3 months ago
ተመድ በፓኪስታን የአየር ጥቃት ሳቢያ የተከሰተውን ሰብአዊ ቀውስ አወገዘ
#ethiopia | የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ፓኪስታን በአፍጋኒስታን ካቡል በሚገኝ ሆስፒታል ላይ የፈጸመችውን እና የከፋ የሰው ህይወት መጥፋት ያስከተለውን ጥቃት በፅኑ አውግዟል።
ድርጅቱ በጥቃቱ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በመግለጽ፣ ሀገራት ለአለም አቀፍ ህጎች ተገዥ እንዲሆኑና የሌሎችን ሉዓላዊነት እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርቧል።
ተመድ በተለይም የህክምና ተቋማት፣ የጤና ባለሙያዎች እና ንፁሃን ዜጎች ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች በምንም መልኩ ተቀባይነት እንደሌላቸው አሳስቧል።
በካቡል ሆስፒታል ላይ በተፈጸመው በዚህ ጥቃት ከ400 በላይ ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ፣ ከ250 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ከባድና ቀላል የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል።
ፓኪስታን በበኩሏ ጥቃቱ የታለመው በአፍጋኒስታን የጦር ሰፈሮች ላይ እንደነበር በመጥቀስ የቀረበባትን ክስ ለማስተባበል ሞክራለች። ሆኖም የአፍጋኒስታን መንግስት ድርጊቱን በከፍተኛ ሁኔታ በመቃወም፣ በፓኪስታን ላይ ተመጣጣኝ የአፀፋ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።
ክስተቱ በሁለቱ ጎረቤት ሀገራት መካከል ያለውን ውጥረት ይበልጥ እንዳባባሰው ተገልጿል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #unitednations #afghanistan #pakistan #kabul #internationalnews #breakingnews #humanrights #globalconflict