4 months ago
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአዲስ መልክ የተደራጀውን የአርማውር ሐንሰን የምርምር ማዕከል መረቁ
#ethiopia | ለበርካታ ዓመታት በአለርት የሕክምና ማዕከል ውስጥ በተወሰነ አቅም የምርምር ሥራዎችን ሲያከናውን የቆየው የአርማውር ሐንሰን የምርምር ተቋም በመንግሥት ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት በአዲስ መልክ ሪፎርም ተደርጓል።
ይህ ተቋም በአዋጅ በድጋሚ እንዲደራጅ ከተደረገ በኋላ አስፈላጊው የግንባታ ሥራ ተጠናቆለትና ዘመናዊ ግብዓቶች ተሟልተውለት በዛሬው ዕለት በኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በይፋ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።
ተቋሙ ወደዚህ አዲስ ምዕራፍ የተሸጋገረው በሀገሪቱ የጤና ምርምር ዘርፍ ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመሙላትና የሳይንስ ምርምርን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ታቅዶ መሆኑ ተገልጿል።
ይህ ዘመናዊ የምርምር ማዕከል በውስጡ 40 የሚደርሱ ላቦራቶሪዎችን የያዘ ሲሆን በተለይም የላቁ የጂኖሚክስ እና የባዮኢንፎርማቲክስ የምርምር ቦታዎችን በማካተቱ በዘርፉ ትልቅ አቅም ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።
ከዚህ በተጨማሪም ማዕከሉ በሀገር ውስጥ የሚመረቱ መድኃኒቶችን ጥራት፣ ደህንነትና ብቃት በተገቢው ሁኔታ የሚያረጋግጥ የባዮኢኩዊቫለንስ ማዕከልን በውስጡ አካቶ የያዘ በመሆኑ ለሀገር በቀል የመድኃኒት ኢንዱስትሪ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል።
ይህ ግዙፍ የምርምር ተቋም መገንባቱ ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ ራሷን ችላ የሕዝቧን ደህንነት ለመጠበቅ ለምታደርገው ጥረት እንደ ትልቅ ስኬት የሚቆጠር ነው።
#ethiopia #ahri #medicalresearch #healthinnovation #abiyahmed #scienceandtechnology #genomics #bioinformatics #publichealth

Comments