5 months ago
በስፓይና ቢፊዳ እና ሀይድሮሴፋለስ ግንዛቤ የፈጠረ የተማሪዎች ውድድር ተካሄደ
#ethiopia | ሆፕ ኤስ.ቢ.ኤች ከኒው አይሲቲ እና ኢቨንት ኦርጋናይዘር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የተማሪዎች የኪነ-ጥበብ እና የክህሎት ውድድር በወዳጅነት አደባባይ ተካሄደ።
መርሃ ግብሩ በተለይም በስፓይና ቢፊዳ (የነርቭ ዘንግ ክፍተት) እና በሀይድሮሴፋለስ (በጭንቅላት ውስጥ ፈሳሽ መከማቸት) ዙሪያ ማህበረሰባዊ ግንዛቤን ለማሳደግ ያለመ መሆኑን አዘጋጆቹ ገልጸዋል።
በዕለቱ በተካሄደው ውድድር ላይ ተማሪዎች በግጥም፣ ሙዚቃ፣ ስዕል እና ሞዴሊንግ እና በጥያቄና መልስ እንዲሁም አነቃቂ ንግግሮች ውድድር ተካሂዷል።
በተለይም በስፓይና ቢፊዳ (የነርቭ ዘንግ ክፍተት) እና በሀይድሮሴፋለስ (በጭንቅላት ውስጥ ፈሳሽ መከማቸት) አስቀድሞ ለመከላከል የሚረዱ የጥንቃቄ መንገዶች እና የአመጋገብ ስርዓት ላይ ያተኮሩ መልዕክቶች ተላልፈዋል።
የሆፕ ኤስ.ቢ.ኤች መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ቤዛ በሻህ እንደገለጹት፤ እነዚህ የአፈጣጠር ችግሮች የጤና ተግዳሮት ብቻ ሳይሆኑ ሰፊ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ስነ-ልቦናዊ ጫና የሚያሳድሩ ጉዳዮች መሆናቸውን ገልጸው ችግሩን ከ70-75 በመቶ ፎሊክ አሲድ በመውሰድ መከላከል እንደሚቻል ተናግረዋል።
በዝግጅቱ ላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ ምሁራን፣ የታሪክ ተመራማሪዎች፣ የጥበብ ባለሙያዎች፣ መምህራን እና ተማሪዎች ተገኝተዋል።
ይህ የተማሪዎች ላይ ትኩረት አድርጎ የተጀመረው የግንዛቤ ማስጨበጫ ውድድር በየሶስት ወሩ በተከታታይ እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ ገልጸዋል።
#spinabifida #hydrocephalus #awareness #hopesbh #publichealth #childhealth #ethiopia #prevention #educationalevent #friendshipsquare

Comments