4 months ago
የጨፌ ኦሮሚያ 10ኛ መደበኛ ጉባዔ በሹመቶችና በአዳዲስ ውሳኔዎች ተጠናቀቀ
#ethiopia | በአዳማ ከተማ በአባ ገዳ አዳራሽ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የኦሮሚያ ጨፌ 6ኛ የሥራ ዘመን፣ 5ኛ ዓመት፣ 10ኛ መደበኛ ጉባዔ ዛሬ ፍጻሜውን አግኝቷል። በቆይታውም ክልላዊ ፋይዳ ያላቸውን ሪፖርቶች መርምሮ ከማጽደቁም በላይ ልዩ ልዩ ሹመቶችን ሰጥቷል።
ቁልፍ ውሳኔዎችና የተከናወኑ ተግባራት፦
የስድስት ወራት አፈጻጸም፦ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የሥራ አስፈጻሚ አካላትን የ6 ወራት የሥራ ሪፖርት ለጉባዔው አቅርበዋል። አባላቱ በሪፖርቱ ላይ በሰፊው ከመከሩ በኋላ በሙሉ ድምፅ አጽድቀውታል።
አዳዲስ ሹመቶች፦
ወይዘሮ ሮዛ ቢያ
የኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።
የ88 ዳኞች ሹመት በጉባዔው ጸድቋል።
የሕግ ድጋፍ አዋጅ፦ ነፃ የሕግ አገልግሎት ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ድጋፍ ለመስጠት የወጣውን አዋጅ ጨፌው መርምሮ አጽድቋል።
ያለመከሰስ መብት፦ በከፍተኛ ወንጀል የተጠረጠሩ የአንድ የጨፌ አባል ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ተወስኗል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #oromia #caffeeoromia #shimelisabdisa #ethiopia #adama #news