24 days ago
ብሪክስ ለኢትዮጵያ ያመጣው ድል ምንድነው?
የብሪክስ የኒው ዴልሂ የአቋም መግለጫ መልሱን ይዟል።
➡ ይበልጥ ለመረዳት ሙሉ የአቋም መግለጫውን ያንብቡ፦ brics2026.gov.in/brics-document/
#pmoethiopia #ethiopiadelivers

የብሪክስ ስብስብ ማዕከላዊነት እና የኢትዮጵያ በሳል ዲፕሎማሲያዊ ስኬት
**********************
በዘመናችን የዓለም አቀፍ የጂኦ-ፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ምህዳር ውስጥ የብሪክስ (BRICS) ጥምረት መፈጠር እና መጠናከር አዲሱን የባለብዙ ወገን የኃይል ሚዛን እውን በማድረግ ትልቅ ምዕራፍ ሆኗል።
የብሪክስ አባል ሀገራት ዛሬ ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተጽዕኖ አድማሳቸው በከፍተኛ ሁኔታ የሰፋ፣ የዓለም አቀፍ ሀብት፣ የምርጥ ቴክኖሎጂ እና የሰፊ ገበያ ማዕከልና መዳረሻ መሆናቸውን በተግባር እያረጋገጡ ይገኛሉ።
ብሪክስ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ እያሳየ የመጣው የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ዕድገት የዓለምን ትኩረት ስቧል። የዚህ ጥምረት አባል ሀገራት በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ ዋና ዋና የተፈጥሮ ሀብቶች፣ የነዳጅ እና የጋዝ ክምችቶች እንዲሁም የአግሮ-ኢንዱስትሪ ምርቶች ትልቁን ድርሻ ይይዛሉ።
በህዋ ሳይንስ፣ በዲጂታል ኢኮኖሚ፣ በታዳሽ ኃይል እና በኢንዱስትሪ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ እጅግ የገዘፉ የቴክኖሎጂ አቅሞችን በመገንባት የዓለምን የወደፊት አቅጣጫ እየመሩ ይገኛሉ። ከዓለም ሕዝብ ከ49 በመቶ የሚሆነውን የሚሸፍኑ በመሆናቸውም ከፍተኛ የማምረት እና የመግዛት አቅም ያለው ሰፊ ገበያ ያቀፉ ናቸው።
ይህ አቅማቸው ጥምረቱን በዓለም አቀፍ የንግድ፣ የፋይናንስ እና የልማት ሥርዓት ላይ ትልቅ ተጽዕኖ የመፍጠር አቅም እንዲኖረው አድርጎታል።
የብሪክስ አባልነት ጥቅምና ተጽዕኖ እያደገ በመምጣቱ በርካታ ሀገራት የጥምረቱ አባል ለመሆን ከፍተኛ ፍላጎትና ሽሚያ በሚያደርጉበት በዚህ ወቅት፣ ኢትዮጵያ የስብስቡ ሙሉ አባል መሆን መቻሏ ትልቅ የታሪክ እና የዲፕሎማሲ ስኬት ነው።
ይህ ስኬት በአጋጣሚ የመጣ ሳይሆን፣ ሀገራችን የተከተለችው በሳል፣ ገለልተኛ እና የብሔራዊ ጥቅምን አስቀድሞ የማስጠበቅ የዲፕሎማሲያዊ ጥረት ውጤት ነው።
ኢትዮጵያ የነበራትን ታሪካዊ የአፍሪካ የዲፕሎማሲ ማዕከልነት በመጠቀም፣ ከምስራቅም ሆነ ከምዕራብ ሀገራት ጋር ሚዛናዊ እና ፍሬያማ ግንኙነት በመገንባቷ ተቀባይነቷን አረጋግጣለች።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ የምትገኝበት አህጉራዊ እና ጂኦ-ፖለቲካዊ ቦታ፣ የሕዝብ ብዛት እና የኢኮኖሚ አቅሟ ጥምረቱ ለሚከተለው ዓላማ ትልቅ እሴት የሚጨምር በመሆኑ ተመራጭ አድርጓታል።
የብሪክስ አባል መሆኗ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተሰሚነት ከፍ ከማድረጉ ባሻገር የተለያዩ ሁለንተናዊ ጥቅሞች እንድታገኝ በር ይከፍታል። በዚህም የፋይናንስ እና የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማስፋት በአዲሱ የልማት ባንክ (New Development Bank) በኩል ለታላላቅ የመሰረተ ልማት እና የልማት ፕሮጀክቶች የሚሆን የፋይናንስ አቅርቦት የማግኘት ዕድልን ያሰፋል።
ከታዳጊ እና ከበለፀጉት የብሪክስ አባላት ጋር የሚደረግ የቴክኖሎጂ እና የእውቀት ሽግግር የሀገራችንን የኢንዱስትሪ እና የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ያፋጥናል። እንዲሁም የኢትዮጵያ ምርቶች ወደ ግዙፎቹ የብሪክስ ሀገራት ገበያ ያለአንዳች እንቅፋት እንዲገቡ እና የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት (FDI) ፍሰት እንዲጨምር በማድረግ ትልቅ ሚና ይጫወታል።
በመሆኑም የኢትዮጵያ የብሪክስ አባልነት የዲፕሎማሲያዊ ልህቀት ውጤት ሲሆን፣ ሀገራችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ተጽዕኖ ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገረ፣ ለወደፊት እድገቷም ትልቅ መሰረት የጣለ ታሪካዊ ክስተት ነው።
በአድማሱ አራጋው
#ethiopia #ebc #brics #brics2026 #globalsouth

ከ1.2 ትሪሊዮን ዶላር የንግድ ልውውጥ እስከ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ክፍት ቀጣና፤ የብሪክስ መሪዎች አዳዲስ የትብብር ሥልቶችን ነደፉ
*************************
የአባል ሀገራቱን በማስፋት በሕንድ ኒው ዴልሂ የተካሄደው 18ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ ላይ በቴክኖሎጂ፣ በፀጥታ እና በኢኮኖሚ ዘርፎች የጋራ ትብብርን ለማጠናከር የሚያስችሉ አዳዲስ ሥልቶች ተነድፈዋል።
የብሪክስ አባል ሀገራት መሪዎቹ የጥምረቱ መፍትሔዎች ለመላው የደቡቡ ክፍለ ዓለም ሀገራት ተደራሽ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ጠንካራ የአፍሪካ ውክልና እንዲኖር፣ የፋይናንስ እና የገበያ ተደራሽነት ይበልጥ እንዲሰፋ፣ እንዲሁም ንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና ትሥሥርን ለማሳደግ ተግባራዊ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ጠይቀዋል።
የ‘ኒው ዴቨሎፕመንት ባንክ’ አድማሱን በመላው አፍሪካ እንዲያስፋፋ በማለም የባንኩን ቢሮ በአዲስ አበባ ለማስተናገድ ኢትዮጵያ በሙሉ አቅም ዝግጁ መሆኗንም አረጋግጠዋል።
በአዲስ አበባ የሚካሄደው 32ኛው የዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 32) በብሪክስ ሙሉ ድጋፍ ለአየር ንብረት ጥበቃ ሥራዎች እና ለዘላቂ ልማት መፋጠን ሁሉንም ድምፆች የሚያሰባስብ ሁሉን አቀፍ መድረክ ሆኖ ማገልገል እንደሚችል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አስገንዝበዋል።
የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የሀገራቸውን የሊቀመንበርነት ጊዜ በማጠቃለል ባደረጉት ንግግር፣ የብሪክስ ሀገራት የተላላፊ በሽታዎች ወረርሽኝን በጋራ ለመከላከል የሚያስችል የተቀናጀ ሥርዓት ለመፍጠር መስማማታቸውን አስታውቀዋል።
በተጨማሪም በድንገተኛ አደጋዎች ጊዜ የቅድመ-ማስጠንቀቂያ መረጃዎችን ለመለዋወጥ እና የሎጂስቲክስ አቅርቦት ሰንሰለትን ለማጠናከር የሚያስችሉ የትብብር ማዕቀፎች መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
በፈጠራ ዘርፍ፣ የጀማሪ ቢዝነሶችን (Start-ups) እና ኢንኩቤተሮችን የሚያስተሣሥር የብሪክስ ኔትወርክ፣ የብሪክስ ስታርት-አፕ የፈጠራ ፈንድ፣ እንዲሁም አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን እና የጂኦ-ስፓሻል ቴክኖሎጂዎችን ለአርሶ አደሮች እውነተኛ ፍላጎት የሚያውለው የብሪክስ የዲጂታል ግብርና ኔትወርክ መጀመሩን አብራርተዋል።
ከዚህም በተጨማሪ ክህሎትን ለማሳደግ እና ሴቶችን ለማብቃት ያለመው ‘ብሪክስ ኮኔክት’፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን የሚደግፍ ፖርታል እና በትራንስፖርት ጉዳዮች ላይ ልምድ ለመለዋወጥ "የብሪክስ የከተሞች የወደፊት ፎረም" መቋቋማቸውን አስታውቀዋል።
በዘላቂ ልማት ዘርፍም የስማርት ግሪድ የዲጂታል ልህቀት ማዕከል መቋቋሙን ጠቅሰዋል።
የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በበኩላቸው፣ ዛሬ ላይ ብሪክስ ባለብዙ ወገንተኝነትን ከሚያጠናክሩ እና ፍትሐዊ የሆነ የባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓትን ከሚቀርጹ መሪ ኃይሎች አንዱ መሆኑን ገልጸዋል። በብሪክስ ሀገራት መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ 1.2 ትሪሊዮን ዶላር መድረሱን እና አባል ሀገራቱ ከዓለም የወጪ ንግድ ሩብ ያህሉን እንደሚሸፍኑ ያነሱት ፑቲን፣ አሁንም ያልተሟጠጠ ሰፊ አቅም መኖሩን አስረድተዋል።
የጋራ የኢኮኖሚ ዕድገት ፕላትፎርም መፈጠር እንዳለበትም አሳስበው፣ አዲሱ የልማት ባንክ (NDB) እስካሁን 40 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጉ 123 ፕሮጀክቶችን ፋይናንስ ማድረጉን እና ተጨማሪ የረጅም ጊዜ ካፒታልን ለመሳብ ዲጂታል ንብረቶችን የሚጠቀም አዲስ የኢንቨስትመንት ፕላትፎርም መፍጠር እንደሚገባ ጠቁመዋል።
የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ፣ በተግባራዊ ትብብር ላይ ያተኮሩ አምስት አዳዲስ ፕሮጀክቶችን አቅርበዋል። ከእነዚህም መካከል፣ በብሪክስ ሀገራት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂዎችን ለመለዋወጥ የሚያስችል የመጀመሪያውን ክፍት ዞን (open-access zone) መፍጠር፣ በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች መካከል አጋርነት መመሥረት፣ ለዲጂታል ኢንዱስትሪዎች የጋራ የክላውድ (Cloud) ፕላትፎርም ማዘጋጀት እና ከፍተኛ ባለሙያዎችን ለማሠልጠን የብሪክስ የምሕንድስና ተሰጥዖ ልማት ጥምረት እንዲሁም የወጣት ሳይንስ እና ፈጠራ ልውውጥ ፕሮግራም ማቋቋም ይገኙበታል።
የኢራኑ ፕሬዚዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያን፣ ጽናት፣ ትብብር እና ዘላቂ ልማት የጥምረቱ የቀጣይ ሥራ መሠረት ሊሆኑ እንደሚገባ አሳስበው፣ ያለ ደኅንነት ኢኮኖሚያዊ ጽናት ሊኖር እንደማይችል ጠቁመዋል።
ኢራን በጂኦግራፊያዊ አቀማመጧ እና በኢነርጂ እንዲሁም በትራንስፖርት ዘርፍ ያላት አቅም ለብሪክስ ሀገራት አዳዲስ የትብብር መንገዶችን ለመፍጠር እንደሚያግዝ አረጋግጠዋል።
ብሪክስ በማደግ ላይ ላሉ ኢኮኖሚዎች የትብብር መድረክ ብቻ ሳይሆን ማንም ኃይል የሌሎች ሕዝቦችን ዕጣ ፈንታ የመወሰን መብት የሌለበት፣ ይበልጥ ሚዛናዊ እና አካታች ለሆነ ዓለም የሚደረግ ምኞት ተምሳሌት መሆኑ ተገልጿል።
ለሁለት ቀናት በሕንድ መዲና ኒው ዴልሂ የተካሄደው 18ኛው የብሪክስ ሀገራት መሪዎች ጉባኤ፣ 140 አንቀጾች ያሉት የኒው ዴልሂ የአቋም መግለጫን (New Delhi Declaration) በማጽደቅ ተጠናቅቋል።
በዮናስ በድሉ
#ethiopia #ebc #brics #brics2026 #globalsouth #newdelhideclaration

Sponsored by
Surafel
24 days ago
ዲጂታል መደመር፡ የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት በብሪክስ መድረክ
******************
በሕንድ ኒው ዴልሂ እየተካሄደ ባለው 18ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያደረጉት ንግግር፤ ኢትዮጵያ በልማት፣ በዲፕሎማሲ እና በቴክኖሎጂ ዘርፎች የነደፈችውን ግልጽ አቅጣጫ የሚያንፀባርቅ ነው።
"ጽናትን፣ ፈጠራን፣ ትብብርን እና ዘላቂነትን መገንባት" በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው በዚህ ታሪካዊ መድረክ ላይ የተንፀባረቀው ሀሳብ፣ በሀገር ውስጥ እየተተገበረ ካለው የመደመር እሳቤ እስከ ዓለም አቀፉ የብሪክስ የትብብር ማዕቀፍ ድረስ ያለውን ስትራቴጂያዊ ውህደት በሚገባ ያሳያል።
ሁለቱም አስተሳሰቦች አግላይ ከሆነው ነባር የዓለም ሥርዓት ወጥቶ የጋራ ተጠቃሚነትን፣ ፍትሐዊ የባለብዙ-ወገን ማዕቀፍን እና አዎንታዊ ትብብርን መገንባት ላይ ያተኩራሉ።
በኢትዮጵያ ምህዳር ውስጥ የዳበረው የመደመር እሳቤ ቀደምት ዕውቀቶችን በመጠበቅ፣ የወቅቱን አቅሞች በማጣመር እና ጉድለቶችን በመሙላት አዲስ አቅም መገንባትን መሠረት ያደረገ ነው።
ይህ አካታችነትን ያማከለ ፍልስፍና የብሪክስ ጥምረት በዓለም አቀፍ ደረጃ በፖለቲካ እና በኢኮኖሚ ውሳኔዎች የተገለሉ አዳጊዎችን ከሚያሳትፈው ሰፊ ዓላማ ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት አለው።
ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሁለተኛዋ ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ያላት፣ የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ እና የሰፊው አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ማዕከል በመሆኗ፤ የብሪክስ የትብብር ማዕቀፍ ወደ አፍሪካ አህጉር በስፋት እንዲሰርፅ ትልቅ ድልድይ ሆና ታገለግላለች።
ካፒታልን፣ ቴክኖሎጂን እና ገበያን በማጣመር የጋራ ዕድገት ማምጣት የሚለው የብሪክስ መርህም፣ ሀብት እና አቅምን አቀናጅቶ የላቀ ውጤት ከማምጣቱ የመደመር እሳቤ ጋር ጥልቅ ውህደት ይፈጥራል።
ይህ የዲፕሎማሲ እና የልማት ትስስር ወደ ቴክኖሎጂው ዘርፍ ሲሰፋ ይበልጥ ጎልቶ ይታያል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዚሁ የኒው ዴልሂ የብሪክስ ጉባኤ ላይ፣ “የመደመር አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲ አፍሪካ የነገውን የቴክኖሎጂ ዘመን በባለቤትነት እንድትመራ ትልቅ ሚና ይጫወታል” በማለት ያነሱት ሀሳብ፤ ኢትዮጵያ በሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ዘርፍ አህጉራዊ መሪ ለመሆን ያላትን ጽኑ አቋም ያረጋግጣል።
በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፀደቀው እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በዓይነቱ ልዩ የሆነው ይህ ዩኒቨርሲቲ፣ ኢትዮጵያ ከቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት አልፋ ወደ ቴክኖሎጂ አመንጪነት እንድትሸጋገር የሚያስችል ታሪካዊ ተቋም ነው።
የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ጥናት እንደሚያመለክተው፣ አፍሪካ ለዘርፉ ተገቢውን መሰረተ ልማት እና ዝግጅት ካደረገች የሰው ሠራሽ አስተውሎት የአህጉሪቱን ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት በ4 በመቶ ሊያሳድገው ይችላል። የዩኒቨርሲቲው መቋቋም ይህን ግዙፍ የኢኮኖሚ አቅም እውን ለማድረግ የተወሰደ ትልቅ ርምጃ ነው።
የሰው ሠራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን ለሀገር በቀል ችግሮች መፍቻነት የማዋሉ ሥራ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ከተቋቋመው የኢትዮጵያ ሰው ሠራሽ አስተውሎት ኢንስቲትዩት ተግባራት ጋር ተቀናጅቶ የላቀ ውጤት እያመጣ ይገኛል።
የሰብል በሽታዎች መቆጣጠሪያ ሥርዓት፣ ከ50 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ያቀፈው የፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ፣ ከ130 በላይ የመንግሥት አገልግሎቶችን የሚሰጠው የመሶብ ፖርታል እንዲሁም የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ፕሮግራም የዚሁ ስትራቴጂያዊ ጉዞ አካላት ናቸው።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ ኢትዮጵያ በብሪክስ ውስጥ መገኘቷ የዘርፉን ዕድገት ለማፋጠን ተጨማሪ ዕድል ይፈጥራል።
የብሪክስ አባል ሀገራት በሴሚኮንዳክተር፣ በሱፐር ኮምፒዩቲንግ እና በዲጂታል መሰረተ ልማት ያላቸውን የበለፀገ አቅም ለቴክኖሎጂ ሽግግር እና የመረጃ ማዕከላት ግንባታ መጠቀም ሰፊ አማራጭ ይከፍታል።
በጉባኤው ላይ እንደተብራራው የቀጣዩ ትውልድ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ሞዴሎች በምዕራባውያን ቋንቋዎች ላይ ብቻ ሳይገደቡ የአፍሪካን ሀገር በቀል ዕውቀቶች፣ ባህሎች እና ቋንቋዎች ያካተቱ መሆን አለባቸው።
አዲሱ የልማት ባንክም ለዚህ ዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ወሳኝ የሆነውን አማራጭ ፋይናንስ ለማቅረብ ያስችላል።
ከቴክኖሎጂው መስፋፋት ጎን ለጎን የሚመጡትን የሳይበር ደኅንነት ሥጋቶች፣ የግል መረጃ መጣስ እና የአልጎሪዝም አድልዎን ለመከላከል ኢትዮጵያ ጠንካራ የሕግ እና ፖሊሲ ማዕቀፎችን ዘርግታለች።
በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፀደቀው ብሔራዊ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ፖሊሲ የዘርፉ የአሠራር ሥርዓቶች ግልፅ፣ ተጠያቂነት ያለባቸው እና ከሰው ልጅ ቁጥጥር የማይወጡ መሆናቸውን ያረጋግጣል።
በተጨማሪም የግል መረጃ ጥበቃ አዋጅ እና የኮምፒዩተር ወንጀል አዋጅ የዜጎችን የመረጃ ሉዓላዊነት ከማረጋገጥ ባሻገር ብሔራዊ የመረጃ ደኅንነትን ለመጠበቅ ጉልህ ድርሻ አላቸው።
የመደመር እሳቤ እና የብሪክስ ዓላማ በፅንሰ-ሀሳብ እና በስትራቴጂ ደረጃ የሚደጋገፉ፣ አካታችነትን እና የጋራ ብልፅግናን ማዕከል ያደረጉ የፖሊሲ አተያዮች ናቸው።
ኢትዮጵያ በብሪክስ ውስጥ መገኘቷ ፍትሃዊ ዓለም አቀፍ ሥርዓት እንዲጎለብት ከማድረጉም በላይ፣ የአፍሪካን ድምፅ እና የቴክኖሎጂ ፍላጎት በዓለም መድረክ ለማስተጋባት አቅም ሆኗታል።
በሰው ሠራሽ አስተውሎት ዘርፍ የወጡት ብሔራዊ ፖሊሲዎች እና የሕግ ማዕቀፎች ደግሞ የቴክኖሎጂውን ሥጋቶች አስቀድሞ በመገደብ በራስ መተማመን እና በሉዓላዊነት ላይ የተመሠረተ የቴክኖሎጂ ዕድገትን ለማረጋገጥ አስችለዋል።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #digitalethiopia #brics2026 #medemer #artificialintelligence #techtransfer #aiuniversity #globalsouth #innovation

"ለኢትዮጵያ የባሕር በር ማግኘት ከምንም ነገር በላይ ቀዳሚው እና ወሳኙ የኢኮኖሚ ጉዳይ ነው" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
******************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ18ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ለኢትዮጵያ የባሕር በር ማግኘት ከምንም ነገር በላይ ቀዳሚው እና ወሳኙ የኢኮኖሚ ጉዳይ መሆኑን አስምረውበታል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው፣ "ግዙፍ እና እያደገ ያለ ኢኮኖሚ እንደመሆናችን መጠን፣ አስተማማኝ እና የተለያዩ የዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮች ተደራሽነት ያስፈልገናል" ብለዋል።
ኢትዮጵያ ይህንን ዓላማዋን በሰላማዊ እና በድርድር ላይ በተመሠረቱ መንገዶች ከዳር ለማድረስ መሥራቷን እንደምትቀጥልም አረጋግጠዋል።
የዚህ ጥረት ዋና ዓላማም የንግድ ወጪን መቀነስ፣ የላቀ የመቋቋም አቅምን መገንባት እና የጋራ ብልጽግናን ማረጋገጥ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል።
#ethiopia #ebc #pmabiyahmed #brics #brics2026 #seaaccess

የብሪክስ መሪዎች የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አጠቃላይ ሪፎርም እንዲደረግበት ጠየቁ
*****************
በሕንድ ኒው ዴልሂ እየተካሄደ ባለው 18ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) እና የፀጥታው ምክር ቤትን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ተቋማት ይበልጥ ዴሞክራሲያዊ እና ውክልናን ያረጋገጡ እንዲሆኑ አጠቃላይ የማሻሻያ (ሪፎርም) ዕርምጃዎች እንዲወሰዱ ጠየቀ።
ከዚህ ቀደም ተመድ እና የፀጥታው ምክር ቤት ሪፎርም እንዲደረግባቸው እና አፍሪካ ተገቢውን ውክልና እንድታገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መጠየቃቸው አይዘነጋም።
የብሪክስ መሪዎች ባወጡት የጋራ የአቋም መግለጫ ላይ፣ በተለይም አሁን ያለውን የዓለም አቀፍ ግንኙነት መዋቅር የወቅቱን ነባራዊ ሁኔታዎች ይበልጥ እንዲያንጸባርቅ አድርጎ ማሻሻል እንደሚያስፈልግ አፅንኦት ሰጥተዋል።
መግለጫው በተለየ ሁኔታ አሁን እየተካሄደ ያለውን የቀጣዩን የተመድ ዋና ጸሐፊ ምርጫ ሒደት በማንሣት፣ በድርጅቱ ታሪክ እስካሁን ድረስ አንዲትም ሴት ለዋና ጸሐፊነት ተመርጣ እንደማታውቅ በትኩረት አንሥቷል።
ከዚህም በተጨማሪ ከላቲን አሜሪካ እና ካሪቢያን አንድ ሰው ብቻ፣ ከአፍሪካ እና ከእስያ ደግሞ እያንዳንዳቸው ሁለት ሰዎች ብቻ ይህንን ቦታ መያዛቸውን በማስታወስ የውክልና ክፍተቱን አመላክቷል።
የተመድን የፀጥታው ምክር ቤት ሪፎርምን በተመለከተም መሪዎቹ ጠንካራ አቋም አንፀባርቀዋል። ምክር ቤቱ አሁን ላለው ዓለም አቀፍ ፈተና ተገቢውን ምላሽ መስጠት እንዲችል የአዳጊ ሀገራትን ውክልና ማሳደግ እንደሚያስፈልግ እና በተለይም በአፍሪካ ሀገራት በ‘ኤዙልዊኒ ስምምነት’ እና በ‘ሲርቴ የአቋም መግለጫ’ ላይ የተንጸባረቀው ሕጋዊ ጥያቄ ዕውቅና ሊኖረው እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።
የፀጥታው ምክር ቤት ሪፎርም የደቡቡን ክፍለ ዓለም ድምፅ እንዲጎላ የሚያደርግ መሆን እንዳለበትም አስገንዝበዋል። የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባላት የሆኑት ቻይና እና ሩሲያ፣ ብራዚል እና ሕንድ በተመድ ውስጥ የላቀ ሚና እንዲጫወቱ ያላቸውን ድጋፍ ዳግም አረጋግጠዋል።
በተመድ ሴክሬታሪያት እና በሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የውሳኔ አሰጣጥ ሒደቶች ላይ አፍሪካን፣ እስያን እና ላቲን አሜሪካን ጨምሮ አዳጊ ሀገራት ፍትሐዊ የጂኦግራፊያዊ ውክልና ሊኖራቸው እንደሚገባ የብሪክስ መሪዎች አሳስበዋል።
በእነዚህ ተቋማት ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ የሴቶችን በተለይም ከአዳጊ ሀገራት የመጡ ሴቶችን ተሳትፎ ማሳደግ እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል።
የተመድ የሥራ አስፈጻሚዎች እና የከፍተኛ ኃላፊዎች ሹመት የትኛውንም ሀገር ወይም የሀገራት ስብስብ የበላይነት የሌለበት እና ግልጽነትን የተከተለ መሆን እንዳለበት አቋማቸውን አንፀባርቀዋል።
መሪዎቹ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኃላፊነቱን እንዲወጣ የሚያስፈልገውን ድጋፍ ሁሉ ለመስጠት ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ጠቅላላ ጉባኤውን ለማነቃቃት፣ የኢኮኖሚ እና ማኅበራዊ ምክር ቤቱን (ECOSOC) ለማጠናከር እና የሰላም ግንባታ መዋቅሩን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት እንደሚደግፉ አስታውቀዋል።
በሌላ በኩል ሆን ብሎ የገንዘብ መዋጮን በመከልከል የዓለም አቀፍ የባለብዙ ወገን ተቋማትን ሥራ ለማዳከም የሚደረጉ የተናጠል ሙከራዎችን አጥብቀው አውግዘዋል።
በዮናስ በድሉ
#ethiopia #ebc #brics #newdelhideclaration #brics2026

25 days ago
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢንዶኔዥያው ፕሬዚዳንት ፕራቦዎ ሱቢያንቶ ጋር ተወያይተዋል
#ethiopia #ebc #pmabiyahmed #indonesia #diplomacy #brics2026
#ethiopia #ebc #pmabiyahmed #indonesia #diplomacy #brics2026
25 days ago
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋር ተወያዩ
********************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በብሪክስ ጉባኤ ጎን ለጎን ከቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋር መወያየታቸውን ገልጸዋል።
#ethiopia #ebc #pmabiyahmed #china #diplomacy #brics2026
********************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በብሪክስ ጉባኤ ጎን ለጎን ከቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋር መወያየታቸውን ገልጸዋል።
#ethiopia #ebc #pmabiyahmed #china #diplomacy #brics2026
Sponsored by
Surafel
25 days ago
የኢትዮጵያ ሚዛናዊ የዲፕሎማሲ ስሌት፦ ብሔራዊ ጥቅምን የማስከበር ጥበብ
****************************
ዓለማችን ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ አይታው ወደማታውቀው የባለብዙ ዋልታ የሽግግር ምዕራፍ ውስጥ ገብታለች።
በዚህ ታሪካዊ ዘመን የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ከዕርዳታ እና ከብድር ጥገኝነት ወጥቶ እንዲሁም ከታዛቢነት ወደ አጀንዳ ቀራጭነት ተሸጋግሯል።
ኢትዮጵያ የዓለምን 49 በመቶ ሕዝብ እና 40 በመቶ ጠቅላላ ኢኮኖሚ የሚወክለውን የብሪክስ (BRICS) ስብስብ ሙሉ አባል መሆኗ የዚህ የልዕልና ጉዞ ማሳያ ተደርጎ ይወሰዳል።
የብሪክስ አባልነት በአጋጣሚ የተገኘ ሳይሆን ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ ያላትን የጂኦ-ፖለቲካዊ ተሰሚነት እና የዲፕሎማሲ አካሄድ ውጤት ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕንድ ኒው ዴልሂ እየተካሄደ ባለው 18ኛው የብሪክስ ጉባኤ ላይ ከሕንድ፣ ሩሲያ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች፣ ማሌዢያ፣ ኢራን እና ከካዛኪስታን መሪዎች ጋር ያደረጉት ሁለገብ ውይይት የዚህ ማሳያ ነው።
ውይይቶቹ የቴክኖሎጂ ሽግግርን፣ ማዕድን ልማትን፣ ኢንቨስትመንትን እና በተለይም የቀይ ባሕርን ደኅንነት ያማከሉ መሆናቸው ዲፕሎማሲያችን ምን ያህል ስትራቴጂያዊ እና ቀዳሚ ዕርምጃ ወሳጅ እንደሆነ ያመላክታሉ።
ከምዕራቡም ሆነ ከምሥራቁ ዓለም ጋር የጥቅም ሚዛንን የጠበቀ ግንኙነት መመሥረቱ በማንም ወገን ሳንጠለል ሁለንተናዊ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የተዘረጋ የተመጣጠነ ፖሊሲ ነው።
ይህ አዲሱ የዲፕሎማሲ ከፍታ የተገነባው በኃይል ማስገደድ ሳይሆን "ልዝብ ኃይል" (Soft Power) በሚባለው የማሳመን ጥበብ ነው።
ዘመናዊው የኮሪደር ልማት፣ የአረንጓዴ ዐሻራ፣ የአየር ንብረት ዲፕሎማሲ እና የፓን-አፍሪካኒዝም አቀንቃኝነታችን እንዲሁም ሰንደቅ ዓላማችንን ከፍ ያደረጉ አየር መንገዳችን እና አትሌቶቻችን ኢትዮጵያን ለቱሪዝም እና ኢንቨስትመንት ተመራጭ እያደረጓት ነው።
ከጎረቤት ሀገራት ጋር በኃይል እና በመሠረተ-ልማት የተዘረጋው ትሥሥር እንዲሁም የባሕር በር ለማግኘት የሚደረገው ጥረት፣ የዚሁ ብሔራዊ ልዕልናን የማረጋገጥ አካል ነው።
ሆኖም ይህ እጅግ ተስፋ ሰጪ የሆነ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ የዲፕሎማሲ ስኬት ዘላቂ እንዲሆን የሀገር ውስጥ የሰላም ግንባታን እና የተጀመረውን ሀገራዊ መግባባትን ከምንም በላይ ቅድሚያ ሰጥተን ማረጋገጥ አለብን። ጠንካራ እና የተረጋጋች ሀገር ለዲፕሎማሲ ስኬት ዋስትና ናት እና።
እንዲሁም በብሪክስ አባልነት የተከፈቱትን ሰፊ የገበያ እና የፋይናንስ አማራጮች ወደ ተግባር ለመቀየር፣ አምራች ኢንዱስትሪዎችን የበለጠ ማዘመን እና የሎጂስቲክስ አቅማችንን ማሳደግ የግድ ይለናል። የተገኙት የዲፕሎማሲ ድሎችም በጥናት እና ምርምር ላይ በተመሠረተ ጠንካራ ተቋማዊ አሠራር ውስጥ ሊዋሐዱ ይገባል።
በተጨማሪም የባሕር በር የማግኘት ጥረታችን የቀጣናው የጋራ ብልጽግና ማሳለጫ እንጂ የጸጥታ ስጋት አለመሆኑን ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ይበልጥ እንዲገነዘበው ስልታዊ የማግባባት ሥራው ተጠናክሮ ሊቀጥልም ይገባል።
ኢትዮጵያ የጥገኝነትን አዙሪት ሰብራ ዜጋ ተኮር እና የጋራ ተጠቃሚነትን ባረጋገጠ ስትራቴጂ የዓለምን መድረክ በክብር መቀላቀሏ በተግባር ተገልጿል። አሁን የሚጠበቅብን ይህንን የልዕልና ጉዞ በመደመር ዕሳቤ፣ በአንድነት እና በከፍተኛ የሥራ ባህል ከዳር ማድረስ ነው።
ዛሬ የምንጽፈው የዲፕሎማሲ ጥበብ፣ ነገ ልጆቻችን በኩራት የሚያነቡት የኢትዮጵያ የማይናወጥ ከፍታ ይሆናል።
በበረከት ሽመልስ
#ethiopia #ebc #pmabiyahmed #diplomacy #brics2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአቡ ዳቢ አልጋ ወራሽ ከልዑል ሼህ ኻሊድ ቢን ሙሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር ተወያይተዋል
#ethiopia #ebc #pmabiyahmed #abudabi #brics2026
25 days ago
አዲስ አበባ — የBRICS እና የአፍሪካ አህጉር አዲሷ የኃይል ማዕከል
➡ https://youtu.be/OSXEjO5at...
#brics2026 #agenda2063 #africandiplomacy #ethiopianairlines #addisababa
25 days ago
ፍትሃዊ የዓለም ሥርዓትን የመገንባቱ የብሪክስ ጉዞ እና ተፅዕኖው!
#ethiopia | የብሪክስ ስብስብ ከአለም አቀፍ የኢኮኖሚ የፖለቲካ እና የማህበራዊ እድገት አንጻር የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ እና እየጎለበተ መጥቷል።
የብሪክስ ስብስብ ለዘመናት የቆየውንና "አንድ ወገን ብቻ የሚወስንበትን" የዓለም የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ሥርዓት በመቀየር፣ ፍትሃዊ ሚዛናዊ እና ብዙ ማዕከላት ያሉት አዲስ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ምህዳር መገንባት ችሏል።
በአሁኑ ወቅት ስብስቡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ግዙፍ ቁጥራዊ እና ስትራቴጂካዊ ተፅዕኖዎች በመፍጠር ላይ ይገኛል።
የብሪክስ አባል ሀገራት የዓለምን ሕዝብ ከ45 በመቶ በላይ የሚሸፍኑ ሲሆን፣ በዓለም አቀፍ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ደግሞ ከ30 በመቶ በላይ የሚሆነውን ድርሻ ይይዛሉ።
ይህ ግዙፍ የገበያ እና የሕዝብ አቅም ስብስቡ በዓለም አቀፍ የንግድ እንቅስቃሴ የኢንቨስትመንት ፍሰት እና የዋጋ ተመን ላይ ወሳኝ ተፅዕኖ እንዲኖረው አድርጎታል።
ስብስቡ ከአለም ባንክ እና ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ውጭ አማራጭ የፋይናንስ ምንጭ የሚሆን "አዲስ የልማት ባንክ" በማቋቋም ታዳጊ የፖለቲካ ጫና ሳይደረግባቸው ለልማት ፕሮጀክቶቻቸው ብድር የሚያገኙበትን መንገድ አመቻችቷል።
በተጨማሪም አባል ሀገራቱ በሁለትዮሽ ንግዶቻቸው ወቅት የአሜሪካ ዶላርን ከመጠቀም ይልቅ በሀገር ውስጥ ገንዘቦቻቸው መነጋደድ መጀመራቸው የምንዛሬ ተመን መናጋት በታዳጊ ሀገራት ላይ የሚያደርሰውን ጫና እንዲቀንስ አድርጓል።
ለዘመናት በምዕራባውያን ሀገራት ቁጥጥር ስር የነበሩት እንደ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የጸጥታው ምክር ቤት ያሉ ተቋማት የዛሬውን የዓለም ነባራዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ እንዲሻሻሉ አድርገዋል።
ሀገራት በተቋማቱ ፍትሃዊ ተወካይነት እንዲኖራቸው የብሪክስ ስብስብ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል።
የዓለም ግዙፍ የነዳጅ የግብርና ምርቶች እና የኢንዱስትሪ ጥሬ ዕቃዎች አምራች ሀገራትን በአንድ ጃንጥላ ስር ያቀፈው ይህ ስብስብ የምግብ ዋስትናን እያረጋገጠ ይገኛል።
በአባላቱ መካከል የሚያደርገው የንግድና የቴክኖሎጂ ሽግግር የዓለምን የምግብ እና የኃይል አቅርቦት ሰንሰለት በማረጋጋት ረገድ ቁልፍ ሚና እየተጫወተ መሆኑ መረጃዎች ጠቁመዋል።
የ2026 የብሪክስ አባል ሀገራት ጉባኤ በህንድ ኒው ዴልሂ እየተካሄደ ይገኛል።
በጉባኤው የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቪላዲሚር ፑቲን፣ የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ፣ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ እና የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድን ጨምሮ በርካታ የዓለም መሪዎች ታድመዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #brics2026 #brics #india #newdelhi #narendramodi

26 days ago
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ18ኛው የብሪክስ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ኒው ዴልሂ ህንድ ገቡ
********************************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “ጽናትን፣ ፈጠራን፣ ትብብርን እና ዘላቂነትን መገንባት” በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው 18ኛው የብሪክስ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ኒው ዴልሂ፣ ህንድ ገብተዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመራው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን፤ ከጉባኤው ጎን ለጎን ቀጣናዊና ዓለም አቀፍ ትብብሮችን የሚያጠናክሩ የሁለትዮሽ ውይይቶችን እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።
#pmabiyahmed #brics #newdelhi #ethiopia #brics2026

ብሔራዊ የእደ ጥበብ ሙዚየም እና የሀስትካላ አካዳሚ
(National Crafts Museum & Hastkala Academy)
የጉዞ ማስታወሻ ( ክፍል - 2 )
#ethiopia |በኒው ዴልሂ በሚገኘው ብሔራዊ የዕደ-ጥበብ ሙዚየምና ሀስትካላ አካዳሚ (National Crafts Museum & Hastkala Academy) ዘለቅን። የብሪክስ ባዛር (BRICS Bazaar - ከመስከረም 10–15, 2026) እየተካሄደ ነው።
የብሪክስ ባዛር፦ ባህሎችን መቅረጽ፣ ሕዝቦችን ማገናኘት (BRICS Bazaar: Crafting Cultures, Connecting People) መሪ ቃል ይዟል። የንግድ ትርኢቱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በጨርቃጨርቅ ሚኒስቴር አዘጋጅነት የቀረበ ሲሆን፣ አማርኛ፣ ህንዲ፣ አረብኛ፣ እስፓንኛ፣ ፖርቱጋልኛ፣ ቻይንኛ ጨምሮ በተለያዩ ቋንቋዎች የተዘጋጁ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክቶችን ያካተተ ነው።
Ms. Shakshi Gupta - አስጎብኚያችን ስለሙዚየሙ መተንተን፤ ማስረዳት ጀመረች።
የቤንጋል መንደር ገጽታ (ምዕራብ ቤንጋል)
በ'ኩምሃር' (የሸክላ ሰሪ) ባለሙያዎች ማህበረሰብ ከተሰሩ የክሪሽናናጋር (ናዲያ ዞን) የሸክላ ምስሎች፣ ከሳርና የቀርከሃ ጎጆዎች እንዲሁም ከጌጣጌጥ ስራዎች ጋር የገጠር ሕይወትን ያሳያል።
የኪንሃል አሻንጉሊቶች (ካርናታካ)
ከኪንሃል የመጡ በእጅ በእንጨት የተቀረጹ አሻንጉሊቶች ሲሆኑ፣ በኮምጣጤ ፍሬ የተወለወሉና በደማቅ የከለር ቀለም የተሸለሙ ናቸው፤ በታሪክ ለሙሽሮች በስጦታ መልክ ይሰጡ ነበር።
የፓታቺትራ ስዕል (ኦዲሻ)፦ ከፑሪ፣ ራጉራጅፑር እና ቡባኔስዋር የመነጨ ባህላዊ የጨርቅ ላይ ስዕል (ፓታ + ቺትራ) ሲሆን፣ ከራማያና፣ ማሃባራታ እና ባጋቫታ ታሪኮችን ያቀርባል።
የናጋ ጥበብ (ናጋላንድ / ሰሜን-ምስራቅ ህንድ)፦ የጎሳ ባህል ያላቸው የእንጨት የቀደመ አባቶች ምስሎች፣ የተሸመኑ የሸንበቆና ቀርከሃ ቅርጫቶች፣ እንዲሁም በዐጥንት፣ ቀንድ እና ፀጉር ያጌጡ የትንባሆ ማጫሻዎች፣ ጦሮች እና ባርኔጣዎች ናቸው።
የፓቡጂ ፋድ (Phad of Pabuji - ራጃስታን)
በታጠበ የጥጥ ጨርቅ ላይ የሚሳሉ የመጠቅለያ (ስክሮል) ስዕሎች ሲሆኑ፣ በ13ኛው ክፍለ ዘመን በምዕራብ ራጃስታን ኮሉ (ማርዋር) ይኖር የነበረውን የፓቡጂ የተባለ የህዝብ ጀግና ህይወትና ተረቶች ያሳያሉ።
ታሪኩ ሙሉ ሌሊት በሚከናወኑ ስነ-ስርዓቶች ላይ 'ቦፓስ' (ከናያክ ማህበረሰብ የተወጣጡ ዘማሪዎች) በትልልቅ የሸክላ ማማዎች እየታጀቡ 'ፓቡጂ ራ ፓንዋራ' የተሰኙ የጀግንነት ዜማዎችን ሲዘምሩ ይተረካል።
ስዕሎቹ በቢልዋራ (ሜዋር) ሻህፑራ በሚገኙ የ'ጆሺ' ቤተሰብ ባለሙያዎች ብቻ የሚሳሉ ሲሆን፣ ጨርቁን አዘጋጅተው መልካም ቀን በመጠበቅ በባህላዊ ተፈጥሯዊ ቀለሞች ይስሏቸዋል።
አስጎብኚያችን Ms. Shakshi Gupta - ፈትፍታ የማጉረስ ትህትና ያላት ናት።
ጥያቄ አለ? - አለች።
የዶክራ ብረታ ብረት ዕደ-ጥበብ (Dhokra Metal Craft - ቻቲስጋርህ እና ማዕከላዊ/ምስራቅ ህንድ) ጥበብ ማውጋት ቀጠለች።
በሸክላ ቅርጾች ላይ በሚቀልጥ ሰም (cire perdue) የሚሰራ የ5,000 ዓመታት ዕድሜ ያለው የብረት ማቅለጥና ማፍሰስ ጥበብ ሲሆን፣ የተጠላለፈ ወይም የተጠቀለለ የላይኛው ገጽታ ቅርፅ በመያዙ ይታወቃል።
በቻቲስጋርህ (ባስታር)፣ ኦዲሻ፣ ጃርካንድ፣ ምዕራብ ቤንጋል እና አንድራ ፕራዴሽ ባሉ ከፊል-ዘላን የጎሳ ብረት ሰሪዎች የተሰራ ሲሆን፣ የእህል መለኪያ ማሰሮዎችን፣ የከብት ቃጭሎችን እና የነሐስ የጎሳ ምስሎችን (እንደ ከአደን የሚመለሱ አደንኞችን ምስል) ያመርታሉ።
የኮንድሃ / ኮንድ ነሐስ ስራዎች
(Kondha Bronzes - ኦዲሻ)
በኦዲሻ የራያጋዳ እና ጋጃፓቲ ዞኖች በሚኖሩ የኮንድሃ (ዶንጋሪያ ኮንድሃ) የጎሳ ቡድኖች በብረት ሰሪዎች ለዘመናት የተከናወነ የነሐስ ማፍሰስ ጥበብ ነው።
ሙሉ በሙሉ በማፍሰስና ሰም በማቅለጥ ቴክኒኮች ለ'ዳራኒ ፔኑ' (የምድር አምላክ) የመስዋዕት ስጦታዎች፣ የክብረ-በዓል ምልክቶች፣ የተለያዩ ቅርሶች እና በስጦታ (ሚዜ) የሚሰጡ አሻንጉሊቶችን ለመስራት ያገለግላል።
የካርናታካ የቡታ እምነት ቅርጻ ቅርጾች
(Bhuta Cult Sculptures - ካርናታካ)
በባህር ዳርቻይቱ ካርናታካ ኡዱፒ ዞን ከ19ኛው ክፍለ ዘመን የመጡ በእንጨት የተቀረጹ ምስሎችና የነሐስ ጭንብሎች ሲሆኑ፣ ከ'ቡታራዳኔ' (የመንፈስ አምልኮ ስነ-ስርዓት) ጋር የተያያዙ ናቸው።
በ'ጉዲጋር' የእደ-ጥበብ ማህበረሰብ ከጽኑ የጃክፍሩት እንጨት የሚቀረጹ ሲሆን፣ እንደ 'ፓንጁርሊ' (የዱር አሳማ መንፈስ)፣ 'ፒሊቻንዲ' (የነብር መንፈስ)፣ 'ጁማዲ' እና እንደ 'ኮቲ እና ቼናያ' ያሉ የአባቶች ጀግኖችን ይወክላሉ።
በወፍ በረር ማጠቃለያ ላይ ደረሰች
የማዱባኒ ስዕል (Madhubani Painting - ቢሃር)
በሰሜን ቢሃር የሚቲላ አካባቢ የሚገኝ ጥንታዊና መስመራዊ የህዝብ ስዕል ዘይቤ ሲሆን፣ በባህላዊ መልኩ በመንደር ሴቶች በግድግዳዎችና ወለሎች ላይ ይሳላል።
'ኮህባርቺትራ' (ለአዲስ ተጋቢዎች የመኝታ ክፍል ግድግዳ ስዕል) እና 'አሪፓና' (ለስለትና ባህላዊ ስነ-ስርዓቶች የሚሰራ የወለል ጌጣጌጥ) የሚያካትት ሲሆን፣ በአሁኑ ጊዜ በወረቀትና በሸራ ላይ ይሰራል።
ጠቅላላ የብረታ ብረት ዕደ-ጥበብ
(General Metal Crafts)
ከዕለት ተዕለት ቁሳቁሶች፣ የማስቀመጫ ሳጥኖችና የአልጋ እግሮች እስከ ባህላዊ ምስሎችና የወፍ እና የእንስሳት ቅርጽ ያላቸው የሱፓሪ መቁረጫዎች (sarota) ድረስ ያሉትን ባህላዊ የህንድ የነሐስና የብረት ጥበቦችን ያጎላል።
***
ከሙዚየም ወደ ባዛር ዘለቅን
ኢትዮጵያውያን የእደ ጥበብ ባለሙያዎች በBRICS Bazaar 2026 ላይ ተሳትፈዋል
በሕንድ ኒው ዴልሂ በሚገኘው ብሔራዊ የእደ ጥበብ ሙዚየም እና ሀስትካላ አካዳሚ (National Crafts Museum & Hastkala Academy) ከመስከረም 10 እስከ 15 ቀን 2026 እየተካሄደ ባለው BRICS Bazaar 2026 ላይ ኢትዮጵያውያን የእደ ጥበብ ባለሙያዎች ሀገራቸውን ወክለው ተሳትፈዋል።
ዝግጅቱ “Crafting Cultures, Connecting People” — “ባህሎችን መቅረጽ፣ ሕዝቦችን ማገናኘት” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ሲሆን፣ የተለያዩ የBRICS አገራትን ባህላዊ የእደ ጥበብ፣ ፋሽን፣ ጨርቃ ጨርቅ፣ ሸክላ ስራ እና ሌሎች ባህላዊ የእጅ ሥራዎችን ለዓለም አቀፍ ጎብኚዎች ያስተዋውቃል።
እጂጋየሁ ኃይለጊዮርጊስ አራርሶ
ከኢትዮጵያ በHandweaving – የእጅ ጨርቃ ጨርቅ ሥራ የተሳተፈችው እጅጋየሁ ኃይለጊዮርጊስ አራርሶ የፋሽን ዲዛይነርና ሥራ ፈጣሪ ስትሆን፣ Ejig Tibeb መስራች እና Ethiopian Fashion Designers Association ተባባሪ መስራች ናት።
የኢትዮጵያን ቡና ለታዳሚዎቹ በክብር አጠጥታለች።
መዓዛ አሰግድ አሰፋ
በሌላ በኩል መአዛ አሰግድ አሰፋ (Meaza Asegid Assefa) በHand Modelling / Pottery – የእጅ ሸክላ ሥራ ዘርፍ ኢትዮጵያን ወክላለች።
“Meaza Pottery – መአዛ ሸክላ ሥራ” በሚል የንግድ ስም ትሠራለች። በእጅ የተሰሩ ባህላዊ የሸክላ እቃዎችንና መያዣዎችን በማምረት የባህላዊ የሸክላ ጥበብን ለመጠበቅና ለማስቀጠል እየሰራች መሆኑ ተናግራለች።
የኢትዮጵያ የእደ ጥበብ ውበት በዓለም መድረክ
የኢትዮጵያ የእደ ጥበብ ባለሙያዎች በዚህ ዓይነት ዓለም አቀፍ መድረክ መሳተፋቸው፣ የአገሪቱን ባህላዊ የእጅ ሥራዎች፣ ፋሽንና የፈጠራ ሥራዎችን ለዓለም ማስተዋወቅ ከመቻሉ ባሻገር ለእደ ጥበብ ምርቶች አዳዲስ የገበያና የትብብር ዕድሎችን የሚከፍት አጋጣሚ ነው።
የጉዞ ማስታወሻ
ከፍል ( 3 ) ይቀጥላል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
Special thanks :
#india in Ethiopia (Embassy of India, Addis Ababa) #indiaethiopia #brics #financialcooperation #banking #economiccooperation #ministry of External Affairs, #government of IndiaIndia in Ethiopia (Embassy of India, #addis Ababa)Press Information Bureau - PIB, #government of IndiaDiaspora India ConnectMinistry of Information & Broadcasting, #government of #indiamygovindiaddnewsliveasian News #international (ANI)All India Radio News #india in ethiopia (embassy of india addis ababa) #manohar Lal #ethiopian Airlines #ministry of External Affairs
Government of India
# India - External Publicity & Public Diplomacy Division External Language Media Section #mr . Amit Raghav, Publicity Officer (XLM) #unesco #brics2026 #bricsbazaar2026 #ethiopia #india #newdelhi #crafts #handicraft #handweaving #pottery #ethiopianfashion #getutemesgen

3 months ago
ኢነርጂ ለሁሉም፦ የኢትዮጵያና የብሪክስ የጋራ ራዕይ
******************
ኢትዮጵያ በህንድ በተካሄደው 11ኛው የብሪክስ የኢነርጂ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ በታዳሽ ኃይል ዘርፍ እያስመዘገበችው ያለውን ተስፋ ሰጪ ዕድገት እና የወደፊት ራዕይዋን በስፋት አስተዋውቃለች።
ሀገራችን እ.አ.አ በ2030 መላው ዜጋ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆን ያስቀመጠችውን ብሔራዊ ግብ ለማሳካት ያላትን ጽኑ ቁርጠኝነት በዚሁ ዓለም አቀፍ መድረክ ላይ በድጋሚ አረጋግጣለች።
በዚሁ መድረክ ላይ ኢትዮጵያ በዘመናዊ የኃይል መረብ ግንባታ፣ በኃይል ማከማቻ ቴክኖሎጂዎች፣ በማስተላለፊያ መሠረተ ልማት እና ከብሔራዊ ግሪድ ውጪ ባሉ የኃይል አማራጮች ላይ በከፍትኛ ደረጃ ኢንቨስት እያደረገች መሆኑን አብራርታለች።
በተጨማሪም የኑክሌር ኃይልን ለሰላማዊ ዓላማ ለማልማት እንዲሁም አረንጓዴ ሃይድሮጅንን ለማዳበሪያ ምርት፣ ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እና ለኤክስፖርት ለመጠቀም ሰፊ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑ ተገልጿል።
በሌላ በኩል ህንድ በብሪክስ ማዕቀፍ ስር የዲጂታል ስማርት ግሪድ እና የኃይል ማከማቻ የልህቀት ማዕከል እንዲቋቋም ሃሳብ ያቀረበች ሲሆን፣ በዚህም ማዕከሉ በአባል ሀገራቱ መካከል የቴክኖሎጂና የእውቀት ሽግግር ለማድረግ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ገልጻለች።
የግል ባለሀብቶችን በስፋት በመሳብ እና ቀጣናዊ የኃይል ትስስርን ይበልጥ በማጠናከር የብሪክስን “ኢነርጂ ለሁሉም” ራዕይ እውን ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደምትሠራም አስታውቃለች።
በሔዋን ጌታቸው
#ethiopia #ebc #brics2026 #renewableenergy #greenenergy #smartgrid #sustainability #energyforall

Comments