3 months ago
ስፔን ኦስትሪያን 3 ለ 0 በማሸነፍ 16ቱን ተቀላቀለች
*******************
በ23ኛው የዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ስፔን ኦስትሪያን 3 ለ 0 በመርታት ወደ 16ቱ ጥሎ ማለፍ ተሸጋግራለች።
ስፔንን ለድል ያበቋትን ሦስት ግቦች ሚኬል ኦያርዛባል በ36ኛው እና በ89ኛው ደቂቃ ላይ ሲያስቆጥር፤ ቀሪዋን አንድ ግብ ፔድሮ ፖሮ በ66ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል።
ስፔን በቀጣይ ዙር ጨዋታዋ ከፖርቹጋል እና ክሮሺያ አሸናፊ ጋር የምትገናኝ ይሆናል።
#worldcup #spain #austria #sports #ebc #fifa2026

9 months ago
በርካታ ዓለም አቀፍ አየር መንገዶች
ወደ ኢራን የሚደረጉ በረራዎችን ሰረዙ
በኢራን ውስጥ እየተካሄደ ያለውን መጠነ ሰፊ ፀረ-መንግስት ተቃውሞ፣ የመንግስት የኃይል እርምጃ እና የተጣለውን የኮሙኒኬሽን እገዳ ተከትሎ በርካታ ዓለም አቀፍ አየር መንገዶች ወደ ሀገሪቱ የሚያደርጉትን በረራ ማቋረጣቸውን አስታወቁ።
✈️ በረራቸውን ያቋረጡ አየር መንገዶች፦
ቅዳሜ (ጥር 2/2018 ዓ.ም) በረራቸውን ካቋረጡት መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦
Lufthansa (ጀርመን)
Turkish Airlines (ቱርክ) - 17 በረራዎችን ሰርዟል።
Flydubai (ዱባይ) - 17 በረራዎችን ሰርዟል።
Qatar Airways (ኳታር)
Emirates (ዱባይ)
Austrian Airlines፣ A-Jet እና Pegasus።
📉 የችግሩ መንስኤ፦
ተቃውሞው የጀመረው ታህሳስ 19 ቀን በቴህራን "ግራንድ ባዛር" የሀገሪቱ ገንዘብ (ሪያል) ዋጋ መርከስንና የኑሮ ውድነትን በመቃወም ሲሆን፣ አሁን ግን ወደ መንግስት ለውጥ ጥያቄ ተሸጋግሮ በመላ ሀገሪቱ ተስፋፍቷል።
⚠️ የሰብአዊ መብት ጥሰት ስጋት፦
መንግስት ተቃውሞውን ለመግታት ኢንተርኔትና ስልክ ሙሉ በሙሉ የዘጋ ሲሆን፣ በኖርዌይ የሚገኘው የኢራን ሰብአዊ መብቶች ድርጅት (IHR) እስካሁን 9 ህጻናትን ጨምሮ ቢያንስ 51 ሰዎች በጸጥታ ኃይሎች መገደላቸውን ገልጿል። በመቶዎች የሚቆጠሩ መቁሰላቸውና ከ2,200 በላይ ሰዎች መታሰራቸው ተዘግቧል።
ቀጣይ ሁኔታ፦
አየር መንገዶቹ ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተሉ መሆኑንና እንደ አስፈላጊነቱ የበረራ መርሃ ግብራቸውን እንደሚያስተካክሉ ገልጸዋል።

Comments