26 days ago
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኦሲስ አጠቃላይ ሆስፒታልን መርቀው ሥራ አስጀመሩ
*****************
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኦሲስ አጠቃላይ ሆስፒታልን መርቀው ሥራ አስጀምረዋል።
ሆስፒታሉ በሀገራችን ጥራት ያለው የሕክምና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ በትልቅ አማራጭነት የቀረበ ማዕከል መሆኑ ተገልጿል።
ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጽ ባስተላለፉት መልዕክት፤ አቅም ያላቸው ዜጎች ወደ ውጭ ሀገር ሄደው የመታከም ዕድል ቢኖራቸውም፣ አቅም የሌላቸው ዜጎቻችን ግን በሀገር ውስጥ ዘመናዊ ሕክምና አግኝተው እንዲድኑ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
ለዚህም ስኬት በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ ትብብር ዘመኑን የዋጁ ሆስፒታሎች እንዲገነቡና አገልግሎት እንዲሰጡ እየተደረገ መሆኑን አመላክተዋል።
አክለውም ተቋሙ አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ለጀመርነው ጉዞ ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር በመሆኑ ስኬታማ እንዲሆን እመኛለሁ ብለዋል።
#ethiopia #addisababa #healthsector #oasishospital #healthtourism #ethiopianbroadcastingcorporation