Logo
Getu Temesgen
ትርክት ምንድን ነው? (Narration)

በአለማየሁ ዋሴ (ዶ/ር)

📌(ከአምስት አመት በፊት ከጻፍኩት ማስታወሻ የተወሰደ)

እንደ መግቢያ
#ethiopia | ትርክት አንድን ማህበረሰብ ለጋራ ዓላማ ለማሠለፍ የሥነ ልቦና ውቅርን መቅረጫ ስልት ነው፡፡ ትርክት ታሪክ ማለት አይደለም፡፡ ይልቁንም ግብ ያለው የታሪክ አረዳድ ነው፡፡

ከትምክህት ሳይሆን በራስ ከመተማመን መንፈስ አንፃር ተቃኝቶ እኛ ማን ነን? ያለፈ ታሪካችን ምንድን ነበር? አሁን የት ላይ ነን? ወደፊትስ ምን ይገባ’ናል? የሚሉ ጥያቄዎችን መልስ በመስጠት ቁጭት የሚፈጥር፣ የሚያጀግን፣ መተባበርን የሚያመጣ መንፈስ ነው፡፡

እርግጥ እያወራሁ ያለሁት ስለበጎ ትርክት ነው፡፡ በጎ ትርክት እንዳለ ሁሉ መጥፎ ትርክትም ይኖራል፡፡ መጥፎ ትርክት ዛሬን ቀምቶ፣ ነገንም አሳጥቶ፣ ትናንት ላይ እግር ከወርች አስሮ ካለፈ የታሪክ እንቅፋት ላይ ሊቸክለን ይችላል፡፡ መጥፎ ትርክት ማህበረሰብን አበጣብጦ ሀገርን መቀመቅ ሊከት ይችላል፡፡

ኢትዮጵያ ሀገራችን የመጥፎ ትርክት ስለባ መሆኗን በእርግጥ ተረድተናል ወይ? ኢትዮጵያን እየጎዱ ያሉ ትርክቶች የትኞቹ ናቸው? የመጥፎ ትርክቶች አመንጭዎች እነማን ነበሩ? ያንን መጥፎ ትርክት የትውልድ ዕዳ እንዲሆን እንማን አቀነቀኑት ? እንዴት? የሚሉት ጥያቄዎች መሠረታዊና መመለስ ያለባቸው ናቸው፡፡

ይሁን እንጅ የኢትዮጵያን ታሪክ ጠንቅቆ ለተረዳና ጂኦ ፖለቲክስ ለሚያውቅ ሰው ብዙም ከባድ አይሆኑም፡፡ ስለሆነም የዚህ ጹህፍ ዓለማ በየቀኑ ግፍ ስልሚያስጎነጨን ክፉ ትርክት ማውራትና ማልመዝመዝ ሳይሆን ተስፋችንን ስልተሸከመው ስለ በጎ ትርክት ማውሳት ይሆናል፡፡

በጎ ትርክት ድንጋይን ዳቦ፤ ውኃን እሳት፤ መርዝን መድኃኒት የማድረግ ወንዝን ሽቅብ የማፍሰስ፤ ብረትን ሀይቅ ላይ የማንሳፈፍ አቅም አለው፡፡ ‹እኛ ከሌሎች ልዩ ነን! /Unique/ ይህ ልዩ የሚያደርገን ችሎታ፣ ስጦታ፣ ታሪክ፤ ነባራዊ ሁኔታ፣ ልምድ ወደ ከፍታ ሊወስደን ይገባል!› የሚል መረዳትና ስምምነት ነው፡፡

ትርክት ሌሎች በመልካምና በበጎ ዓይን እንዲያዩን ለራሳችን ደግሞ በጎ ስሜት እንዲኖረን የሚያደርግ የአዕምሮ ጉልበት አለው፡፡

ትርክት የመንግሥት የፖሊሲ ሀሳቦች ማለት አይደለም፡፡ ሕዝብን ማስተማር፣ ግብርናን ማዘመን፣ ኢንዱስትሪ ማስፋፋት፣ ቱሪዝም ማልማት የመሣሠሉት የፖሊሲ ሀሳቦች ናቸው፡፡ ትርክት የፖሊስ ማስፈፀሚያ መደላድል፣ የልቦና ውቅር መፍጠሪያ ነው፡፡ ፖሊሲ ደግሞ የትርክቱን መንፈስ ሥጋ ማልበሻ ነው፡፡
በጎ ትርክት እንዴት እንፍጠር?

ይቀጥላል.....

8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.