1 month ago
የነገዋ ታዳጊ ተማሪዎች በቴክኖሎጂ የታገዘ የፈጠራ ስራዎቻቸውን ለእይታ አቀረቡ
#ethiopia | ነገን በቴክኖሎጂ ለመቀየርና የሀገራቸውን ችግሮች በፈጠራ የሳይንስ ጥበብ ለመፍታት ቆርጠው የተነሱ ህጻናትና ታዳጊዎች፣ ማህበረሰባዊ ፋይዳ ያላቸውንና አስደናቂ የሆኑ የሮቦቲክስ ፈጠራ ስራዎቻቸውን ለዕይታ አብቅተዋል።
እነዚህ ታዳጊዎች በዕድሜ ለጋ ቢሆኑም፣ ያቀረቧቸው የፈጠራ ውጤቶች ግን የነገዋን ኢትዮጵያ ብሩህ ተስፋ ፍንትው አድርገው የሚያሳዩ ሆነዋል።
ከተሳታፊዎቹ መካከል የ15 ዓመቷ ታዳጊ ሮዳ ፈታ አንዷ ስትሆን፣ አካል ጉዳተኞችንና የአእምሮ ህመም ያለባቸውን ሰዎች ያለምንም ሰው እገዛ በራሱ ጊዜ መመገብ የሚችል ማሽን ሰርታ ለእይታ አቅርባለች። «ኢትስ ኤ ፊደር» (It's a feeder) የሚል ስያሜ የሰጠችው ይሄው ማሽን፣ የብርሃንና የከለር ሴንሰሮችን በመጠቀም በአንድ ጊዜ እስከ አራት ሰዎችን ማብላት የሚያስችል አቅም አለው ብላለች።
ሆስፒታል ውስጥ የሚገኙ የህክምና ባለሙያ ዘመዷን ለመጠየቅ በምትሄድበት ወቅት የተቸገሩ ሰዎችን አይታ ይሄንን የፈጠራ ስራ ለመስራት መነሳሳቷን የገለጸችው ታዳጊ ሮዳ፣ ማሽኑ ተንቀሳቃሽ እንዲሆን ከስሩ ጎማዎች የተገጠሙለት መሆኑንና ወደፊትም በትምህርቷ ገፍታ በትውልድ ሀገሯ ትልልቅ የቴክኖሎጂ ስራዎችን የመስራት ትልቅ ህልም እንዳላት በልበ ሙሉነት ተናግራለች።
በተመሳሳይ መልኩ ናስናፍ ይስሐቅ እና ኢቫን ዘረይ የተባሉ ታዳጊ ተማሪዎች የሀገራቸውን የቡና ምርት ሂደት ለማቃለል የሚያስችል «ኮፊ ቢን ኮሌክተር» የተሰኘ ዘመናዊ የቡና ፍሬ መልቀሚያ ማሽን ይዘው ቀርበዋል።
የኢትዮጵያ ዋነኛ ችግር ቡና በእጅ መለቀሙ እንደሆነ በመረዳት ችግሩን ለመፍታት መነሳሳታቸውን የገለጹት ታዳጊዎቹ፣ የሰሩት ማሽን በአራት ሞተሮችና በተለያዩ ፕሬዠር ሴንሰሮች የታገዘ ሲሆን፣ ከሰው ጉልበት በተሻለ በ10 እጥፍ ፍጥነት ቡናን ሰብስቦ በተዘጋጀለት ቅርጫት ውስጥ ማስገባት እንደሚችል በተግባር አስረድተዋል።
የስቴም ፎር ኪድስ ፍራንቻይዝ ባለቤትና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ኤርሚያስ ሰለሞን በበኩላቸው፣ የትምህርት ፕሮግራሙ ዋና ዓላማ ህጻናት እየተጫወቱና እየተደሰቱ ክሬቲቪቲን፣ ኮሙኒኬሽንንና ክሪቲካል ቲንኪንግን እንዲያሳድጉ ማድረግ እንደሆነ ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት በአለም ላይ መደበኛ የሆኑ ስራዎች በሙሉ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስና በማሽን ለርኒንግ እየተተኩ በመሆኑ፣ ልጆችን ከወዲሁ ለዚህ አዲስ ዓለም ማዘጋጀት እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ባለፉት ሶስት ዓመታት ተኩል ጊዜ ውስጥ ወደ 5,000 የሚጠጉ ተማሪዎችን ማስተማር መቻላቸውን የገለጹት አቶ ኤርሚያስ፣ ወደፊትም ከኢትዮ ቴሌኮምና ከሳፋሪኮም ጋር በመተባበር ትምህርቱን በኦንላይን በማስፋፋት አቅም ለሌላቸውና በየክፍለ ሀገሩ ለሚገኙ በርካታ የመንግስት ትምህርት ቤት ልጆች ጭምር በስፋት ለማድረስ ከፍተኛ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን ጠቁመው፣ ቴክኖሎጂውን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ያለውን የእቃ አቅርቦትና የፖሊሲ ፈተናዎች መንግስት ተረድቶ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
በጌትነት ተመስገን
📷ከበደ መክብብ
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#stemethiopia #stemforkids # #technologyethiopia #ethiopiangenius #digitaltransformationethiopia

4 months ago
ይምረጡ | Vote - የብሄራዊ ኩራት ጥሪ
ናትናኤልን የዓለም ሻምፒዮን እናድርገው! 🇪🇹🏆
#ethiopia | ኢትዮጵያዊው የሶፍትዌር መሃንዲስ ናትናኤል ጌታነው በአማዞን (AWS) የዓለም አቀፍ AI ውድድር ላይ ከ10,000 ተወዳዳሪዎች መካከል ተለይቶ ለፍፃሜ ደርሷል! የፈጠረው "Ivy" የተሰኘው መተግበሪያ ኢንተርኔት በሌለበት ሁኔታ ተማሪዎችን የሚያስተምር ድንቅ የቴክኖሎጂ ውጤት ነው።
ናትናኤል በዓለም 1ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ግን የህንድና የአውሮፓ ተወዳዳሪዎች ከፍተኛ ድምፅ በማሰባሰብ 1ኛነቱን ለመንጠቅ እየተረባረቡ ነው።
ውድድሩ ሊጠናቀቅ የቀረው 34 ሰዓታት ብቻ ነው!
ናትናኤልን ለማሸለም እነዚህን 3 ደረጃዎች ይከተሉ፦
ሊንኩን ይጫኑ፦ የናትናኤል የውድድር ገጽ
ይግቡ (Sign In)፦
በGoogle ወይም በኢሜልዎ "Sign in" ያድርጉ (ይህ ድምፅዎ ትክክለኛ መሆኑን ለማረጋገጥ ነው)።
ላይክ (👍 Like) ያድርጉ፦
የላይክ ምልክቷን በመጫን ናትናኤልን ወደ 1ኛነት ይመልሱት።
የኢትዮጵያዊያን ስኬት የሁላችንም ኩራት ነው፤ በቴክኖሎጂው ዓለም ዋንጫውን ወደ ሀገራችን እናምጣ!
#getu #nathnaelgetaneh #aws #ai #ivyai #ethiopiangenius #voteforethiopia #techinnovation #africarising #ናትናኤልጌታነው #ኢትዮጵያ #አማዞን #ድምፅእንስጥ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

Comments