3 months ago
አርቲስት ዓሊ ቢራ - የኅብረ-ብሔራዊነት እና የወንድማማችነት ምልክት
********************
ዓሊ ቢራ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ውስጥ የፍትሕ፣ የእኩልነት እና የሰብዓዊነት ድምፅ ሆኖ ኖሯል።
የእርሱ ዐርበኝነት የሚጀምረው ገና በልጅነቱ ለጭቁኖች እና ድምፅ ለሌላቸው ወገኖቹ ድምፅ ሆኖ በመነሣት ነው።
ዓሊ በዜማዎቹ ሕዝብን ከማዝናናት ባለፈ፣ የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦች በነፃነት እና በእኩልነት የሚኖሩባትን ሀገር አልሟል፤ ለዚህም በተግባር ታግሏል።
ዓሊ ቢራ ኢትዮጵያዊነት ማለት በልዩነት ውስጥ ያለ ጥልቅ ውበት መሆኑን ሰብኳል።
ያቀነቀናቸው ዜማዎች የሕዝቦችን ልብ የሚያቀራርቡ እና የጥላቻን ግንብ የሚያፈርሱ የፍቅር ድልድዮች ነበሩ።
የዘመኑ ዐርበኝነት በእርሱ ዕይታ፣ የራስን መብት እያስከበሩ የሌላውን ክብር መጠበቅ፣ በወንድማማችነት እና በእህትማማችነት መንፈስ ለጋራ ብልጽግና መቆም ነው።
ዘፈኖቹንም ከአፋን ኦሮሞ በተጨማሪ በአማርኛ፣ በሐረሪ፣ በሶማሊኛ፣ በዓረብኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎችም በማቀንቀን ከአንድ ብሔር አልፎ ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ተደራሽነት እንዲኖረው አድርጓል።
ዓሊ፣ "አንድ ሰው የራሱን ማንነት ሲያከብር እና ሲወድ ነው ሌላውን ማክበር የሚችለው" የሚል ጽኑ አቋም ነበረው።
ኢትዮጵያን የሚያያት እንደ ተለያዩ ውብ ቀለሞች ስብስብ ነው። አንዱ ቀለም ሌላውን ሳይውጥ፣ ሁሉም በየራሳቸው ደምቀው የሚፈጥሩት ውበት እንደሆነ ይረዳ ነበር። ለዚህም ነው በተለያዩ የሀገራችን ቋንቋዎች በመዝፈን ድልድይ ለመሆን የሞከረው።
ዓሊ ኢትዮጵያዊነትን በተግባር ከገለጸባቸው መንገዶች አንዱ በትምህርት ላይ የነበረው እምነት ነው።
ዓሊ ቢራ ለኦሮሞ ሕዝብ ኩራት፣ ለኢትዮጵያውያን የጥበብ ተምሳሌት፣ ለአፍሪካ ደግሞ የነፃነት እና የማንነት ድምፅ ነው።
የእርሱ ኢትዮጵያዊነት "በእኩልነትና በመከባበር ላይ የቆመ የጋራ ቤት" የመገንባት ራዕይ ነበር።
ለዚህ የነፃነት እና የእኩልነት ምልክት ለሆነ ጀግና የቆመለት ሐውልት፣ ትውልዱ ልዩነቱን እንደ ጌጥ እንጂ እንደ ጦር መሣሪያ እንዳይጠቀምበት ያስተምራል።
ዐርበኝነት ማለት ለፍትሕ መቆም፣ ደካሞችን መርዳት እና በኪነ-ጥበብ አማካኝነት ብሔራዊ መግባባትን መፍጠር መሆኑን ያሳየናል።
ለሀገር መሞት ብቻ ሳይሆን፣ በሥራ እና በጥበብ ለሀገር መኖር ታላቅ ዐርበኝነት ለመሆኑ ዓሊ ቢራ ሕያው ምስክር ነው።
#ebc #ethiopia #alibirra #patriotism

6 months ago
🎷 በአንጋፋው አሊ ቢራ ስም የሙዚቃ ትምህርት ቤት ሊቋቋም ነው! 🎵
#ethiopia | "የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለ60 ዓመታት የጥበብ ንጉስ ታሪካዊ ክብር ሊሰጥ ነው"
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ፤ ከ260 በላይ የሙዚቃ ሥራዎችን ለኢትዮጵያ እና ለዓለም ያበረከተውን አንጋፋ ድምፃዊ፣ የዜማ ደራሲ እና አቀናባሪ ዶ/ር አሊ ቢራን ለመዘከር በስሙ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ለማቋቋም ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ።
የሙዚቃ ትምህርት ቤቱ ዓላማ፡-
1️⃣ የድሬዳዋን የኪነ-ጥበብ ጸጋ መጠቀም፣
2️⃣ የአሊ ቢራን ዘመን አይሽሬ ውርስ ለትውልድ ማሸጋገር፣
3️⃣ የተለያዩ የሙዚቃ ጥበቦችን እና የአካባቢውን ባህል መሰረት ያደረጉ ትምህርቶችን መስጠት ነው።
አሁን ላይ ዩኒቨርሲቲው አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እያከናወነ ሲሆን፤ የቦርዱ ውሳኔ በትምህርት ሚኒስቴር ሲጸድቅ ወደ ተግባር እንደሚገባ ተገልጿል።
ለአሊ ቢራ ይህ ይነስበታል እንጂ አይበዛበትም! 👏
አዲስ ዘመን (በነፃነት አለሙ)
#alibirra #diredawauniversity #musicschool #ethiopianmusic #legend #art #diredawa

Comments