3 hours ago
ምክር ቤቱ የግብርና ቢዝነስ ኩባንያ እና የፌዴራል ታክስ አስተዳደር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጆችን ለየቋሚ ኮሚቴዎቹ መራ
**********************
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 23ኛ መደበኛ ስብሰባው የግብርና ቢዝነስ ኩባንያ እና የፌዴራል ታክስ አስተዳደር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ ለዝርዝር ዕይታ ወደሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች መርቷል።
በምክር ቤቱ የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ሁለቱንም ረቂቅ አዋጆች አስመልክተው ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፤ የግብርና ቢዝነስ ኩባንያ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ግብርና ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት፣ ለኢንዱስትሪ ልማትና ለሥራ ዕድል ፈጠራ መሠረት በመሆኑ የአሠራር ሥርዓቱን በማላቅ ወደ ዘመናዊ፣ ተወዳዳሪና የገበያ መር ሥርዓት ማሸጋገር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።
አክለውም አዋጁ አነስተኛ ይዞታ ያላቸውን አርሶ አደሮች፣ አርብቶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮችን በግብርና ቢዝነስ ኩባንያ በማደራጀትና በማቀናጀት ምርታማነትንና የምርት ጥራትን ለማሳደግ፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማስፈን ወሳኝ ሚና እንዳለው አስረድተዋል።
ምክር ቤቱም በአባላቱ የተሰጡትን ሐሳብና አስተያየቶች ካዳመጠ በኋላ ረቂቅ አዋጁን ለግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር ዕይታ መርቶታል።
በተመሳሳይ መልኩ ምክር ቤቱ የፌዴራል ታክስ አስተዳደር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅን ለፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር ዕይታ መርቷል።
ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) በማብራሪያቸው ረቂቅ አዋጁ የታክስ አስተዳደር ሥርዓቱን በማዘመን በታክስ ከፋዩ ዘንድ የሚነሱ መሠረታዊ የፍትሐዊነትና የመልካም አስተዳደር ቅሬታዎችን በዘላቂነት መፍታት የሚያስችል መሆኑን ጠቁመዋል።
ይህ የማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ በሀገራችን የታክስ አስተዳደር ሥርዓት ውስጥ ተጠያቂነትን፣ ቅልጥፍናን፣ ፍትሐዊነትንና ግልጽነትን ለማስፈን የታክስ ሕጎችን በተጠናከረ መልኩ ለማስፈጸም እንዲሁም በታክስ ከፋዩና ሰብሳቢው መካከል ያለውን ግንኙነት በሕግ የበላይነት ላይ እንዲመሠረት የሚያስችሉ ቁልፍ ድንጋጌዎችን የያዘ መሆኑን አብራርተዋል።
በሌላ በኩል የታክስ አስተዳደር ሥርዓቱን ከዘመናዊና ዓለም አቀፍ ልምዶች ጋር ለማጣጣም፣ የታክስ አለመግባባቶችን በፍትሐዊነት፣ በሰላማዊ መንገድና በቅልጥፍና ለመፍታት እንዲሁም የመንግሥትን የገቢ አሰባሰብ አቅም በታማኝነት ላይ መሥርቶ ለማጠናከር ከፍተኛ ፋይዳ ያለው የሕግ ማዕቀፍ መሆኑን አስገንዝበዋል።
የምክር ቤቱ አባላት በረቂቅ አዋጁ ላይ ሰፊ ሐሳብና አስተያየት ከሰጡበት በኋላ ለዝርዝር ዕይታ ወደ ቋሚ ኮሚቴው መመራቱን የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል።
#hpr #agribusinesslaw #taxreform #agriculturaldevelopment #fiscalmodernization #ethiopianbroadcastingcorporation

22 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በጋምቢያ ባንጁል እየተካሄደ በሚገኘው 87ኛው የአፍሪካ የሰብዓዊ እና የህዝቦች መብት ኮሚሽን (ACHPR) መደበኛ ጉባኤ ላይ የተገኘው የኤርትራ ልዑክ፣ ሀገሪቱ ተደራራቢ እና ቀጣይነት ያላቸው ዓለም አቀፍ ጫናዎች ቢኖሩባትም በሰብዓዊ መብት አያያዝ እና በዜጎች ሁለንተናዊ የኑሮ ደረጃ መሻሻል ላይ ተጨባጭ ለውጦችን እያስመዘገበች መሆኗን አስታወቀ። የፊታችን (እ.ኤ.አ) ሜይ 24 35ኛ ዓመት የነጻነት በዓሏን "ጽናታችን፡ ዋስትናችን" በሚል መሪ ቃል ለማክበር በዝግጅት ላይ የምትገኘው ኤርትራ፣ የሰብዓዊ መብት ጥበቃን ከህዝብ ተኮር የልማት አቅጣጫዎች ጋር አዋህዳ እየሰራችበት መሆኑን የልዑካን ቡድኑ ገልጿል።
ልዑኩ ለኮሚሽኑ ባቀረበው ሰፊ ሪፖርት በቁጥር የተደገፉ እና በመሰረተ ልማት አቅርቦት ላይ የታዩ ለውጦችን አብራርቷል። እ.ኤ.አ. በ1991 ሀገሪቱ ነጻነቷን ስትቀዳጅ የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ የነበረው ህዝብ 13 በመቶ ብቻ የነበረ ሲሆን፣ ይህንንም ከፍተኛ የሆነ የአካባቢ እና የአየር ንብረት ፈተናዎችን በመቋቋም አሁን ላይ ወደ 85 በመቶ ከፍ ማድረግ መቻሉ ተገልጿል። በተመሳሳይ በነጻነት ማግስት 138 ብቻ የነበሩት ግድቦች እና የውሃ ማጠራቀሚያዎች በተደረገው መጠነ ሰፊ ሀገራዊ ኢንቨስትመንት በአሁኑ ወቅት ከ850 በላይ መድረሳቸው ተጠቁሟል። የህብረተሰቡን ጤና ከመጠበቅ አኳያ ወሳኝ በሆነው የንጽህና አጠባበቅ ረገድም፣ እ.ኤ.አ. በ2015 32 በመቶ የነበረው ከሜዳ ላይ እዳሪ ነጻ የመሆን ምጣኔ አሁን ላይ 93 በመቶ በሚሆኑ የሀገሪቱ መንደሮች መረጋገጡን ልዑኩ አብራርቷል። በግብርናው ዘርፍም ባለፈው የ2025 ዓመት ብቻ ከግማሽ ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት መልማቱ ተጠቅሷል።
በትምህርት እና ጤና ዘርፍ መንግስት እየወሰዳቸው ያሉትን ተከታታይ እርምጃዎች ያወሳው መግለጫው፣ ትምህርት እንደ መሰረታዊ ሰብዓዊ መብት ተቆጥሮ ከቅድመ መደበኛ (መዋዕለ ህጻናት) እስከ ከፍተኛ ትምህርት ድረስ ለሁሉም ዜጎች በነጻ እየተሰጠ መሆኑን አመልክቷል። አሁን ላይም የትምህርት ጥራትን ለማሳደግ አዳዲስ የማስተማሪያ እና የመገምገሚያ ዘዴዎች ተግባራዊ እየተደረጉ ይገኛሉ። በጤናው ዘርፍም አዲሱ የ2026-2030 ስትራቴጂካዊ እቅድ የሁሉንም ዜጎች የጤና ሽፋን በማረጋገጥ ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ በተለይም ባለፈው ዓመት (2025) በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ ታካሚዎች ላይ የተሰሩ የዓይን ህክምና እና ቀዶ ጥገና ስራዎች ትልቅ ስኬት የተመዘገበባቸው መሆናቸውን ዘገባው ያሳያል።
ከእነዚህ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እርምጃዎች ባሻገር ሀገሪቱ አጠቃላይ የህግ ማሻሻያ እና የለውጥ ሂደት ላይ መሆኗም ተገልጿል። በዚህም የፍትሐ ብሔር እና የወንጀለኛ መቅጫ ህጎችን ጨምሮ ሌሎች መመሪያዎች የሀገሪቱን እሴት፣ ታሪክ እና ዓለም አቀፍ የስምምነት ግዴታዎችን ባገናዘበ መልኩ በድጋሚ እየተመረመሩ እና እየተከለሱ እንደሚገኙ ተጠቅሷል። በኢኮኖሚው ዘርፍም የአነስተኛ ብድር እና ቁጠባ ፕሮግራም በመላ ሀገሪቱ ለሚገኙ ወደ አንድ ሚሊዮን ለሚጠጉ ግለሰቦች ብድር በማቅረብ የዜጎችን ህይወት እያሻሻለ መሆኑ ታውቋል።
የኤርትራ ልዑክ እነዚህ ሁሉ ለውጦች ቢመዘገቡም አሁንም ያልተፈቱ በርካታ ተግዳሮቶች መኖራቸውን አምኖ ተቀብሏል። ይሁን እንጂ መንግስት ህዝብን ማዕከል ያደረገውን የልማት ጉዞ በማስቀጠል፣ ተቋማትን በማጠናከር፣ ለመሰረታዊ አገልግሎቶች ያለውን ተደራሽነት በማስፋት እና የዜጎችን የሰብዓዊ መብት ሙሉ በሙሉ ለማረጋገጥ የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል። በአፍሪካ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ACHPR) መድረክ ላይም አዎንታዊ እና ገንቢ የሆነ የትብብር መንፈሱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ቃል በመግባት መግለጫውን አጠናቋል።

4 months ago
⚖️ የ50 የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች ሹመት ጸደቀ! 🏛️
#ethiopia | 23 ሴቶች እና 27 ወንዶች... ምክር ቤቱ ለዳኝነት ሙያ የሴቶችን ተሳትፎ ያጎላ ሹመት አፀደቀ
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ጥር 28 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው 11ኛ መደበኛ ስብሰባ፤ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እጩ ዳኞችን ሹመት አጽድቋል።
የሹመቱ ዝርዝር:
✅ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት:
በድምሩ 50 እጩ ዳኞች የተሾሙ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ 23ቱ ሴቶች እንዲሁም 27ቱ ወንዶች ናቸው። ይህም የሴት ዳኞችን ተሳትፎ ያጎላ ሆኖ ተገኝቷል።
✅ የከፍተኛ ፍ/ቤት አመራር:
ምክር ቤቱ አቶ ልዑል ካህሳይ ወልዱን እና አቶ ምትኩ ማዳ ድልነሳውን የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ ሾሟል።
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለተሾሚ ዳኞች እና አመራሮች መልካም የስራ ዘመን ተመኝቷል።
ለፍትህ ስርዓቱ መጠናከር የበኩላችሁን እንድትወጡ አደራ እንላለን!
#parliament #judgesappointment #federalcourt #justice #ethiopia #law #hpr #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

😭 "ረሃቤን ለእናቴ አልነግራትም!" - ህጻን ማራኪ
#ethiopia | ልብ የሚሰርሰር እና እንባ የሚያራጭ እውነተኛ የህይወት ታሪክ በ VIP SHOW
አንዲት ህጻን እንዴት እንዲህ ትላለች?
"ረሃቤን ለእናቴ አልነግራትም!"... ይህ የቃላት ድርድር ብቻ አይደለም፤ የኑሮን ክብደት፣ የህይወትን ፈተና እና ያለእድሜ የሚሸከሙትን የልጅነት ትከሻ የሚያሳይ እንጂ።
በ"በረዶ ዘመን" እና የምናውቃት ደራሲና አዘጋጅ ሔለን ታደሰ፤ ይህንን የህጻን ማራኪን ዘመን ተሻጋሪ ታሪክ ይዛላችሁ ቀርባለች።
ኑሮ ሲከብድ፣ ፈተና ሲበዛ... የዚህች ህጻን ጥንካሬ እና ለእናቷ ያላት ፍቅር ምን ይመስላል?
ይህንን ልብ ሰርሳሪ ታሪክ እንዳያመልጥዎ!
በየሳምንቱ አዳዲስ ተረኮች
VIP SHOW ETHIOPIA
https://youtu.be/IcyIkh-PV...
#vipshow #helentadesse #maraki #lifestory #ethiopia #reallife #touching

7 months ago
መክሊት ሲትኮም :
በየሳምንቱ በፋና ፕላስ መተላለፍ ይጀምራል
#ethiopia | መክሊት እውነቱን ተናግራ፣ የምትወደውን ከውና ፣ በነጻነት መኖር የምትፈልግ ሴት ነች፡፡
በግልና በማህበራዊ ህይወቷ የሚያጋጥሟትን ፈተናዎች ተቋቁማ ህልሟን ለመኖር የምታደርገው ጥረትና ፈተናዎቿ በሲትኮሙ ከሌሎች ታሪኮች ጋር ተሰናስሎ በየሳምንቱ ወደ ተመልካች ይደርሳል።
የመክሊት ሲትኮም ታሪክ በዋናነት በትዳር እና በማህበራዊ ችግሮቻችን ላይ ያጠነጥናል። ሲትኮሙ ህልምን ለማሳካት የሚደረግ ጥረትን ብቻ ሳይሆን የትውልዶች
ን ማህበራዊ ጥያቄዎች ያነሳል። መካሊት ሲትኮም ከማዝናናት ባለፈ በእለት ተእለት ህይወታችን ያሉብንን ህጸጾች ቁልጭ አድርጎ ያሳየናል፡፡
በመንሽ ፕሮዳክሽን ፕሮዲዩስ የተደረገው መክሊት ሲትኮም ከፊታችን አርብ ጥቅምት 28 ጀምሮ ምሽት 3 ሰአት በየሳምንቱ በፋና ፕላስ መተላለፍ ይጀምራል !
www.menshproduction.com
Sponsored by
Surafel