Logo
Getu Temesgen
🎷 በአንጋፋው አሊ ቢራ ስም የሙዚቃ ትምህርት ቤት ሊቋቋም ነው! 🎵
#ethiopia | ​"የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለ60 ዓመታት የጥበብ ንጉስ ታሪካዊ ክብር ሊሰጥ ነው"

​የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ፤ ከ260 በላይ የሙዚቃ ሥራዎችን ለኢትዮጵያ እና ለዓለም ያበረከተውን አንጋፋ ድምፃዊ፣ የዜማ ደራሲ እና አቀናባሪ ዶ/ር አሊ ቢራን ለመዘከር በስሙ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ለማቋቋም ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ።

​የሙዚቃ ትምህርት ቤቱ ዓላማ፡-
1️⃣ የድሬዳዋን የኪነ-ጥበብ ጸጋ መጠቀም፣
2️⃣ የአሊ ቢራን ዘመን አይሽሬ ውርስ ለትውልድ ማሸጋገር፣
3️⃣ የተለያዩ የሙዚቃ ጥበቦችን እና የአካባቢውን ባህል መሰረት ያደረጉ ትምህርቶችን መስጠት ነው።

​አሁን ላይ ዩኒቨርሲቲው አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እያከናወነ ሲሆን፤ የቦርዱ ውሳኔ በትምህርት ሚኒስቴር ሲጸድቅ ወደ ተግባር እንደሚገባ ተገልጿል።

​ለአሊ ቢራ ይህ ይነስበታል እንጂ አይበዛበትም! 👏

​አዲስ ዘመን (በነፃነት አለሙ)

​#alibirra #diredawauniversity #musicschool #ethiopianmusic #legend #art #diredawa

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.