16 hours ago
የአርጀንቲና እግር ኳስ አዲስ ምዕራፍ
ቦነስ አይረስ
#ethiopia | ዛሬ ዓለም የእግር ኳስ ታላቅ ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ ከአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ጋር የሚያደርገውን የመጨረሻ ጨዋታ በልዩ ስሜት እየጠበቀች ነው።
39 ዓመቱ ሜሲ በቦነስ አይረስ በሚገኘው Monumental Stadium ከቤኒን ጋር በሚደረገው የወዳጅነት ጨዋታ የአርጀንቲናን ማሊያ ለመጨረሻ ጊዜ ለብሶ ሊቀርብ ነው።
“የማያበቃ ምሽት” የተባለው የሜሲ ስንብት
የዛሬው ጨዋታ በአርጀንቲና “The Night That No One Wants to End” — ማንም እንዲያበቃ የማይፈልገው ምሽት በሚል ስያሜ እየተጠበቀ ነው። የአርጀንቲና እግር ኳስ ማኅበርም የሜሲን ከ20 ዓመታት በላይ የዘለቀ የብሔራዊ ቡድን ጉዞ ለማክበር ልዩ የስንብት ሥነ-ሥርዓት አዘጋጅቷል።
ሜሲ ከአርጀንቲና ጋር 207 ጨዋታዎችን ተጫውቶ 125 ጎሎችን አስቆጥሯል። ከእነዚህ 21 ጎሎች በዓለም ዋንጫ የተቆጠሩ ናቸው። በብሔራዊ ቡድኑ ታሪክ ከፍተኛ የጨዋታ ብዛትና የጎል ብዛት ያለው ተጫዋች ሆኖ ይሰናበታል።
ከትችት ወደ የሀገር ጀግናነት
የሜሲ ከአርጀንቲና ጋር ያለው ጉዞ ሁልጊዜ ቀላል አልነበረም። በመጀመሪያዎቹ ዓመታት በክለብ ደረጃ የሚያሳየውን ብቃት በብሔራዊ ቡድን ማሳየት አልቻለም በሚል ከፍተኛ ትችት ይደርስበት ነበር። እ.ኤ.አ. 2016 ከኮፓ አሜሪካ ዋንጫ የፍጻሜ ሽንፈት በኋላም ከብሔራዊ ቡድን ለጊዜው መሰናበቱ ይታወሳል።
ነገር ግን በኋላ ታሪኩ ተቀየረ። ሜሲ አርጀንቲናን በመምራት፦
🏆 2021 — ኮፓ አሜሪካ
🏆 2022 — Finalissima
🏆 2022 — የዓለም ዋንጫ
🏆 2024 — ኮፓ አሜሪካ
በማሸነፍ የሀገሩን የዋንጫ ጥማት አስታግሷል።
የ2026 የዓለም ዋንጫ ስንብት
ሜሲ በ2026 የዓለም ዋንጫ ደግሞ አርጀንቲናን ወደ ፍጻሜ አድርሷል። አርጀንቲና በኒው ጀርሲ በተደረገው የፍጻሜ ጨዋታ በስፔን 1–0 ተሸንፋ ዋንጫውን ሳታስጠብቅ ቀርታለች። ከዚያ በኋላ ሜሲ ከብሔራዊ ቡድን ለመሰናበት ውሳኔ አድርጓል።
አርጀንቲና ዛሬ ለሜሲ ተነስታለች
የዛሬው ስንብት በMonumental ብቻ አይደለም። በሜሲ የትውልድ ከተማ ሮሳሪዮ ውስጥ ትልቅ የአርጀንቲና ቁጥር 10 ማሊያ በMonument to the National Flag አካባቢ ተተክሎ “Gracias” የሚል መልዕክት ተሰጥቷል። ደጋፊዎችም በጎዳናዎችና በቤቶቻቸው ላይ ለኮከቡ ምስጋና እየገለጹ ነው።
ትኬቱን ማግኘት ላልቻሉ ደጋፊዎችም በBuenos Aires የዩኒቨርሲቲው ከተማ የ**“Gracias, Leo” Fan Fest** ተዘጋጅቷል፤ በዚያም ትልቅ ስክሪን ላይ ጨዋታውን ለመከታተል ዕድል ተፈጥሯል።
ሜሲ ግን እግር ኳስን አይሰናበትም!
ይህ ስንብት የሜሲ የእግር ኳስ ህይወት መጨረሻ አይደለም። ከአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ቢሰናበትም፣ በInter Miami የክለብ እግር ኳሱን ለመቀጠል ነው። በቅርቡም ከInter Miami ጋር የCampeones Cup ዋንጫን አሸንፏል።
“ሜሲ ከአርጀንቲና ማሊያ ተሰናብቷል፤ ከእግር ኳስ ግን ገና አልተሰናበተም።”
የሜሲ የ21 ዓመታት የአርጀንቲና ታሪክ ዛሬ ሲዘጋ፣ የ“ቁጥር 10” ወንበር በአርጀንቲና እግር ኳስ ውስጥ ትልቅ ባዶ ቦታ ይተዋል። የሜሲ ታሪክ ግን በዋንጫዎቹ ብቻ ሳይሆን፣ በትጋት፣ በትዕግሥት እና በተደጋጋሚ ውድቀት ከተነሳ በኋላ ወደ የሀገር ጀግናነት በመድረሱ ይታወሳል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#messi #lionelmessi #argentina #graciasleo #football #goat #ethiopia #getutemesgen
23 days ago
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለአንድ የማስታወቂያ ጽሑፍ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ያስከፍላል
#ethiopia | በእግር ኳሱ ዓለም ያላቸው ፉክክርና ዝና ወደ ማኅበራዊ ትስስር ገጾችም ተሻግሮ፣ ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና ሊዮኔል ሜሲ በገቢያቸውም ውድድር ጀምረዋል።
ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአንድ የኢንስታግራም የማስተዋወቂያ ጽሑፍ ብቻ 3.2 ሚሊዮን ዶላር በማግኘት በዓለም ከፍተኛ ተከፋይ ስፖርተኛ ሆኖ በግንባር ቀደምትነት እየመራ ይገኛል።
ይህ አስገራሚ ገቢው በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ያለውን ግዙፍ ተደራሽነትና ተጽዕኖ በግልጽ ያሳያል።
በእግር ኳስ ሜዳው ላይ ሁሌም የሚፎካከረው አርጀንቲናዊው ሊዮኔል ሜሲ ደግሞ በአንድ ጽሑፍ 2.7 ሚሊዮን ዶላር በማግኘት በቅርብ ርቀት ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።
ሁለቱ የእግር ኳስ ታላላቅ ተጫዋቾች (GOATs) በሜዳ ላይ ከሚያሳዩት ድንቅ ብቃት በተጨማሪ፣ ከሜዳ ውጪ ባለው የዲጂታል ገበያም ከፍተኛውን ገቢ በመሰብሰብ የበላይ ናቸው ።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

2 months ago
አባቴ... አሁንም ከእኛ መለየትህን ማመን አልቻልኩም"
The Goat ሊዮኔል ሜሲ ለአባቱ ለጆርጅ ሜሲ የጻፈው ልብ የሚነካ የመሰናበቻ ደብዳቤ
አባቴ ከእንግዲህ አይንህን የማላየው፣ ከእኔ ጋር የማትነጋገር መሆኑን መቀበል ከብዶኛል። የምትሰቃይ እንደነበር እና አሁን ማረፍህ የተሻለ መሆኑን ባውቅም፣ ግን በጣም ፈጥነህ ተለየኸን። ገና አብረን የምናሳልፈውና የምንደሰትበት ብዙ ነገር ነበረን።
በመጨረሻው የዓለም ዋንጫ እንድጫወት ሁልጊዜ ትነግረኝ ነበር፤ ውድድሩ ከመጀመሩ ጥቂት ቀናት በፊት ግን ጤናህ እየታወከ መጣ።
በውድድር ላይ ሳለሁ የማትገኝበት የመጀመሪያው ጊዜ ነበር፤ ነገር ግን እናቴ ደህና እንደምትሆን እና ለመጓዝ እንደምትችል ነግራኝ ነበር። ወደ ፍፃሜው እንደምንደርስና መጥተህ ጨዋታውን እንደምትመለከት ነግሬህ ነበር።
ስለተፈጠረው ነገር ሁሉ ማውራት ስላልቻልኩ ወደ አንተ መጣሁ። ምንም ነገር መደሰት አልቻልክምና። ሻምፒዮን ባንሆንም እያንዳንዱን ጨዋታ እንዴት እንደተደሰትንበት በፍጹም አላወቅክም። አሁንም ቢሆን አንተ ልክ ነበርክ፤ በዚያ መገኘት እና መጫወት ነበረብህ።
ይህንን የምነግርህ ልናወራው ያልቻልነው ብቸኛው ነገር ስለሆነ ነው፤ ምክንያቱም ሌላውን ነገር ሁሉ አስቀድመህ ታውቀዋለህ። በየቀኑ እናወራ ነበር፣ በእኔ ፕሮግራሞች ምክንያትም በቻልንበት ጊዜ ሁሉ እንገናኝ ነበር።
ያለ አንተ ምን እንደማደርግ አላውቅም፣ እንዴትስ ለመቀጠል እንደምችል አላውቅም። እኔ እግር ኳስ ብቻ ነው የምጫወተው፣ አሁን ግን ለረጅም ጊዜ መጫወቴን እቀጥላለሁ ወይ የሚል ብዙ ጥርጣሬ አደረብኝ።
ከጅምሩ ጀምሮ ከጎኔ ነበርክ፣ እስከ መጨረሻውም በጣም ቅርብ ነበርክ። ለምን ጥቂት ጊዜ ታግሰህ አብረን አልጨረስንም?
ደስታህ ቤተሰብህን፣ ባለቤትህን፣ ልጆችህን ማየት እንደሆነ አውቃለሁ፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ ሌሎች ሳይረዱ እኔ ስጫወት ማየት እንደነበር አውቃለሁ...
ከትንሽነቴ ጀምሮ ሁልጊዜ እንደዚያ ነበር። ከስራ እንደተመለስክ ወደ ልምምድ ቦታ ሁሉ ትወስደኝ ነበር።
በእርግጥም አንዱንም ጨዋታ አታልፍም ነበር። እኔን ስትመለከት እንዴት ትጨነቅ እንደነበር እና እንዴት ትዝናናበት እንደነበር አስታውሳለሁ::
አባት፣ ጓደኛ እና ወኪሌ ነበርክ። በየወቅቱ መሆን ያለብህን ሰው ሁልጊዜ ነበርክ፤ በፍጹም አልተሳሳትክም። ከአንዳንድ ቅርታዎች ወይም ጭቅጭቆች ባሻገር ሁልጊዜ ልክ ነበርክ። በመጨረሻም ሁሉም ነገር አንተ ባልከው ይደመደማል።
በጣም እናፍቅሃለሁ፣ ነገር ግን ሁልጊዜ በልቤ ውስጥ ትኖራለህ፤ በተለይም በልጆቼ አስተዳደግ ውስጥ፣ ምክንያቱም አንተ እኔን ባደገከኝ እና ባስተማርከኝ መንገድ ነው ልጆቼን የምኮተታቸው እና የማደግደው።
በሰላም እረፍ፣ እዚህ እንዳደረግከው ሁሉ ከላይ ሆነህ ጠብቀን። ስለ ሁሉም ነገር አመሰግናለሁ።
እወድሃለሁ አባቴ! ❤️"
Seledadotio

4 months ago
ሊዮኔል ሜሲ የዓለም ዋንጫ ታሪክ አዲስ ንጉሥ
የአርጀንቲናው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ በዓለም ዋንጫ ታሪክ ብዙ ግቦችን ያስቆጠረ ተጫዋች በመሆን አዲስ ክብረ ወሰን አስመዘገበ። ሜሲ ይህንን ታሪካዊ ድል ያሳካው አሁን በአርጀንቲና እና በኦስትሪያ መካከል እየተካሄደ ባለው የዓለም ዋንጫ የምድብ ጨዋታ ላይ ባስቆጠረው ግብ ነው።
በጨዋታው 38ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠራት ግብ የሜሲን የዓለም ዋንጫ የግብ መጠን ወደ 17 ከፍ በማድረግ፣ የጀርመኑን አጥቂ ሚሮስላቭ ክሎዜ የነበረውን የ16 ግቦች ክብረ ወሰን በይፋ እንዲያፈርስ አስችሎታል።
በጨዋታው 10ኛው ደቂቃ ላይ የተሰጠውን የፍፁም ቅጣት ምት መቶ ሳይጠቀምበት ቀርቶ የነበረ ቢሆንም፣ በመቀጠል ባሳየው ብቃት ኳሷን መረብ ላይ በማሳረፍ አዲስ ታሪክ መጻፍ ችሏል። ይህ ድል ሜሲ በ6ኛው ተከታታይ የዓለም ዋንጫ ተሳትፎው ያመዘገበው ሲሆን፣ የዘንድሮውን የዓለም ዋንጫ ድንቅ አጀማመር በይበልጥ ደምቆ እንዲታይ አድርጎታል።
ሜሲ ከዚህ ቀደም የነበረውን የክሎዜን ክብረ ወሰን ለመጀመሪያ ጊዜ እኩል ያደረገው በአልጄሪያ ላይ በነበረው የምድብ ጨዋታ ላይ ነበር። አሁን ግን ይህንን ክብረ ወሰን ብቻውን በመቆጣጠር የእግር ኳስ ዓለሙን የ"GOAT" ደረጃውን በይበልጥ አጠናክሯል።

7 months ago
🐐 የኢንተር ሚያሚው ፊት አውራሪ
#ethiopia | በሜጀር ሊግ ሶከር (MLS) ታላቅ የፍሎሪዳ ደርቢ፣ ሊዮኔል ሜሲ ለተቃዋሚ አሰልጣኞች ድፍረትና ንቀት ምላሹ "በሜዳ ላይ የሚሰጥ ትምህርት" መሆኑን በድጋሚ አስመስክሯል።
ኢንተር ሚያሚ በኦርላንዶ ሲቲ ተመሪ ሆኖ የቆየበትን ጨዋታ በሜሲ አስደናቂ ብቃት 4 ለ 2 በሆነ ውጤት በመቀልበስ አሸንፏል።
🔄 ጨዋታው እንዴት ተቀለበሰ?
ጨዋታው ሲጀመር ኦርላንዶ ሲቲዎች ብርቱ ነበሩ። እስከ እረፍት ድረስ 2 ለ 0 እየመሩ ወደ መልበሻ ክፍል ሲያመሩ፣ የድሉ ባለቤት የሚሆኑ መስሎ ነበር። ሆኖም ከእረፍት መልስ ሜዳው የሊዮኔል ሜሲ የፈጠራ መድረክ ሆነ።
* ሜሲ በቁጥር፦ 2 ግቦችን አስቆጠረ፣ 1 ግብ የሚሆን ኳስ አመቻችቶ አቀበለ።
* አስገራሚው ስታቲስቲክስ፦ ሜሲ ከ2018 ወዲህ ብቻ 36 የቅጣት ምት ግቦችን ከመረብ አሳርፏል። ይህ ቁጥር በዚሁ ጊዜ ውስጥ ካስቆጠራቸው የፍፁም ቅጣት ምቶች (Penalties) በላይ መሆኑ ንጉሱ ኳስና መረብን ለማገናኘት የቆመ ኳስ ብቻ እንደሚበቃው ማሳያ ነው።
🗣️ "ልፈርምልህ?" — ሜሲ አሰልጣኙን ዝም ያስባለበት ቅጽበት
የምሽቱ ዋነኛ መነጋገሪያ ግን ከግቦቹ ባሻገር በሜሲ እና በኦርላንዶ ሲቲ አሰልጣኝ መካከል የተፈጠረው ፍጥጫ ነው።
የኦርላንዶ አሰልጣኝ ቡድናቸው 2 ለ 0 እየመራ ወደ እረፍት በሚወጡበት ወቅት ሜሲን ተጠግተው የሆነ ነገር ሲናገሩት ታይተዋል። ሜሲ በአሰልጣኙ ንግግር ደስተኛ እንዳልነበረ ፊቱ ላይ ይነበብ ነበር።
ምላሹ ግን እንዲህ ነበር፦
ሜሲ በሁለተኛው አጋማሽ አስደናቂ የቅጣት ምት ጎል አስቆጥሮ ቡድኑን ወደ አሸናፊነት ካመራ በኋላ፣ ወደ ተቃዋሚው አሰልጣኝ በማቅናት "ልፈርምልህ እንዴ?" የሚል ትርጉም ያለው የምልክት ምላሽ ሰጥቷቸዋል። "በንግግር ሳይሆን በኳስ እናሸንፋለን" የሚል መልዕክት ያዘለ ትዕይንት ነበር።
ሊዮኔል ሜሲ አሁንም በ30ዎቹ እድሜው መጨረሻ ላይ ሆኖ የእግር ኳስ ጥበብ ምን እንደሆነ ለዓለም እያሳየ ይገኛል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #lionelmessi #intermiami #mls #messimagic #footballnews #intermiamivsorlandocity #goat

8 months ago
ሮናልዶ በጎል ተመለሰ፤ አል ነስር አል ፈታህን በጎል አጥለቅልቋል
#ethiopia | በሳውዲ ፕሮ ሊግ መርሃ-ግብር አል ነስር ከአል ፈታህ ጋር ባደረገው ጨዋታ 3 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት ወሳኝ ድል ተቀዳጅቷል።
ባለፉት ጨዋታዎች በተለያዩ ምክንያቶ ከሜዳ ርቆ የነበረው ድንቅ ተጫዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ፣ ወደ ሜዳ በተመለሰበት በዚህ ጨዋታ ክለቡን መሪ ያደረገችውን የመጀመሪያ ጎል ከመረብ አሳርፏል። ቀሪውን የማሸነፊያ ግብ ደግሞ አይማን አህመድ አስቆጥሯል።
የሮናልዶ አስገራሚ ጉዞ በቁጥር
* የውድድር ዓመቱ ግቦች፦
ሮናልዶ በዚህ የውድድር ዘመን ያስቆጠራቸውን የሊግ ግቦች ወደ 18 አሳድጓል።
* ወደ 1000 ግቦች፦
ሮናልዶ በእግር ኳስ ታሪክ 1,000 ግቦችን ያስቆጠረ የመጀመሪያው ተጫዋች ለመሆን አሁን የሚቀሩት 38 ግቦች ብቻ ናቸው።
የደረጃ ሰንጠረዥ ሁኔታ
ከዚህ ድል በኋላ የሁለቱ ክለቦች ደረጃ የሚከተለውን ይመስላል፦
* አል ነስር፦
በ 52 ነጥብ 2ኛ ደረጃ ላይ በመቀመጥ የሻምፒዮናነቱን ፉክክር አጥብቆ ቀጥሏል።
* አል ፈታህ፦
በ 24 ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ronaldo #alnassr #saudiproleague #cr7 #footballnews #alfateh #goat #cristianoronaldo

Sponsored by
Surafel
10 months ago
ሰው መኾን የደከመው
#ethiopia | እንግሊዛዊው ቶማስ ትዋይትስ ከልጅነቴ ጀምሮ አስበው ነበር ያለውን ለመተግበር ቆርጧል።
የዜናው ምንጭ ኢንዲፔንደንት ከራሱ ከአቶ ከቶማስ ትዋይትስ ሰማሁት ብሎ እንደነገረን፥ ትዋይትስ ገና የ9 ዓመት ሕጻን ሳለ በጠዋት ከእንቅልፉ ተቀስቅሶ ወደ ትምህርት ቤት መኼድ አስመርሮታል፤ ምነው ድመት በሆንሁና ትምህርት በቀረልኝ፣ እንደልቤ በተኛሁ ብሎ ይመኝ ነበር።
አሁን ካደገ በኋላም ቢኾን ሰው መኾንን ማምለጥ፣ ከሰውነት ዕረፍት ማድረግ ቢቻል ብሎ ዳግም የተመኘው በአንድ አጋጣሚ ነው፥ አንድ ዘመዱ ለሥራ ከመንደሬ ስለምርቅ ውሻዬን ተንከባከብሎኝ ሲል ጠየቀው።
በአደራው መሰረት ውሻውን ሲንከባከብም በድጋሚ ያ የልጅነት ምኞቱ ተቀሰቀሰበት፥ እንስሳት ምንም ዐሣብ የለባቸውም፣ ቤት ኪራይ አይከፍሉም፣ የሥራ ደርሶ መልስ ብሎ ነገር የለባቸውም፣ መብላት መጠጣትና መተኛት ብቻ ነው።
ይህን ዓለም መኖር አለብኝ፣ የልጅነት ሕልሜም ተዳፍኖ አይቀርም ብሎ የቆረጠው ትዋይትስ ታዲያ በፕላስቲክ የተሠሩ ኮቴ፣ ቀንድ፣ አፍ ይዞ አልፕስ ተራራን ወጣ፥ የያዛቸውን ቁሶች አጥልቆም ከፍየል መንጋ ተቀላቀለ።
እንደ እነርሡው ሣር እየበላ፣ ፍሣሽ ውኃ እየጠጣ ለ3 ቀናት አብሯቸው ቆይቶ ሲመለስም GoatMan: How I Took A Holiday From Being a Human የተሰኘ መጽሐፍ ጽፏል።
ሰሚ ባገኘ ቁጥርም የፍየል ዓለም በጣም አስደሣች ነው ብሎ እንደሚናገር የዘገበልን ኢንዲፔንደንት ነው ያለው ትርታ ኤፍ ኤም ነው።

ሊዮናርዶ ዲካፒርዮ የፊልም GOAT
#ethiopia | ሊዮናርዶ ዲካፒርዮ ከሁሉም የሆሊውድ ተዋናዮች በልጦ በትወና ችሎታው በአንደኛነት ደረጃ ተቀምጧል።
ሊዮናርዶ ዲካፕሪዮ አድናቆትን ያተረፈ አሜሪካዊ ተዋናይ፣ ፕሮዲዩሰር እና የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋችም ነው።
በህጻንነቱ ተዋናይነት ህይወቱን ጀምሮ ወደ አለምአቀፍ ዝና ያመራ ሲሆን ተወዳጅ እና ከተለመደው ውጪ የሆኑ ገጸ-ባህሪያትን በታላላቅ ፊልሞች ላይ በመጫወት ይታወቃል።
የመጀመሪያ ስራዉ Critters 3 የሚል ሲሆን ከዛም በኃላ Titanic, Romeo&Juliet,The Wolf of Wall Street የመሳሰሉ ምርጥ ምርጥ ፊልሞች ላይ ተዉኗል።
The Revenant ፊልም ላይ ባሳየው ምርጥ የትወና ብቃት የምርጥ ተዋናይ የአካዳሚ [oscar] ሽልማት አሸንፏል። አሁን ደግሞ የምንጊዜም ምርጡ ቁጥር አንዱ ተዋናይ ተብሏል። 🐐
#selamshowbiz

የቦሊውድ ንጉስ ሻሩክ ካሃን ከእግርኳሱ 'GOAT' ሜሲ ጋር የፊታችን ቅዳሜ ሊገናኙ ነው
#ethiopia ||ሊዮኔል ሜሲ በህንድ የሚያደርገውን የ ‘GOAT india tour’ በመጀመሪያ ወደ ኮልካታ የሚያቀና ሲሆን፣ ሻሩክ ካሃንም ታህሳስ 13 በሳልት ሌክ ስታዲየም የእግርኳሱ ንጉስ ሜሲን ለማግኘት ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።
የኮልካታ ናይት ራይደርስ ክሪኬት ቡድን ባለቤት የሆነው ሻሩክ፣ አስደሳች ዜናውን በX ገፁ ላይ ያጋራ ሲሆን፣ አድናቂዎችም ቀድሞውንም በደስታ ተውጠዋል።
የቦሊውድ ባድሻ ሻሩክ እና የአርጀንቲናውን ኮከብ ግንኙነት በዓለም ህዝብ ዘንድ በጉጉት ይጠበቃል።

Comments