3 months ago
የዲጂታል ዲፕሎማሲ አዲስ ምዕራፍ፦ የኢትዮጵያ ገጽታ በዓለም አደባባይ
***************
ዓለም ከተለመደው የሚዲያ እና የሕዝብ ግንኙነት አሠራር ወጥታ፣ ፈጣን ወደሆነው የዲጂታል ሚዲያ ዓለም ተሻግራለች።
በዚህ ዘመን ሀገርን ለማስተዋወቅ ዲፕሎማቶችን ማሰማራት እና መደበኛ መገናኛ ሚዲያን ‘ሎቢ’ ማድረግ ብቻ በቂ አይደለም።
ዘመኑን ለመዋጀት በደቂቃዎች ውስጥ ሚሊዮኖችን የሚደርሰውን የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጭ መጠቀም ብልህነት ነው።
በርካታ ሀገራት ከፍተኛ በጀት በመመደብ የሰዎች ዓይን በሚያርፍባቸው ታዋቂ መድረኮች ላይ ማስታወቂያዎችን ይገዛሉ።
ለዚህም ለታዋቂው የአርሴናል እግር ኳስ ክለብ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር በመክፈል፣ "ሩዋንዳን ይጎብኙ" (Visit Rwanda) በሚል ራሷን እያስተዋወቀች ያለችው ሩዋንዳ ተጠቃሽ ምሳሌ ናት።
የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ገፅታ ለዓመታት በምዕራባውያን ሚዲያዎች በተዛባ ትርክት ስር ወድቆ መቆየቱ ይታወቃል።
ይህ ኢትዮጵያን የችግር እና የጉስቁልና ተምሳሌት ብቻ አድርጎ የሳለው ትርክት፣ ከሀገራቸው የተሰደዱ ኢትዮጵያውያን ሁልጊዜም በቁጭት የሚያነሱት ጉዳይ ነው።
በአሁኑ ወቅት ግን ሀገራችን በጀመረችው አዲስ የዲጂታል ዲፕሎማሲ ስትራቴጂ፣ እውነተኛ እና ብሩህ ገፅታዋን ለዓለም ማሳየት ጀምራለች።
ከተለመዱት የሕዝብ ግንኙነት ዘመቻዎች በመውጣት፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተከታዮች ባሏቸው ዓለም አቀፍ የማኅበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች አማካኝነት የራሷን ታሪክ በራሷ አንደበት እየተረከች ትገኛለች።
በቅርቡ ታዋቂው አሜሪካዊ ዩቲዩበር ‘አይሾውስፒድ’ በአዲስ አበባ ባደረገው እና አህጉራዊ የተመልካች ክብረ ወሰንን በሰበረው የቀጥታ ሥርጭት የከተማዋን ዘመናዊነት አስተዋውቋል።
ይህ የ‘አይሾውስፒድ’ የቀጥታ ሥርጭት በ20 ሰዓታት ውስጥ ብቻ 10 ሚሊዮን እይታዎችን ከማስመዝገቡም በላይ፣ ሥርጭቱ በነበረበት ወቅት ከ260 ሺህ በላይ አዳዲስ ሰብስክራይበሮችን አግኝቷል።
በተመሳሳይ በቲክቶክ የዜና አቅራቢነቱ የሚታወቀው ዲለን ፔጅ (ኒውስ ዳዲ) እና የጉዞ ቪሎገሩ ድሩ ቢንስኪ የተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎችን በመጎብኘት፣ ሀገራችን ያላትን ጥንታዊ የታሪክ በረከት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ለዓለም ሕዝብ አጋርተዋል።
ከዚህም ባሻገር ታዋቂው ጋናዊ ዩቲዩበር ዎዴ ማያ በሁለት የተለያዩ የጉብኝት መርሐ ግብሮቹ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በማሳየት በግድቡ ላይ የሚነዛውን አሉታዊ ትርክት ሰብሯል።
ዎዴ ማያ ከሕዳሴ ግድብ በተጨማሪ እስከ ዓድዋ ድረስ በመጓዝ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ የነጻነት ችቦ የለኮሰችበትን ታሪካዊ ምድር ጎብኝቷል።
በርካታ ታላላቅ የኢትዮጵያ ፕሮጀክቶችን ለዓለም በማሳየት የምዕራባውያንን አሉታዊ ትርክት ከማክሸፉም በላይ፣ የፓን አፍሪካኒዝም ትብብርን አጉልቶ አሳይቷል።
ይህ የትርክት ለውጥ በቅርቡ አዲስ አበባ ባስተናገደችው የአፍሪካ ማኅበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ ይበልጥ ተቋማዊ መልክ እንዲይዝ ተደርጓል።
ከ321 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች ያሏቸው 61 የአፍሪካ ይዘት ፈጣሪዎች በተሳተፉበት በዚህ ጉባኤ፣ ኢትዮጵያ የአፍሪካ የዲጂታል ትርክት ማዕከል መሆኗ ተረጋግጧል።
እነዚህ ስኬቶች እውን ሊሆኑ የቻሉት ደግሞ እንደ አዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ባሉ ሰፊ የመሠረተ ልማት ዝርጋታዎች አማካኝነት ነው።
ውበትን እየተላበሰች እና እየዘመነች ያለችው አዲስ አበባ ለዲጂታል ቀረጻ ምቹና ማራኪ ከመሆኗም በላይ፣ የአፍሪካ መዲናነቷን በተግባር እያረጋገጠች መምጣቷ የእነዚህን ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ቀልብ ሊገዛ ችሏል።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #digitaldiplomacy #visitethiopia #nationbranding #wodemaya #africa #addisababa

Comments