2 months ago
እነዚህን 69 ደረጃቸውን ያልጠበቁ የምግብ ምርቶች እንዳትጠቀሙ!
#ethiopia | የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ባደረገው የገበያ ቁጥጥርና ፍተሻ፣ ጥራትና ደህንነታቸው ያልተረጋገጡ እንዲሁም አስገዳጅ መስፈርቶችን ያላሟሉ 69 የምግብ ምርቶችን ለይቶ ይፋ አድርጓል።
በ570 የንግድ ተቋማት ላይ በተደረገ ፍተሻ 32 የገበታ ጨው፣ 19 የምግብ ዘይት፣ 6 የለውዝ ቅቤ፣ 6 የማር ዓይነቶች እንዲሁም ከረሜላና የሕፃናት ምግቦች ደረጃቸውን ያልጠበቁ ሆነው ተገኝተዋል።
ማንኛውንም ምርት ሲገዙ የገላጭ ጽሑፍ፣ የአምራች መረጃ፣ የመለያ ቁጥር (Batch Number) እና የጥራት ምልክት መኖሩን ማረጋገጥ ይገባል።
ባለስልጣኑ እንዳትጠቀሟቸው የከለከላቸው ዋና ዋና ምርቶች፦
የገበታ ጨው ዓይነቶች (ከፊሉ)፦
ሰይፋ፣ ቲና፣ እሙሹ፣ ቃሊ፣ አዮዲን፣ እኑ፣ አራዳ፣ ንጉስ፣ ሀሮት፣ ኩል፣ አሜን፣ ሰቦኑማ፣ እቱ፣ መክሊት፣ ዳግም፣ መርሰን፣ ኒሀል፣ ሊቅ፣ ስካይ፣ ናፊ፣ አቤ፣ ሳሮማ፣ ፀሐይ፣ ማሩ፣ እንቁ፣ ሰኒ፣ ሚያዋ፣ ስኬት፣ ሔራል፣ ቤዝ፣ ገዳ።
የምግብ ዘይት ዓይነቶች፦
ምስራቅ ፀሐይ፣ ቃል፣ አፍራን፣ ኒያ፣ ሪሃ፣ ኤአይ ሻኪር፣ ኤ1-ኑር፣ ጥራ፣ ረዲ፣ አያን፣ ሳፊያ፣ እሰይ፣ አማን፣ ላምሮት ኬኬ፣ እድገት፣ ራኒያ፣ ሸገር፣ ሀይላለ፣ ፍፁም የተጣራ።
ማርና የለውዝ ቅቤ፦
ሀራ፣ ሶራ፣ ብሉ፣ ስዊት ክሬም፣ ሉሲ፣ ስንቅ (ለውዝ ቅቤ)፤ ቤዛ ማር፣ ውብሸት የማር ጠጅ፣ ጂጂ ማር፣ አምባሰል ነጭ ማር፣ የኢሉባቦር ማር።
ከረሜላ፦
ቡርቃ ሎሊፖፕ፣ አዩ ፓፕ፣ አፍሪ፣ ዴሉክሴ።
#getu #efda #foodsafetyethiopia #publichealth #addisababa #ethiopia #consumerprotection #healthyeating #alert #ጥራትቁጥጥር #ጤና #ምግብናመድኃኒት #አዲስአበባ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

6 months ago
ዛሬ በተለያዩ አካባቢዎች የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል
#ethiopia | የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በዛሬው ዕለት ታህሳስ 21 ቀን 2018 ዓ.ም አስፈላጊ የጥገና እና የመልሶ ግንባታ ስራዎችን ለማከናወን በተወሰኑ የአዲስ አበባ አካባቢዎች ላይ የኃይል አቅርቦት እንደሚቋረጥ አስታውቋል።
🕒 የጊዜ ሰሌዳ እና የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች፦
1. ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 9፡30፦
ለገሐር፣ ቤተዛታ ሆስፒታል፣ ኦሮሚያ ባሕል ማዕከል ጀርባ፣ ጊዮን ሆቴል፣ እስጢፋኖስ ድልድይ አካባቢ፣ ኃይለ ዓለም ሕንጻ፣ ጎተራ የጋራ መኖሪያ ቤቶች፣ ወንጌላዊት፣ ዩኒማክ፣ መስቀል ፍላውር፣ ተሻላ ጋራዥ፣ ዳኞችና አቃቢ ሕግ ቢሮ፣ ኮስሞስ ሕንፃ፣ ድሪም ላይነር፣ የካ አባዶ እና የካሰዴ አካባቢ።
2. ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 7፡00፦
አምባሳደር አካባቢ፣ ሸራተን ሆቴል፣ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ታችኛው ቤተ-መንግስት፣ ባሻወልዴ የጋራ መኖሪያ ቤት እና በቱሪስት ጀርባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች።
3. ከጠዋቱ 3፡00 እስከ ቀኑ 9፡00፦
አትላስ ሆቴል፣ ሻላ መናፈሻ፣ ኤስኦኤስ (SOS)፣ ደሳለኝ ሆቴል ጀርባ፣ ፕሬዚደንሺያል ሆቴል እና ወደ ሩዋንዳ ኦቨርፓስ የሚወስደው መንገድ።
4. ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 10፡00 (ለመልሶ ግንባታ)፦
ኮካኮላ ፋብሪካ፣ ሰበታ ከተማ፣ አቀበና ውሃ ማምረቻ፣ ዲማ ሆስፒታል፣ ቦሌ ሁላሳ፣ ዓለም ገና፣ አርባ ምንጭ ጨርቃጨርቅ፣ ኖህ አደባባይ፣ ካፒታል ሲሚንቶ፣ ዋልያ ብረታ ብረት፣ ለጣፎ ከተማ፣ ለገዳዲ፣ 44 ማዞሪያ፣ አሸዋ ሜዳ፣ ዲያስፖራ፣ ፊሊደሮ፣ አንፎ ዓለም ባንክ፣ ሽሮ ሜዳ፣ እንጦጦ ማርያም፣ ስፔስ ሳይንስ፣ ሽንቁሩ ሚካኤል፣ 10 ኪሎ በከፊል፣ ዶሮ እርባታ እና አፍሪካ ልሕቀት ማዕከል አካባቢዎች።
📢 ማሳሰቢያ
የኤሌክትሪክ አገልግሎቱ የጥገና ስራው ተጠናቆ ኃይል እስኪመለስ ድረስ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠብቁ እየጠየቀ፤ ለሚፈጠረው መጉላላት አስቀድሞ ይቅርታ ጠይቋል።
ውድ ተከታታዮቻችን፦ ይህ መረጃ ለወዳጅ ዘመድዎ እንዲደርስ Share በማድረግ ይተባበሩ። መብራት ከመጥፋቱ በፊት አስፈላጊ የሆኑ የኃይል ዝግጅቶችን (እንደ ስልክ ቻርጅ ማድረግ) እንዳይዘነጉ!
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #addisababa #electricpower #maintenancenotice #poweroutage #eea #citynews #alert

9 months ago
የግብረ ሰናዩ ላየንስ ክለብ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ እና ሎሬት ዶ/ር ጥበበ የማነብርሃን
#ethiopia | COVID 19 - ኮሮና ከነጠቀን ባለአበርክቶዎች ኢትዮጵያውያን የጤና ዘርፉ ሻምፒዮኖች መካከል የላየንስ ክለብ አለም አቀፍ ማህበር ዐብይ ተልዕኮ ፈፃሚው ሎሬት ዶ/ር ጥበበ የማነብርሃን አይዘነጉም።
እኔ ሳውቃቸው ትኩረት በሚሹ የሃሩራማ በሽታዎች በተለይም የዓይን ማዝ (Trachoma) እና ጊኒ ዎርምን ጨምሮ በወባ መከላከል፥ቁጥጥር እና በሕክምና ከነበራቸው ጉልህ አስተዋጽኦ ጋር በተያያዘ ነው።
በተለይም በአማራ ክልል የትራኮማ (Trachoma) ስርጭት ከፍተኛ መሆኑን ተከትሎ ወባም (Malaria) እንዲሁ የሕብረተሰብ ጤና ስጋት ስለነበር ሁለቱን በሽታዎች ባቀናጀ በካርተር ሴንተር የሕብረተሰብ አቀፍ የጤና ቁጥጥር ፕሮጄክት (Mal-Tra)ጉልህ ድርሻ ነበራቸው።
በዚህ ረገድ ሎሬቱ ከቲ.ኤፍ. ግሎባል ሄልዝ (Taskforce for Global Health) የአፍሪካ ተጠሪ ከዶ/ር ተሾመ ገብሬ እና ከካርተር ሴንተር የኢትዮጵያ ተጠሪ ከዶ/ር ዘሪሁን ታደሰ ጋር በአጋርነት የከወኑትን አካትቼ በሰፊው እመለስበታለሁ።
ዛሬ ላይ ይህ የላየንስ ክለብ እንቅስቃሴ እንዴት ነው?
"እናገለግላለን" (We Serve) የሚል መሪ ቃልን አንግቦ ነው የተነሳው።
በሕብረተሰብ አገልግሎት ልቆ ለመገኘት ሰውን በጥልቅ የልብ ፍቅር መውደድ ይሻል።
በኢትዮጵያ ላየንስ ክለብ የግብረ ሰናይ ስራ ከጀመረ ከስድስት አስርት አመት በላይ ሆኖታል።
የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዚደንት ነፍስኄር ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ከላየንስ ክለብ ኢትዮጵያ አምስት የቻርተር አባላት አንዱ ነበሩ።
ለዓይነ ስውርነት የሚዳርጉ በሽታዎችን ለምሳሌ በዓይን ማዝ (Trachoma)፥ በዓይን ሞራ ግርዶሽ Cataract)፥ በውሃ ወለድ መዘዝ የዓይነ ስውርነት (River blindness) በሽታዎች ለሚሰቃዩ ቅድሚያ በመስጠት በሕክምና ጥበብ እይታቸው እንዲመለስና ወደ አዲስ የተሻለ ሕይወት እንዲሸጋገሩ ማድረግ የግብረሰናይ ተልዕኮው ቀዳሚ ትኩረት ሆኖ ነው የቆየው።
እነኚህን በሽታዎች በዘላቂነት ለመከላከል ከእህት የላየንስ ክለቦች፥ ከካርተር ሴንተር፥ ከኢንተርናሽናል ትራኮማ ኢኒሺዪቲቭ፥ ከክሪስቶፌል ብላየንድነስ ሚሽን እና ከሌሎችም አጋሮች ጋር በመሆን የ2ኛ ደረጃ የዓይን ሕክምና አገልግሎትን በማስፋፋት የጤና ዘርፉን ሲደግፍ ቆይቷል።
በቀዶ ሕክምና ዜጎች በተለይ አቅመ ደካሞች የዓይን ብርሃንቸው ተነጥቀው እንዳይቀሩ ብሎም 2ኛ ደረጃ የዓይን ማዕከላት በባህርዳር፥ ደብረ ብርሃን፥ አርባምንጭና ጅግጅጋ መቋቋማቸውን የድርጅቱ ሰነድ ያመለክታል።
የመንግስት ሆስፒታሎችን አቅም በማሳደግ ረገድ ራስ ደስታ፥ ልዕልት ዘነበወርቅ ሆስፒታል፥ ራስ ደስታና ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታሎች ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው።
60 አመታትን ያስቆጠረው ላየንስ ክለብ በተጨማሪም በአዲስ አበባ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ግቢ የስኳር ሕሙማን ማዕከል እንዲቋቋምም አድርጓል።
ላየንስ ክለብ በኢትዮጵያ ሕብረተሰባዊ ምግባረ ሰናይ ተግባሩ እንዲጠናከር አባላት በማፍራት ያለበትን ውሱንነት በመቅረፍ የአባላት ማቀፍ እድሎችን ማስፋፋት እንደሚያሻ የክለቡ የኢትዮጵያ አመራሮች በአፅንኦት የሚያነሱት ነው።
ሎሬት ዶ/ር ጥበበ የማነ ብርሃን ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው የቆዳ ሕክምና ስፔሻሊስቶች (Dermatologists) መካከል ተጠቃሽ ናቸው።
የቆዳ፣ የስጋ ደዌ፣ የአባላዘር፣ የትራኮማ እና ሌሎች ችግሮች የት የሃሩራማ በሽታዎች ቁጥጥር ላይ በተለይም በአለም አቀፍ ዲፕሎማሲ የሕብረተሰብ ጤና ትኩረት እንዲያገኝ ወሳኝ አካላትን በማግባባት (በ-advocacy) ሚናቸው ታላቅ እንደነበር ለዘርፉ ባለኝ ቅርበት ምስክር ነኝ።
ከሐኪምነታቸው በተጨማሪ የሀገር ሽማግሌ፣ እርዳታ አስተባባሪ፣ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን አባል፣ የእርቀ ሰላም ኮሚሽን አባል እና በብዙ የበጎ ፈቃደኝነት ስራ ሀገራቸውን አገልግለዋል።
ጥቅምት 22 ቀን በ1941 ዓ.ም በሐረርጌ ጠቅላይ ግዛት፣ ሐረር ከተማ የተወለዱት ዶ/ር ጥበበ ትምህርት የተከታተሉት በአዲስ አበባ ሽመልስ ሀብቴ ት/ቤት ነው።
አባታቸው ሻለቃ የማነብርሃን ወ/ሥላሴ በጦር ሰራዊቱ መኮንን ስለነበሩና የሚታየው ዲሲፕሊንና አለባበስ ከስካውት (Scout) ዲስፕሊንና አለባበስ ጋር የሚቀራረብ ስለነበር ጥበበ በዚያ ተማርከው የስካውት ክበብ አባል ሆነዋል።
ጥበበ 8ኛ ክፍልን ሳሉ የተቸገሩ ልጆችን በት/ቤቱ አካባቢ አይተው ከጓደኞቻቸው ጋር ተማከሩና ከድርሻ የኪስ ገንዘባቸው ቀንሰው በማጠራቀም ሞከሩና፤ ኋላም ‹‹የ10 ወንድማማቾች ማኅበር›› የተባለ ማኅበር መሰረቱ።
የጦር ሰራዊት እና የክብር ዘበኛ የሙዚቃ ቡድኖችን ጋብዘው ስራዎቻቸውን ለተማሪዎች እንዲያሳዩ በማድረግ ከዚያ የሚገኘውን ገንዘብ ለችግረኛ ተማሪዎቹ እንዲሰጥ መላ ዘየዱ።
ከዝግጅቶቹ ያገኙት ገንዘብ የተማሪዎቹን የምግብና የደንብ ልብስ ወጪ ለመሸፈን አስቻላቸው።
ይህ የበጎ ፈቃደኝነት ጥረት ተጠናክሮ ከተደገፉት ተማሪዎች ውስጥ እስከ ዩኒቨርሲቲ ተምረውና ትልቅ ደረጃ ደርሰው በምዕራባውያኑ ባህር ማዶ ሀገራት የሚኖሩም አሉ።
ጥበበ በልጅነታቸው ዲፕሎማት የመሆን ምኞት የነበራቸው ቢሆንም እናታቸው ታመው ሆስፒታል የገቡበት አጋጣሚ ግን የጥበበን ፍላጎትና የሕይወት መንገድ ቀየረው።
እናታቸው ታመው አሁን ጦ/ኃይሎች ሆስፒታል ከሚባለው የልዕልት ፀሐይ መታሰቢያ ሆስፒታል ገቡ።
የእናታቸውን ቀዶ ሕክምና በስኬት ያከናወኑትን ኢትዮጵያውያን ዶክተሮችን (ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን፣ ፕሮፌሰር ታዬ መኩሪያንና ሌሎች ሐኪሞችን) ሲመለከቱ ሐኪም የመሆን ምኞት አሸነፋቸውና ሃሳብ ቀየሩ።
ከዚያም የሩስያ ወዳጅነት ማኅበር የትምህርት እድል ሲሰጥ ጥበበ እድሉን አግኝተው ወደ ሩሲያ ሄደው ለ6 አመታትየሩስያ ቋንቋና የሕክምና ትምህርትን ተምረው በማዕረግ አጠናቀዋል።
በቆዳ ሕክምና የ2ኛ እና የ3ኛ ዲግሪያቸውንም አገኙ፤ የአለም አቀፍ የፖለቲካ ሳይንስ ትምህርትን ማከላቸው ለኋላው ዲፕሎማሲን ለሚሻው የጤና ልማት የማግባባት አድቮኬሲ ስራ ብዙ እንዳገዛቸው መገመት ይቻላል።
ዶ/ር ጥበበ ከ1972 እስከ 1985 ዓ.ም ድረስ በሉቮቭ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ በአማካሪ ስፔሻሊስትነትና ተባባሪ ፕሮፌሰርነትም አገልግለዋል።
ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው የመላው አፍሪካ የሥጋ ደዌ ማገገሚያና ስልጠና ማዕከል (All Africa Leprosy Rehabilitation & Training Center - ALeRT) ዋና የቆዳ ሐኪምና የክፍሉም ኃላፊ ሆነው ሰርተዋል።
የዶ/ር ጥበበ ከተሳተፉባቸው ዋነኛ ጉዳዮች አንዱ የላየንስ ክለብ ኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን (Lions Clubs International) ነው።
በዚህ ክለብ ተሳትፏቸው በተለይ አፍለኛ የዓይን ማዝ ቁጥጥር (control of active trachoma) እና የዓይን ሞራ ግርዶሽ (cataracts) ሕክምና እንዲሁም የዓይን ቆብ ቀዶ ሕክምና (trachomatus trichiasis) ላይ ሳይጠቀሱ አይታለፍም።
ትኩረት ከሚሹ የሃሩራማ በሽታዎች አንዱ የጊኒ ወርም በሽታ ሲሆን ከጊኒ በመወገዱ የኢትዮጵያ ዎርም ተብሎ ስም ለውጥ እንዳይደረግ ያሰጋል።
እናም ይህን በሽታ ለማጥፋት በተያዘ ፕሮግራም የበጎ ፈቃድ አምባሳደርም ሆነው አገልግለዋል።
ሎሬት ዶክተር ጥበበ የሎሬትነት ማዕረግን ያገኙት ከሰሜን አሜሪካ ነው።
የዓለም ሎሬቱ ዶ/ር ጥበበ በርካታ ሽልማቶችን አግኝተዋል። እንደውም በአንድ የሽልማት ሁነት ላይ እንዲህ እል:-
"… ማንም ሰው የትም አገር ሄዶ ሽልማት ሊሸለም ይችላል፤ በአገሩ የተሸለመው ሽልማት ግን ታላቁ ነው ብዬ አምናለሁ። ለእኔ ትልቁ ሽልማቴ በ2002 ዓ.ም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሰጠኝ የክብር ዶክትሬት ነው"።
በዓለም የጤና ድርጅት፣ በዓለም ባንክ፣ በብሪታኒያና አሜሪካ የቆዳ ሕክምና ማህበርና አካዳሚ፣በዓለም አቀፍ የቆዳ ሕክምና ማኅበር፣ በአፍሪካ የኤድስ (AIDS) መከላከል መርሃ ግብር፣ በዊልያም ዱ ቦይስ የአፍሮ-አሜሪካ የምርምር ተቋም እንዲሁም በሌሎች ተቋማትም አገልግለዋል።
ከሩሲያው ፕሬዝደንት ቩላድሚር ፑቲን ዘንድ ለሩሲያም ሆነ ለቀሪው ዓለም መልካም ተግባር ላከናወኑ ሰዎች የሚሰጠውን ከፍተኛ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
ከ39ኛው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጂሚ ካርተር ጋር በ-Carter Center እና ሎሬቱ ከፍተኛ አመራር በነበሩበት የላየንስ ክለብ ኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን ጥምረት አማካይነት ሰፊ የጤና ልማት ስራ ስለመከናወኑ በብዙ የመስክ ስራዎች ራሴም ተገኝቼ መሬት የነካ ሃቅ መሆኑን ታዝቤያለሁ።
‹‹ገና ላሳካው ፈልጌ ያልፈጸምኩት ብዙ ቀሪ ክንውኖች አሉኝ›› ሲሉ የነበሩት ሎሬት ዶ/ር ጥበበ ዓለምን ባርበደበደው ኮሮና በሽታ የካቲት 13 ቀን 2013 ዓ.ም በ72 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።
በቺካጎ ከተማ የዛሬ110 አመት ገደማ ላየንስ ክለብ የተመሰረተው ሲሆን 1.4 ሚሊዮን አባላትን በማቀፍ በ183 ሀገራት ውስጥ ከ43,300 ክለቦች በላይ በ714 የአገልግሎት ማስተባበሪያ አውራጃዎች ተቀናጅቶ እየተመራ ነው።
ክለቦቹ ከመደበኛ ማህበራዊ ስብስብነት በላይ አባላቱ ተልኳቸው ጊዜያቸውን፥ እውቀታቸውንና ሃብታቸውን አቀናጅተው ለበጎ ምግባር በማዋል እርዳታናድጋፍ የሚሹትን የሕብረተሰብ ክፍሎች መታደግ ነው።
........
(Composed by:- Eshetu Geletu - Public health advocate & Champion of NTDs Control)

🌍 ለሚያቀርቡት ምርትና አገልግሎት ከEthio Tenders Alert /ETA/ ጋር በመሆን የገቢያ አድማሶን ያስፉ!
የጨረታ እና ፐርፎርማ ማስታወቂያዊችን ማፈላለግ አድካሚ ሆኖቦታል? የጨረታ እድሎችስ ያመለጦ ተቸግረዋል? እንግዲያውስ Ethio Tenders Alert ጉዳዩን ቀላል አድርጎታል።
✨ ቻናላችን ምን ተመራጭ ያደርገዋል?
• 📲 የጨረታ እና ፐርፎርማ ማስታወቂያዎች በታወጁበት ቅጽበት በእጅ ስልኮ በቴሌግራም ያገኛሉ።
• 🔍 የጨረታው ግዥ መለያ ቁጥር “Reference No” በመጫን ብቻ ዝርዝር መረጃው ወደሚያገኙበት ፖርታል ይገባሉ ይህም ፍለጋዎን እጅግ ቀላል ያደርገዋል።
• ⏰ እያንዳንዱ ጨረታ ከፍት ሆኖ የሚቆይበት ጊዜ በደቂቃዎች ያሳውቆታል።
• 📑 በፌደራል እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ተቋማት ደረጃ የሚታወጁ የፐርፎርማና ጨረታ መረጃ ሁሉንም በአንድ ስፍራ ያገኛሉ።
ተቋራጭ፥ ምርትና አገልግሎት አቅራቢ፥ አማካሪ አሊያም ስራ ፈጣሪ ከሆኑ ይህ ቻናል ከተወዳዳሪዎ በመረጃ ቀድመው ሽያጮ እንዲያሳድጉ ወሳኝ ሚና ይጫወታል።
⚡️ በመረጃ ይቅደሙ፤ ተወዳዳሪነቶን ያሳድጉ፤ ተጨማሪ የሽያጭ በሮችን ይክፈ።
📲 አሁኑኑ ቻናላችንን ይቀላቀሉ
👉 t.me/Ethiopia_Government_Tenders

11 months ago
EXCLUSIVE GOLD GIVEAWAY ALERT!
1 KG of Pure Gold – Ready in Our Office NOW!
Look Senior Realtor Dagi holding the actual gold that YOU could take home!
This summer, Brook Real Estate is doing what no other company has ever done!!
We're giving away 1 KILOGRAM of REAL 24K GOLD to our customers, physically available now in our office!
When you buy property with us, you’ll get your share of this gold — As a bracelet, necklace, ring, or any form of your choice!
📌 No Draw. No Waiting.
📌 The More You Buy, The More You Receive.
This is not a promise — it’s in our office and ready for you.
Be part of the first real estate gold campaign in Dubai history.
📞 Contact us now and turn your property into GOLD!
#brookrealestate #goldgiveaway #1kggold #goldensummer #realestaterewards #dubailuxuryliving #investsmart #exclusiveoffer #noothercompanydoesthis #jewelryrewards #propertywithperks #brookexperience #dubairealestatedeals #necklacebraceletgold #realestatepromotion #ownitandshine
11 months ago
ለዩኒቨርሲቲ መምህሩ አስናቀ ብርሃኑ እንድረስለት
Lets support Our Teacher
Yilkal Andualem is organizing this fundraiser.
Donation protected
መምህራችን_ታሞብናል
ወደ ካንሰር ሊቀየር ይችላል....ሀኪሞች
ወጣት መ/ር አስናቀ ብርሃኑ አላምነህ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በቅንነትና በታማኝነት እያገለገለ ያለ በሙያውም አንቱታን ያተረፈ በሥነ ምግባሩ ምስጉን ሰው አክባሪ፣ ለተቸገሩ ፈጥኖ ደራሽ ወንድማችን ነው::
በሒሳብ ትምህርት ክፍል የኑሜሪካል አናላይሲስ መምህር ሲሆን በዩኒቨርሲቲ ቆይታውም ከማስተማር ስራው ጎን ለጎን በጥናትና ምርምር ዘርፍ በሙያው አለም አቀፍ ተቀባይነት ያላቸው 6 (ስድስት) ጥናትና ምርምሮችን በማሳተም ለአንባቢያን አድርሷል::
ወንድማችን መ/ር አስናቀ ድንገት በገጠመው የጤና እክል በህይወት እና በሞት መካከል ሆኖ የድረሱልኝ ተማፅኖውን እያሰማ ይገኛል:: በገጠመው የጤና ዕክል በተለያዩ ስድስት (6) ሆስፒታሎች ህክምና ሲያደርግ ቆይቷል::
ከነዚህም ውስጥ በአንዱ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ሰርጀሪ ተሰርቶ ሊሻለው ባለመቻሉ ወደ አዲስ አበባ አለርት ኮምፕርሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሪፈር ተፅፎለት ክትትል እያደረገ ይገኛል::
በመሆኑም የአለርት ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህክምና ቦርድ 30% አጠቃላይ ቋሚ የአካል ጉዳተኛ እንደሆነና የሚከተሉትን ውሳኔዎችን ወስኗል::
1ኛ. በግራ እግሩ ላይ ስድስት (6) ዓመት የቆየ ከባድ ቁስለት ወደ ካንሰር የመቀየር እድሉ እጅግ በጣም ከፍተኛ መሆኑን፣
2ኛ. ሁለቱም እግሮቹ ነርቫቸው የተጎዳና ስሜት አልባ መሆናቸውን፣
3ኛ. የግራ እግሩ ሙሉ አጥንቶቹ የተጎዱና ይዘታቸውን የቀየሩ መሆናቸውን
4ኛ. ቁሞ ማስተማርም ሆነ በእግሩ መንቀሳቀስ እንደማይችል የአለርት ሆስፒታል ሜዲካል ቦርዱ አረጋግጧል
መምህር አስናቀ ባለብዙ ተስፋና ብዙ ህልም የነበረዉ ሩጦ ያልጠገበ ወንድማችን እግሮቹ ደክመው እቤት እንዲውል ተገዷል::
የህመሙ ሁኔታ አሳሳቢ እና ለህይወቱም አስጊ ደረጃ ላይ በመድረሱ ወደ ህንድ አገር ሂዶ ህክምና እንዲያደርግ ሪፈር ተፅፎለታል:: የህክምና ወጭውም ከሁለት ሚሊየን (2,000,000) ብር በላይ እንደሚያስፈልገው ተነግሮታል::
ወንድማችንን ለማገዝ አነሰ በዛ ሳንል በአገር ውስጥና በውጭ ያላችሁ ትዉልደ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን የእርዳታ እጃችሁን ትዘርጉ ዘንድ በፈጣሪ ስም እንጠይቃለን::
Asinake Birihanu Alamneh
ስልክ_ቁጥር 09 23 53 45 01
Lecturer Asnake Berhanu, who has been serving Hawassa University with integrity and honesty, is a respected, respectful, and helpful person who has earned a reputation in his profession.
He is a Numerical Analysis Lecturer in the Department of Mathematics.
During his time at the university, he has published 6 (six) internationally recognized studies and research papers in his field, and has reached readers.
Our brother,Teacher Asnake is suddenly in the middle of life and death due to a health problem he encountered.
He has been receiving treatment in six (6) different hospitals for his health problem. In one of them, he underwent surgery at Hawassa University Referral Hospital and was referred to Addis Ababa Alert Compressive Specialized Hospital for follow-up.
Therefore, the Alert Specialized Hospital Medical Board has determined that he is 30% permanently disabled and has made the following decisions:
1st. The six (6) year old severe ulcer on his left leg has a very high chance of turning into cancer,
2nd. Both his legs are nerve damaged and numb,
3rd. The entire bones of his left leg are damaged and their contents have changed,
4th. The Alert Hospital Medical Board has confirmed that he cannot stand or walk.
Our brother, Teacher Asnake, who had many hopes and dreams, has been forced to stay home due to tired legs. His condition is serious and life-threatening, so he has been referred to India for treatment. He has been told that the medical expenses will cost more than $15000 .
Please help support this visionary teacher as they navigate through an incredibly difficult time. The funds raised will go towards the cost of surgical treatment , and to help to cover the loss of income while taking some much needed time to recover.
Thank you for your generosity.
I am grateful for your help and wishes.
Thank you
"Let's save the life of the visionary teacher with sincere hearts and united hands!
Show your support for this GoFundMe

Sponsored by
Surafel
Comments