6 months ago
የኤርዶጋን የአዲስ አበባው ንግግር ቅሬታ አስነሳ
#ethiopia | የቱርኩ መሪ ኤርዶጋን በአዲስ አበባ ባደረጉት ጉብኝት፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር በነበራቸው የጋራ መግለጫ የወዳጅነት መልእክታቸውን ብቻ ሳይሆን፣ የአፍሪካ ቀንድን ዲፕሎማሲ የሚያናውጥ አስተያየትም ይዘው ብቅ ብለዋል። ፕሬዝዳንቱ አፅንዖት የሰጡት በሁለት ዋና ነጥቦች ላይ ነው፦
* ሉዓላዊነት፦ ቱርክ ለአገራት የግዛት አንድነት ያላትን ፅኑ አቋም በመግለጽ፣ ሶማሊያን ያላገለለ አካሄድ እንደምትደግፉ ገልፀዋል።
* የእስራኤል "ካርድ"፦ እስራኤል ለሶማሊላንድ እውቅና መስጠቷን በጽኑ በመተቸት፣ ይህ እርምጃ ለቀጣናው ሰላም ጠንቅ እንጂ ፋይዳ እንደሌለው ገልጸዋል።
የሶማሊላንድ ቁጣ፦ "ዲፕሎማሲያዊ ጣልቃ ገብነት"
ይህ የኤርዶጋን ንግግር በሀርጌሳ በኩል በቀላሉ አልታለፈም። የሶማሊላንድ መንግስት በሰጠው ምላሽ፣ የቱርክን አቋም "የሉዓላዊነት ጥሰት" እና "ያልተገባ ጣልቃ ገብነት" ሲል ኮንኖታል። ሶማሊላንድ የራሷን የውጭ ግንኙነት የመወሰን መብት እንዳላት በማሳሰብ፣ የኤርዶጋን ንግግር የቀጣናውን ሚዛን የሚያዛባ ነው የሚል ጠንካራ ተቃውሞ አሰምታለች።
አሁን ላይ ኢትዮጵያ በሁለት ኃያላን ወዳጆቿ መካከል ያለች ትመስላለች። በአንድ በኩል ለኢትዮጵያ ሰላምና ልማት ቁልፍ አጋር የሆነችው ቱርክ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በስትራቴጂካዊ ግንኙነቷ ስሟ የሚነሳው እስራኤል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ethiopia #turkey #somaliland
#israel #diplomacy #africahorn #erdogan #abiyahmed

የፕሬዚዳንት ኤርዶጋን የኢትዮጵያ ጉብኝት እንደተጠበቀ ነው
#ethiopia | የቱርኩ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬቶችና ወደ ኢትዮጵያ ለማቅናት አቅደው የነበረ ቢሆንም፣ የኤምሬቱ ጉዟቸው በፕሬዚዳንት መሐመድ ቢን ዛይድ የጤና እክል ምክንያት ለሌላ ጊዜ መራዘሙ ታውቋል።
ሁለቱ መሪዎች በስልክ ባደረጉት ውይይትም ፕሬዚዳንት ኤርዶጋን ለቢን ዛይድ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ወደ ኢትዮጵያ የሚደረገው ጉዞ ስለመራዘሙ ሲነሳ ለነበረው ጥያቄ የቱርክ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ምላሽ ሰጥቷል። የቢሮው ዳይሬክተር ቡርሃኔትን ዱራን እንደገለጹት፤ የፕሬዚዳንቱ የኢትዮጵያ ጉብኝት ምንም ዓይነት ለውጥ አልተደረገበትም፤ እንደተጠበቀ ነው።
የጉብኝቱ ዋና ዋና ዓላማዎች፦
* ግብዣ፦ ጉብኝቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የቀረበ ይፋዊ ግብዣ ነው።
* የውይይት አጀንዳዎች፦ መሪዎቹ በሁለትዮሽ ግንኙነቶች፣ በንግድ ትስስር እና በወቅታዊ ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በስፋት ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
* ስምምነቶች፦ በቆይታቸውም ድርድር የተጠናቀቀባቸው የንግድ፣ የመከላከያ እና የመሠረተ ልማት ስምምነቶች በይፋ እንደሚፈረሙ ተጠቁሟል።
ይህ ጉብኝት በኢትዮጵያና በቱርክ መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ ግንኙነት ይበልጥ ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግረዋል ተብሎ ይታመናል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ኢትዮጵያ #ቱርክ #ኤርዶጋን #ዐቢይአህመድ #ዲፕሎማሲ #ንግድ #መከላከያ #ethioturkey #diplomacy #erdogan #ethiopia

Comments