27 days ago
18ኛው የብሪክስ አባል ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ በህንድ ኒው ዴልሂ መካሄድ ጀመረ
#ethiopia | ለማይበገር አቅም፣ ለፈጠራ፣ ለጋራ ትብብር እና ለደህንነት ግንባታ በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው 18ኛው የብሪክስ መሪዎች ጉባኤ በህንድ ኒው ዴልሂ መካሄድ ጀምሯል።
ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ ታላቅ ዓለም አቀፋዊ መድረክ ላይ የኢትዮጵያን ልዑክ የሚመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በቦታው ተገኝተው ተሳትፏቸውን ጀምረዋል።
የወቅቱ የብሪክስ ሊቀ መንበር በሆነችው ህንድ አስተናጋጅነት በሚካሄደው በዚህ ጉባኤ ላይ ወደ አምስት መቶ የሚጠጉ የሀገር መሪዎች፣ የአጋር ሀገራት ተወካዮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ኃላፊዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
በተጨማሪም ከመድረኩ ጎን ለጎን በሚካሄደው የንግድ ፎረም ላይ ከሁለት ሺህ በላይ የንግድ ልዑካን ተሳታፊ ሆነዋል።
የዘንድሮው ጉባኤ በዋናነት በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ተደማጭነት ማሳደግ፣ ዓለም አቀፍ አስተዳደርን ማጠናከር፣ የአቅርቦት ሰንሰለት ደህንነትን ማረጋገጥና የዲጂታል ኢኮኖሚን ማስፋት ላይ ትኩረት አድርጓል።
ከዚህ በተጨማሪ በኢነርጂ፣ በምግብ ዋስትናና በጂኦፖለቲካዊ ውጥረቶች ዙሪያ የመፍትሔ አማራጮች የሚቀርቡበት ውይይት ይደረጋል።
በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ከጉባኤው ጎን ለጎን ከህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር ተገናኝተው መክረዋል።
ሁለቱ መሪዎች በመከላከያ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በአቅም ግንባታ፣ በማዕድን ዘርፍና በኮፕ32 አጀንዳዎች ዙሪያ አብሮ ለመስራት ተስማምተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እንደገለጹት ኢትዮጵያና ህንድ ያላቸውን የቆየ ታሪካዊ ትስስር ወደ ላቀ የኢንቨስትመንት፣ የቴክኖሎጂና የጋራ ተጠቃሚነት አጋርነት ለማሸጋገር አሁን ትክክለኛው ጊዜ ነው።
Special thanks : #india in Ethiopia (Embassy of India, Addis Ababa) #indiaethiopia #brics #financialcooperation #banking #economiccooperation #ministry of External Affairs, #government of IndiaIndia in Ethiopia (Embassy of India, #addis Ababa)Press Information Bureau - PIB, #government of IndiaDiaspora India ConnectMinistry of Information & Broadcasting, #government of #indiamygovindiaddnewsliveasian News #international (ANI)All India Radio News #india in ethiopia (embassy of india addis ababa) #manohar Lal #ethiopian Airlines #ministry of External Affairs
Government of India
# India - External Publicity & Public Diplomacy Division External Language Media Section #mr . Amit Raghav, Publicity Officer (XLM) #unesco #brics #narendramodi #india #bricsbusinessforum #economy #trade #ethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa #brics #bricssummit #pmabiyahmed #narendramodi #ethiopiaindiaties #cop32 #diplomacy #india #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Comments