28 days ago
ከዕዳ ትርክት ወደ ብልጽግና እና ታላቅነት በረከት - ላለፉት ስምንት ዓመታት የተገነባው የወል ትርክት እመርታ #ebcdotstream #prosperity #narration #nationalidentity #ethiopiarise #strategicvision
" target="_blank" class="inline-link">https://new-en.yenevibe.co...

7 months ago
🎧 የቤተ-እስራኤሎች የትግል ታሪክ በድምጽ ትረካ
"አቶ ዮና ቦጋለና የቤተእስራኤሎች ትግል"
#ethiopia | በቤተ-እስራኤላውያን የትግል ታሪክ ውስጥ ስማቸው ጎልቶ የሚነሳውን የአቶ ዮና ቦጋለን የህይወት ታሪክ እና የማህበረሰቡን ውጣ ውረድ የሚዳስሰው መጽሐፍ፤ በድምጽ ተተርኮ ሊቀርብ ነው።
ስለ ትረካው ምን ማወቅ አለብዎ?
📖 መጽሐፉ: በዘካርያስ (ዘውዱ ዮና) የተጻፈ ሲሆን፤ አቶ ዮና ወገኖቻቸውን ከድንቁርና አውጥተው ለነጻነት ለማብቃት የከፈሉት መስዋዕትነት ተካቶበታል።
🎙 ተራኪ: ጋዜጠኛ አይናለም ሀድራ።
📺 ቦታ: ተወዳጅ ሚድያ ቲዩብ (Tewedaj Media Tube)።
📅 የሚጀምረው: ነገ ሰኞ ጥር 11 ቀን 2018 ዓ.ም.።
የአቀራረብ መርሐ-ግብር:
በየቀኑ 2 ክፍሎች (ጠዋት 2:30 እና ማታ 3:00) ይለቀቃል።
አጠቃላይ 40 ክፍሎች ያሉት ሲሆን፤ በ20 ቀናት ተተርኮ ይጠናቀቃል።
ይህንን የ17 ሰዓት ታሪካዊ ሰነድ በማድመጥ የታሪክ እውቀትዎን ያዳብሩ!
#betaisrael #yonabogale #audiobook #history #ethiopia #tewedajmedia #narration

8 months ago
ትርክት ምንድን ነው? (Narration)
በአለማየሁ ዋሴ (ዶ/ር)
📌(ከአምስት አመት በፊት ከጻፍኩት ማስታወሻ የተወሰደ)
እንደ መግቢያ
#ethiopia | ትርክት አንድን ማህበረሰብ ለጋራ ዓላማ ለማሠለፍ የሥነ ልቦና ውቅርን መቅረጫ ስልት ነው፡፡ ትርክት ታሪክ ማለት አይደለም፡፡ ይልቁንም ግብ ያለው የታሪክ አረዳድ ነው፡፡
ከትምክህት ሳይሆን በራስ ከመተማመን መንፈስ አንፃር ተቃኝቶ እኛ ማን ነን? ያለፈ ታሪካችን ምንድን ነበር? አሁን የት ላይ ነን? ወደፊትስ ምን ይገባ’ናል? የሚሉ ጥያቄዎችን መልስ በመስጠት ቁጭት የሚፈጥር፣ የሚያጀግን፣ መተባበርን የሚያመጣ መንፈስ ነው፡፡
እርግጥ እያወራሁ ያለሁት ስለበጎ ትርክት ነው፡፡ በጎ ትርክት እንዳለ ሁሉ መጥፎ ትርክትም ይኖራል፡፡ መጥፎ ትርክት ዛሬን ቀምቶ፣ ነገንም አሳጥቶ፣ ትናንት ላይ እግር ከወርች አስሮ ካለፈ የታሪክ እንቅፋት ላይ ሊቸክለን ይችላል፡፡ መጥፎ ትርክት ማህበረሰብን አበጣብጦ ሀገርን መቀመቅ ሊከት ይችላል፡፡
ኢትዮጵያ ሀገራችን የመጥፎ ትርክት ስለባ መሆኗን በእርግጥ ተረድተናል ወይ? ኢትዮጵያን እየጎዱ ያሉ ትርክቶች የትኞቹ ናቸው? የመጥፎ ትርክቶች አመንጭዎች እነማን ነበሩ? ያንን መጥፎ ትርክት የትውልድ ዕዳ እንዲሆን እንማን አቀነቀኑት ? እንዴት? የሚሉት ጥያቄዎች መሠረታዊና መመለስ ያለባቸው ናቸው፡፡
ይሁን እንጅ የኢትዮጵያን ታሪክ ጠንቅቆ ለተረዳና ጂኦ ፖለቲክስ ለሚያውቅ ሰው ብዙም ከባድ አይሆኑም፡፡ ስለሆነም የዚህ ጹህፍ ዓለማ በየቀኑ ግፍ ስልሚያስጎነጨን ክፉ ትርክት ማውራትና ማልመዝመዝ ሳይሆን ተስፋችንን ስልተሸከመው ስለ በጎ ትርክት ማውሳት ይሆናል፡፡
በጎ ትርክት ድንጋይን ዳቦ፤ ውኃን እሳት፤ መርዝን መድኃኒት የማድረግ ወንዝን ሽቅብ የማፍሰስ፤ ብረትን ሀይቅ ላይ የማንሳፈፍ አቅም አለው፡፡ ‹እኛ ከሌሎች ልዩ ነን! /Unique/ ይህ ልዩ የሚያደርገን ችሎታ፣ ስጦታ፣ ታሪክ፤ ነባራዊ ሁኔታ፣ ልምድ ወደ ከፍታ ሊወስደን ይገባል!› የሚል መረዳትና ስምምነት ነው፡፡
ትርክት ሌሎች በመልካምና በበጎ ዓይን እንዲያዩን ለራሳችን ደግሞ በጎ ስሜት እንዲኖረን የሚያደርግ የአዕምሮ ጉልበት አለው፡፡
ትርክት የመንግሥት የፖሊሲ ሀሳቦች ማለት አይደለም፡፡ ሕዝብን ማስተማር፣ ግብርናን ማዘመን፣ ኢንዱስትሪ ማስፋፋት፣ ቱሪዝም ማልማት የመሣሠሉት የፖሊሲ ሀሳቦች ናቸው፡፡ ትርክት የፖሊስ ማስፈፀሚያ መደላድል፣ የልቦና ውቅር መፍጠሪያ ነው፡፡ ፖሊሲ ደግሞ የትርክቱን መንፈስ ሥጋ ማልበሻ ነው፡፡
በጎ ትርክት እንዴት እንፍጠር?
ይቀጥላል.....

1 year ago
𝙅𝙞𝙢𝙢𝙖𝙖 𝙈𝙖𝙜𝙖𝙖𝙡𝙖𝙖 𝙅𝙖𝙖𝙡𝙖𝙡𝙖𝙖
ጅማ የፍቅር ከተማ ❤
አባ ጅፋር - [ የጅማ ፀሐይ ]
#ethiopia | Nooru, ulfinni
ኖር፣ ክብር (መከባበር) ከቤት ይወጣል (ይጀምራል)
ጅማዎች - በፍቅር እና በክብር ኖር ብለው ተቀብለውናል - ❤
***
ተብሎ ተብሎ ነገሩ
ጅማ አባ ጅፋር ነው የሰው ልጅ ሀገሩ ፡፡
ማረስ የትም ሲሆን መንገድ ጅማ ነው
መታጠቅ ወንጨሬ (ተፈሪ ) መያዝ ምንሽር ነው፡፡
መኖር በሀገር ላይ ማስከተል ወንድምን ነው
በኣድና ቡታንቲ ገበና ገላጭ ነው ፡፡
መሸታ ሲገቡ ገበና ገላጭ ነው ፡፡
መሸታ ሲገቡ ሳንቲም የሌለው ሰው
አይሄድም ወይ ጅማ ምን አልከሰከሰው፡፡
መሄድ ነው ጅማ መሄድ ነው ጎሬ
ይገኝ ጀመር አሉ ገንዘብና በሬ ……..
እየተባለ ስለ ጅማ ታላቅነት ይዘፈን ነበር፡፡ ኑሮው ያልሞላለት፣ ኑሮውን ለማሳካት ነግዶ የከሰረውን ወደ ጅማ ሄዶ እድሉን እንደገና ለመሞከር እና ለመበልጸግ የበሬ መግዣ ገንዘብ የሌለው ሰው ጅማ ሄዶ ከሰራ እንደሚበለጽግ የታወቀ ሰለሆነ ጅማን ሁሉም ሰው በዘፈን ያወድሳታል፡፡
ትኩስ ፍቅር የሠፈረባት ኮረዳም ብትሆን ፍቅረኛዋን ተከትላ ወደ ጅማ መኮብለሏ አይቀርም፡፡
መሄድ ነው ጅማ መሄድ ነው ጅማ
ፍቃድ ብጠይቃት እምቢ አለችኝ እማማ
ጅማ የተቆረቆረችው በ1880 ዓ.ም ገደማ እንደሆነ ይነግርላታል፡፡ ጅማ ሲነሣ የአባ ጅፋርም ስም አብሮ መምጣቱ የማይቀር ነው፡፡ "ጅማ አባ ጅፋር" ማለት የተለመደ ነው ፡፡ ጅማን የአባ ጅፋር ከተማ ማለት ይቻላል ፡፡
ጅማን በአንድ መሪ ጥላ ሥር ያሰባሰቧቸው የመጀመሪያው ተጠቃሽ ‹‹አባ ፉሮ›› ይባላሉ፡፡ እርሳቸው ሲሞቱ ልጃቸው አባ መጋል ተተክተው የጅማን ግዛት አስፋፍተዋል፡፡
በ1830 ሥልጣኑን "አባ ጅፋር" ጎዳ (አባ ጅፋር ትልቁ) ተረክበው ለሃያ አምስት አመት ያህል መርተዋል፡፡ በዚህም ወቅት ሊሙን እና ኢናርያን ለመያዝ አስከ 1884 ዓ.ም ድረስ ብዙ ጦርነት ቢካሄዱም ኢትዮጵያን በከፍተኛ ደረጃ ለማማከል የተነሱት አጼ ምንልክ ሊሙን በቁጥጥራቸው ሥር አድርገዋል፡፡
አባ ጅፋር አንደኛን በመጨረሻ ወንድማቸው አባ ፌቡ ይተኳቸዋል፡፡ አባ ፌቡ በዘመን ሥልጣናቸው በህዝቡ ላይ በደል ስላደረሱ ህዝቡ በአመጽ እንደገደላቸው ይነገራል፡፡
አባ ሬቦ ቀጥሎ በጅማ የበላይነት የያዙት የአባ ጅፋር አንደኛና የአባ ሬቦ ወንድም የሆኑት አባ ቦቃ ናቸው፡፡ እርሳቸውም ከ1885 ዓ.ም ጅምሮ ይዞታቸውን ከማስፋፋት ጋር እስልምናን በማስፋፋት ታላቅ አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡
እስልምና ወደ አካባቢው የገባው በአረቡ አለም በንግድ ሥራ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚዘዋወሩ የሙሰሊም ነጋዴዎች እና ሸኾች አማካይነት እንደሆነ ይነገራል፡፡ በዚህ ዘመን ሥልጣኑን የያዙት አባ ጎመል የአባ ጅፋር 2ኛ አባት ነበሩ፡፡
ከ1850ዎቹ ጀምሮ የጅማ ባላባቶች የአስተዳደር ማእከል የ”ጅሬን” ከተማ ተራራማ እና ነፋሻ ናት፡፡ ከፍታዋ 2ሺ ሜትር ሲሆን የአባ ጅፋር 2ኛ ቤተ መንግስትም በዚች ከተማ ይገኛል፡፡
በአፈ ታሪክ “ጅሬን” ሁለት ትርጉም ሲኖረው አንዱ “ነዋሪነት” ወይም “ኑሮ” ማለት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ አካባቢ “ጅሬ” በምትባል ሴት ይተዳደር ስለነበር በእርሷ ስም “ጅሬን” ተብሎ እንደተጠራ ይነገራል ፡፡
አባ ጂፋር ሁለተኛ
አባ ጅፋር 2ኛ ከወይዘሮ ጎማይቱና ከአባ ጎመል እ.ኤ.እ በ 1859 ተወለዱ።
በ1932 ዓ. ም ዐረፉ።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እባ ጅፋር ሁለተኛ እንደሌሎች የጅማ ቀደምት መሪዎች ሁሉ ከሊሙ፣ ጋር በርካታ ጦርነቶችን እድርገዋል።
በ1880 ዎቹ በፊት በምዕራብና በደቡብ ምዕራብ ያለውን አካባቢ ለመቆጣጠር በሸዋው ንጉሥ ምኒልክ እና በጎጃሙ ንጉሥ ተክለሃይማኖት መካከል ከፍተኛ ውድድር ቢደረግም የአጼ ምንልክ ጦር እየገፋ ጅማን በሰላማዊ መንገድ እና ሁኔታ ሊያዋህድ ችሏል፡፡ በመጨረሻም በ1894 ዓ.ም ከአጼ ምንልክ ጦር ጋር በመሆን ሊሙን ለማእከላዊ መንግስት በማስገበር ተካፍለዋል፡፡
ከ1897 እስከ 1900 ባለው ጊዜ ውስጥ ሁለተኛው አባጅፋር በጅማ ላይ ሊሙን ተሹመው አስተዳድረዋል፡፡
አምና በአባ ጅፋር የልጅ፣ ልጅ፣ ልጅ Ababiya Abajobir Abajifar (በአባ ቢያ ) ቤት በክብር ምሳ ተጋብዘን ነበር።
ገናናው ታሪካችን ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ🇪🇹
መልከ መልካም፤ ስልጡን፤ አስተዋይ፤ አዛኝ፤ ብልህ ዲፕሎማት፤ ፍትሐዊ ንጉሥ
«...የስትራቴጂ አመራርን፣ ዘመናዊ ዲፕሎማሲን እና ዘመናዊነትን (Strategic leadership, Modern Diplomacy and Modernization) ከንጉሥ አባጂፋር አለመማራችን የአለም ጭራ እንዳደረገን መራረ እውነት ነው።
የዳር ታሪካችንን ወደ መሐል (making mainstream narration) እስካላመጣን ድረስ ጭራውም እንዳይጠፋ ስጋቴ ነው።»
የተከበሩ ዶ/ር Abdusemed Husen
***
ጅማ ሙዚየም ዘለቅን።
ሙዚየሙ በ1972 በፕሬዝዳንት መንግስቱ ኃይለማርያም አማካኝነት “ሙዚየም” ሆኖ በይፋ እንደጀመረ ይነገራል
የጅማ ሙዚየም በውስጡ “ከ2ሺህ በላይ ቅርሶች” ይዟል።
የጅማ ሙዚየም ኢትዮጵያ ካሏት ትልቅ ታሪክ ያላቸው ሙዚየሞች ከቀዳሚዎቹ የሚጠቀስ ነው፡፡ ሙዚየሙ በውስጡ በተለይም የጅማ ወርቃማ ዘመን ተብሎ በሚጠራው ጊዜ ከ1942 እስከ 1933 ዓ.ም የተሰሩ የተለያዩ ቅርሶች ይገኙበታል፡፡
መረጃዎች እንደሚያሳዩት በነዚያ ዓመታት ስምንት ነገስታት ጅማን ያስተዳደሩ ሲሆን ከስምንቱ ሁለቱ አባ ጅፋሮች ናቸው፡፡
ዘመኑ የእንጨት፣ የአልባሳት፣ ብረታ ብረት እና የቆዳ ስራ ውጤቶች የተዋወቁበት "የከፍታ ዘመን" ነበርም ይባላል፡፡
ሙዚየሙ አሁን ያለበትን ደረጃ ላይ እንዲደደርስ የዛሬ 50 ዓመታት የተዘጋጀው የ1965ቱ የከፋ ልማት ኤክስፖ ትልቅ ሚና እንደተጫወተም ነው የታሪክ ሰነዶች የሚያመለክቱት፡፡
የቅርስ ባለሙያና የጅማ ሙዚየም ኃላፊ ነጂብ ራያ አባገላን Najiib Raayyaa Og/Hambaa fi Itti Gaafatmaa God-Hambaa እንደተናገሩት በ1965ቱ የከፋ ኤክስፖ ላይ ለእይታ የቀረቡት የጅማ ቅርሶች የወቅቱን ንጉሰ ነገስት አጼ ኃይለ ሥላሴን እና የኤክስፖው ታዳሚ የነበሩትን የሆላንዷን ንግስት ጁሊያናን “ቀልብ መሳብ የቻሉ ድንቅ ቅርሶች” ነበሩ፡፡
አቶ ነጂብ የመሪዎቹን ቀልብ የገዙት ቅርሶቹ ለ1 ወር ያክል ለህዝብ ክፍት ተደርገው በህዝብ ተጎብኝተዋልም ብለዋል፡፡
ሙዚየሙ የተለያዩ ምእራፎችን ተሻግሮና ጠቅላላ ቅርሶቹ ከተሰበሰቡ በኋላ ፤ በ1972 በፕሬዝዳንት መንግስቱ ኃይለማርያም አማካኝነት “ሙዚየም” ሆኖ በይፋ ስራውን እንደጀመረም ገልጸዋል አቶ ነጂብ፡፡
“ሙዚየሙ በውስጡ ከ2 ሺህ በላይ ቅርሶችን ይዞ ይገኛል፤ 75 በመቶ የሚሆኑ ቅርሶቹ የራሱ የአባጅፋር ሲሆኑ የተቀሩት ጅማ በከፋ ጠቅላይ ግዛት በነበረችበት ወቅት ከ6ቱ አውራጃዎች የተሰበሰቡ እንዲሁም ጣሊያን ድል ካደረግን በኋላ ሁለተኛው ወረራ ባካሄደችበት ሰአት የተሰበሰቡ የጣሊያን ቅርሶች ናቸው”ም ነው ያሉት የቅርስ ባለሙያው አቶ ነጂብ ራያ፡፡
ከሙዚየሙ ቅርሶች አብዛኞቹ ከ100 እስከ 120 ዓመታት ያስቆጠሩ ናቸው ያሉት አቶ ነጂብ አብዛኞቹ ከቆዳ የተሰሩ፣ ከግዙፍ ግንድ የተፈለፈሉ የእንጨት ውጤቶች፣ አልባሳት፣ የቀንድ ውጤቶች፣ የብርታ ብረት እና መሰል ውጤቶች መሆናቸውም ተናግረዋል፡፡
***
ጂ . . . ማ
ሲኞሪና ውብ ከተማ
ፒኮሌዋ የኛ ሮማ
ከአባጂፋር ደብር ጎራ
ከጂሬን ጫፍ ዉብ ተራራ
ተ ን ሸ ራ ት ታ
ተ ን ሸ ራ ት ታ
ቁልቁል ወርዳ ተዘርግታ
ጤና ሣይንስን ጎትታ
ቆጪ መንደራን አግባብታ
ከሠጦ ሜዳ አቆራኝታ
ዘና ብላ በስተ ግራ
በአጂፕ በኩል አሣብራ
በመናኸሪያ ተንቀባርራ
በሸዋ በር ተሽከርክራ
ታላቁን መስጊድ ዘይራ
አውደ መርካቶን አብሺር ብላ
በመንቲና ሽቅብ ሄዳ
ኪቶን አቅፋ ቁልቁል ወርዳ
አየር ማረፊያ እረፍት ወስዳ
እንደገና
ኮራ ብላ ተጀንና
ሽቅብ ዳገቱን ገስግሣ
እነ ሔርማታን በዐይኗ ጠቅሣ
ጊቤ አዳራሽን ገላምጣ
ቤተ መንግሥቱን እጅ ነስታ
ግራና ቀኝ ቦሣን አቅፋ
በፈረንጅ አራዳ አቆላልፋ
እንደ ዘበት እንደ ዋዛ
በደጊቱ ተጠምዝዛ
በሣር ሠፈር ሸውዳ
በእርሻ ኮሌጅ ቁልቁል ወርዳ
ሼንትራዲዮን ከዚያ ጠርታ
ከፉሩስታሌ አስማምታ
ዞራ ዞራ ተንፈላስሳ
በሊሙ በር ተመልሳ
የአዌቱን ወንዝ ድንቅ ፀጋ
ወገብዋ ላይ ሸብ አድርጋ
ዋ! ስታምር ይህች ጂማ
ፒ ኮ ሌ ዋ የ እ ኛ ሮ ማ።
መ/ር ሙሉጌታ ደሳለኝ
ፎቶግራፈር : ከበደ መክብብ

Comments