Logo
Getu Temesgen
⚖️ የ50 የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች ሹመት ጸደቀ! 🏛️

​#ethiopia | 23 ሴቶች እና 27 ወንዶች... ምክር ቤቱ ለዳኝነት ሙያ የሴቶችን ተሳትፎ ያጎላ ሹመት አፀደቀ

​የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ጥር 28 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው 11ኛ መደበኛ ስብሰባ፤ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እጩ ዳኞችን ሹመት አጽድቋል።

​የሹመቱ ዝርዝር:
✅ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት:
በድምሩ 50 እጩ ዳኞች የተሾሙ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ 23ቱ ሴቶች እንዲሁም 27ቱ ወንዶች ናቸው። ይህም የሴት ዳኞችን ተሳትፎ ያጎላ ሆኖ ተገኝቷል።

​✅ የከፍተኛ ፍ/ቤት አመራር:
ምክር ቤቱ አቶ ልዑል ካህሳይ ወልዱን እና አቶ ምትኩ ማዳ ድልነሳውን የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ ሾሟል።

​የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለተሾሚ ዳኞች እና አመራሮች መልካም የስራ ዘመን ተመኝቷል።

ለፍትህ ስርዓቱ መጠናከር የበኩላችሁን እንድትወጡ አደራ እንላለን!

​#parliament #judgesappointment #federalcourt #justice #ethiopia #law #hpr #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.