25 days ago
የብሪክስ ስብስብ ማዕከላዊነት እና የኢትዮጵያ በሳል ዲፕሎማሲያዊ ስኬት
**********************
በዘመናችን የዓለም አቀፍ የጂኦ-ፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ምህዳር ውስጥ የብሪክስ (BRICS) ጥምረት መፈጠር እና መጠናከር አዲሱን የባለብዙ ወገን የኃይል ሚዛን እውን በማድረግ ትልቅ ምዕራፍ ሆኗል።
የብሪክስ አባል ሀገራት ዛሬ ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተጽዕኖ አድማሳቸው በከፍተኛ ሁኔታ የሰፋ፣ የዓለም አቀፍ ሀብት፣ የምርጥ ቴክኖሎጂ እና የሰፊ ገበያ ማዕከልና መዳረሻ መሆናቸውን በተግባር እያረጋገጡ ይገኛሉ።
ብሪክስ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ እያሳየ የመጣው የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ዕድገት የዓለምን ትኩረት ስቧል። የዚህ ጥምረት አባል ሀገራት በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ ዋና ዋና የተፈጥሮ ሀብቶች፣ የነዳጅ እና የጋዝ ክምችቶች እንዲሁም የአግሮ-ኢንዱስትሪ ምርቶች ትልቁን ድርሻ ይይዛሉ።
በህዋ ሳይንስ፣ በዲጂታል ኢኮኖሚ፣ በታዳሽ ኃይል እና በኢንዱስትሪ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ እጅግ የገዘፉ የቴክኖሎጂ አቅሞችን በመገንባት የዓለምን የወደፊት አቅጣጫ እየመሩ ይገኛሉ። ከዓለም ሕዝብ ከ49 በመቶ የሚሆነውን የሚሸፍኑ በመሆናቸውም ከፍተኛ የማምረት እና የመግዛት አቅም ያለው ሰፊ ገበያ ያቀፉ ናቸው።
ይህ አቅማቸው ጥምረቱን በዓለም አቀፍ የንግድ፣ የፋይናንስ እና የልማት ሥርዓት ላይ ትልቅ ተጽዕኖ የመፍጠር አቅም እንዲኖረው አድርጎታል።
የብሪክስ አባልነት ጥቅምና ተጽዕኖ እያደገ በመምጣቱ በርካታ ሀገራት የጥምረቱ አባል ለመሆን ከፍተኛ ፍላጎትና ሽሚያ በሚያደርጉበት በዚህ ወቅት፣ ኢትዮጵያ የስብስቡ ሙሉ አባል መሆን መቻሏ ትልቅ የታሪክ እና የዲፕሎማሲ ስኬት ነው።
ይህ ስኬት በአጋጣሚ የመጣ ሳይሆን፣ ሀገራችን የተከተለችው በሳል፣ ገለልተኛ እና የብሔራዊ ጥቅምን አስቀድሞ የማስጠበቅ የዲፕሎማሲያዊ ጥረት ውጤት ነው።
ኢትዮጵያ የነበራትን ታሪካዊ የአፍሪካ የዲፕሎማሲ ማዕከልነት በመጠቀም፣ ከምስራቅም ሆነ ከምዕራብ ሀገራት ጋር ሚዛናዊ እና ፍሬያማ ግንኙነት በመገንባቷ ተቀባይነቷን አረጋግጣለች።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ የምትገኝበት አህጉራዊ እና ጂኦ-ፖለቲካዊ ቦታ፣ የሕዝብ ብዛት እና የኢኮኖሚ አቅሟ ጥምረቱ ለሚከተለው ዓላማ ትልቅ እሴት የሚጨምር በመሆኑ ተመራጭ አድርጓታል።
የብሪክስ አባል መሆኗ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተሰሚነት ከፍ ከማድረጉ ባሻገር የተለያዩ ሁለንተናዊ ጥቅሞች እንድታገኝ በር ይከፍታል። በዚህም የፋይናንስ እና የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማስፋት በአዲሱ የልማት ባንክ (New Development Bank) በኩል ለታላላቅ የመሰረተ ልማት እና የልማት ፕሮጀክቶች የሚሆን የፋይናንስ አቅርቦት የማግኘት ዕድልን ያሰፋል።
ከታዳጊ እና ከበለፀጉት የብሪክስ አባላት ጋር የሚደረግ የቴክኖሎጂ እና የእውቀት ሽግግር የሀገራችንን የኢንዱስትሪ እና የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ያፋጥናል። እንዲሁም የኢትዮጵያ ምርቶች ወደ ግዙፎቹ የብሪክስ ሀገራት ገበያ ያለአንዳች እንቅፋት እንዲገቡ እና የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት (FDI) ፍሰት እንዲጨምር በማድረግ ትልቅ ሚና ይጫወታል።
በመሆኑም የኢትዮጵያ የብሪክስ አባልነት የዲፕሎማሲያዊ ልህቀት ውጤት ሲሆን፣ ሀገራችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ተጽዕኖ ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገረ፣ ለወደፊት እድገቷም ትልቅ መሰረት የጣለ ታሪካዊ ክስተት ነው።
በአድማሱ አራጋው
#ethiopia #ebc #brics #brics2026 #globalsouth

1 month ago
ከጥገኝነት ወደ አምራችነት፦ የኢትዮጵያ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ እመርታ እና የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ስኬቶች
***************************
የአንዲት ሀገር የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት እና የረጅም ጊዜ ዕድገት የሚረጋገጠው ከውጭ ጥገኝነት ተላቅቃ የራሷን ፍላጎት በራሷ ማምረት ስትችል ነው።
የመደመር መንግሥት ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ የጀመራቸው “ኢትዮጵያ ታምርት” በሚል ሀገራዊ ንቅናቄ እና በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ ግብር፣ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን በማነቃቃት አስደናቂ ለውጦችን ማምጣት ጀምረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው የሰጡት ማብራሪያ፣ እንዲሁም የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአፈጻጸም ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት፣ የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ከውጭ ጥገኝነት በመላቀቅ የሀገር ውስጥ አቅምን ወደ መገንባት በተኪ ምርት የተሳካ ሽግግር እያደረገ ይገኛል።
የማምረት አቅም ማደግ እና የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ሚና
ለረጅም ጊዜ የኢትዮጵያ አምራች ኢንዱስትሪዎች ከነበራቸው የማምረት አቅም ከግማሽ በታች (በአማካይ 47 በመቶ) ብቻ ሲጠቀሙ ቆይተዋል። ይህ ዝቅተኛ አፈጻጸም በኃይል አቅርቦት መቆራረጥ፣ በውጭ ምንዛሬ እጥረት እና በጥሬ ዕቃ አቅርቦት ችግሮች የተተበተበ ነበር።
ሆኖም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምክር ቤቱ እንዳብራሩት፣ አሁን ላይ አጠቃላይ የማኑፋክቸሪንግ የማምረት አቅም ከ47 በመቶ ወደ 67 በመቶ ከፍ ሊል ችሏል።
የዚህ ከፍተኛ ለውጥ ዋነኛ ሞተር በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እየተመራ ያለው የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ ነው። ይህ ንቅናቄ በተለያዩ ምክንያቶች ተዘግተው የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፋብሪካዎች ወደ ሥራ እንዲመለሱ በማድረግ፣ እንዲሁም የአምራቾችን የፋይናንስ እና የመሠረተ ልማት ማነቆዎች በመፍታት ምርታማነትን በእጅጉ አነቃቅቷል።
➡ የኢንዱስትሪ ፓርኮች መስፋፋት እና የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ፖሊሲ ሌላኛው የትኩረት አቅጣጫ ምቹ የኢንቨስትመንት መሠረተ ልማት ማቅረብ ነው። እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ፣ ነባር ከሆኑት የኮምቦልቻ፣ የመቐለ እና የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በተጨማሪ ዐሥር አዳዲስ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን መገንባት ተችሏል።
የእነዚህ ፓርኮች መስፋፋት የሀገር ውስጥ አቅምን ከማጎልበት ባለፈ፣ ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነውን የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት (FDI) ወደ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ለመሳብ ትልቅ ሚና ተጫውቷል።
የውጭ ኢንቨስተሮች ቴክኖሎጂን ወደ ሀገር ውስጥ እንዲያመጡ እና የዕውቀት ሽግግር እንዲያደርጉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረጉ ይገኛሉ።
➡ የገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ መተካት፦ የ5 ቢሊዮን ዶላር ስኬት
ለዘመናት የኢትዮጵያን ማክሮ ኢኮኖሚ ሲፈታተን የነበረው ዋነኛ ችግር፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረት እና በገቢ ምርቶች ላይ ያለ ከፍተኛ ጥገኝነት ነበር።
ይህንን ለመቀልበስ "የውጭ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት የመተካት" ስትራቴጂ በተጠናከረ መልኩ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።
ሲሚንቶ፣ ብረት፣ ብርጭቆ እና ሴራሚክስን የመሳሰሉ ከባድ እና ወሳኝ የግንባታ/የኢንዱስትሪ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በማምረት ብቻ ወደ 5 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የውጭ ምንዛሬ ማዳን ተችሏል።
መንግሥት ቀደም ሲል በብዙ ቢሊዮን ዶላር ወደ ሀገር ውስጥ ይገቡ የነበሩ ምርቶችን በሒደት በሀገር ውስጥ ምርት የመተካት ፖሊሲውን በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል።
በግብርናው (በተለይም በስንዴ ምርት) የተገኘው የገቢ ምርትን የመተካት ስኬት ወደ ኢንዱስትሪው ዘርፍም በተጨባጭ ተሸጋግሯል።
➡ የተቀናጀ የዘርፎች ዕድገት
የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ መነቃቃት በሌሎች ተያያዥ ዘርፎች ላይም አዎንታዊ ተጽዕኖ አሳድሯል። የኢንዱስትሪ ዕድገት ብቻውን ሊመጣ አይችልም፤ ኃይል እና የጥሬ ዕቃ ግብዓት ይፈልጋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዘርፉ እያስመዘገበ ባለው ፈጣን ዕድገት ምክንያት፦ በማዕድን ዘርፍ 24 በመቶ፣ በማኑፋክቸሪንግ 20.3 በመቶ፣ እና በኢነርጂ ዘርፍ 23 በመቶ ጭማሪ መታየቱን አብራርተዋል። እነዚህ ሦስቱ ዘርፎች (ማዕድን፣ ኢንዱስትሪ እና ኢነርጂ) እርስ በርስ በመመጋገባቸው የመጣ "የተቀናጀ ዕድገት" (Synergy) መሆኑን ያሳያል።
➡ የወደፊቱ አቅጣጫ እና ራዕይ
የተገኙት ስኬቶች የጉዞው ጅማሮ እንጂ ማቆሚያ አይደሉም። ይህንን ስኬት ዘላቂ ለማድረግ በመጪው ዓመት ግልጽ ዒላማዎች ተቀምጠዋል። እነዚህም፦
በኢንዱስትሪ ፓርኮች ብቻ የ12.7 በመቶ ዕድገት ለማስመዝገብ እና ከኢንዱስትሪ ምርቶች ኤክስፖርት (ወጪ ንግድ) የ1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘት ሲሆኑ ለስኬቱም በትኩረት እየተሠራ ይገኛል።
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ዘርፍ እውነተኛ ዕምርታ እያሳየ ነው። “ኢትዮጵያ ታምርት” በሚለው ብሔራዊ ንቅናቄ በመመራት፣ የፋብሪካዎችን የማምረት አቅም ወደ 67 በመቶ ማሳደግ ተችሏል።
አዳዲስ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመክፈት ኢንቨስትመንትን መሳብ እና ቁልፍ የገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት 5 ቢሊዮን ዶላር ማዳን መቻሉም ሀገራችን ከሸማችነት ወጥታ ጠንካራ እና ራሷን የቻለች አምራች ኢኮኖሚ ወደ መገንባት የተጨበጠ ዕርምጃ መጀመሯን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
ራዕዩ ግቡን ሲመታም፣ የኢትዮጵያ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የብልጽግናዋ ዋነኛ የጀርባ አጥንት መሆኑ አይቀርም።
በዮናስ በድሉ
#ethiopia #ebc #industry #madeinethiopia #successstory

የኢትዮጵያ ስትራቴጂያዊ ዲፕሎማሲ፦ በተለዋዋጭ የዓለም ጂኦ-ፖለቲካዊ አውድ ሉዓላዊነትን እና የጋራ ተጠቃሚነትን የማረጋገጥ ጥበብ
**************************
ዓለማችን እጅግ ውስብስብ፣ ፈጣን እና ወደ ባለብዙ-ዋልታ የኃይል ሥርዓት እየተሸጋገረች ባለችበት በአሁኑ የታሪክ ምዕራፍ፣ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲን በብልሃት መምራት የሀገራት የሕልውና መሠረት ሆኗል።
ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ያጋጠሟትን ዐበይት ሀገራዊ ፈተናዎች እና ከባድ ዓለም አቀፍ ጫናዎች በብቃት በመቋቋም የተጓዘችበት ስልታዊ የዲፕሎማሲ አቅጣጫ፣ ሀገራችንን በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ያላትን የጂኦ-ፖለቲካዊ ተጽዕኖ ፈጣሪነት ወደ አዲስ ከፍታ አሸጋግሮታል።
ይህ እርምጃ ብሔራዊ ጥቅሟን እና ሉዓላዊነቷን በማስከበር ረገድም ታሪካዊ ፋይዳ ያለው ስኬት አስመዝግቧል።
ይህ ስኬት በአጋጣሚ የተገኘ ሳይሆን፣ ገቢር ነበብ የሆነው የውጭ ጉዳይ ፖሊሲያችን የዓለምን ፖለቲካዊ የኃይል ሚዛን መለዋወጥ በጥልቀት በማንበብ የተተገበረ በመሆኑ ነው።
ፖሊሲው ወዳጅ ማብዛትን እና በማንም ላይ ያላነጣጠረ ስትራቴጂያዊ ገለልተኝነትን መሪ መርሑ አድርጓል።
በዚህም፣ ከባህላዊ የምዕራባውያን አጋሮች ጋር ያለውን ታሪካዊ ግንኙነት በጋራ መከባበር ላይ በማነጽ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ከሩቅ ምሥራቅ፣ ከባህረ ሰላጤው ሀገራት እንዲሁም በፍጥነት በማደግ ላይ ካሉ ‘የግሎባል ሳውዝ’ ሀገራት ጋር ያለውን የትብብር ማዕቀፍ በማስፋት ጽኑ የኢኮኖሚ እና የኢንቨስትመንት ትሥሥርን መፍጠር ችሏል።
ኢትዮጵያ ከዓለም ጋር ያላትን ግንኙነት የምትበይንበት ማጠንጠኛ ሀገራዊ ሉዓላዊነትን፣ የዜጎችን ክብር እና የጋራ ተጠቃሚነትን መሠረት ያደረገ ነው።
ይህ በመርሕ ላይ የተመሠረተ አቅጣጫ ደኅንነቷን ከማስጠበቅ እና ኢኮኖሚዋን ከማሳደግ ባሻገር፣ ብሔራዊ ጥቅምን እና ሉዓላዊነትን ማንም የማይደፍረው ቀይ መስመር አድርጎ ይንቀሳቀሳል።
በሁለትዮሽም ሆነ በብዝኃ-ወገን መድረኮች፣ ሀገራችን ለየትኛውም የኃይል ጎራ በጭፍን ሳታደላ፣ በምክንያታዊነት ላይ የተመሠረተ ገቢር ነበብ ዲፕሎማሲን ትከተላለች።
የዚህ የነቃ ዲፕሎማሲ ደማቅ ፍሬዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ በግልጽ እየታዩ ነው። ከእነዚህ ታሪካዊ እና ዘላቂ ድሎች መካከል የኢትዮጵያ የብሪክስ አባልነት በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል።
ይህ ስትራቴጂያዊ ክስተት ኢትዮጵያ በደቡብ-ደቡብ ትብብር ውስጥ ያላትን መሪነት ያረጋገጠ፣ የፋይናንስ እና የንግድ አማራጮቿን ያሰፋ፣ እንዲሁም በዓለም አቀፍ የውሳኔ ሰጪ ተቋማት ውስጥ ያላትን የድርድር አቅም እና የጂኦ-ፖለቲካዊ ድምፅ በእጅጉ ያጎለበተ ነው።
በተመሳሳይ፣ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ የተመራው ጥበብ እና ጽናት የተሞላበት የውኃ ዲፕሎማሲ ሌላው የሉዓላዊነት ማረጋገጫ ነው። ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቷን ሦስተኛ ወገንን በማይጎዳ፣ ነገር ግን ፍትሐዊ እና ምክንያታዊ በሆነ መንገድ የመጠቀም መብቷን ለዓለም ማኅበረሰብ በማስረዳት፣ ጫናዎችን በሕግ እና በምክንያታዊነት በመመከት የግድቡን ግንባታ እና የውኃ ሙሌት በስኬት ማከናወን መቻሏ፣ ለአፍሪካ ሀገራት ትልቅ ማሳያ ሆኗል።
በቀጣናዊ ጂኦ-ፖለቲካ አኳያ፣ የአፍሪካ ቀንድ እና የቀይ ባሕር አካባቢ የዓለም ኃያላን ሀገራት የፍላጎት ግጭት ማዕከል በሆነበት በዚህ ዘመን፣ ኢትዮጵያ የቀጣናው የሰላም መልሕቅ ሆና ቀጥላለች። በአፍሪካ ቀንድ አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን፣ በኢጋድ እና በአፍሪካ ኅብረት በኩል የምታደርገው መሪነት የተሞላበት ጥረት፣ ለጎረቤት ሀገራት ደኅንነት እና ለአፍሪካውያን ፍትሐዊ ውክልና ያላትን ጽኑ አቋም ያረጋገጠ ነው።
እነዚህ ተከታታይ የዲፕሎማሲ ስኬቶች የፖለቲካዊ ትርፍ ብቻ ሳይሆኑ ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚ ዕድገት የተቀየሩ ናቸው። የተሳካው የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት (FDI) ፍሰትን በማሳደግ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርን በማፋጠን፣ እንዲሁም የንግድ እና የቱሪዝም ዘርፎችን በማነቃቃት ለሀገራዊ ብልጽግና ጠንካራ መሠረት ጥሏል።
ከዚህም ባሻገር፣ ዲፕሎማሲያችን የኢትዮጵያን የለስላሳ ኃይል በሚገባ የተጠቀመ ዜጋ-ተኮር አካሄድ ነው። በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን መብት እና ክብራቸው ተጠብቆ እንዲኖሩ ከመሥራት አልፎ ዳያስፖራው የሀገርን ገጽታ በመገንባት፣ ኢንቨስትመንትን በማሳደግ እና በሕዳሴ ግድቡ የትግል ወቅት እንዳስመሰከረው ብሔራዊ ጥቅምን በሚፈታተኑ ጫናዎች ላይ በአንድነት በመቆም የሉዓላዊነታችን ዋነኛ የጀርባ አጥንት መሆኑን አረጋግጧል።
በተለዋዋጭ የዓለም ሁኔታዎች ውስጥ የኢትዮጵያ መንግሥት እየተከተለው ያለው ዘመኑን የዋጀ፣ በምክንያታዊነት ላይ የተመሠረተ እና ንቁ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ፣ የሀገራችንን ብሔራዊ ጥቅም እና ሉዓላዊነት ከማስጠበቅ ባለፈ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን ተሰሚነት እና የጂኦ-ፖለቲካዊ ተጽዕኖ ፈጣሪነት ሚና ይበልጥ አጠናክሮት የሚቀጥል አስተማማኝ ጎዳና መሆኑን በተግባር አስመስክሯል።
በብሌን ደምበሎ
#ethiopia #ebc #diplomacy #nationalinterest #multipolar

2 months ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና ዳሰሳ) ጥምር ዜግነት (Dual Citizenship) በዓለማችን ላይ በርካታ ሀገራት የሚተገብሩት እና ዜጎቻቸው በሁለት ሀገራት ሙሉ መብት ኖሯቸው እንዲንቀሳቀሱ የሚያስችል ስርዓት ቢሆንም፣ በኢትዮጵያ ግን ይህ ጉዳይ አሁንም አከራካሪ እና የፖለቲካ ትኩሳት ሆኖ ቀጥሏል። ትናንት የተካሄደው የ500 ቡድኖች የምክክር መድረክም የዚሁ ውዝግብ ማሳያ ነው። በቀረበው ሰነድ መረጃ መሰረት፣ ጥምር ዜግነት በኢትዮጵያ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ እንዲፈቀድ አልተደረገም፤ ይልቁንም ወደፊት የሀገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ እየታየ፣ የተቋማት ግንባታ፣ የህግ የበላይነት እና የሰብአዊ መብቶች አያያዝ እያደገ ሲሄድ ሊታሰብበት እንደሚገባ ከስምምነት ላይ ተደርሷል። በዚህ የምክክር መድረክ ላይ የተሳተፉት የቁጫ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ተወካይ አቶ ዓለማየሁ አክሊሉ እንደገለጹት፣ በጉዳዩ ላይ ሀሳብ በነጻነት መንሸራሸሩን እና ልዩነቶች ቢኖሩም ወደ አላስፈላጊ ግጭት ሳይገባ መግባባት ላይ መደረሱን አብራርተዋል።
መድረኩ ጥምር ዜግነትን ለጊዜው እንዲታገድ ያደረገበት ዋነኛ ምክንያት "ከሀገር ሉዓላዊነት እና ደህንነት" ጋር በተያያዘ ነው። የጥምር ዜግነት መብት መፍቀድ ማለት የመምረጥ እና የመመረጥ መብትን የሚያጎናጽፍ በመሆኑ፣ አሁን ባለው የሀገሪቱ የእድገት ደረጃ ይህንን መብት መስጠት የሀገርን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ ሊጥል እና ወደ ወንጀል ሊያመራ ይችላል የሚል ጠንካራ ስጋት ተነስቷል። በተለይም ጥምር ዜግነት ሲፈቀድ እንደ ግብጽ፣ ኤርትራ እና ሱዳን ባሉ ሀገራት ለሚገኙ ዜጎች መብት እንዲያገኙ የሚያደርግ በመሆኑ፣ ይህ ደግሞ የሀገር ሚስጥርን አሳልፎ እስከመስጠት ሊያደርስ ስለሚችል ለጊዜው መከልከሉ እና ወደፊት የሀገሪቱን እድገት ግምት ውስጥ በማስገባት ሊከለስ እንደሚችል በ50 ንዑሳን፣ በ250 ወረዳዎች እና በ500 ቡድኖች አብላጫ ስምምነት ተደርሷል። ይሁን እንጂ፣ በውጭ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን አሁን ባለው አሰራር (በቢጫ ካርድ) ተጠቃሚ ሆነው በማንኛውም የሀገሪቱ ክፍል እየተንቀሳቀሱ በልማት እና በኢንቨስትመንት ዘርፍ የሚያደርጉትን ተሳትፎ እንዲቀጥሉ መግባባት ላይ ተደርሷል። በተጨማሪም በዚህ አጀንዳ ስር የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የሚከታተል ልዩ ፍርድ ቤት እንዲቋቋም ስምምነት ተደርሷል።
ነገር ግን ይህንን የኢትዮጵያን ስጋት ከዓለም አቀፍ ተሞክሮ ጋር አነጻጽረን ስንገመግመው ጥምር ዜግነትን ሙሉ በሙሉ መከልከል የራሱ የሆኑ ከባድ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዋጋዎች አሉት። ዛሬ ላይ እንደ አሜሪካ፣ ካናዳ፣ እንግሊዝ የመሳሰሉ የበለጸጉ ሀገራት ብቻ ሳይሆኑ፣ እንደ ኬንያ፣ ናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ሩዋንዳ የመሳሰሉ አፍሪካውያን ሀገራትም ጥምር ዜግነትን ፈቅደዋል። የእነዚህ ሀገራት ተሞክሮ እንደሚያሳየው ጥምር ዜግነት የዳያስፖራውን ሙሉ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ባለቤትነት ስሜት በማረጋገጥ ከፍተኛ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት (FDI) እና የዕውቀት ሽግግር እንዲመጣ ያደርጋል። ዜጎች በሁለቱም ሀገራት ያላቸውን ትስስር ተጠቅመው ለትውልድ ሀገራቸው ጠንካራ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ አምባሳደር (ሎቢስት) እንዲሆኑ እድል ይፈጥራል።
በመሆኑም የኢትዮጵያ መንግስት በአንድ በኩል ዳያስፖራው በልማት እና በኢንቨስትመንት እንዲሳተፍ ሲጋብዝ፣ በሌላ በኩል ግን የፖለቲካ ተሳትፎውን መገደቡ፣ በዳያስፖራው ዘንድ "ለሀገር ሀብት እንጂ ውሳኔ ሰጪ እንድንሆን አይፈለግም" የሚል ስሜት ሊፈጥር ይችላል። እርግጥ ነው፣ በአፍሪካ ቀንድ ያለው ፖለቲካዊ ውጥረት እና የጎረቤት ሀገራት የጂኦ-ፖለቲካዊ ፍጥጫ ጥንቃቄን ግድ ይላል። ይሁንና "የሀገር ሚስጥር አሳልፎ ከመስጠት" ጋር ተያይዞ የተነሳው ስጋት መሬት ላይ ያለ እውነት ቢሆንም፣ ይህንን መፍታት የሚቻለው መብቱን ሙሉ በሙሉ በማገድ ሳይሆን በህግ ማዕቀፍ በማስተካከል ነው። ለምሳሌ ሌሎች ሀገራት እንደሚያደርጉት፣ ጥምር ዜግነት ያላቸው ሰዎች ከፍተኛ የደህንነት፣ የመከላከያ ወይም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የሀገር መሪ እንዳይሆኑ ህገ-መንግስታዊ ገደብ በማበጀት፣ ሉዓላዊነትን ከማስጠበቅ ጎን ለጎን የዳያስፖራውን አቅም በተሻለ መልኩ መጠቀም ይቻላል። የጥምር ዜግነት መብትን "ለወደፊት የሀገሪቱ የዕድገት ደረጃ" ብሎ ማራዘም ከስጋት ለማምለጥ የሚደረግ ጊዜያዊ ማስታገሻ እንጂ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠረውን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አቅም በአግባቡ ለመጠቀም የሚያስችል ዘላቂ ስትራቴጂካዊ መፍትሔ አይመስልም።

5 months ago
ከ80 በላይ አገራትና ተቋማት ተወካዮች የኢትዮጵያን ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ጎበኙ
*******************
የተለያዩ አገራት አምባሳደሮች፣ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት እና የዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ተወካዮች ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችን ጎብኝተዋል።
ልዑካኑ የኮሙኒኬሽንና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (ICT) ፓርክን፣ የቦሌ ለሚ እና የቂሊንጦ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ጨምሮ የተለያዩ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችን ነው የጎበኙት።
ከ80 በላይ ከሚሆኑ ኤምባሲዎች የተውጣጡ አምባሳደሮች፣ የሚሲዮን መሪዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም የዓለም አቀፍ የልማት አጋር ተቋማት ከፍተኛ አመራሮችን ያካተተ የመስክ ምልከታ እየተካሄደ ይገኛል።
ጉብኝቱ ኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ያለችበትን ደረጃ ለማሳወቅና ያሉትን እምቅ ሀብቶች ለማስተዋወቅ ያለመ ነው።
በዚህ ወቅት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ሮዛ የሩቅነህ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ዘርፏን ይበልጥ እያጠናከረች ትገኛለች።
ኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ባከናወናቸው ስራዎች ቀዳሚ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት (FDI) ማዕከል መሆን መቻሏንም አምባሳደሯ ገልጸዋል።
በአባዲ ወይና
Ethiopian Broadcasting Corporation #

6 months ago
የአፍሪካ ድምፅ በቻይና
የሕግ ባለሙያው ቴዎድሮስ ጌታቸው በባዎ (BOAO) ፎረም
#ethiopia | ኢትዮጵያዊው ዓለም አቀፍ የህግ ባለሙያና አማካሪ ቴዎድሮስ ጌታቸው (TP)፣ አፍሪካን ወክለው በቻይና ሄይናን ግዛት በተካሄደውና 25ኛ ዓመቱን ባከበረው ታላቁ የኢንቨስትመንት ፎረም (Boao Forum) ላይ የጥናት ጽሁፋቸውን አቅርበዋል።
ታሪካዊ ውክልና
በአህጉር ደረጃ ተመርጠው በ"Rule of Law" ፓነል ላይ ከአውሮፓና እስያ ታዋቂ መሪዎችና ባለሙያዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።
አብረውት የተሳተፉ ታዋቂ ሰዎች
የቀድሞው የስሎቬንያ ፕሬዝዳንት ዳኒሎ ቱርክ፣ የዓለም አቀፉ ሜዲዬሽን ተቋም (IOMed) ዋና ፀሃፊ ቴሬሳ ቼንግ እና የBRILSA ፕሬዝዳንት ዋንግ ጁፌንግ።
ትኩረት ያደረጉባቸው ነጥቦች
የኢትዮጵያና የአፍሪካ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት (FDI) ዕድሎች፣ የድንበር ተሻጋሪ ንግድ ፈተናዎች፣ እና የነፃ ንግድ ቀጠናዎች አስፈላጊነት።
ተሳታፊዎች
የሲንጋፖር፣ አዘርባጃን፣ ስሪላንካና ካዛኪስታን መሪዎችን ጨምሮ ከ60 ሀገራት የተወከሉ 2,000 ልዑካን።
"multilateral cooperation እና Rule of Law ለዓለማችን ወቅታዊ ፈተናዎች ቁልፍ መፍትሄዎች ናቸው!" — ቴዎድሮስ ጌታቸው
#getu #lawandinvestment #internationaltrade #boaoforum #ethiopia #africarising #legalexcellence #hainan #china #tewodrosgetachew #ኢትዮጵያ #ንግድ #ህግ #ባዎፎረም #ጌጡተመስገን #getutemesgen

Sponsored by
Surafel
7 months ago
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ነገር እየተሳለጠ ነው ተባለ
#ethiopia | የኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት መስክ ማንም ሊያስቆመው የማይችል ፍጥነት ላይ የደረሰ ይመስላል። በስድስት ወራት ውስጥ ብቻ የተመዘገበው የ2.34 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት (FDI) ፍሰት “ሪከርድ” የተባለ ስኬት ሆኖ ተመዝግቧል።
የኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ዶክተር ዘለቀ ተመስገን ለስፑቲኒክ አፍሪካ እንደገለጹት ከሆነ፣ ይህ አሃዝ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ20% እድገት አሳይቷል። በነዚህ ስድስት ወራት ውስጥ ብቻ 245 አዳዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃዶች መሰጠታቸው የሀገሪቱን የኢንቨስትመንት ከባቢ ማራኪነት ማሳያ ሆኗል።
በአፍሪካ መሪነት ላይ
ይህ አስደናቂ እድገት ኢትዮጵያን በአህጉራዊ ደረጃ የጥንካሬ ምልክት አድርጓታል። እንደ ኮሚሽነሩ ገለጻ፦
* ኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ፍሰት ከአፍሪካ ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች።
* በምስራቅ አፍሪካ ደግሞ ቀዳሚዋ ሀገር መሆን ችላለች።
ወደፊት ምን ይጠበቃል?
የኢንቨስትመንት ጉዞው በዚሁ የሚያበቃ አይደለም። ከመጋቢት 17 እስከ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. በሚካሄደው 4ኛው "በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ" (Invest in Ethiopia) የኢንቨስትመንት ፎረም ላይ ትልቅ ተስፋ ተጥሏል። በዚሁ ፎረም ላይ ብቻ የ2.4 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው አዳዲስ የኢንቨስትመንት ስምምነቶች ይፈረማሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ባለሀብቶች ወደ ኢትዮጵያ እያደረጉት ያለው ይኸው ግስጋሴ፣ ሀገሪቱ ለዓለም አቀፍ ንግድና ልማት ያላትን ዝግጁነት በግልጽ የሚያሳይ ነው።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ethiopia #investment #economy #fdi #investinethiopia #africabusiness #eastafrica #ኢትዮጵያ

8 months ago
የዶላር ዳግም ልደት ወይስ የኢኮኖሚ ቁማር? የኢትዮጵያ “ቢግ ባንግ” ሪፎርም እና የነፃ ገበያ መገፋፋት
1. የካቲት 4 ቀን 2018 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ይፋ ያደረገው የውጭ ምንዛሪ መመሪያ፣ ዝም ብሎ የቴክኒክ ሰነድ አይደለም፤ ይልቁንም ላለፉት 50 ዓመታት የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ደም ስር አንቆ የያዘውን “የቁጥጥር ሰንሰለት” የሚበጣጥስ መጥረቢያ ነው። ይህ 19 ነጥቦችን የያዘው አዋጅ፣ ኢትዮጵያ በታሪኳ አድርጋው የማታውቀውን የኢኮኖሚ “ቢግ ባንግ” (Big Bang) ሽግግር መጀመሯን ያበስራል። በኢኮኖሚ ፈላስፎች መነጽር ሲታይ፣ ይህ እርምጃ አዳም ስሚዝ “የማይታየው እጅ” (Invisible Hand) ብሎ የጠራውን ገበያ መር ስርዓት በኢትዮጵያ ምድር ለመትከል የተደረገ ደፋር ሙከራ ነው።
2. የዚህ ሪፎርም ዋነኛው መነሻ ከአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ጋር የተደረሰው የ 3.4 ቢሊዮን ዶላር የብድር ስምምነት ቢሆንም፣ ውስጣዊ ፍላጎቱ ግን የኢትዮጵያን የውጭ ምንዛሪ ረሃብ በዘላቂነት መፍታት ነው። ቀደም ሲል በኦፊሴላዊው የምንዛሪ ዋጋ እና በጥቁር ገበያው መካከል የነበረው ልዩነት (Premium) ከ 100% በላይ ማደጉ፣ ምርት ወደ ውጭ የሚላክበትን ሳይሆን ዶላር የሚሸሸግበትን ኢኮኖሚ ፈጥሮ ነበር። አዲሱ መመሪያ ይህንን “የጥላ ኢኮኖሚ” አፍርሶ፣ ዶላርን ከጓዳ ወደ ባንክ አደባባይ ለማውጣት የታለመ ነው።
3. የአገልግሎት ላኪዎች 100% ገቢያቸውን እንዲይዙ መፈቀዱ (አንቀጽ 1)፣ ከቲዮሪ አንጻር “የባለቤትነት መብት” (Property Rights) ማረጋገጫ ነው። ጆን ሎክ እንደሚለው፣ አንድ ሰው በጥረቱ ያገኘውን ሀብት የመጠቀም ሙሉ መብት ሊኖረው ይገባል። መንግስት ቀደም ሲል ከላኪዎች ላይ ይነጥቅ የነበረውን 50% እና ከዚያ በላይ ድርሻ መተዉ፣ ላኪዎች ይበልጥ እንዲያመርቱ ትልቅ ማበረታቻ (Incentive) ይፈጥራል። ይህ ደግሞ በረዥም ጊዜ የሀገሪቱን የወጪ ንግድ ገቢ በቢሊዮን ዶላሮች እንደሚያሳድገው ይጠበቃል።
4. ግለሰቦች ለቤተሰቦቻቸው እስከ 3,000 ዶላር እንዲልኩ መፈቀዱ (አንቀጽ 8)፣ የመንግስትን የቁጥጥር ስፋት (State Scope) በእጅጉ ይቀንሳል። ይህ እርምጃ ሚልተን ፍሪድማን “Capitalism and Freedom” በሚለው መጽሐፉ የጠቀሰውን የግል ኢኮኖሚ ነፃነት የሚያንፀባርቅ ነው። ዜጎች በገዛ ገንዘባቸው የልጆቻቸውን ትምህርትና ህክምና እንዲከፍሉ መፈቀዱ፣ በህዝብና በመንግስት መካከል ለዘመናት ተሸርሽሮ የነበረውን ማህበራዊ ውል (Social Contract) መልሶ የማደስ አቅም አለው።
5. ዳታዎች እንደሚያሳዩት፣ ኢትዮጵያ በየአመቱ ከዳያስፖራ የምታገኘው ሬሚታንስ (Remittance) ከ 5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ቢሆንም፣ ከግማሽ በላይ የሚሆነው በህገ-ወጥ መንገድ ይዘዋወር ነበር። አዲሱ መመሪያ ዶላርን ያለ ሰነድ መመንዘር መፍቀዱ (አንቀጽ 7)፣ ይህን በጥቁር ገበያ የሚመላለሰውን ቢሊዮን ዶላር ወደ ህጋዊው ስርዓት የሚመልስ “መግነጢሳዊ ኃይል” ነው። ይህ የገንዘብ ፍሰት ወደ ባንኮች ሲገባ፣ ባንኮች ለኢንዱስትሪው የሚሰጡት የብድር አቅም (Liquidity) በእጥፍ ሊያድግ ይችላል።
6. የውጭ ኢንቨስተሮች ትርፋቸውን ያለ ገደብ እንዲያወጡ መፈቀዱ (አንቀጽ 16) ግን የሁለት ስለት ቢላዋ ነው። ለዴቪድ ሪካርዶ የንግድ ቲዮሪ ተከታዮች፣ ይህ እርምጃ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን (FDI) የሚስብ ማር ነው። ሆኖም፣ እንደ ጆሴፍ ስቲግሊዝ ያሉ ሊቃውንት “የካፒታል ሽሽት” (Capital Flight) ስጋትን ያነሳሉ። በሀገር ውስጥ የፖለቲካ አለመረጋጋት ቢከሰት፣ ኢንቨስተሮች ያላቸውን ዶላር ይዘው በአንድ ጀምበር ቢወጡ፣ የኢትዮጵያ የውጭ መጠባበቂያ ክምችት (Foreign Reserve) ድንገት ሊሟጠጥ ይችላል።
7. የባንኮች ራስ-ገዝነት (Autonomy) መጨመር ሌላው የዚህ ሪፎርም ምሰሶ ነው። ባንኮች የፎርዋርድ ግብይት (Forward Transaction) እንዲያካሂዱ መፈቀዱ (አንቀጽ 9)፣ ነጋዴዎች ለወደፊት ግዢዎቻቸው የምንዛሪ ዋጋን ቀድመው እንዲቆልፉ (Hedging) ይረዳቸዋል። ይህ በንግድ ዓለም ውስጥ ያለውን እርግጠኛ አለመሆን (Uncertainty) በመቀነስ፣ የዋጋ ግሽበትን ለማረጋጋት የሚረዳ ዘመናዊ የፋይናንስ መሳሪያ ነው።
8. ይሁን እንጂ፣ ባንኮች ከካፒታላቸው 10% ዋስትና እንዲሰጡ መፈቀዱ (አንቀጽ 14) ልብ አንጠልጣይ አደጋ አለው። የኢትዮጵያ ባንኮች በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ቀውስ የመመታት ልምድ የላቸውም። ባንኮች የገቡት ዋስትና ተቀባይነት አጥቶ ወይም ብድሩ ሳይከፈል ቢቀር፣ የሀገር ውስጥ ባንኮች መክሰር (Bank Failure) ደረጃ ሊደርሱ ይችላሉ። ይህ ደግሞ በዜጎች ቁጠባ ላይ ትልቅ አደጋ ስለሚደቅን፣ የብሔራዊ ባንክ የቁጥጥር ዓይን (Supervision) እጅግ ንቁ መሆን አለበት።
9. የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች ጥሬ ገንዘብ የመያዝ አቅማቸው ወደ 25% ማደጉ (አንቀጽ 18)፣ የገበያውን የዶላር ዝውውር (Circulation) ያቀልጠዋል። ይህ እርምጃ የጥቁር ገበያ ደላሎችን ከስራ የሚያስወጣ ቢሆንም፣ አዲሶቹ የፍቃድ ባለቤቶች ራሳቸው ወደ “ህጋዊ ደላላነት” እንዳይቀየሩ ጥብቅ ኦዲት ይፈልጋል። የገንዘብ ማጠብ (Money Laundering) ወንጀሎችን ለመከላከል የዲጂታል ክትትል ስርዓት የግድ ይላል።
10. የቬትናምን ተሞክሮ ብንመለከት፣ ሀገሪቱ በ 1980 ዎቹ መጨረሻ መሰል እርምጃ ስትወስድ፣ በአምራች ዘርፉ ላይ ትልቅ ስራ ሰርታ ነበር። ኢትዮጵያ ግን አሁንም 80% የምትጠቀመውን ሸቀጥ ከውጭ ታስገባለች። ዶላር በነፃነት መዘዋወሩ ብቻውን ለውጥ አያመጣም፤ የምርት አብዮት ካልታከለበት፣ ነፃ ገበያው የውጭ ሀገራት ምርቶች መጣያ (Dumping ground) የመሆን አደጋ አለው።
11. የዋጋ ግሽበት (Inflation) የዚህ ሪፎርም ትልቁ ጠላት ነው። የምንዛሪ ዋጋው ለገበያ ሲተው፣ የብር ዋጋ መውደቁ አይቀሬ ነው። ይህ ደግሞ የመድኃኒት፣ የነዳጅ እና የፋብሪካ ጥሬ እቃዎች ዋጋን ሊያስንረው ይችላል። ኬይንስ እንደሚለው፣ በመካከለኛ ጊዜ ኢኮኖሚው ቢረጋጋም፣ “በመጨረሻ ሁላችንም እንሞታለን”። ስለዚህ ዝቅተኛው ማህበረሰብ በዚህ የሽግግር ወቅት በኑሮ ውድነት እንዳይቀጠቀጥ መንግስት የማህበራዊ ድጋፍ መረቦችን ማጠናከር አለበት።
12. 100 ዶላር የነበረው የሂሳብ መክፈቻ መቅረት (አንቀጽ 5)፣ ለድሃው ዜጋ የተሰጠ የኢኮኖሚ “ዲሞክራሲ” ነው። ይህም የባንክ አገልግሎት ተደራሽነትን (Financial Inclusion) በመጨመር፣ ህዝቡ በዶላር እንዲቆጥብና የሀገር ውስጥ ካፒታል እንዲያድግ ያደርጋል። ይህ የባህሪ ለውጥ (Behavioral Change) በረዥም ጊዜ የሀገሪቱን የቁጠባ ባህል ይቀይረዋል።
13. ድርጅቶች ከሀገር ውጭ መዋእለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ መፈቀዱ (አንቀጽ 6) ግን እጅግ አነጋጋሪ ነው። ኢትዮጵያ ራሷ የካፒታል እጥረት ባለባት ሁኔታ፣ የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ዶላር ይዘው ወደ ውጭ እንዲወጡ መፈቀዱ በምን ስሌት እንደመጣ ግልጽ አይደለም። ይህ ነጥብ ባለሀብቶች ሀብታቸውን ወደ አስተማማኝ ሀገራት እንዲያሸሹ (Flight to Safety) በር ሊከፍት ይችላል።

🚀 የደቡብ አፍሪካው የፋይናንስ ግዙፍ "አብሳ" ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት አይኑን ጥሏል!
— በ78 ቢሊዮን ዶላር ሀብቱ የሚታወቀው አብሳ፣ የኢትዮጵያን የባንክ ዘርፍ ለመቀላቀል የመንግሥትን "አረንጓዴ መብራት" እየጠበቀ ነው —
በአፍሪካ ካሉ ግዙፍ ባንኮች አንዱ የሆነው አብሳ ግሩፕ (Absa Group)፣ በኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ ውስጥ በባለቤትነት ለመሳተፍ ያለውን ዝግጁነት በድጋሚ አረጋገጠ። ባንኩ በቅርቡ የወጣውን የውጭ ባንኮች መግቢያ መመሪያ ቢያደንቅም፣ ይበልጥ "ተለዋዋጭ" የሆኑ ተጨማሪ ማሻሻያዎች እንዲደረጉ ይፈልጋል።
📊 አብሳ ግሩፕ በቁጥር፦ ለምን ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ ትልቅ ዜና ሆነ?
አብሳ ወደ ኢትዮጵያ ገበያ መግባቱ የፋይናንስ ዘርፉን ሊያነቃቃ ይችላል ተብሎ የሚጠበቀው በሚከተሉት ምክንያቶች ነው፦
ግዙፍ የሀብት አቅም፦ በአሁኑ ወቅት የባንኩ ጠቅላላ የሀብት መጠን (Total Assets) ከ 1.5 ትሪሊዮን የደቡብ አፍሪካ ራንድ (በግምት 78 ቢሊዮን ዶላር) በላይ ነው።
አህጉራዊ ተደራሽነት፦ በ12 የአፍሪካ አገራት (ኬንያ፣ ጋና፣ ቦትስዋና፣ ሞሪሸስ...) ከ 12 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች አሉት።
የቴክኖሎጂ አቅም፦ ባንኩ በዲጂታል ባንኪንግ እና በኢንቨስትመንት ዘርፍ በአፍሪካ ቀዳሚ ከሚባሉት አንዱ ነው።
🔍 የአብሳ የኢትዮጵያ "ስትራቴጂ" ምንድነው?
እንደ ዘ ኢስት አፍሪካን ዘገባ፣ አብሳ ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት የሚከተሉትን ስልቶች ይከተላል ተብሎ ይጠበቃል፦
የባንክ ድርሻ መግዛት (Acquisition)፦ ባንኩ አዲስ ቅርንጫፍ ከመክፈት ይልቅ፣ አትራፊ የሆኑ የኢትዮጵያ የግል ባንኮችን ድርሻ (Share) በመግዛት በሽርክና መስራት ይመርጣል።
የድርጅቶች ባንኪንግ (Corporate Banking)፦ ባንኩ በዋናነት ትኩረት የሚያደርገው ግዙፍ ፕሮጀክቶች፣ ማኑፋክቸሪንግ እና የንግድ ፋይናንስ ላይ ነው።
የፖሊሲ ማሻሻያ ጥያቄ፦ ባንኩ የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር እና የትርፍ አወጣጥ (Profit Repatriation) ላይ መንግስት ተጨማሪ ማሻሻያዎችን እንዲያደርግ ፍላጎት አለው።
⚔️ የውጭ ባንኮች "ፉክክር" በኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ባንኮች እስከ 40% ድረስ በሀገር ውስጥ ባንኮች ላይ ድርሻ እንዲኖራቸው መፍቀዱን ተከትሎ፣ አብሳ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም ደጅ እየጠኑ ነው፦
KCB እና Equity Bank (ኬንያ)፦ አስቀድመው ቢሮ በመክፈት ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል።
Standard Chartered እና EFG Hermes፦ ገበያውን ለማጥናት ከፍተኛ ፍላጎት አሳይተዋል።
Standard Bank፦ የአብሳ ዋነኛ ተፎካካሪ ሲሆን፣ እሱም ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት እንቅስቃሴ ጀምሯል።
💡 ለኢትዮጵያውያን ምን ትርጉም አለው?
👉አብሳን የመሰሉ ግዙፍ ባንኮች መግባት፦
ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የብድር አቅርቦት ይጨምራል።
👉የአገልግሎት ጥራት እና የዲጂታል ክፍያ ስርአትን ያዘምናል።
👉የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰትን (FDI) ያሳድጋል።
— በ78 ቢሊዮን ዶላር ሀብቱ የሚታወቀው አብሳ፣ የኢትዮጵያን የባንክ ዘርፍ ለመቀላቀል የመንግሥትን "አረንጓዴ መብራት" እየጠበቀ ነው —
በአፍሪካ ካሉ ግዙፍ ባንኮች አንዱ የሆነው አብሳ ግሩፕ (Absa Group)፣ በኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ ውስጥ በባለቤትነት ለመሳተፍ ያለውን ዝግጁነት በድጋሚ አረጋገጠ። ባንኩ በቅርቡ የወጣውን የውጭ ባንኮች መግቢያ መመሪያ ቢያደንቅም፣ ይበልጥ "ተለዋዋጭ" የሆኑ ተጨማሪ ማሻሻያዎች እንዲደረጉ ይፈልጋል።
📊 አብሳ ግሩፕ በቁጥር፦ ለምን ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ ትልቅ ዜና ሆነ?
አብሳ ወደ ኢትዮጵያ ገበያ መግባቱ የፋይናንስ ዘርፉን ሊያነቃቃ ይችላል ተብሎ የሚጠበቀው በሚከተሉት ምክንያቶች ነው፦
ግዙፍ የሀብት አቅም፦ በአሁኑ ወቅት የባንኩ ጠቅላላ የሀብት መጠን (Total Assets) ከ 1.5 ትሪሊዮን የደቡብ አፍሪካ ራንድ (በግምት 78 ቢሊዮን ዶላር) በላይ ነው።
አህጉራዊ ተደራሽነት፦ በ12 የአፍሪካ አገራት (ኬንያ፣ ጋና፣ ቦትስዋና፣ ሞሪሸስ...) ከ 12 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች አሉት።
የቴክኖሎጂ አቅም፦ ባንኩ በዲጂታል ባንኪንግ እና በኢንቨስትመንት ዘርፍ በአፍሪካ ቀዳሚ ከሚባሉት አንዱ ነው።
🔍 የአብሳ የኢትዮጵያ "ስትራቴጂ" ምንድነው?
እንደ ዘ ኢስት አፍሪካን ዘገባ፣ አብሳ ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት የሚከተሉትን ስልቶች ይከተላል ተብሎ ይጠበቃል፦
የባንክ ድርሻ መግዛት (Acquisition)፦ ባንኩ አዲስ ቅርንጫፍ ከመክፈት ይልቅ፣ አትራፊ የሆኑ የኢትዮጵያ የግል ባንኮችን ድርሻ (Share) በመግዛት በሽርክና መስራት ይመርጣል።
የድርጅቶች ባንኪንግ (Corporate Banking)፦ ባንኩ በዋናነት ትኩረት የሚያደርገው ግዙፍ ፕሮጀክቶች፣ ማኑፋክቸሪንግ እና የንግድ ፋይናንስ ላይ ነው።
የፖሊሲ ማሻሻያ ጥያቄ፦ ባንኩ የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር እና የትርፍ አወጣጥ (Profit Repatriation) ላይ መንግስት ተጨማሪ ማሻሻያዎችን እንዲያደርግ ፍላጎት አለው።
⚔️ የውጭ ባንኮች "ፉክክር" በኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ባንኮች እስከ 40% ድረስ በሀገር ውስጥ ባንኮች ላይ ድርሻ እንዲኖራቸው መፍቀዱን ተከትሎ፣ አብሳ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም ደጅ እየጠኑ ነው፦
💡 ለኢትዮጵያውያን ምን ትርጉም አለው?
👉አብሳን የመሰሉ ግዙፍ ባንኮች መግባት፦
ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የብድር አቅርቦት ይጨምራል።
👉የአገልግሎት ጥራት እና የዲጂታል ክፍያ ስርአትን ያዘምናል።
👉የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰትን (FDI) ያሳድጋል።
9 months ago
u2764ufe0f u120du12e9 u12e8u126bu1208u1295u1273u12edu1295 u1240u1295 u12ddu130du1305u1275! u1208u1325u1242u1275 u1230u12ceu127d u1265u127b! u2764ufe0f
u12e8u12a0u1201u1291u1295 Valentine's Day u1260u1264u1291u1293 u126au120cu1305 u12a8u12f3u12cau1275 u1345u130c u130bu122d u12ebu1233u120du1349!
u12ddu130du1305u1271 u1260u121au1296u1228u12cd u1246u12edu1273 u12e8u121au12a8u1270u1209u1275u1295 u120du12e9 u12a0u1308u120du130du120eu1276u127d u12ebu12abu1275u1273u120du1366
ud83cudfb5 u12e8u134du1245u122d u12dcu121bu1366 u1260u12f3u12cau1275 u1345u130c u1323u134bu132d u12f5u121du1345 u12e8u1273u1300u1260 u120du12e9 u12e8u1219u12dau1243 u12aeu1295u1230u122du1275
ud83dude86 u120du12e9 u1309u12deu1366 u1260u126au12a0u12edu1352 (VIP) u12e8u127bu122du1270u122d u1263u1261u122d u1275u122bu1295u1235u1356u122du1275 (Charter Luxury Train) u12a0u1308u120du130du120eu1275
ud83euddd6u200du2640ufe0f u12e8u12a5u1228u134du1275 u130au12dcu1366 u1230u12cdu1290u1275u1295u1293 u1218u1295u1348u1235u1295 u12e8u121au12ebu12f5u1231 u120du12e9 u120du12e9 u1218u12ddu1293u129bu12ceu127d
ud83dudd6f u12e8u123bu121b u1265u122du1203u1295 u12a5u122bu1275u1366 u12cdu1265 u1260u1206u1290 u121du123du1275 u1260u122eu121bu1295u1272u12ad u12e8u123bu121b u1265u122du1203u1295 u12e8u1273u1300u1260 u12a5u122bu1275
ud83cudf79 u1201u1208u1295u1270u1293u12ca u12a0u1308u120du130du120eu1275u1366 u1219u1209 u12c8u132au12cd u12e8u1270u1238u1348u1290 (All-inclusive) u12e8u121du130du1265u1293 u12e8u1218u1320u1325 u12a0u1245u122du1266u1275
u12d5u12f5u1209u1295 u12edu1320u1240u1219! u12ddu130du1305u1273u1278u12cdu1295 u12a0u1320u1293u1240u12cd u12a5u122du1235u12ceu1295 u12a5u12e8u1320u1260u1241 u1290u12cd!
u12dbu122cu12cdu1291 u12edu1218u12ddu1308u1261u1366 https://shr.et/TheExclusiv...
u1208u1260u1208u1320 u1218u1228u1303u1366 0904040468 | 0933232373 u12edu12f0u12cdu1209!
#valentine #ethiopia #beynounavillage #dawittsigie #kidamemedia #love #exclusivevalentine #u134du1245u122d #u126bu1208u1295u1273u12edu1295 ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"ExternalUrl","__isEntity":"ExternalUrl","url":"https://l.facebook.com/l.p...
❤️ ልዩ የቫለንታይን ቀን ዝግጅት! ለጥቂት ሰዎች ብቻ! ❤️
የአሁኑን Valentine's Day በቤኑና ቪሌጅ ከዳዊት ፅጌ ጋር ያሳልፉ!
ዝግጅቱ በሚኖረው ቆይታ የሚከተሉትን ልዩ አገልግሎቶች ያካትታል፦
🎵 የፍቅር ዜማ፦ በዳዊት ፅጌ ጣፋጭ ድምፅ የታጀበ ልዩ የሙዚቃ ኮንሰርት
🚆 ልዩ ጉዞ፦ በቪአይፒ (VIP) የቻርተር ባቡር ትራንስፖርት (Charter Luxury Train) አገልግሎት
🧖♀️ የእረፍት ጊዜ፦ ሰውነትንና መንፈስን የሚያድሱ ልዩ ልዩ መዝናኛዎች
🕯 የሻማ ብርሃን እራት፦ ውብ በሆነ ምሽት በሮማንቲክ የሻማ ብርሃን የታጀበ እራት
🍹 ሁለንተናዊ አገልግሎት፦ ሙሉ ወጪው የተሸፈነ (All-inclusive) የምግብና የመጠጥ አቅርቦት
ዕድሉን ይጠቀሙ! ዝግጅታቸውን አጠናቀው እርስዎን እየጠበቁ ነው!
ዛሬውኑ ይመዝገቡ፦ https://shr.et/TheExclusiv...
ለበለጠ መረጃ፦ 0904040468 | 0933232373 ይደውሉ!
#valentine #ethiopia #beynounavillage #dawittsigie #kidamemedia #love #exclusivevalentine #ፍቅር #ቫለንታይን
Sponsored by
Surafel
9 months ago
ከ1 ቢሊዮን ወደ 850 ሚሊዮን ዶላር፦ የኢትዮጵያ የዩሮ ቦንድ እዳ እንዲቀንስ ስምምነት ተደረሰ
ኢትዮጵያ ከዩሮ ቦንድ አበዳሪዎች ጋር ስታደርገው የነበረው የብድር ሽግሽግ ድርድር ስኬታማ ውጤት ማስመዝገቡ የተገለጸ ሲሆን፣ በመሰረታዊ ነጥቦች ላይ በተደረሰው ስምምነት መሰረት የሀገሪቱ አጠቃላይ የዩሮ ቦንድ እዳ መጠን በ15 በመቶ ወይም በ150 ሚሊዮን ዶላር እንዲቀንስ ተደርጓል።
ዓለም አቀፍ ጠበቆችን ቀጥራ ከአበዳሪዎች ጋር ስትደራደር የቆየችው ኢትዮጵያ፣ የ1 ቢሊዮን ዶላር እዳ እንዲሸጋሸግላት ባቀረበችው ጥያቄ ላይ ስምምነት ላይ መደረሱን የድርድሩ ሰነድ የሚያሳይ ሲሆን ይህም ለሀገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ ትልቅ እመርታ ተደርጎ ተወስዷል።
በስምምነቱ መሰረት ዋናው የብድር መጠን (Haircut) ተደርጎለት ወደ 850 ሚሊዮን ዶላር ዝቅ እንዲል የተወሰነ ሲሆን፣ ይህ እዳ እስከ 2020 የኢትዮጵያ በጀት ዓመት ተከፍሎ እንዲጠናቀቅ ታቅዷል።
በተጨማሪም ቀደም ሲል በሦስት ዙር መከፈል የነበረበትና ሳይከፈል በመቆየቱ ኢትዮጵያን ለ "ቴክኒካዊ ውድቀት" (Technical Default) ዳርጓት የነበረው የ99 ሚሊዮን ዶላር የወለድ እዳ፣ አሁን ላይ ሀገሪቱ በአንድ ጊዜ ለመክፈል መስማማቷ በሰነዱ ላይ ሰፍሯል።
የረጅም ጊዜ ክፍያውን በተመለከተ፣ በቀጣዮቹ 8 ዓመታት ውስጥ የተሻለ የወጪ ንግድ ገቢ ከተገኘ ከገቢው 2.5 በመቶ በመቀነስ በዓመት 180 ሚሊዮን ዶላር እንድትከፍል ተወስኗል።
ይህ አሃዝ አበዳሪዎች ቀደም ሲል ከጠየቁት የ4.75 በመቶ የክፍያ ምጣኔ በእጅጉ የቀነሰ ሲሆን፣ ይህም በIMF የኢኮኖሚ ግምገማዎች ላይ ተመስርቶ የቀረበ የክፍያ አማራጭ መሆኑ ታውቋል። ስምምነቱ በይፋ ሥራ ላይ እንዲውልም የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት
(IMF) የመጨረሻ ይሁንታ እየተጠበቀ ይገኛል።
ይህ የብድር ሽግሽግ ስምምነት ኢትዮጵያ ወደ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ገበያ በድጋሚ ለመመለስ ለምታደርገው ጥረት ከፍተኛ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሏል።
የእዳ ጫናው መቀነሱ እንደ Fitch እና S&P ያሉ ተቋማት ለሀገሪቱ የሚሰጡትን የክሬዲት ደረጃ ሊያሻሽለው እንደሚችል የሚጠበቅ ሲሆን፣ ይህም በሀገሪቱ ላይ የነበረውን የብድር አለመክፈል ስጋት በመቀነስ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት (FDI) እንዲጨምር ምቹ ሁኔታን ይፈጥራም የሚል ትንበያ ባለሙያዎች ይሰጣሉ።
ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2014 የገባችበት የ1 ቢሊዮን ዶላር የዩሮ ቦንድ እዳ በታህሳስ 2023 መከፈል የነበረበት ቢሆንም፣ በወቅቱ በነበረው የውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት ሳይከፈል መቆየቱ ይታወሳል። ይህ አዲስ ስምምነት ሀገሪቱ ካለባት የብድር ጫና ወጥታ የጀመረችውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ (Macroeconomic Reform) በዘላቂነት ለማስቀጠል የሚረዳ ወሳኝ እርምጃ መሆኑን የድርድሩ ውጤት ያመለክታል።

11 months ago
የኢትዮጵያ"የሀይል ማስፋት" (Power Projection)፡በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የዲፕሎማሲ ጥረት...!
(የሀብታሙ ደባሱ አዲሱ የግል ሀሳብ )
#ethiopia | በቅርቡ የተከናወነው በደቡብ አፍሪካ አዘጋጅነት የG-20 የኢትዮጵያ ተሳትፎ እንዲሁም የማሌዥያና የሲንጋፖር መሪዎች ጉብኝት፣የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ መንግስት እየተከተለው ያለውን የዲፕሎማሲያዊ እና ኢኮኖሚያዊ "የሀይል ማስፋት"ስትራቴጂ ቁልፍ ማሳያዎች ናቸው።ይህ ስትራቴጂ ሀገሪቱ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተጽዕኖ በማስፋት፣ለሀገር ውስጥ ዕድገት የሚያስፈልገውን ሀብትና ዕውቀት ለመሳብ ያለመ መሆኑን ያሳያል።
🔴 የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዲፕሎማሲያዊ ራዕይ፦
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በዋናነት በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ (Economic Diplomacy) እና የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን በማስፋት ላይ ያተኮረ ነው።ከዓለም ደቡብ (Global South) አገሮች በተለይም ከእስያ እና ከመካከለኛው ምስራቅ ጋር አዲስና ጠንካራ ስትራቴጂካዊ አጋርነት መገንባት፤ በሁሉም ወገን የሀገርን መሰረታዊ ብሄራዊ ጥቅም ማስከበር እና ማረጋገጥ አጋርነትን ማስፋትን ያካትታል።
የ"ብልጽግና" ጽንሰ-ሀሳብ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች በሙሉ ከብልጽግና ራዕይ ጋር የተሳሰሩ ሲሆን፣ የውጭ ግንኙነት በዋናነት ለሀገር ውስጥ ኢኮኖሚ ዕድገት እና ለሥራ ዕድል ፈጠራ እንዲያገለግል ለማድረግ ያለመ ነው።
🔴የቡድን ሀያ አባለ ሀገራት (G-20) ተሳትፎ፦የብዙ-ዋልታ ዓለምን (Multipolar World) መቀበል ኢትዮጵያ በG-20 ስብሰባ ላይ እንደ ልዩ እንግዳ መሳተፏ፣በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራው ዲፕሎማሲ ኢትዮጵያን ከአፍሪካ ቀንድ ባሻገር ዓለም አቀፋዊ ተዋናይ አድርጎ ለማስቀመጥ ያለውን ጥረት ያሳያል።በዓለም የፋይናንስ እና የፖለቲካ ውሳኔ ሰጪ ማዕከላት ላይ ድምጽ እንዲኖራት ማድረግ።ክቡር ዶ/ር ዐቢይ በተደጋጋሚ እንደሚገልጹት፣ኢትዮጵያ የአፍሪካ ኀብረት ዋና መስሪያቤት መቀመጫ እንደመሆኗ መጠን የአፍሪካን አጠቃላይ ጥቅም በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ በማንሳት፣ የሀይል ማስፋት ጥረቷን ከአህጉራዊ ሚናዋ ጋር አጣምራለች።
🔴 የእስያ መሪዎች ጉብኝት፦የቴክኖሎጂና የኢንቨስትመንት ድልድይ የማሌዥያ እና የሲንጋፖር መሪዎች ጉብኝት የዶ/ር ዐቢይ የዲፕሎማሲ ጥረት ዋነኛ መገለጫ ነው።ከእነዚህ ፈጣን ዕድገት ካላቸው የእስያ "ነብሮች" (Asian Tigers) ጋር ግንኙነት መፍጠር የኢትዮጵያን የመበልፀግ የማደግ ስትራቴጂ ለመደገፍ ወሳኝ ነው።
🖊እንደ መውጫ ስልታዊ ትኩረት የሀይል ማስፋት ትርጉም⁉️
ሲንጋፖር የላቀ የሎጅስቲክስ አስተዳደር፣ ዘመናዊ የከተማ ልማት (Smart City)፣ የዲጂታል ኢኮኖሚ ልምድ ሽግግር፤ የኢትዮጵያን የባህር በር ፈተና ለመቅረፍ ዘመናዊ የንግድ መስመሮችን መገንባት እንደ አስረጅነት ይጠቀሳል ።( በሀገራችን በአዲስ አበባ እና በሌሎች ክልል ከተሞች እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት ፤ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ይጠቀሳል ።
ማሌዥያ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት (FDI) በኤሌክትሮኒክስና በኢንዱስትሪ ዘርፍ መሳብ፣ የዘይትና ዘይት ነክ ምርቶች ንግድ በማጠናከር የኢኮኖሚ አጋርነትን እና የንግድ አጋሮች ማጎልበትን ያሳያል ።( Industrial Park Development cooperation ስር የሚከናወኑ የእውቀት እና የኢንዱስትሪ ሽግግር መጥቀስ ይቻላል ።)
🔴የማጣቀሻዎች (Reference )
1️⃣Abiy Ahmed (PhD). Medemer: A Collective Journey. (የዶ/ር ዐቢይ የፍልስፍና መሰረት ለዲፕሎማሲያዊ ስትራቴጂያቸው።)
2️⃣ Minister's Office. Official Press Releases on G20 and Bilateral Visits. (የጉብኝቶቹን ዓላማ እና የተደረጉትን ስምምነቶች ለመረዳት።)
3️⃣Think Tank Analysis. ISS, Chatham House or Brookings papers focused on Ethiopia's shift in foreign policy towards Asia and Global South engagement.
ይህ የሚያሳየው የኢትዮጵያ የሀይል ማስፋት እቅድ በዶ/ር ዐቢይ አህመድ መሪነት ኢኮኖሚን ማዕከል ባደረገ እና በብዙ-ዋልታ ትብብር ላይ በተመሰረተ ዘመናዊ ዲፕሎማሲ እየተመራ መሆኑን ያሳያል ።
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም መሳካት የድርሻዬን እወጣለሁ !
#ethiopia
ለበለጠ ወዳጅነት የፃሃፊውን የኤክስ(X) እና የፌስቡክ ገፅ ይከታተሉ :-
🔗የኤክስ(X)ገፅ:-tps://x.com/HDebasu?t=WkEcsELrZrHGV1UGX3oSMg&s=09
🔗የፌስቡክ:-https://www.facebook.com/s...

1 year ago
የጋምቤላ ኢንቨስትመንት እና ቱሪዝም ልማት በዓለም-አቀፍ እንዲተዋወቅ እየሠራን ነው!
- የጋምቤላ ሕዝቦች ክልል መንግሥት
#ethiopia | የጋምቤላ ክልል በሀብት ከከበሩ፣ በተፈጥሮ ከተሞሸሩ፣ በሰላም ከተቀመሩ፣ በታታሪ ሕዝብ ከተማገሩ የኢትዮጵያ ክልሎች ውስጥ አንዱና ቀዳሚው ነው።
ለአይን ማራኪ፣ መንፈስ የሚያድስና ታይቶ በማይጠገብ ውብ በሆነ መልክዓ-ምድር፣ ሠላማዊ ማኅበረሰብ፣ አስደናቂ የባሕል ስብጥር እና የልማት ፍላጎት ያለው ወጣት የሥራ ኃይል፣ በኢንቨስትመንት እንቅስቀሴዎችና መልማት የሚችል ዕምቅ ሐብት (እርሻ፣ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ፣ ደን ልማት፣ አግሮ-ፕሮሰሲንግ፣ ማዕድን ልማትና አገልግሎት) አቅፎ የያዘ፣ በምዕራብ ኢትዮጵያ በቅርቡ ለምቶ የአገር ትሩፋት የሚሆን (The Rising West) ክልል ነው።
ጋምቤላ በዝናብ ሊለማ የሚችለው የእርሻ መሬት ከጠቅላላው የቆዳ ስፋት ውስጥ 16 በመቶ ሲሆን ለዘመናዊ የመስኖ ኮመርሽያል እርሻ የሚሆነው ደግሞ 10 በመቶ ይሆናል። ይህ ማለት ለእርሻ ኢንቨስትመንት ሊውል የሚችለው 26 በመቶ (8,200 ስኩየር ኪሎ ሜትር) ነው። ለዚህ የዘመናዊ እርሻ ልማት የሚሆኑ ባሮ፣ አኮቦ፣ አልዌሮ እና ጊሎን የመሳሰሉ 4 ግዙፍ ወንዞች ከዓመት እስከ ዓመት የሚፈሱበት ክልል ነው።
እነዚህ ወንዞች ከአግሮ-ኢኮሎጂው ምቹነት አንጻር ሰፊ የዓሳ ሐብት ክምችት ያላቸው ሲሆን በዘመናዊ የዓሳ ልማት ዕቅድ ተመርቶ ለገበያ መቅረብ የሚያስችል ዐቅም አላቸው።
ክልሉ ባስጠናው የተቀናጀ የከተማና ገጠር መሬት አጠቃቀምና ልማት ፍኖተ-ካርታ (Integrated Urban and Rural Land-use Development Plan) መሠረትም የመሬት አጠቃቀም፣ የከተሞች ልማት እና የአካባቢ ጥበቃን አቀናጅቶ የመምራት ልምድ በክልሉ እየዳበረ መምጣቱ ለዘላቂ ዕድገት መሠረት ሆኗል።
በአግሮ-ፕሮሰሲንግ ዘርፍ ክልሉ በሁሉም ዞኖች በቂ መጠን ዓመታዊ የዝናብ ውሃ የሚያገኙ በመሆኑ በቡና እና ሻይ ልማት፣ በእንስሳት ልማትና ተዋጽዖ ማቀነባበር፣ በኢንዱስትሪያል ደን ልማት፣ በንብ ማነብና የማር ምርት፣ በዓሳ ልማት፣ በዶሮ ሐብት ልማት፣ በጥራጥሬና የቅባት እህሎች ልማትና ማቀነባበር ዘርፍ ዕሴት በመጨመር ለአገር ውስጥና ለዓለም ገበያ ቢቀርቡ ከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ የሚያስገኝ ክልል ነው።
ይህን ለማሳካትም የምርት-ግብይት ትሥሥሩን ከእርሻ መዘመን እና ሜካናይዜሽን እስከ ግዙፍ የተቀናጀ የአግሮ-ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ፓርክ (Integrated Agro-Processing Industrial Park) በክልሉ እንዲቋቋም ምክረ-ሐሳብ የሚቀርብ ይሆናል።
ከማዕድን ልማት አኳያም በምስራቅ አፍሪካ፣ ጋምቤላ—ምናልባትም በተፈጥሮ የተጌጠ የማዕድን ሐብት ማማ ሊባል የሚችል ነው። ይህን የማዕድን ሐብት ለአገር ልማት እንዲውል፣ ሕጋዊ የአስተዳደር ሥርዓት እንዲዘረጋለት እና ልማታዊ ባለሐብቶች እንዲሰማሩበት ልዩ ልዩ የማትጊያ ሥርዓት ተዘርግቶ እየተሰራበት ይገኛል።
ጋምቤላ ቱሪዝም ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነው። የጋምቤላ ክልል በሀብት ከከበሩ፣ በተፈጥሮ ከተሞሸሩ፣ በሰላም ከተቀመሩ፣ በታታሪ ሕዝብ ከተማገሩ የኢትዮጵያ ክልሎች ውስጥ አንዱና ቀዳሚው ነው።
የጋምቤላ ክልል የዳበረ ባህል፤ ቀደምት ታሪክና መልክአ-ምድራዊ አሰፋፈር፤ የስነ ልቦና አንድነት፤ በጋራ ኤኮኖሚ (Shared Economy) ርዕይ የተዋቀረ የመልማት ፍላጎት ያለው እንዲሁም ጠንካራ የእርስ በእርስ ትስስር ያላቸው የአካባቢው ብሄረሰቦችንና ሌሎች የሀገራችንን ማኅበረሰቦች በጋራ ይዞ የሚገኝ ክልል ነው።
ክልሉ በቱሪስት መስህብነታቸው ተወዳጅ ተብለው ከተያዙት የኢትዮጵያ አካባቢዎች ውስጥ ተጠቃሽ ኮሪደር የያዘ ነው። በሆቴል ልማት፣ በባሮ እና አልዌሮ ወንዞች ላይ ዘመናዊ የሪዞርት ልማትና የጀልባ መዝናኛዎች፣ በኮንፈረንስ ቱሪዝም እና መሰል ተግባራት ሐብት ማመንጨት የሚችል ጸጋ የተላበሰ ነው።
ይህን የክልሉን ሐብት ፍትሐዊነት በታከለበት መንገድ ለማልማትና ለኢትዮጵያ የሕዳሴና ብልጽግና ዘመን እንደ አንድ ቁልፍ አሻጋሪ ድልድይ ለመጠቀም ይረዳ ዘንድ የጋምቤላ ክልል መንግሥት ከሕዝቡ የዕድገት አጋሮች ጋር በመተባበር ‹‹ጋምቤላ ይለማል (Gambella is Rising)›› የኢንቨስትመንት ልማት ዓለም-አቀፍ ንቅናቄ መርሐ-ግብር አዘጋጅቷል።
ክልላዊ ንቅናቄውንም ዛሬ፣ መስከረም 10 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ ለመላው ኢትዮጵያውያን፣ ደጋፊዎቻችን እና ዓለም-አቀፍ አጋሮቻችን በይፋ መጀመራችንን እናበስራለን።
የንቅናቄ መርሐ-ግብሩም ለሁለት ወራት የሚዘልቅ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች የክልሉን ኢንቨስትመንት በማሳደግ፣ ኢትዮጵያውያን እና የውጪ አልሚ ባለሐብቶች (FDI) በስፋት የሚሳተፉበት፣ ዓለም-አቀፍ የልማት ድርጅቶች፣ ኢምባሲዎች እና ከፍተኛ የፌደራልና የክልል መንግሥታት መሪዎች የሚገኙበት የክልሉን ገጽታ ከመቸውም ጊዜ በላቀ መንገድ የሚያጎላ ሆኖ ይጠናቀቃል።

ባርክልን
አዲስ ዝማሬ
በዜማ ራማ ተለቋል
👉 https://youtu.be/_gjgYtCIC...
6ቱ ዘማርያን
ዘማሪ ዲ/ን ብስራት ጨብሲ
ዘማሪ ዲ/ን ዳዊት ጥላሁን
ዘማሪ ዲ/ን ሚኪያስ ጸጋዬ
ዘማሪት በጸሎት አስማረ
ዘማሪት ናርዶስ ካሳሁን
ዘማሪት ባንቺአየሁ ሰይፉ
ግጥም : ዘማሪ ኢንጂነር ታዴዎስ አውግቸው
ዜማ: ዘማሪ ኢንጂነር ታዴዎስ አውግቸውና
ዘማሪ ዲ/ን ዘለዓለም ታከለ
ክራር ዲ/ን ዘለዓለም ታከለ (ዘጎላ)
መሰንቆ እንዳልካቸው አዱኛ
ዋሽንት ስምዖን አረጋይ
ድምጽ ቅጂ ሚክሲንግ ማስተሪንግ
ዘጎላ ሬከርድስ
አዲስ ዝማሬ
በዜማ ራማ ተለቋል
👉 https://youtu.be/_gjgYtCIC...
6ቱ ዘማርያን
ዘማሪ ዲ/ን ብስራት ጨብሲ
ዘማሪ ዲ/ን ዳዊት ጥላሁን
ዘማሪ ዲ/ን ሚኪያስ ጸጋዬ
ዘማሪት በጸሎት አስማረ
ዘማሪት ናርዶስ ካሳሁን
ዘማሪት ባንቺአየሁ ሰይፉ
ግጥም : ዘማሪ ኢንጂነር ታዴዎስ አውግቸው
ዜማ: ዘማሪ ኢንጂነር ታዴዎስ አውግቸውና
ዘማሪ ዲ/ን ዘለዓለም ታከለ
ክራር ዲ/ን ዘለዓለም ታከለ (ዘጎላ)
መሰንቆ እንዳልካቸው አዱኛ
ዋሽንት ስምዖን አረጋይ
ድምጽ ቅጂ ሚክሲንግ ማስተሪንግ
ዘጎላ ሬከርድስ
Comments