይተላለፋል።
የውድድሩ መስፈርት የሚጠይቀውን ብቻ በመመርኮዝ ነፃነት ሱልጣን "ሃላል" በተሰኘው ዘፈኗ አገራችንን ወክላ ለመጀመርያ ግዜ ስለምትሳተፍ ባላሰለሰ ኢትዮጵያዊ ፍቅር ድጋፋችሁን እንድትሰጧት እንጠይቃለን።
ባላገሩ ምርጥም ሶፊ (ሱልጣን ኑሪ) አገራችንን ወክሎ በዳኝነት እንዲሳተፍ ያደረገ መሆኑን ስንገልፅ ድጋፋችሁ የማንነታችን ዋስትና ቁልፍ ስለሆነ ለምታሳዩን ፍቅር ሁሉ ከወዲሁ በማመስገን ነው።
አብርሃም ወልዴ (ባላገሩ ቲም)
#abrahamwolde #intervision2025 #russia #ethiopia #songcontest #music #sofi #netsanetsultan

Comments