2 months ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ሲነሳ ስማቸው ከፊት ከሚሰለፉት ታላላቅ ከዋክብት መካከል፣ እንዲሁም በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን ስፖርት ፌዴሬሽንን (ESFNA) በመመስረትና በማሳደግ ወደር የለሽ አሻራ ካኖሩት የቁርጥ ቀን ልጆች አንዱ የሆኑት ጋሽ ፍስሐ ወልደአማኑኤል ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። "በጎ ስራ የሕይወት ስንቅ ነው" በሚለው የዘወትር መሪ ቃላቸው የሚታወቁት ጋሽ ፍስሐ፣ በኖሩበት አሜሪካ ሎስ አንጀለስ ከተማ ማረፋቸው ተሰምቷል።
ከሐረር ከተማ ወጣ ካለች አንዲት ትንሽ ቀበሌ ተወልደው በኳስ ፍቅር ያደጉት ጋሽ ፍስሐ፣ ቤተሰቦቻቸው ወደ አዲስ አበባ ሲዛወሩ ዳግማዊ ምኒልክ ትምህርት ቤት እየተማሩ ሳለ ነበር በታላቁ የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ዓይን ውስጥ የገቡት። በቅዱስ ጊዮርጊስ ማልያ የኢትዮጵያን እና የአዲስ አበባን ሻምፒዮና ደጋግመው በማንሳት የነገሱ ሲሆን፣ ለብሔራዊ ቡድንም በ5ኛ፣ 6ኛ እና 7ኛ የአፍሪካ ዋንጫዎች ላይ ሀገራቸውን ወክለው በድንቅ ብቃት ተጫውተዋል። ከረር ባሉት የሩቅ ምቶቻቸው "መድፈኛው"፣ በጥበበኛ አጨዋወታቸው ደግሞ "ኳስ ፊደሉ" የሚሉ የክብር ስሞችን አትርፈው ነበር።
እ.ኤ.አ. በ1969 በእግር ኳስ የትምህርት ዕድል (ስኮላርሺፕ) ወደ አሜሪካ ሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ (UCLA) በማቅናት የኳስ ህይወታቸውን በባህር ማዶ ቀጠሉ። ፕሮፌሽናል ተጫዋች በመሆንም የሜጀር ሊግ ሶከር (MLS) ቀዳሚ በነበረው ሊግ ውስጥ ለ'ሎስ አንጀለስ አዝቴካ' ክለብ ፈርመው፣ ከታዋቂው እንግሊዛዊ ጆርጅ ቤስት ጋር በአንድ ቡድን ተጫውተዋል። ጋሽ ፍስሐ በሜዳ ላይ ከዓለማችን ታላላቅ የእግር ኳስ ነገስታት ጋር ፊት ለፊት ተፋልመዋል፤ ከእነዚህም መካከል ብራዚላዊው ፔሌ፣ ጀርመኖቹ ሄንዝ ቤክንባወር እና ጌርድ ሙለር፣ ፖርቹጋላዊው ዩሴቢዮ፣ እንዲሁም ኔዘርላንዳዊው ዮሃን ክራይፍ ይገኙበታል። ይህም በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ እጅግ ብርቅዬ ከሚባሉ ገጠመኞች አንዱ ያደርገዋል።
ከእግር ኳሱ ጎን ለጎን ትምህርታቸውን በመከታተል ሁለት የተለያዩ የማስተርስ ዲግሪዎችን የጫኑት ጋሽ ፍስሐ፣ በ1978 እ.ኤ.አ. 'ሎስ አንጀለስ ስታርስ' የተባለውን ቡድን ከመሰረቱት አንዱ ነበሩ። ከሁሉ በላይ ግን በ1985 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ (ESFNA) የድርጅት ቅርጹን ሲይዝ የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት በመሆን ታሪካዊ ኃላፊነትን ተወጥተዋል።
ፕሬዚዳንትነቱን ካጠናቀቁ በኋላም ከፌዴሬሽኑ አልራቁም። በእግር ኳስ ውድድር ክፍል ውስጥ በበጎ ፈቃደኝነት ለ35 ዓመታት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ አገልግለዋል። ፌዴሬሽኑ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ ለ42 ተከታታይ ዓመታት በየዓመቱ በሚካሄደው ስፖርታዊ በዓል ላይ ያልተለዩ ሲሆን፣ በቅርቡ በተካሄደው የ2026ቱ በዓል ላይ ብቻ በህመማቸው ምክንያት መገኘት ሳይችሉ ቀርተው ነበር።
የጋሽ ፍስሐ በጎነት በስፖርቱ ሜዳ ብቻ የተወሰነ አልነበረም። "አጋር" የተሰኘ የረድኤት ድርጅት ከ27 ዓመታት በፊት በማቋቋም፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ረዳት የሌላቸውን ተማሪዎች እስከ ዶክተርነት እና የከፍተኛ ትምህርት እርከን ድረስ አስተምረዋል።
ለ50 ዓመታት በትዳር አብረዋቸው ከኖሩት ባለቤታቸው ወይዘሮ አልማዝ ጋር ሁለት ሴት ልጆችን (ጽዮን እና ናኦሚን) ያፈሩትና አራት የልጅ ልጆችን ያዩት ጋሽ ፍስሐ፣ በኖሩበት ማኅበረሰብ ዘንድ እጅግ የተከበሩና አገር ወዳድ ዜጋ ነበሩ። የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ በህልፈታቸው የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በመግለጽ፣ "በጎ ስራ የህይወት ስንቅ ነው" የሚለው መርሆቸው እና ግርማ ሞገሳቸው በየዓመቱ በሚደረገው የፌዴሬሽኑ ዝግጅት ላይ በመንፈስ አብሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

7 months ago
The Magic Man ሊዮኔል ሜሲ በነጩ ቤት ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ...
በኤፍሬም የማነ
#ethiopia | ሜሲ አንተ ታላቅ ኮኮብ ነህ ። አሜሪካን መርጠህ የአሜሪካን እግር ኳስ በማነቃቃትህ እንከብርሃለን ። አንተ እና ክርስትያኖ ሮናልዶ ድንቅ ስፖርተኞች ናችሁ ። የእኔ የምንግዜውም ምርጥ ፔሌ ነው ። ፔሌ ታላቅ ተጨዋች ነው ። ከፔሌ እና ከሜሲ ማን ይበልጣል ? ሰውየው በአዳራሹ የተሰበሰው ሰውን ሁሉ ጠየቁ ? ሁሉም ሜሲ አለ ? ዶናልድ ትራምፕ ቀጠሉ ። አዎ ይሄ ሰው ሳይበልጥ አይቀርም ። ፔሌ ድንቅ ነው ። ሜሲ ግን የምንግዜውም ምርጥ ነው ። በዚህ ሀሳብ እኔም እስማማለሁ ። ሜሲ የአሜሪካ እግር ኳስን እስከወዲኛው በመቀየርህ በድጋሜ እናመሰግናለን ። ይሄ ሰው የአለም ሻምፒዮን ነው ። ይሄ ሰው 47 የተለያዩ ታላላቅ ዋንጫዎችን በእግር ኳስ ያሸነፈ ተዓምረኛ ነው ። ሊዮ አንተ ታላቅ ተጨዋች ነህ ። በርካቶችን በዚህ ጥያቄ ማስማማት ችልሃል ። ይህ የአሜሪካው ፔሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በነጩ ቤት ኦቫል ኦፊሳቸው አርጀንቲናዊ ጥበበኛ ሊዮኔል ሜሲና የMLS ሻምፒዮኖቹን በተቀበሉት ዝግጅት የተናገሩት ነው ።
ዘመናዊው እግር ኳስ ባለፉት 20 ዓመታት ለውበት ሞናሊዛዋ አርጀንቲናዊ ክብር እንደሰገደች ዛሬም አለች ። ከሮዛሪዮ ሳንታፌ ተነስቶ በምትሃቱ ዓለምን የወረረው ሊዮኔል ሜሲ በባርሴሎና በከፍታው ጥግ አንፀባርቆ በፔዤ አድርጎ የዓለም እግር ኳስ ዋንጫን ከኳታር ሉሱያል ከህሊና መቼም ከማይጠፋ ተዓምሩ ጋር ድል ነስቶ በኢንተር ሚያሚ ደምቆ ዛሬም አለ ። The Magic Man ሊዮኔል ሜሲ በመጨረሻም ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር የMLS ዋንጫን ከሚያሚ ጋር አሸንፎ በWhite house ተገናኝቷል ። ጥያቄው በዚህ ፕሮግራም ለምን የኢንተር ሚያሚው ባለቤት የእንግሊዙ ኮኮብ ዴቭዴ ቤካም ያልተገኘው የሚለው ሆኗል ። እንደ የተለያዩ ዘገባዎች ቤክስ British Poster Boy በፓሪስ ፈረንሳይ የባለቤቱ
ቪክቶሪያ አንድ የፋሽን ዓለም አቀፍ ዝግጅት ላይ ለመታደም ሲል እንደቀረ ተዘግባል ።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ

ሜሲ ይመጣል ብሉ "ማስታወቂያ" ያሰራው ክለብ ተቀጣ
#ethiopia | ከሁለት ዓመታት በፊት በሜጀር ሊግ ሶከር (MLS) በኢንተር ሚያሚ እና በቫንኩቨር ዋይትካፕስ መካከል የተደረገው ጨዋታ፣ ዛሬም ድረስ በደጋፊዎች ዘንድ ቁጭትን ፈጥሮ ቆይቷል። ለዚህም ዋነኛው ምክንያት ክለቡ እና ሊጉ ሊዮኔል ሜሲን ጨምሮ እንደ ሱዋሬዝ እና ቡስኬትስ ያሉ ኮከቦች በጨዋታው ላይ እንደሚገኙ በሰፊው ማስተዋወቃቸው ነበር።
የቅጣቱ መንስኤ ምን ነበር?
በወቅቱ "ሜሲ ይመጣል" የሚለው ዜና ከፍተኛ ግርግር የፈጠረ ሲሆን፣ የስታዲየም መግቢያ ትኬቶች ከመደበኛው ዋጋ በእጅጉ እንዲንሩ አድርጎ ነበር። ሆኖም ጨዋታው ሲቃረብ ኮከቦቹ ሳይሳተፉ እንደሚቀሩ በመገለጡ፣ ውድ ትኬት የቆረጡ ደጋፊዎች ከፍተኛ ቅሬታ አቀረቡ።
የፍርድ ቤቱ ውሳኔ፦
"ተታለልን" ያሉ ደጋፊዎች በጋራ በመሆን የጀመሩት የሕግ ክርክር አሁን ፍሬ አፍርቷል። ፍርድ ቤቱ የደጋፊዎችን መብት በማስከበር የሚከተለውን ውሳኔ አስተላልፏል፡-
* የካሳ መጠን፦ ቫንኩቨር ዋይትካፕስ እና የሜጀር ሊግ ሶከር (MLS) በድምሩ 347,000 ዶላር ካሳ እንዲከፍሉ ተፈርዶባቸዋል።
* ምክንያት፦ ደጋፊዎች ኮከብ ተጫዋቾችን ለማየት የከፈሉትን ገንዘብ እና ያሳዩትን ታማኝነት ተገቢ ባልሆነ ማስታወቂያ መጠቀማቸው።
ይህ ውሳኔ በስፖርቱ ዓለም ክለቦች "የኮከብ ተጫዋቾችን" ስም ለማስታወቂያ ሲጠቀሙ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ትልቅ ማስጠንቀቂያ ሆኗል።
#lionelmessi #mls #intermiami #vancouverwhitecaps #footballnews #legalaction #messieffect

🐐 የኢንተር ሚያሚው ፊት አውራሪ
#ethiopia | በሜጀር ሊግ ሶከር (MLS) ታላቅ የፍሎሪዳ ደርቢ፣ ሊዮኔል ሜሲ ለተቃዋሚ አሰልጣኞች ድፍረትና ንቀት ምላሹ "በሜዳ ላይ የሚሰጥ ትምህርት" መሆኑን በድጋሚ አስመስክሯል።
ኢንተር ሚያሚ በኦርላንዶ ሲቲ ተመሪ ሆኖ የቆየበትን ጨዋታ በሜሲ አስደናቂ ብቃት 4 ለ 2 በሆነ ውጤት በመቀልበስ አሸንፏል።
🔄 ጨዋታው እንዴት ተቀለበሰ?
ጨዋታው ሲጀመር ኦርላንዶ ሲቲዎች ብርቱ ነበሩ። እስከ እረፍት ድረስ 2 ለ 0 እየመሩ ወደ መልበሻ ክፍል ሲያመሩ፣ የድሉ ባለቤት የሚሆኑ መስሎ ነበር። ሆኖም ከእረፍት መልስ ሜዳው የሊዮኔል ሜሲ የፈጠራ መድረክ ሆነ።
* ሜሲ በቁጥር፦ 2 ግቦችን አስቆጠረ፣ 1 ግብ የሚሆን ኳስ አመቻችቶ አቀበለ።
* አስገራሚው ስታቲስቲክስ፦ ሜሲ ከ2018 ወዲህ ብቻ 36 የቅጣት ምት ግቦችን ከመረብ አሳርፏል። ይህ ቁጥር በዚሁ ጊዜ ውስጥ ካስቆጠራቸው የፍፁም ቅጣት ምቶች (Penalties) በላይ መሆኑ ንጉሱ ኳስና መረብን ለማገናኘት የቆመ ኳስ ብቻ እንደሚበቃው ማሳያ ነው።
🗣️ "ልፈርምልህ?" — ሜሲ አሰልጣኙን ዝም ያስባለበት ቅጽበት
የምሽቱ ዋነኛ መነጋገሪያ ግን ከግቦቹ ባሻገር በሜሲ እና በኦርላንዶ ሲቲ አሰልጣኝ መካከል የተፈጠረው ፍጥጫ ነው።
የኦርላንዶ አሰልጣኝ ቡድናቸው 2 ለ 0 እየመራ ወደ እረፍት በሚወጡበት ወቅት ሜሲን ተጠግተው የሆነ ነገር ሲናገሩት ታይተዋል። ሜሲ በአሰልጣኙ ንግግር ደስተኛ እንዳልነበረ ፊቱ ላይ ይነበብ ነበር።
ምላሹ ግን እንዲህ ነበር፦
ሜሲ በሁለተኛው አጋማሽ አስደናቂ የቅጣት ምት ጎል አስቆጥሮ ቡድኑን ወደ አሸናፊነት ካመራ በኋላ፣ ወደ ተቃዋሚው አሰልጣኝ በማቅናት "ልፈርምልህ እንዴ?" የሚል ትርጉም ያለው የምልክት ምላሽ ሰጥቷቸዋል። "በንግግር ሳይሆን በኳስ እናሸንፋለን" የሚል መልዕክት ያዘለ ትዕይንት ነበር።
ሊዮኔል ሜሲ አሁንም በ30ዎቹ እድሜው መጨረሻ ላይ ሆኖ የእግር ኳስ ጥበብ ምን እንደሆነ ለዓለም እያሳየ ይገኛል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #lionelmessi #intermiami #mls #messimagic #footballnews #intermiamivsorlandocity #goat

10 months ago
ሜሲን ለማየት ጓጉተው ሿሿ የተሰሩት
የሕንድ እግር ኳስ ቤተሰቦች ...
በትሪቡን ስፖርት
#ethiopia | ነገሩ የንጉሱ የሕንድ ጉብኝት ነው ። የእግር ኳስ ውበት ሞናሊዛው ከMLS ገድሉ ማግስት አትላንቲክን አቋርጦ እነ ሻሩክ ሀገር ደርሷል ። የቅርብ ጓደኞቹ ዴፖልና ሱዋሬዝ አብረውት አሉ ።
ከ1.4 ቢሊዮን በላይ ህዝብ ያላት ሕንድ በእግር ኳስ አስቂኝ የአፍዝ አደንግዝ የማጂክ ታሪኳ ብቻ ብትታወቅም ምትሃተኛዋን አርጀንቲናዊ ኮኮብ ሊዮኔል ሜሲ ከእልፍ አድናቂዎቹ ልታገናኝ በዛውም የበለጠ ገፅታዋና ቱሪዝሟን ልታነቃቃ በወጠነችው ዕቅድ በኮልካታ ከተማ የሚገኘው 80 ሺህ በላይ ተመልካች የሚይዘው የሳልት ሌክ ስቴዲየሟን እስከ አፍንጫው ሞልታለች ።
የሜሲ 70 ጫማ 21 ሜትር የሚረዝመው በአድናቂዎቹ የተሰራ ሀውልትም በካልካታ ከተማ ግዛት ይመረቃል ።
የኳስ ምትሃተኛው ከቦሊውድ ዝነኛው ሻሩክም ይገናኛል ። ከአርጀንቲና ሮዛሪዮ ሳንታፌ በመነሳት በምትሃቱ ላለፉት 20 ዓመታት የዓለም እግር ኳስን የወረረው ኮኮብ የሶስት ቀናት ጉብኝት ለማድረግ ሕንድ ደርሷል ።
በሳልት ሌክ ስቴዲየም በተዓምሩ ምክንያት በአድናቆት ጨርቅ እያስጣለ በደስታ ያስፈነጠዛቸውን የሚወዱት ኮኮብ በህይወት ዘመናቸው አንዴ ዕንኳ በዐይናቸው ለመመልከት ከ1,900 ኪሎ ሜትሮች በላይ አቋርጠው ያላቸውን ነገር ሁሉ አሲይዘው ገና ካልሰሩበት ቀጣይ የወር ደሞወዛቸው ጭምር ቀድመው ተበድረው የሰርግ ቀናቸውን ጭምር ሰርዘው ከ1,500 ዶላር በላይ በጥቁር ገቢያ የተቸበቸበው ትኬትን ተሻምተው ገዝተው ስቴዲየም የተሰባሰቡ ሕንዳዊያን የእግር ኳስ ቤተሰቦች ግን ብዙ መስዋትነት በከፈሉለት የናፈቃቸው ቀን ያልተደራጀ መሰናዶ ተበሳጩ ።
የሚወዱትን ለዓመታት ያስጨፈራቸውን ኮኮብ ለደቂቃዎች ብቻ በሩቁ አይተው እንዲሰናበታቸው መደረጉ አበገናቸው ። በአዘጋጆቹ ቅጥፈት የተበሳጩ ደጋፊዎች የሳልት ሌክ ስቴዲየምንም አወደሙ ። ከፍተኛ ተቋውሞ በማስነሳት ከፀጥታ ኋይሎችም ተፋጠጡ ።
ተከድተናል ። ከፍተኛ ቅጥፈት ተፈፅሞብናል ። ሜሲን በአግባቡ ሳናየው ተለየን ። 20 ደቂቃ ሜዳው ላይ አልቆየም ። ምንም ዐይነት ከአድናቂዎቹ የሚገናኝበት ዝግጅት ሜዳው ላይ አልነበረም ። ኳስ ሲገፋ ፔናሊቲ ሲመታ አንዴ ዕንኳን ሜዳውን ዞሮ ሰላምታ እንዲሰጥ ከአድናቂዎቹ ጋር በቅርብ ርቀት እንዲገናኝ አልተደረገም ። አዘጋጆቹ ይሄንን ሁሉ ደጋፊ ሰብስበው አንድም የተዘጋጁበት ነገር አልነበረም ።
ሜሲ ኳስ እንደሚጫወት ጭምር ነው የተነገረን ! ይህ የለየለት ቅጥፈት ነው ። እራሱ ሜሲ በሁኔታው ሳይገረም አይቀርም ። የሚገርመው አዘጋጆቹ የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች የባለስልጣናቱ ልጆች እና የፀጥታ ኋይሎች ወደ መሃል ሜዳው አጅበው አስገብተው እራሳቸው ብቻ ተሻምተው ከሜሲ ፎቶ ተነስተው እንዳጀቡት ይዘውት ወጡ ። ተመልሶ ይመጣል ስንል በዛው ቀረ ። ጉዳዩ ከፀጥታ የደህንነት ስጋት ጋር እንደሆነም ያልተደራጀውን ዝግጅት ለማስተባበል ሲባል ተገለፀ ።
ሜሲ ድንቅ ነው ። ትሁትና የኳስ ምትሃተኛ ነው ። በዛች ውስን ደቂቃ ዕንኳ ለህንድ እግር ኳስ እልፍ አድናቂዎቹ ለተደረገለት አቀባበል ሁሉ ግራሲያስ India እያለ ምስጋናውን አቅርቦ በጥድፊያ ሜዳውን ፎቶ ለመነሳት በሚሻሙ አጀቦች መሃከል ለቀቀ ።
ያኔ messi messi messi በሚል ድምፆች በአድናቆት የደስታ ዕንባ ጭምር የቀለጠው የሳልት ሌክ ስቴዲየም በፍጥነት ወደ ጦር አውድማ ተቀየረ ።
ደጋፊዎች ያገኙትን ንብረት ሁሉ ይሰባብሩ ጀመር ። ወንበሮች የስቴዲየሙ ንብረቶች ሁሉ ወደሙ ። ሜሲን እናያለን ብለን ከፀጥታ ሀይሎች ተፋጠን ተጭበርብረን ከስረን በፖሊስ ተገርፈን ጭምር ወደ ቤታችን ተመለስን ።
አዘጋጆቹ ከፍተኛ ዝርፍያ ፈፅመውብናል ። ቃላቸውን አላከበሩም ። እንዴት ከ80ሺህ በላይ ደጋፊ ስቴዲየም አሰባስበው ሜሲን 20 ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ በሩቁ በብዙ አጀብ መሃከል ሰለምታ ሲሰጠን ብቻ እንድናየው አድርገው ይሸውዱናል ። በስሜታችን ቀልደዋል ። ለህይወት ዘመን ደስታችን አልተጨነቁም ። ለእግር ኳስ ባለን ፍቅር ገንዘባችንን ከስረናል ።
ጊዜያችንን አጥፍተናል ። ወደ ስቴዲየም ለመግባት ትኬት በጥቁር ገቢያ እስከ 1,500 ዶላር ተሽጧል ። ይህ ሜሲን ለማየት የሰርግ ቀኑን ጭምር ሰርዞ ዕድሜ ዘመኑን የሚያደንቀው ኮኮብን ለመመልከት ከመቶሺዎች ተጋፍቶ በርካታ ኪሎሜትሮችን አቋርጦ የነገ የትዳር የህይወት አጋሩን በደስታዋ ቀን አሳዝኖ ስቴዲየም ከተገኙ ደጋፊዎች መሃከል አንደኛው አስተያየየት ነው ። ሜሲን በማየት ከማገኘው የህይወቴ ደስታ የሚበልጥ ነገር ስለሌለ ዛሬ የነበረው የሰርግ ቀኔን ጭምር ሰርዣለሁ ።
ብዙ ዋጋ የከፈልኩበት ፕሮግራም ግን ያልተደራጀና በደጋፊዎች ስሜት ላይ ያላገጠ የቀጣፊዎች ነበር ። የነገ የትዳር አጋሬ ባለቤቴንም አሳዝኜ ዕድሜ ዘመኔን በኳስ ፍቅሬ ያስደሰተኝ ሜሲንም ለአንድ ደቂቃ ዕንኳ በአግባቡ ሳላይ ቀርቻለሁ ። ሜሲን ለማየት ዕዚህ ስቴዲየም ለመግባት የሰርግ ቀኔን ጭምር በመሰረዜ ምክንያት ስለ ደረሰብኝ የገንዘብ ኪሳራ ማስታወስ አልፈልግም ሲል በብስጭት ተናግሯል ።
የሕንድ ፖሊስ ከፍተኛ ንብረት ካወደሙ የተበሳጩ ደጋፊዎችን ድርጊት ካረጋጋ በኋላ ሜሲን ለማስመጣት ስራውን በሃላፊነት የወሰዱ የዝግጅቱ ዋና አስተባባሪዎችን ለፈፀሙት ያልተቀናጀ ደጋፊዎችን የማታለል ተግባር በቁጥጥር ስር በማዋል መጠየቅ ጀምሯል ።
ለተፈፀመው ገፅታን የሚያበላሽ ተግባር ደጋፊዎችንም ሊዮኔል ሜሲንም ይቅርታ ጠይቋል ። ነገሩ የዓለም ሚዲያዎችን ጭምር እያነጋገረ ይገኛል ። የአርጀንቲናዊው ጥበበኛ ሊዮኔል ሜሲ India tour ለሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን ከስቴዲየሙ ብጥብጥ በኋላ ከዝነኛው የቦሊውድ አክተር ሻሩክም መገናኘቱ ተገልጿል ። ሜሲ የሀገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ጭምር እንደሚያገኝ ተነግሯል ።
ታላቁን የዘመናዊው እግር ኳስ የማይደገም ምትሃተኛ ኮኮብ ለማየት ኪሣቸውን አራቁተው ስራቸውን ትተው የሰርግ ቀናቸውንም ጭምር ሰርዘው ከየአቅጣጫው የተመሙ የሕንድ እግር ኳስ ቤተሰቦች ግን ብዙ ዋጋ በከፈሉለት አጋጣሚ የተመኙትን ሳያገኙ የሚያደንቁት ኮኮብ ሜሲ ሲጫወት ለማየት የጓጉለለት አርጀንቲናዊው ምትሃተኛን ለደቂቃዎች ብቻ ሜዳ ላይ አሳይተው የነሷቸው ሿሿ የሰሯቸው የዝግጅቱ አስተባባሪዎችን እየረገሙ የሳልት ሌክ ስቴዲየምን አውድመው ከፀጥታ ሀይሎች ግርፍያ ጋር ወደ መጡበት በሀዘን ተመልሰዋል ።

Sponsored by
Surafel
10 months ago
ሜሲን ለማየት ጓጉተው ሿሿ የተሰሩት
የሕንድ እግር ኳስ ቤተሰቦች ...
ነገሩ የንጉሱ የሕንድ ጉብኝት ነው ። የእግር ኳስ ውበት ሞናሊዛው ከMLS ገድሉ ማግስት አትላንቲክን አቋርጦ እነ ሻሩክ ሀገር ደርሷል ። የቅርብ ጓደኞቹ ዴፖልና ሱዋሬዝ አብረውት አሉ ። ከ1.4 ቢሊዮን በላይ ህዝብ ያላት ሕንድ በእግር ኳስ አስቂኝ የአፍዝ አደንግዝ የማጂክ ታሪኳ ብቻ ብትታወቅም ምትሃተኛዋን አርጀንቲናዊ ኮኮብ ሊዮኔል ሜሲ ከእልፍ አድናቂዎቹ ልታገናኝ በዛውም የበለጠ ገፅታዋና ቱሪዝሟን ልታነቃቃ በወጠነችው ዕቅድ በኮልካታ ከተማ የሚገኘው 80 ሺህ በላይ ተመልካች የሚይዘው የሳልት ሌክ ስቴዲየሟን እስከ አፍንጫው ሞልታለች ። የሜሲ 70 ጫማ 21 ሜትር የሚረዝመው በአድናቂዎቹ የተሰራ ሀውልትም በካልካታ ከተማ ግዛት ይመረቃል ። የኳስ ምትሃተኛው ከቦሊውድ ዝነኛው ሻሩክም ይገናኛል ። ከአርጀንቲና ሮዛሪዮ ሳንታፌ በመነሳት በምትሃቱ ላለፉት 20 ዓመታት የዓለም እግር ኳስን የወረረው ኮኮብ የሶስት ቀናት ጉብኝት ለማድረግ ሕንድ ደርሷል ።
በሳልት ሌክ ስቴዲየም በተዓምሩ ምክንያት በአድናቆት ጨርቅ እያስጣለ በደስታ ያስፈነጠዛቸውን የሚወዱት ኮኮብ በህይወት ዘመናቸው አንዴ ዕንኳ በዐይናቸው ለመመልከት ከ1,900 ኪሎ ሜትሮች በላይ አቋርጠው ያላቸውን ነገር ሁሉ አሲይዘው ገና ካልሰሩበት ቀጣይ የወር ደሞወዛቸው ጭምር ቀድመው ተበድረው የሰርግ ቀናቸውን ጭምር ሰርዘው ከ1,500 ዶላር በላይ በጥቁር ገቢያ የተቸበቸበው ትኬትን ተሻምተው ገዝተው ስቴዲየም የተሰባሰቡ ሕንዳዊያን የእግር ኳስ ቤተሰቦች ግን ብዙ መስዋትነት በከፈሉለት የናፈቃቸው ቀን ያልተደራጀ መሰናዶ ተበሳጩ ። የሚወዱትን ለዓመታት ያስጨፈራቸውን ኮኮብ ለደቂቃዎች ብቻ በሩቁ አይተው እንዲሰናበታቸው መደረጉ አበገናቸው ። በአዘጋጆቹ ቅጥፈት የተበሳጩ ደጋፊዎች የሳልት ሌክ ስቴዲየምንም አወደሙ ። ከፍተኛ ተቋውሞ በማስነሳት ከፀጥታ ኋይሎችም ተፋጠጡ ።
ተከድተናል ። ከፍተኛ ቅጥፈት ተፈፅሞብናል ። ሜሲን በአግባቡ ሳናየው ተለየን ። 20 ደቂቃ ሜዳው ላይ አልቆየም ። ምንም ዐይነት ከአድናቂዎቹ የሚገናኝበት ዝግጅት ሜዳው ላይ አልነበረም ። ኳስ ሲገፋ ፔናሊቲ ሲመታ አንዴ ዕንኳን ሜዳውን ዞሮ ሰላምታ እንዲሰጥ ከአድናቂዎቹ ጋር በቅርብ ርቀት እንዲገናኝ አልተደረገም ። አዘጋጆቹ ይሄንን ሁሉ ደጋፊ ሰብስበው አንድም የተዘጋጁበት ነገር አልነበረም ። ሜሲ ኳስ እንደሚጫወት ጭምር ነው የተነገረን ! ይህ የለየለት ቅጥፈት ነው ። እራሱ ሜሲ በሁኔታው ሳይገረም አይቀርም ። የሚገርመው አዘጋጆቹ የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች የባለስልጣናቱ ልጆች እና የፀጥታ ኋይሎች ወደ መሃል ሜዳው አጅበው አስገብተው እራሳቸው ብቻ ተሻምተው ከሜሲ ፎቶ ተነስተው እንዳጀቡት ይዘውት ወጡ ። ተመልሶ ይመጣል ስንል በዛው ቀረ ። ጉዳዩ ከፀጥታ የደህንነት ስጋት ጋር እንደሆነም ያልተደራጀውን ዝግጅት ለማስተባበል ሲባል ተገለፀ ። ሜሲ ድንቅ ነው ። ትሁትና የኳስ ምትሃተኛ ነው ። በዛች ውስን ደቂቃ ዕንኳ ለህንድ እግር ኳስ እልፍ አድናቂዎቹ ለተደረገለት አቀባበል ሁሉ ግራሲያስ India እያለ ምስጋናውን አቅርቦ በጥድፊያ ሜዳውን ፎቶ ለመነሳት በሚሻሙ አጀቦች መሃከል ለቀቀ ። ያኔ messi messi messi በሚል ድምፆች በአድናቆት የደስታ ዕንባ ጭምር የቀለጠው የሳልት ሌክ ስቴዲየም በፍጥነት ወደ ጦር አውድማ ተቀየረ ። ደጋፊዎች ያገኙትን ንብረት ሁሉ ይሰባብሩ ጀመር ። ወንበሮች የስቴዲየሙ ንብረቶች ሁሉ ወደሙ ። ሜሲን እናያለን ብለን ከፀጥታ ሀይሎች ተፋጠን ተጭበርብረን ከስረን በፖሊስ ተገርፈን ጭምር ወደ ቤታችን ተመለስን ። አዘጋጆቹ ከፍተኛ ዝርፍያ ፈፅመውብናል ። ቃላቸውን አላከበሩም ። እንዴት ከ80ሺህ በላይ ደጋፊ ስቴዲየም አሰባስበው ሜሲን 20 ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ በሩቁ በብዙ አጀብ መሃከል ሰለምታ ሲሰጠን ብቻ እንድናየው አድርገው ይሸውዱናል ። በስሜታችን ቀልደዋል ። ለህይወት ዘመን ደስታችን አልተጨነቁም ። ለእግር ኳስ ባለን ፍቅር ገንዘባችንን ከስረናል ። ጊዜያችንን አጥፍተናል ። ወደ ስቴዲየም ለመግባት ትኬት በጥቁር ገቢያ እስከ 1,500 ዶላር ተሽጧል ። ይህ ሜሲን ለማየት የሰርግ ቀኑን ጭምር ሰርዞ ዕድሜ ዘመኑን የሚያደንቀው ኮኮብን ለመመልከት ከመቶሺዎች ተጋፍቶ በርካታ ኪሎሜትሮችን አቋርጦ የነገ የትዳር የህይወት አጋሩን በደስታዋ ቀን አሳዝኖ ስቴዲየም ከተገኙ ደጋፊዎች መሃከል አንደኛው አስተያየየት ነው ። ሜሲን በማየት ከማገኘው የህይወቴ ደስታ የሚበልጥ ነገር ስለሌለ ዛሬ የነበረው የሰርግ ቀኔን ጭምር ሰርዣለሁ ። ብዙ ዋጋ የከፈልኩበት ፕሮግራም ግን ያልተደራጀና በደጋፊዎች ስሜት ላይ ያላገጠ የቀጣፊዎች ነበር ። የነገ የትዳር አጋሬ ባለቤቴንም አሳዝኜ ዕድሜ ዘመኔን በኳስ ፍቅሬ ያስደሰተኝ ሜሲንም ለአንድ ደቂቃ ዕንኳ በአግባቡ ሳላይ ቀርቻለሁ ። ሜሲን ለማየት ዕዚህ ስቴዲየም ለመግባት የሰርግ ቀኔን ጭምር በመሰረዜ ምክንያት ስለ ደረሰብኝ የገንዘብ ኪሳራ ማስታወስ አልፈልግም ሲል በብስጭት ተናግሯል ።
የሕንድ ፖሊስ ከፍተኛ ንብረት ካወደሙ የተበሳጩ ደጋፊዎችን ድርጊት ካረጋጋ በኋላ ሜሲን ለማስመጣት ስራውን በሃላፊነት የወሰዱ የዝግጅቱ ዋና አስተባባሪዎችን ለፈፀሙት ያልተቀናጀ ደጋፊዎችን የማታለል ተግባር በቁጥጥር ስር በማዋል መጠየቅ ጀምሯል ። ለተፈፀመው ገፅታን የሚያበላሽ ተግባር ደጋፊዎችንም ሊዮኔል ሜሲንም ይቅርታ ጠይቋል ። ነገሩ የዓለም ሚዲያዎችን ጭምር እያነጋገረ ይገኛል ። የአርጀንቲናዊው ጥበበኛ ሊዮኔል ሜሲ India tour ለሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን ከስቴዲየሙ ብጥብጥ በኋላ ከዝነኛው የቦሊውድ አክተር ሻሩክም መገናኘቱ ተገልጿል ። ሜሲ የሀገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ጭምር እንደሚያገኝ ተነግሯል ። ታላቁን የዘመናዊው እግር ኳስ የማይደገም ምትሃተኛ ኮኮብ ለማየት ኪሣቸውን አራቁተው ስራቸውን ትተው የሰርግ ቀናቸውንም ጭምር ሰርዘው ከየአቅጣጫው የተመሙ የሕንድ እግር ኳስ ቤተሰቦች ግን ብዙ ዋጋ በከፈሉለት አጋጣሚ የተመኙትን ሳያገኙ የሚያደንቁት ኮኮብ ሜሲ ሲጫወት ለማየት የጓጉለለት አርጀንቲናዊው ምትሃተኛን ለደቂቃዎች ብቻ ሜዳ ላይ አሳይተው የነሷቸው ሿሿ የሰሯቸው የዝግጅቱ አስተባባሪዎችን እየረገሙ የሳልት ሌክ ስቴዲየምን አውድመው ከፀጥታ ሀይሎች ግርፍያ ጋር ወደ መጡበት በሀዘን ተመልሰዋል ።
Via ephrem yemaneh

🤗 የሊዮኔል ሜሲ 48ኛ ዋንጫ🏆
* የአንካራ ሜሲ አንካራ ሜሲ ገድል
ከአሜሪካ ሚያሚም ቀጥሏል ...
#ethiopia | ሊዮኔል ሜሲ በአሜሪካም ሚያሚም ነግሷል ።
ኢንተር ሚያሚ በታሪኩ ለመጀመሪያ ግዜ ቫንኮቨርን በመርታት የMLS ዋንጫ አሸናፊ ሆኗል ። ስፔናዊ የቀድሞዎ የባርሴሎና ድንቆች ጆርዲ አልባ እና ሰርጂዮ ቡስኬት በውጤታማ የእግር ኳስ ህይወታቸው የመጨረሻው መጨረሻ የሆነው የፍፃሜ ጨዋታን በሌላ የዋንጫ ክብር ፈፅመዋል ። ሜሲ እንደ ልማዱ የፍፃሜው ጨዋታ ኮኮብ ሆኖ አምሽቷል ። ሚያሚም የቶማስ ሙለር ቫንኮቨርን 3ለ1 ረቶ የሜጀር ሊግ ሶከር አውራ ሆኗል ።
የአርጀንቲናዊው ጥበበኛ ሊዮኔል ሜሲም በድል ምትሃት የደመቀ አንፀባራቂ የእግር ኳስ ህይወት ከልዕለ ኋያሏ የዓለማችን ሀገር አሜሪካም ቀጥሏል ።
የዴቪድ ቤካም ክለብ የሆነው የሆሊውድ ቅንጡዎች መናኻሪያው ክለብ ኢንተር ሚያሚ የሜሲን ግልጋሎት ማግኘት ከጀመረ በኋላ ህይወቱ እስከወዲኛው ባለፉት ዓመታት ከነበረበት የውጤት ዝቅታ ከመንደፋደፍ ወጥቶ ወደ ሻምፒዮንነት ተቀይሯል ።
አሰልጣኝ ሃቪየር ማሼራኖም በስልጠና ኬሪየሩ የመጀመሪያውን ዋንጫ ከሚያሚ ጋር ምትሃተኛው የሀገሩ ልጅ ሜሲን ይዞ አሸንፏል ። ሜሲ በረገጠበት ቦታ ሁሉ ለሰከንድ የማይጠፋው ታታሪው ሮድሪጎ ዴፖልም ከቦዲጋርድ ሚናው ጋር በቅርቡ አትሌቲኮን ለቆ በተቀላቀለው አንተር ሚያሚ ሻምፒዮን መሆን ችሏል ።
ሉዊስ ሱዋሬዝን ጨምሮ ንጉሱ የቅርብ ወዳጃቸውን ተከትለው ወደ ሚያሚ የጎረፉ እንደ ሰርጂዮ ቡስኬት ጆርዲ አልባ ሮድሪጎ ዴፖል የመሳሰሉ ኮኮቦች ከሚያሚ ጋር አዲስ ታሪክ ማስፃፍ ችለዋል ። አንካራ ሜሲ አንካራ ሜሲ ከአሜሪካ ሚያሚም ቀጥሏል ።
tribune sport

1 year ago
ከአሜሪካ ተጓዡ ቡድን አንድ ባለሙያ እዛው ቀርቷል
#ethiopia | ከዲሲ ዩናይትድ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ ወደ አሜሪካ ከተጓዘው የቡድኑ ስብስብ ውስጥ አንድ ባለሙያ አለመመለሱን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።
ያለፉትን ሁለት ተከታታይ ዓመታት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አሜሪካ በሚጓዝበት ወቅት ብዙ መወያያና አወዛጋቢ ርዕሶች የማይጣታ ሲሆን ቡድኑም ከትናንት በስትያ ከዲሲ ዩናይትድ ጋር ያደረገውን ጨዋታ በድል አጠናቆ በአሁኑ ሰዓት ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ በዋሽግተን ዲሲ ኤርፖርት ይገኛሉ።
ወደ ዩናይትድ ስቴስ ከተጓዙት 31 የልዑካን ቡድኑ አባላት መካከል አንድ ባለሙያ በዛው መቅረቱን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች። ይህም ግለሰብ የብሔራዊ ቡድኑ የኪት ማናጀር የሆነው አቶ ደምበላሽ እሸቱ(ሻምበል) መሆኑን ሰምተናል።
የዲሲ ዩናይትድ ክለብ መልማዮች የተመለከቷቸው አራት ተጫዋቾች ቢንያም በላይ፣ ከነዓን ማርክነህ፣ ሀብታሙ ተከስተ እና ራምኬል ጀምስ በአሜሪካ MLS እና USL ለመጫወት የሙከራ እድል ያገኙትን ሳይጨምር 27 የልዑካን ቡድን ወደ አዲስ አበባ የሚመለሱ ይሆናል ሲል #ሶከር ኢትዮጵያ በገጹ አስነብቧል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የትጥቅ ተቆጣጣሪ በአሜሪካ ቀረ
ከዲሲ ዩናይትድ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ ወደ አሜሪካ ከተጓዘው የቡድኑ ስብስብ ውስጥ አንድ ባለሙያ አለመመለሱን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።
ያለፉትን ሁለት ተከታታይ ዓመታት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አሜሪካ በሚጓዝበት ወቅት ብዙ መወያያና አወዛጋቢ ርዕሶች የማይጣታ ሲሆን ቡድኑም ከትናንት በስትያ ከዲሲ ዩናይትድ ጋር ያደረገውን ጨዋታ በድል አጠናቆ በአሁኑ ሰዓት ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ በዋሽግተን ዲሲ ኤርፖርት ይገኛሉ።
ወደ ዩናይትድ ስቴስ ከተጓዙት 31 የልዑካን ቡድኑ አባላት መካከል አንድ ባለሙያ በዛው መቅረቱን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች። ይህም ግለሰብ የብሔራዊ ቡድኑ የኪት ማናጀር የሆነው አቶ ደምበላሽ እሸቱ (ሻምበል) መሆኑን ሰምተናል።
የዲሲ ዩናይትድ ክለብ መልማዮች የተመለከቷቸው አራት ተጫዋቾች ቢንያም በላይ፣ ከነዓን ማርክነህ፣ ሀብታሙ ተከስተ እና ራምኬል ጀምስ በአሜሪካ MLS እና USL ለመጫወት የሙከራ እድል ያገኙትን ሳይጨምር 27 የልዑካን ቡድን ወደ አዲስ አበባ የሚመለሱ ይሆናል።
ሶከር ስፖርት

Comments