2 months ago
ወፍ ዝር የማይልበት የሰሜን ኮርያ ባለ 105 ፎቁ ግዝፍ ሆቴል
#ethiopia | በሰሜን ኮሪያ ፒዮንግያንግ ከ330 ሜትር በላይ ተንደራርቦ የሚገኘውና በ1987 ግንባታው የተጀመረው ባለ 105 ፎቁ የሪዩግዮንግ ሆቴል ከአራት አስርት ዓመታት ገደማ በኋላም አንድም ተስተናጋጅ እንግዳ ሳያገኝ እስካሁን ደረቱን ገልብጦ ይታያል።
ሀገሪቱ የዘመናዊነቷና የታላቅነቷ መገለጫ እንዲሆን አቅዳ የገነባችው ይህ በፒራሚድ ቅርጽ የተሰራ ግዙፍ ሕንፃ በ1990ዎቹ መጀመሪያ በገጠመ ከባድ የኢኮኖሚ ውድቀት ምክንያት ግንባታው ተቋርጦ ለዓመታት በባዶ ኮንክሪትነቱ ቆሞ ነበር።
በሂደት የውጭ መስታወቱ ተገጥሞለት ከፊሉን ክፍሎች ለመክፈት ተደጋጋሚ ዕቅዶች ቢወጡም ሳይሳኩ ቀርተዋል።
የውስጥ አካሉ ሙሉ በሙሉ ባለመጠናቀቁ ምክንያት አሁንም ቢሆን እንደ ሆቴል አገልግሎት መስጠት ያልቻለው ይህ ሕንፃ በአሁኑ ወቅት የውጭ አካሉ መንግሥታዊ መልእክቶችና አኒሜሽኖች የሚያልፉበት ግዙፍ የኤልኢዲ ስክሪን ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

የሙቀት ማዕበል በሰሜን ኮሪያ፡ መንግሥት ዜጎች የውሻ ሥጋ ሾርባ እንዲመገቡ መከረ
በሰሜን ኮሪያ ታሪካዊ የሙቀት ማዕበል በመከሰቱ መንግሥት ዜጎች አካላቸውን ለማቀዝቀዝ የውሻ ሥጋ ሾርባ እንዲመገቡ መከረ።
በሀገሪቱ የሙቀት መጠን ከዚህ ቀደም ተመዝግቦ የማያውቅ 36.7 ዲግሪ ሴልሺየስ የደረሰ ሲሆን፣ ይህም በሀገሪቱ የአየር ሁኔታ ታሪክ ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል። 'ሳምቦክ' በተሰኘው በዚህ የከፋ የሙቀት ወቅት የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን እንደ የውሻ ሥጋ ሾርባ፣ የዓሣ ገንፎ፣ ሀብሐብ እና ዱባ ያሉ ምግቦች የሰውነትን ጥንካሬ ለመጠበቅና ሙቀቱን ለመቋቋም ይረዳሉ ብለዋል።
የኮሪያ ማዕከላዊ ዜና ኤጀንሲ (KCNA) እንደገለጸው፣ በዋና ከተማዋ ፒዮንግያንግ የሚገኙ ምግብ ቤቶች እነዚህን ባህላዊ ምግቦች ለሚፈልጉ ደንበኞች አስተናጋጅነት እየሰጡ ይገኛሉ።
ጎረቤት ደቡብ ኮሪያ ከሙቀት ማዕበሉ ጋር በተያያዘ ከ20 በላይ ሰዎች ሕይወት ማለፉን ብታረጋግጥም፣ ሰሜን ኮሪያ እስካሁን የሞት መረጃ አላወጣችም።
Seledadotio

ሰሜን ኮሪያ ወደ ጃፓን ባሕር ባሊስቲክ ሚሳይል አስወነጨፈ
#ethiopia | ሰሜን ኮሪያ ዛሬ ከምሥራቅ ጠረፏ ከዎንሳን (Wonsan) አካባቢ ወደ ጃፓን ባሕር (በደቡብ ኮሪያ “ምሥራቅ ባሕር” ተብሎ የሚጠራው) አጭር ርቀት የሚጓዝ ተጠርጣሪ ባሊስቲክ ሚሳይል ማስወንጨፏን የደቡብ ኮሪያ ጦር እና የጃፓን ባሕር ዳርቻ ጥበቃ አስታውቀዋል።
በጃፓን ባለሥልጣናት መረጃ መሠረት ሚሳይሉ በጃፓን ግዛት ወይም በኢኮኖሚያዊ የባሕር ቀጠናዋ (EEZ) ውስጥ አላረፈም፤ እስካሁንም የደረሰ ጉዳት ወይም ሰው ጉዳት አልተዘገበም።
የደቡብ ኮሪያ፣ የአሜሪካ እና የጃፓን ወታደራዊ ኃይሎች የሚሳይሉን አይነትና የበረራ መረጃ በጋራ እየመረመሩ ነው።
ይህ የሚሳይል ሙከራ በአሜሪካና በደቡብ ኮሪያ የጋራ ወታደራዊ ልምምዶች ሊጀመሩ ጥቂት ቀናት ሲቀሩ የተፈጸመ ሲሆን፣ ፒዮንግያንግ እነዚህን ልምምዶች ለወረራ ዝግጅት አድርጋ እንደምትመለከታቸው ትገልጻለች።
ከቀናት በፊትም ሰሜን ኮሪያ በጃፓን የመከላከያ አቅም መስፋፋት ምክንያት “ተጨማሪ ወታደራዊ እርምጃዎች” ልትወስድ እንደምትችል አስጠንቅቃ ነበር።
የደቡብ ኮሪያ እና የጃፓን መንግሥታት የሚሳይሉን ሙከራ በማውገዝ የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ምክር ቤት ውሳኔዎችን የሚጥስ ነው ብለዋል፤ በቀጣይ ተጨማሪ የሚሳይል ሙከራዎች ሊኖሩ እንደሚችሉም በከፍተኛ ንቃት እየተከታተሉ መሆኑን ገልጸዋል።

4 months ago
ሺ ጂንፒንግ ሰሜን ኮሪያ ገቡ
#ethiopia | የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሰሜን ኮሪያ የገቡ ሲሆን፥ በፒዮንግያንግ አየር ማረፊያ ሲደርሱም በሀገሪቱ መሪ ኪም ጆንግ ኡን ከፍተኛና ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ይህ በሁለቱ መሪዎች መካከል የሚካሄደው ታሪካዊ ምክክር በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ትኩረትን የሳበ ሲሆን፥ በቆይታቸውም ቀጣናዊ ደህንነትንና የሁለትዮሽ ስትራቴጂካዊ ግንኙነትን ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው አበይት ጉዳዮች ላይ በስፋት ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#china #northkorea #xijinping #kimjongun #geopolitics #asiapacific #breakingnews

5 months ago
የፕሬዚዳንት ኪም ትዕዛዝ
#ethiopia | ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡን በደቡባዊ የአገራቸው ድንበር መከላከያው እንዲጠናከር ትዕዛዝ ሰጡ።
ከሰሜን ኮሪያ የተለያዩ ዕዞች ከተውጣጡ ወታደራዊ ሀላፊዎች ጋር ስለዝግጁነት መክረዋል ኪም ጆንግ ኡን።
ከዕዝና ብርጌድ አዛዦች ጋር የተወያዩት ኪም በደቡባዊ የሰሜን ኮሪያ ክፍል ያለው ድንበር ላይ ዝግጅት እንዲደረግ ማሳሰባቸው ለደቡብ ኮሪያ ፖለቲከኞች አዲስ ወታደራዊ ስጋት ጋርጦባቸዋል ።
ሊቀሰቀስ የሚችልን ማንኛውንም ጦርነት ለመቀልበስ የጦሩን ትጥቅ ማዘመን፣ቁልፍ ዕዞችን ማጠናከር እና መሰል ዝግጅቶች እንዲደረጉም ጥሪ ቀርቧል።
በደቡብ ኮሪያ እና አሜሪካ መካከል ያለው ወታደራዊ ትስስር ስጋት የሆነባቸው ኪሞቹ በተለያየ ጊዜ የሚፈፀምብንን ወታደራዊ ትንኮሳ መመከት አለብን የሚል ዕምነት አላቸውም ተብሏል።
በፒዮንግያንግ እና ሴዑል መካከል ያለው ወታደራዊ ውጥረት መልኩን እየለወጠ መምጣቱን የሚጠቁም ትዕዛዝ ሆኖም ተመዝግቧል።
ኪም ጆንግ ኡን አዳዲስ የጦር መሳሪያ ስርዓቶች ወደ ውጊያ አውድ እንዲገቡ ተደጋጋሚ ማሳሰቢያ መስጠታቸውም አይዘነጋም።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu #nbcethiopia #skorea #leader #sk

ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡን በደቡባዊ የአገራቸው ድንበር መከላከያው እንዲጠናከር ትዕዛዝ ሰጡ።
ከሰሜን ኮሪያ የተለያዩ ዕዞች ከተውጣጡ ወታደራዊ ሀላፊዎች ጋር ስለዝግጁነት መክረዋል ኪም ጆንግ ኡን።
ከዕዝና ብርጌድ አዛዦች ጋር የተወያዩት ኪም በደቡባዊ የሰሜን ኮሪያ ክፍል ያለው ድንበር ላይ ዝግጅት እንዲደረግ ማሳሰባቸው ለደቡብ ኮሪያ ፖለቲከኞች አዲስ ወታደራዊ ስጋት ጋርጦባቸዋል ።
ሊቀሰቀስ የሚችልን ማንኛውንም ጦርነት ለመቀልበስ የጦሩን ትጥቅ ማዘመን፣ቁልፍ ዕዞችን ማጠናከር እና መሰል ዝግጅቶች እንዲደረጉም ጥሪ ቀርቧል።
በደቡብ ኮሪያ እና አሜሪካ መካከል ያለው ወታደራዊ ትስስር ስጋት የሆነባቸው ኪሞቹ በተለያየ ጊዜ የሚፈፀምብንን ወታደራዊ ትንኮሳ መመከት አለብን የሚል ዕምነት አላቸውም ተብሏል።
በፒዮንግያንግ እና ሴዑል መካከል ያለው ወታደራዊ ውጥረት መልኩን እየለወጠ መምጣቱን የሚጠቁም ትዕዛዝ ሆኖም ተመዝግቧል።
ኪም ጆንግ ኡን አዳዲስ የጦር መሳሪያ ስርዓቶች ወደ ውጊያ አውድ እንዲገቡ ተደጋጋሚ ማሳሰቢያ መስጠታቸውም አይዘነጋም።
seledadotio

Sponsored by
Surafel
5 months ago
"ኪም ጆንግ ኡን ከተገደሉ ሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር ጥቃት ትሰነዝራለች:-አዲሱ ድንጋጌ‼️
የሰሜን ኮሪያ መንግስት በሕገ መንግስቱ ላይ ባደረገው አዲስ ማሻሻያ፣ መሪው ኪም ጆንግ ኡን በጠላት ሃይሎች ከተገደሉ ወይም የግድያ ሙከራ ከተፈጸመባቸው ወታደራዊ ሃይሉ አውቶማቲክ የሆነ የኒውክሌር አጸፋዊ ጥቃት እንዲሰነዝር አዝዟል።
ይህ ውሳኔ የተላለፈው የአይሑድ እና የአሜሪካ ጥምረት በቴሕራን ላይ በሰነዘሩት ጥቃት የኢራኑ የበላይ መሪ አሊ ካሜኒ እና የቅርብ አማካሪዎቻቸው መገደላቸውን ተከትሎ መሆኑ ተገልጿል።
ኪም ጆንግ ኡንም ተመሳሳይ “የአመራር ማጥፋት” (Decapitation Strike) ጥቃት ሊሰነዘርብኝ ይችላል በሚል ከፍተኛ ስጋት ውስጥ መውደቃቸው ተነግሯል።
በፒዮንግያንግ በተካሄደው 15ኛው የሰሜን ኮሪያ የሕዝብ ምክር ቤት ጉባኤ ላይ በጸደቀው የኒውክሌር ፖሊሲ ሕግ አንቀጽ 3 ላይ እንደሰፈረው፣ የአገሪቱ የኒውክሌር ሃይል ዕዝ እና ቁጥጥር ስርዓት በጠላት ሃይሎች ጥቃት አደጋ ላይ ከወደቀ፣ የኒውክሌር ጥቃት “በአውቶማቲክ መንገድ እና ወዲያውኑ” ይፈጸማል።
ይህ ማለት መሪው ኪም ጆንግ ኡን ትዕዛዝ መስጠት በማይችሉበት ሁኔታ ላይ ቢሆኑ ወይም ቢገደሉ፣ ወታደራዊ መኮንኖቹ ያለምንም ተጨማሪ ትዕዛዝ አጸፋውን እንዲመልሱ ስልጣን ተሰጥቷቸዋል።

ሰሜን ኮርያ የጎረቤቷን የደቡብ ኮርያን ድራማዎችን የተመለከቱ ሰዎችን በሞት መቅጣት መቀጠሏ ተሰማ
በሰሜን ኮሪያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በተከሰተበት ወቅት የሞት ቅጣት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል ሲል ሴኡል ላይ የተመሰረተዉ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ገልጿል።ከጃንዋሪ 2020 እስከ 2024 መጨረሻ ድረስ ቢያንስ 153 ሰዎች ተገድለዋል ወይም ሞት ተፈርዶባቸዋል፡፡ወረርሽኙ ከመከሰቱ በፊት በነበሩት አምስት ዓመታት ውስጥ 44 ሰዎች ተቀጥተዉ እንደነበረ የሽግግር ፍትህ የስራ ቡድን አስታዉቋል።
በጣም ከተለመዱት ጥፋቶች መካከል አንዳንዶቹ ከሃይማኖት፣ ከአጉል እምነት እና ከውጪ የባህል ይዘት ጋር የተያያዙ ሲሆን የደቡብ ኮርያ ድራማዎን መመልከት ለቅጣቱ ምክንያት ሆኗል፡፡ እ.ኤ.አ. በ 2015 እስከ በ 2019 መካከል ባሉት ዓመታት የሞት ቅጣት ቁጥሩ ቀንሶ ነበር፡፡ ለመቀነሱም ዋና ምክንያቱ ዓለም አቀፍ ጫናዎች የመንግስታቱ ድርጅት ጥያቄን ተከትሎ ነዉ። ነገር ግን ፒዮንግያንግ ድንበሯን ከዘጋች በኋላ በ2020 ግድያ ጨምሯል ሲል የሽግግር ፍትህ የስራ ቡድን አስታዉቋል።
መንግሥታዊ ያልሆነው ድርጅት በሰሜን ኮሪያ በኪም የግዛት ዘመን መጀመሪያ ላይ የሞት ፍርድ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱንና በ2013 ከ80 በላይ ሰዎች ተገድለዋል ሲል አስታዉሷል።ፒዮንግያንግ ስልታዊ በሆነ መንገድ የሰብአዊ መብት ረገጣ እየፈፀመች መሆኑን ያረጋገጠውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባደረገው ጥናት መሰረት ቁጥሩ እየቀነሰ የመጣ ይመስላል።በ2020 ግን ቢያንስ 54 ሰዎች ተገድለዋል ፣በ2021 ደግሞ 45 ሰዎች ሲገደሉ በአንድ ዓመት ከፍተኛ አመዘጋገብ የተፈጸመበት ነዉ፡፡

6 months ago
የሞስኮ እና ፒዮንግያንግ ድርና ማግ ሆነናል አሉ
#ethiopia | የሩሲያው መከላከያ ሚኒስትር አንድሬ ቤሎሶቭ ከሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ የሁለቱ ሀገራት ወታደራዊ ትብብር ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን አስታውቀዋል።
ይህ ጉብኝት በቃላት ደረጃ ከሚገለጽ ዲፕሎማሲ ባለፈ፣ በተግባር የሚታይ ስልታዊ ዝግጅት የታየበት ነው።
ሁለቱ ሀገራት ከ2027 እስከ 2031 የሚዘልቅ የጋራ ወታደራዊ ግንኙነት ፍኖተ ካርታ ላይ ተስማምተዋል። ይህም ትብብራቸው ለረጅም ጊዜ የሚቆይ መሆኑን ያሳያል።
በሰኔ 2024 የተፈረመው ስምምነት አንዱ ሀገር ጥቃት ቢሰነዘርበት ሌላኛው ወታደራዊ ድጋፍ እንዲያደርግ ያስገድዳል። ይህም ሰሜን ኮሪያን የሩሲያ ቀጥተኛ የጦር አጋር አድርጓታል።
ቤሎሶቭ ሰሜን ኮሪያ በዩክሬን ጦርነት ወቅት ለሩሲያ ላሳየችው "ወንድማዊ ድጋፍ" እና በኩርስክ ክልል ለተሳተፉት የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና ሰጥተዋል።
ይህ ጥምረት በ"እጅ በእጅ" ግብይት ላይ የተመሰረተ ይመስላል። ምዕራባውያን እንደሚሉት ከሆነ፦
ወደ 14,000 የሚጠጉ ወታደሮችን እና የጦር መሣሪያዎችን ለሩሲያ ግንባር አሰልፋለች።
ሩሲያ ምን ትሰጣለች? በምላሹ ዘመናዊ የወታደራዊ ቴክኖሎጂ ድጋፍ፣ የምግብ ዋስትና እና የኃይል (ኢነርጂ) አቅርቦትን ለሰሜን ኮሪያ ታረጋግጣለች።
ይህ ጥምረት በምዕራባውያን ዘንድ ከፍተኛ ስጋት የፈጠረው ሰሜን ኮሪያ በምትገኝበት ቀጠና (ምስራቅ እስያ) ያለውን የኃይል ሚዛን ሊያናጋ ስለሚችል እና የዩክሬን ጦርነትን መልክ ሊቀይር ስለሚችል ነው።
የሩሲያ ቴክኖሎጂ እና የሰሜን ኮሪያ የሰው ኃይል መቀላቀል ለኔቶ (NATO) አባላት ቀላል የማይባል የቤት ስራ ሆኖባቸዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
#ሩሲያ #ሰሜንኮሪያ #ወታደራዊትብብር #ኪምጆንግኡን #አንድሬቤሎሶቭ #የዓለምፖለቲካ #ዩክሬን #ዜና

7 months ago
የቤላሩስ ፕሬዝዳንት ለሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ወዳጅነታቸውን የሚያጠናክር የጠመንጃ ስጦታ አበረከቱላቸው
የቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ በፒዮንግያንግ የጓደኝነት ስምምነት በተፈራረሙበት ወቅት ለሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ጠመንጃ በስጦታ ማበርከታቸውን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ሁለቱም መሪዎች ሩሲያ በዩክሬን የምታካሂደው ጦርነት ቁልፍ ደጋፊዎች ሲሆኑ፤በቅርበት ለመተባበር እና ከምዕራባውያን የሚመጣባቸውን ጫና ለመቋቋም ተስማምተዋል።
የቤላሩስ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን በለቀቁት ቪዲዮ፤ሉካሼንኮ ለኪም አውቶማቲክ ጠመንጃውን ሲያበረክቱ ‹‹ጠላቶች ቢመጡ በሚል ነው›› ሲሉ በቀልድ መልክ ተናግረዋል።
በምላሹም ኪም ለሉካሼንኮ ሰይፍ እና የቤላሩስ መሪ ምስል ያለበት የአበባ ማስቀመጫ በስጦታ ሰጥተዋል።
ሉካሼንኮ ለኪም እንደተናገሩት፤"እንደ ጓደኛ በዚህ ዓለም ውስጥ ሁሉንም ነገር እንዳየ ሰው ልነግርህ የምችለው ነገር ቢኖር፤ ይህንን ታታሪ እና ስነ-ስርዓት ያለው ህዝብ ይዘህ ሀገርህን ታላቅ ታደርጋታለህ " ማለታቸውን የቤላሩስ ዜና አገልግሎት ቤልታ ዘግቧል።
አክለውም "የዓለም አቀፍ ህግጋት በኃያላን መንግስታት በግልጽ ችላ በሚባሉበት እና በሚጣሱበት በዚህ ወቅት ሀገራት ሉዓላዊነታቸውን ለመጠበቅ እና የዜጎቻቸውን ደህንነት ለማሻሻል መተባበር አለባቸው ብለዋል።
ሉካሼንኮ የጓደኝነት ስምምነቱን ‹‹መሰረታዊ›› ሲሉ የገለጹት ሲሆን፤ኪም በበኩላቸው ስምምነቱ "የሁለትዮሽ ግንኙነቱ የተረጋጋ እድገት እንዲኖረው ዋስትና ይሰጣል" ማለታቸውን ቤልታ ዘግቧል።
በተጨማሪም ሁለቱ መሪዎች ከግብርና እስከ መረጃ ቴክኖሎጂ እና የህዝብ ጤና ባሉ ዘርፎች ላይ ለመተባበር ተስማምተዋል።
ሰሜን ኮሪያ እና ቤላሩስ በሰብዓዊ መብት ጥሰት እና ሩሲያን በዩክሬን ጦርነት በመደገፋቸው በምዕራባውያን ከባድ ማዕቀብ ተጥሎባቸዋል።
በዚህ ወቅት ፒዮንግያንግ ለሩሲያ ጦር ወታደሮችን እያቀረበች ሲሆን፤ ባለፈው ዓመት የምዕራባውያን ባለስልጣናት ለቢቢሲ እንደተናገሩት በዩክሬን ጦርነት የመጀመሪያዎቹ ጥቂት ወራት ውስጥ 1 ሺህ የሚገመቱ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ተገድለዋል።
ዩክሬን በበኩሏ ሩሲያ በዩክሬን ኢላማዎች ላይ ጥቃት ለመሰንዘር የቤላሩስን ግዛት እንደ ጦር ሰፈር ትጠቀማለች ስትል ከሳለች።
ሀና ሰይፉ

⚠️ የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን አሜሪካን "የሽብርተኛ ሀገር" ሲሉ ወነጀሉ!
የሰሜን ኮሪያው ከፍተኛ መሪ ኪም ጆንግ ኡን በቅርቡ በሰጡት መግለጫ አሜሪካን "የሽብርተኛ ሀገር" (Terrorist State) በማለት የጠሩ ሲሆን፣ ዋሽንግተን በመላው ዓለም ሰላምን እያደፈረሰች መሆኗን በጽኑ ተችተዋል። መሪው አክለውም አሜሪካ በዓለም ዙሪያ የምታደርገው ጣልቃ ገብነት እና ወታደራዊ እንቅስቃሴ ለዓለም አቀፋዊ ሰላምና ደህንነት ትልቅ ስጋት እየሆነ መምጣቱን ገልጸዋል።
ይህ የኪም ጆንግ ኡን ጠንካራ መግለጫ የመጣው በፒዮንግያንግ እና በዋሽንግተን መካከል ያለው ዲፕሎማሲያዊ ውጥረት በከፍተኛ ሁኔታ በጨመረበት ወቅት ነው። ሰሜን ኮሪያ አሜሪካ በኮሪያ ልሳነ ምድር የምታደርገውን ወታደራዊ ልምምድ እና የምትጥለውን ማዕቀብ እንደ ጠብ ጫሪነት እንደምትመለከተው በተደጋጋሚ ስትገልጽ ቆይታለች። አሁን የቀረበው ክስም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ወደ ከፋ ደረጃ ሊያሸጋግረው እንደሚችል የጂኦ-ፖለቲካ ባለሙያዎች ስጋታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።
መሪው በንግግራቸው ወቅት አሜሪካ የራሷን ጥቅም ለማስጠበቅ ስትል የተለያዩ ሀገራትን ሉዓላዊነት እየጣሰች እንደሆነ እና ይህ ድርጊቷም በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ የሰላም መደፍረስ እያመጣ መሆኑን አስረድተዋል።
ይህ ንግግር ሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር እና ሚሳኤል አቅሟን እያሳደገች ባለችበት ወቅት መሰማቱ፣ በምስራቅ እስያ ቀጠና ያለውን የኃይል ሚዛን እና የጸጥታ ሁኔታ ይበልጥ አሳሳቢ እንዲሆን አድርጎታል።

ሉካሼንኮ ለኪም ጆንግ ኡን የጦር መሳሪያ በስጦታ አበረከቱ
የቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ በሰሜን ኮሪያ ፒዮንግያንግ ባደረጉት ጉብኝት ለሀገሪቱ መሪ ኪም ጆንግ ኡን አውቶማቲክ ጠመንጃ በስጦታ አበረከቱ።
ሉካሼንኮ ስጦታውን ሲያስረክቡ "ጠላቶች ቢመጡ ትጠቀምበታለህ" በማለት በቀልድ መልክ መናገራቸው ተዘግቧል። ኪም ጆንግ ኡንም በምላሹ የራሳቸው ምስል ያለበትና ከባህር ዛጎል የተሰራ ትልቅ የአበባ ማስቀመጫ ሰጥተዋል።
ሁለቱ መሪዎች በምዕራባውያን ላይ ያላቸውን ተቃውሞ በመግለጽ የ"ወዳጅነትና ትብብር" ስምምነት ተፈራርመዋል።
ቤላሩስና ሰሜን ኮሪያ በዩክሬን ጦርነት ሩሲያን በግልጽ የሚደግፉ ሲሆን፣ ጉብኝታቸውም አዲስ የትብብር ምዕራፍ መክፈቻ መሆኑ ተገልጿል።
ስምምነቱ ከግብርና እስከ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ያሉ ዘርፎችን ያጠቃልላል።
ምንጭ፦ AFP

ኪም ጆንግ ኡን እና ልጃቸው በአዲሱ የጦር ታንክ ልምምድ ላይ
#ethiopia | የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን፣ ታዳጊ ሴት ልጃቸውን ጁ ኤን አስከትለው አዲስ የተመረተውን ዘመናዊ የጦር ታንክ ሲያስመርቁና ሲያስፈትኑ ታይተዋል። የሀገሪቱ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን (KCNA) ዛሬ ባወጣው መረጃ መሰረት፣ ታዳጊዋ ጁ ኤ አባቷ በቅርብ ርቀት ሆኖ እየተከታተላት የጦር ታንኩን በብቃት ስታሽከረክር ታይታለች።
የአዲሱ ታንክ ልዩ ባህሪያት
ይህ አዲስ ታንክ የሰሜን ኮሪያ ወታደራዊ ቴክኖሎጂ ምን ያህል እንደገፋ የሚያሳይ ነው ተብሏል። ዋና ዋናዎቹም፦
* የላቀ የመንቀሳቀስ ብቃት፦ በማንኛውም አስቸጋሪ መሬት ላይ በፍጥነት መጓዝ የሚችል፤
* ከፍተኛ የተኩስ ኃይል፦ ኢላማዎችን በከፍተኛ ጥራት መምታት የሚያስችል ቴክኖሎጂ የታጠቀ፤
* የመከላከያ ዘዴ፦ ሚሳኤሎችንና ድሮኖችን የመመከት ልዩ አቅም ያለው መሆኑ ተገልጿል።
የጊዜው ስልታዊ መልዕክት
ይህ ወታደራዊ ትርኢት በአጋጣሚ የተከናወነ አይደለም። አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ "Freedom Shield" የተሰኘውን መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ልምምድ ባጠናቀቁ ማግስት የተደረገ በመሆኑ፣ ፒዮንግያንግ ለጠላቶቿ የሰጠችው ቀጥተኛ ማስጠንቀቂያ እንደሆነ ተንታኞች ይገልጻሉ።
የጁ ኤ መገኘት ምን ያሳያል?
ታዳጊዋ ጁ ኤ በጦር ሜዳ ልምምዶች እና በከፍተኛ ወታደራዊ ዝግጅቶች ላይ በብዛት መታየቷ፣ የሰሜን ኮሪያ ቀጣይ መሪ ለመሆን እየተዘጋጀች እንደሆነ ፍንጭ ይሰጣል። መሪው ኪም ጆንግ ኡን ልጃቸው በታንክ አሽከርካሪነት መቀመጫ ላይ ሆና ልምምድ ስታደርግ በኩራት ሲመለከቱ የሚያሳዩት ምስሎች፣ የቤተሰቡን የሥልጣን ቀጣይነት የሚያረጋግጥ ተምሳሌታዊ ትርጉም አለው ተብሎ ይታመናል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ሰሜንኮሪያ #ኪምጆንግኡን #ጁኤ #የጦርታንክ #ወታደራዊልምምድ #ጂኦፖለቲካ #northkorea #kimjongun

ሰሜን ኮሪያ 10 የሚደርሱ ሚሳዔሎችን ወደ ጃፓን አስወነጨፈች።
ሚሳዔሎቹ ከሰናን ግዛት ተነስተው 350 ኪሎሜትር በመጓዝ በጃፓን ባህር አርፈዋል።
ፒዮንግያንግ ሚሳዔልቹን ያስወነጨፈችው አሜሪካ እና ጃፓን የሚያካሂዱትን የጋራ ወታደራዊ ልምምድ በመቃወም ነው።
ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡን ከሳምንታት በፊት ፓርቲያቸው ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ሰሜን ኮሪያ ከአሜሪካ ጋር ለመነጋገር ዝግጁ መሆኗን ጠቁመዋል።
ኪም ዋሽንግተን ለድርድር የፒዮንግያንግን ብሄራዊ ጥቅም አምና መቀበል እንዳለባት አሳስበዋል። #trtworld

ሰሜን ኮሪያ 10 የሚጠጉ የባሊስቲክ ሚሳይሎችን መተኮሷ ተነገረ
የደቡብ ኮሪያ ጦር ዛሬ ባወጣው መግለጫ፤ ሰሜን ኮሪያ 10 የሚጠጉ አጫጭር ርቀት ተኳሽ የባሊስቲክ ሚሳይሎችን ወደ ምስራቃዊ የባሕር ጠረፏ መተኮሷን አስታውቋል።
አል አረቢያ የደቡብ ኮሪያን የጦር ኃይሎች ጠቅሶ እንደዘገበው፤ ሚሳይሎቹ የተተኮሱት ከሰሜን ኮሪያ ዋና ከተማ ፒዮንግያንግ አቅራቢያ ካለው የሱናን አካባቢ ነው።
እነዚህ ሚሳይሎች ወደ 350 ኪሎ ሜትር የሚጠጋ ርቀት ከተጓዙ በኋላ በምስራቃዊው የባሕር ክፍል (የጃፓን ባሕር) ላይ ማረፋቸውን የደቡብ ኮሪያ የጋራ ኤታማዦር ሹም ገልጸዋል።
የደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ባለሥልጣናት ድርጊቱን "ግልጽ ትንኮሳ" ሲሉ የጠሩት ሲሆን፤ ጥቃቱን ተከትሎ ከጃፓን እና ከአሜሪካ ጋር በመተባበር ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተሉ መሆኑን አስታውቀዋል።
ይህ መጠነ ሰፊ የሚሳይል ሙከራ የተደረገው፤ ሰሜን ኮሪያ ከጥቂት ቀናት በፊት ወታደራዊ የሰላዮች ሳተላይት ወደ ህዋ ለማምጠቅ ያደረገችው ሙከራ መክሸፉን ተከትሎ መሆኑ ትኩረት ስቧል።
ፒዮንግያንግ በቅርቡ በቆሻሻ የተሞሉ ፊኛዎችን ወደ ደቡብ ኮሪያ ድንበር በመላክ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ውጥረት ይበልጥ አባብሳው እንደነበር ይታወሳል።
የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ በበኩላቸው፤ ሰሜን ኮሪያ የባሊስቲክ ሚሳይል በመተኮስ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ውሳኔዎችን ጥሳለች ሲሉ ድርጊቱን አውግዘዋል።
ልዑል ወልዴ

ጦርነቱን እቀላቀላለሁ:-ኪም ጆንግ‼️
"አንድም የሰሜን ኮሪያ ዜጋ ቢነካ ጦርነቱን እቀላቀላለሁ!" __የኪም ጆንግ ኡን‼️
የዓለምን ፖለቲካ እጅግ አስደንጋጭ በሆነ መልኩ የለወጠ መግለጫ ከሰሜን ኮሪያ ተሰምቷል። የሀገሪቱ መሪ ኪም ጆንግ ኡን በመካከለኛው ምስራቅ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ጣልቃ ለመግባት የሚያስችል እጅግ አደገኛና ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።
መሪው በይፋዊ መግለጫቸው እንዳሳወቁት፣ በኢራን ምድር የሚገኙ የሰሜን ኮሪያ ዜጎች ደህንነት ላይ ምንም ዓይነት ድርድር እንደማያደርጉና "አንድም የሀገሬ ዜጋ ላይ ጉዳት ከደረሰ ሰሜን ኮሪያ ያለምንም ማመንታትና ቅድመ ሁኔታ ወደ ጦርነቱ ትገባለች" ሲሉ ዓለምን ያስደነገጠ ዛቻ ሰንዝረዋል።
ይህ የኪም ጆንግ ኡን ንግግር በቀጠናው ያለውን ውጥረት ወደ ሦስተኛው የዓለም ጦርነት ሊቀይረው ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋት በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ፈጥሯል።
ተንታኞች እንደሚሉት፣ የፒዮንግያንግ ቁጣ ለኢራን ትልቅ ወታደራዊ የጀርባ አጥንት ሊሆን የሚችል ሲሆን፣ አሜሪካና አጋሮቿን ደግሞ ወደ ከፋ ወታደራዊ አጣብቂኝ ውስጥ የሚከት ነው።

ሰሜን ኮሪያ በኢራን ላይ የተፈጸመውን ጥቃት አወገዘች፤ የኪም ጆንግ ኡን “አወዛጋቢ” ንግግር ግን ውሸት ሳይሆን አልቀረም
የሰሜን ኮሪያ መንግሥት አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የሰነዘሩትን ወታደራዊ ጥቃት “ሉዓላዊነትን የጣሰ የጥቃት ድርጊት” ሲል በጽኑ አውግዟል።
የፒዮንግያንግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አሜሪካን ለአለም ሰላም ጠንቅ የሆነች “ቀስቃሽ” ብሏታል።
ይሁን እንጂ ባለፉት ጥቂት ሰዓታት በኢንተርኔት ላይ የተሰራጨውና የኪም ጆንግ ኡን ነው የተባለው “አንድ ሚሳይል እስራኤልን ከካርታ ለማጥፋት ይበቃል” የሚለው ንግግር በገለልተኛ ወገን አልተረጋገጠም።
የሰሜን ኮሪያ መንግሥታዊ የዜና ወኪል (KCNA) እንዲህ ያለ መግለጫ አላወጣም።
እንደ እውነቱ ከሆነ፣ ሰሜን ኮሪያ ለኢራን ያላትን ድጋፍ ብትገልጽም፣ በቀጥታ ግጭት ውስጥ ላለመግባት በመጠኑ “የተገደበ” የቃላት አጠቃቀም መምረጧ ተስተውሏል።
ይህም በክልሉ ያለውን ውጥረት ከማባባስ ይልቅ ሁኔታውን በንቃት ለመከታተል የፈለገች ይመስላል።

‹‹ኢራን 50 ሰሜን ኮሪያዎችን ትሆናለች›› የኔታንያሁ
#ethiopia | በመካከለኛው ምስራቅ እየተካሄደ ያለው ወታደራዊ ፍጥጫ አዲስና አደገኛ ምዕራፍ ላይ መድረሱ ተሰምቷል። የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን እርስ በእርስ የሚወራወሯቸው ጠንካራ ቃላት፣ ዓለምን ለከፋ ስጋት ዳርገዋል።
ኔታንያሁ ለምን ኢራንን ከሰሜን ኮሪያ ጋር አነጻጸሩ?
ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ባስተላለፉት የቪዲዮ መልዕክት፣ ኢራን ለዓለም ሰላም ካላት አደገኝነት አንጻር "50 ሰሜን ኮሪያዎችን ትሆናለች" ሲሉ ገልጸዋል። እንደ ኔታንያሁ ገለጻ፣ ሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር እና የባለስቲክ ሚሳኤል አቅም ቢኖራትም፣ እንደ ኢራን ግን "ሞት ለአሜሪካ" የሚል ግልጽ የጥፋት ርዕዮተ ዓለም አትከተልም።
"ኢራን የአሜሪካን እና የእስራኤልን መጥፋት እንደ ዋና ግብ ይዛ የተነሳች በመሆኗ፣ አጥፊነቷ ከሰሜን ኮሪያ በብዙ እጥፍ ይበልጣል" — ቤንያሚን ኔታንያሁ
የሰሜን ኮሪያው ምላሽ፦ "እስራኤልን ለማጥፋት አንድ ሚሳኤል ይበቃል"
የኔታንያሁ ንግግር ያልተዋጠላቸው የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን፣ ለቴህራን ያላቸውን ወታደራዊ ድጋፍ በይፋ አረጋግጠዋል። እስራኤልን ከዓለም ካርታ ላይ ለማጥፋት "አንድ ሚሳኤል ብቻ" በቂ እንደሆነ የገለጹት መሪው፣ አስፈላጊ ከሆነም የላቁ ሚሳኤሎችን ለኢራን ለማቅረብ ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
ይህ የፒዮንግያንግ መግለጫ የወጣው በሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች መሆኑ ይነገራል፡-
* አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱት "ኦፕሬሽን ኤፒክ ፉሪ" (Operation Epic Fury) መጠናከሩ።
* የኢራኑ የበላይ መሪ አያቶላ አሊ ኻሜኒ መገደላቸው መረጋገጡ።
አዲሱ የኃይል አሰላለፍ እና የዓለም ስጋት
በኢራን፣ ሩሲያ፣ ቻይና እና ሰሜን ኮሪያ መካከል እየተፈጠረ ያለው ወታደራዊ ጥምረት፣ ግጭቱን ከቀጣናዊነት አልፎ ዓለም አቀፍ ጦርነት ሊያደርገው ይችላል የሚል ስጋት አንዣብቧል።
* የቻይና ሚና፦ ቻይና ለኢራን የላቁ ሚሳኤሎችን እያቀረበች ነው የሚሉ ዘገባዎች ቢወጡም፣ ቤጂንግ ግን ውንጀላውን አስተባብላለች።
* የትራምፕ ማስጠንቀቂያ፦ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቀደም ሲል "ትልቁ ጦርነት ሊመጣ ይችላል" ሲሉ የሰጡት ማስጠንቀቂያ አሁን ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር እየተገጣጠመ ይገኛል።
ይህ ወታደራዊ ውጥረት በዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ላይ ከፍተኛ መናወጥን የፈጠረ ሲሆን፣ የጂኦ-ፖለቲካዊ መረጋጋትንም ጥያቄ ምልክት ውስጥ ከትቶታል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ethiofm #middleeastcrisis #israeliranconflict #netanyahu #kimjongun #globalsecurity #operationepic Fury #breakingnews

8 months ago
ኪም ጆንግ ኡን በ100% ድምፅ በማሸነፍ የፒዮንግያንግ በትረ ስልጣን አስጠበቁ
#ethiopia | የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን፣ በሀገሪቱ በተካሄደው የቅርብ ጊዜ ምርጫ መቶ በመቶ (100%) ድምፅ በማግኘት በስልጣናቸው ላይ መቀጠላቸው ታወቀ። ምንም እንኳን እንዲህ ዓይነት የድምፅ ውጤቶች በዲሞክራሲያዊው ዓለም ብርቅ ቢሆኑም፣ በሰሜን ኮሪያ ግን ለመሪው ያላቸውን "ፍጹም ታማኝነት" ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።
የምርጫው ዋና ዋና ነጥቦች
* የድምፅ መጠን፦ መሪው ምንም አይነት ተቃዋሚ ድምፅ ሳይገጥማቸው በሙሉ ድምፅ ተመርጠዋል።
* የስልጣን ዘመን፦ ኪም ጆንግ ኡን እ.ኤ.አ በ2011 ስልጣን ከያዙ በኋላ፣ አሁን በ2026 ለ14 ተከታታይ ዓመታት ሀገሪቱን እየመሩ ይገኛሉ።
* የመሪው ዕድሜ፦ የ42 ዓመቱ መሪ አሁንም የሰሜን ኮሪያ የሰራተኞች ፓርቲ እና የመንግስት የበላይ መሪ ሆነው ይቀጥላሉ።
ከአስር ዓመት በላይ በቤተሰባዊ አገዛዝ
ኪም ጆንግ ኡን ስልጣን የተረከቡት አባታቸው ኪም ጆንግ ኢል ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ተከትሎ ነበር። ባለፉት 14 ዓመታት ውስጥ መሪው የሀገሪቱን ወታደራዊ አቅም ወደ አዲስ ምዕራፍ ማሸጋገራቸው ይነገራል። በተለይም የኒውክሌር መርሃ-ግብር ማስፋፋት የዘመናቸው ዋነኛ መገለጫ ሲሆን፣ በአዲሱ የስልጣን ዘመናቸውም ይሄው ወታደራዊ ጡንቻን የማፈርጠም ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ይጠበቃል።
የሀገሪቱ የዜና ወኪሎች ውጤቱን አስመልክቶ ሲዘግቡ፣ ይህ "ታሪካዊ" ድምፅ በህዝቡ እና በመሪው መካከል ያለውን የማይበጠስ አንድነት የሚያሳይ ነው ብለውታል። እርግጥ ነው፣ 100 በመቶ ድምፅ ማግኘት በሂሳብ ስሌትም ሆነ በፖለቲካው ዓለም እጅግ ብርቅዬ ቢሆንም፣ በፒዮንግያንግ ግን ሌላ አማራጭ ማሰብም ቢሆን የተለመደ አይደለም።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ሰሜንኮሪያ #ኪምጆንግኡን #ምርጫ2026 #ዓለምአቀፍዜና #ፒዮንግያንግ

ኪም ጆንግ ኡን ለዘማች ቤተሰቦች የቤት ቁልፍ አበረከቱ
#ethiopia | የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን፣ ከሩሲያ ጎን ተሰልፈው በዩክሬን ጦርነት ህይወታቸውን ላጡ ወታደሮች ቤተሰቦች በዋና ከተማዋ ፒዮንግያንግ አዳዲስ የመኖሪያ ቤቶችን አስገንብተው አስረክበዋል።
ኪም በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፣ መንግስታቸው ለዘማች ቤተሰቦች የሚያደርገውን አስፈላጊ ድጋፍ እና እንክብካቤ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ቃል ገብተዋል። ይህ እርምጃ ሀገሪቱ ለሞስኮ ያላትን የጸና ወታደራዊ አጋርነት እና ለጦርነቱ የከፈለችውን መስዋዕትነት የሚያሳይ ነው ተብሏል።
የክፍለ ጦሩ ተሳትፎ በቁጥር ሲታይ፦
* ወደ ሩሲያ የተላኩ ወታደሮች፦ 15,000
* በጦርነቱ ህይወታቸውን ያጡ፦ 2,000 ገደማ
* የተሰጠው ማበረታቻ፦ በዋና ከተማዋ ፒዮንግያንግ ውስጥ የተሰሩ ዘመናዊ ቤቶች።
ይህ የቤቶች ስርጭት ለቤተሰቦቹ እንደ መጽናኛ ቢታይም፣ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች በሩቅ ምስራቅ አውሮፓ እየከፈሉት ያለው የህይወት ዋጋ ግን ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ መምጣቱን መረጃዎች ያመለክታሉ።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #northkorea #kimjongun #russiaukrainewar #pyongyang #worldnews #militaryalliance #ethiopia #thiqaheth #upi

9 months ago
ፒዮንግያንግ "ለበቀል ተዘጋጅቻለሁ" አለች
#ethiopia | በሁለቱ ኮሪያዎች መካከል ያለው የቆየ ጠላትነት አሁን ደግሞ በ"ድሮን ቅኝት" ክስ ሳቢያ ወደ ከፋ ምዕራፍ ተሸጋግሯል። ሰሜን ኮሪያ የደቡብ ኮሪያ ሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮኖች) በግዛቷ ላይ የቅኝት ስራ እያከናወኑ መሆኑን በመግለጽ የጦርነት ያህል የሚቆጠር ማስጠንቀቂያ አስተላልፋለች።
🛡️ የፒዮንግያንግ ክስ እና ማስጠንቀቂያ
እንደ ፒዮንግያንግ መግለጫ ከሆነ፣ ሲኡል ካለፈው መስከረም ወር ጀምሮ በሰሜን ኮሪያ የአየር ክልል ላይ ተደጋጋሚ የድሮን ማንዣበብ እያደረገች ትገኛለች። ፒዮንግያንግ ይህንን ድርጊት እንዲህ ስትል ገልጻዋለች፦
* "ከባድ ዋጋ ያስከፍላል"፦ የሲኡል የጠብ ጫሪነት ባህሪ ለበቀል የሚጋብዝ መሆኑን ገልጻለች።
* "ተመጣጣኝ ምላሽ"፦ ለተፈጸመው "የአየር ክልል ወረራ" ተመጣጣኝና ጠንካራ ወታደራዊ ምላሽ እንደምትሰጥ አስታውቃለች።
* ውድቅ የተደረገ ማስተባበያ፦ ደቡብ ኮሪያ የሰጠችውን ማስተባበያ "የሀሰት መግለጫ" ስትል አጣጥላዋለች።
🚫 ሲኡል ምላሽ
የደቡብ ኮሪያ መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ የቀረበበትን ክስ "መሰረተ ቢስ" ሲል ውድቅ አድርጎታል። ሚኒስቴሩ ስለተባለው የድሮን ጥቃትም ሆነ ቅኝት ምንም ዓይነት እውቅና እንደሌለው ገልጿል።
🌍 የጂኦ-ፖለቲካ ተንታኞች ስጋት
የሁለቱ ኮሪያዎች የረዥም ጊዜ ጠላትነት በኮሪያ ልሳነ ምድር ላይ ያለው ውጥረት በማንኛውም ሰዓት ወደ ግጭት ሊያመራ እንደሚችል ተንታኞች ያስረዳሉ። አሁን የተከሰተው የድሮን ውዝግብም በቀጣናው ላይ የነበረውን ስጋት ይበልጥ እንዲባባስ አድርጎታል።
ሰሜን ኮሪያ በቃል አቀባይዋ በኩል ባስተላለፈችው መልዕክት፣ "ጠላት ያልተገባ ትንኮሳ እየፈጸመ ነው፤ እርምጃ ከመውሰድ አንመለስም" በማለት ጉዳዩ ወታደራዊ መልክ ሊይዝ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥታለች።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ሰሜንኮሪያ #ደቡብኮሪያ #የኮሪያልሳነምድር #ድሮን #ወታደራዊውጥረት #ዓለምአቀፍዜና #ፒዮንግያንግ #ሲኡል #የጦርነትስጋት

🗺️ የሰሜን ኮሪያ አዲሱ አነጋጋሪ ካርታ ሆኗል
#ethiopia | በማህበራዊ ሚዲያ (በተለይም በሬዲት) ላይ በስፋት እየተሰራጨ የሚገኝ አንድ የዓለም ካርታ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል። ይህ ካርታ ከተለመደው የምዕራባውያን የካርታ አሰራር (Mercator Projection) ፈጽሞ የተለየ መልክ ያለውና ሰሜን ኮሪያ ራሷን የዓለም ማዕከል አድርጋ የሳለችበት መሆኑ ተገልጿል።
📍 የካርታው ልዩ ባህሪያት፦
* የኮሪያ አንድነት፦ ካርታው ሰሜን እና ደቡብ ኮሪያን እንደ ሁለት የተለያዩ ሀገራት ሳይሆን፣ እንደ አንድ ወጥ ሀገር አድርጎ በጉልህ ይስላቸዋል።
* የፓስፊክ ማዕከል፦ አትላንቲክ ውቅያኖስን ማዕከል ከሚያደርገው የለመድነው ካርታ በተቃራኒ፣ ይህኛው የፓስፊክ ውቅያኖስን በመሃል ያደርጋል።
* የጠፉት አህጉራት፦ በካርታው ላይ የሰሜን አሜሪካ እና የአውሮፓ ክፍሎች እጅግ አነስተኛ ሆነው የተሳሉ ሲሆን፣ አንዳንዶቹ ደግሞ ጨርሶ አይታዩም።
* የጃፓን ቦታ፦ የጃፓን መገኛ ቦታም ቢሆን ከተለመደው ስፍራው ተቀይሮ መሳሉ ተጠቃሚዎችን አስገርሟል።
ታዛቢዎች እንደሚሉት ይህ ካርታ የሰሜን ኮሪያን የፖለቲካ አቋም ያንፀባርቃል። ሀገራት የዓለምን ካርታ ሲስሉ ራሳቸውን ማዕከል ማድረጋቸው የተለመደ ቢሆንም፣ የፒዮንግያንግ ካርታ ግን "ዓለምን እኛ በምንፈልገው መነጽር ብቻ እዩ" የሚል መልዕክት እንዳለው ይነገራል።
🌐 የዲጂታል መድረኮች ክርክር
ምንም እንኳን የሰሜን ኮሪያ መንግስት ይህ ካርታ በትምህርት ቤቶች ውስጥ በቋሚነት ጥቅም ላይ መዋሉን ይፋ ባያደርግም፣ በዲጂታል መድረኮች ላይ ግን "ካርታ እንዴት ለፕሮፓጋንዳ ያገለግላል?" የሚል ሰፊ ክርክር ቀስቅሷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ሰሜንኮሪያ #የዓለምካርታ #ፖለቲካ #ጂኦግራፊ #ፒዮንግያንግ #ድንቅመረጃ #ካርታ #northkorea #worldmap #geography

10 months ago
ሰሜን ኮሪያ እና ሩሲያ በዩክሬን ጦርነት ውስጥ ደምን፣ ሕይወትን እና ሞትን ተጋርተዋል ሲሉ ኪም ጆንግ ኡን ተናገሩ
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ለሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ባስተላለፉት የአዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፤ ሰሜን ኮሪያና ሩሲያ በዩክሬኑ ጦርነት ውስጥ "የደም፣ የሕይወት እና የሞት" ትስስር አላቸው ብለዋል።
በሰሜን ኮሪያ የዜና ወኪል በታተመው በዚህ መልዕክት፤ ኪም 2025 በፒዮንግያንግ እና በሞስኮ መካከል ያለው ጥምረት "በአንድ ቦይ ውስጥ በጋራ በፈሰሰ ደም፣ በሕይወት እና በሞት" የጠነከረበት "በእውነትም ትርጉም ያለው ዓመት" ነው ብለዋል።
የደቡብ ኮሪያ እና የምዕራባውያን የስለላ ድርጅቶች ፒዮንግያንግ በዩክሬን ጦርነት ከሞስኮ ጎን ተሰልፈው እንዲዋጉ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን መላኳን ቀድመው ዘግበው ነበር። ሰሜን ኮሪያ ባለፈው አመት ሚያዚያ ወር ላይ ወታደሮቿ የሩሲያን ወታደራዊ ዘመቻ ለመደገፍ መሰማራታቸውን እና አንዳንዶቹም በውጊያው ላይ መገደላቸውን አረጋግጣለች።
በታህሳስ ወር መጀመሪያ ላይ ፒዮንግያንግ በነሐሴ ወር ውስጥ ከዩክሬን ድንበር አቅራቢያ በሚገኘው የኩርስክ ክልል ፈንጂዎችን ለማጽዳት ወታደሮችን ልካ እንደነበር አምናለች።
ወታደራዊ ክፍሉ ወደ ሀገር ሲመለስ ታህሳስ 4 ቀን ኪም ባደረጉት ንግግር፥ በ120 ቀናት ቆይታቸው ቢያንስ ዘጠኝ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች መገደላቸውን ተናግረዋል።

ኪም ጆንግ ኡን ለጦርነት ዝግጁነት የሚውሉ ሚሳይሎች በከፍተኛ መጠን እንዲመረቱ አዘዙ
#ethiopia | የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ሀገራቸው ሊሰነዘርባት የሚችለውን ማንኛውንም ወታደራዊ ጥቃት ለመመከትና እንደ "ጦርነት መከላከያ" የሚያገለግሉ ሚሳይሎች በከፍተኛ መጠን እንዲመረቱ ጥብቅ መመሪያ አስተላልፈዋል።
መሪው ይህንን ትዕዛዝ የሰጡት ዋና ዋና የጦር መሣሪያ ማምረቻ ፋብሪካዎችን በጎበኙበት ወቅት እንደሆነ የሀገሪቱ የመንግስት መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
የኪም ጆንግ ኡን ጉብኝት ትኩረት ያደረገው ስልታዊ ሚሳይሎችን፣ የሮኬት ማስወንጨፊያዎችን እና ሌሎች የጦር ሜዳ መሣሪያዎችን በሚያመርቱ ተቋማት ላይ ነው። መሪው በጉብኝታቸው ወቅት እንደገለጹት፣ ሰሜን ኮሪያ ጠላቶቿን ሊያስደነግጥ የሚችል እጅግ ዘመናዊና ግዙፍ ወታደራዊ አቅም መገንባት ይኖርባታል።
ይህ የጦር መሣሪያ ምርት ማሳደጊያ እቅድ ሀገሪቱ ማንኛውንም የጠላት ወታደራዊ እንቅስቃሴ ለመመከትና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም አጥቂ ኃይሎችን ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት የሚያስችል ዝግጁነት እንዲኖራት ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
ይህ እንቅስቃሴ የተጀመረው አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ በጋራ የሚያካሂዱትን ወታደራዊ ልምምድ ተከትሎ እንደሆነ ይገመታል። ሰሜን ኮሪያ እነዚህን የጋራ ወታደራዊ ልምምዶች ለወረራ እንደታቀዱ የዝግጅት እርምጃዎች አድርጋ ስለምትመለከታቸው፣ የሚሳይል ምርቷን ማሳደጓ ለነዚህ እንቅስቃሴዎች የሚሰጥ ምላሽ መሆኑን ተንታኞች ይናገራሉ።
በተጨማሪም ኪም ጆንግ ኡን በፋብሪካዎቹ በነበራቸው ቆይታ፣ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶች በጦር መሣሪያ ምርት ላይ እንዲካተቱ እና የማምረት አቅሙን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የላቁ የኢንጂነሪንግ ስራዎች እንዲከናወኑ አሳስበዋል። ይህ የፒዮንግያንግ አቋም በኮሪያ ልሳነ ምድር ያለውን ውጥረት ይበልጥ ሊያባብሰው እንደሚችል ተሰግቷል።
አለም አቀፉ ማህበረሰብ በተለይም የምዕራባውያን አገራት የሰሜን ኮሪያን የሚሳይል ምርት ማሳደግ እና ተደጋጋሚ ሙከራዎችን አጥብቀው እያወገዙ ይገኛሉ።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰሜን ኮሪያ ላይ የጣለው ማዕቀብ አሁንም እንደቀጠለ ቢሆንም፣ ሀገሪቱ ግን የሚሳይል እና የኒውክሌር ፕሮግራሟን ከማስፋፋት ወደኋላ አላለም።
#menaharia_fm

ሰሜን ኮሪያ ቁሰለኛ ወታደሮችን ሸለመች
#ethiopia | የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጁንግ ኡን ከሩሲያ ጎን ተሰልፈው ሲዋጉ ለነበሩ የሀገሪቱ ወታደሮች 'ጀግኖች' የሚል ማዕረግ ሰጡ።
በፒዮንግያንግ በተዘጋጀው ወታደሮችን የመቀበል ስነ ስርዓት ላይ ቁስለኛ ወታደሮችን እያቀፉ ታይተዋል ኪም።
የሰሜን ኮሪያ ህዝብ ወታደራዊ ክፍል እና የ528ኛ ሬጂመንት ኢንጂነር ወታደሮች በሩሲያ ላደረጉት ተጋድሎ ነው የጀግንነት እውቅና የተሰጣቸው የተባለው።
ታላቅ ታምር እና ጀብድ በአስቸጋሪ የጦር ቀጠና ውስጥ ስለፈፀማችሁ ብሎም ለዓመታት የማይቻል መስሎ የሚታየውን ስላደረጋችሁ ጀግኖች ናችሁ ብለዋል።
ምዕራባውያን ምንም እንኳ ዘመናዊ መሳሪያ ቢታጠቁም፣ በጥልቅ መንፈሳዊነት የተገነባውን አብዮታዊ ሰራዊት ማሸነፍ አልቻሉም ሲሉም ወታደሮቻቸውን አሞካሽተዋል።
ከሬጂመንቱ ውስጥ ዘጠኝ ጓዶች ማጣታችን ልብ የሚሰብር ቢሆንም፣ ለነፃነት እና ክብር ስለተዋደቁ እናወድሳቸዋለን ብለዋል።
ሩሲያ በኩርስክ ግዛት ባደረገችው ጦርነት 10ሺህ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች መሳተፋቸውን የምዕራባውያን ሚዲያዎች እና መሪዎች መግለፃቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ሞስኮ እና ፒዮንግያንግ ግን ይህን ክስ ማስተባበላቸው አይዘነጋም ያለው ኤን ቢ ሲ ነው።

11 months ago
ትራምፕ ደቡብ ኮሪያ ከመድረሳቸው በፊት ሰሜን ኮሪያ ተቃውሞዋን ለማሳየት ሚሳኤሎችን አስወነጨፈች
#ethiopia | የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለእስያ-ፓስፊክ የኢኮኖሚ ትብብር (APEC) ጉባኤ በደቡብ ኮሪያ እንደደረሱ ወዲያውኑ፣ ሰሜን ኮሪያ ስትራቴጂካዊ የክሩዝ ሚሳኤሎችን ከባሕር ወደ ምድር የማስወንጨፍ ሙከራ ማድረጓን የመንግስት ሚዲያዋ ኬሲኤንኤ (KCNA) ዘገበ።
ሙከራው የተካሄደው ማክሰኞ ከሰዓት በኋላ በ3:00 ሰዓት (በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር) አካባቢ ሲሆን፣ ሚሳኤሎቹ የተተኮሱት ከኮሪያ ልሳነ ምድር ምዕራባዊ ክፍል በሚገኘው ቢጫ ባህር (Yellow Sea) ውስጥ ነው። የሰሜን ኮሪያ የመንግስት ሚዲያ እንዳለው፣ ሚሳኤሎቹ በተወሰነላቸው መስመር ላይ ከሁለት ሰዓት በላይ (ከ7,800 ሰከንድ በላይ) በአየር ላይ ከበረሩ በኋላ ኢላማቸውን በትክክል መምታት ችለዋል። የደቡብ ኮሪያ ተንታኞች እንደሚገምቱት፣ እነዚህ ሚሳኤሎች እስከ 1,500 ኪሎ ሜትር የመምታት አቅም አላቸው።
ፒዮንግያንግ ይህንን የጦር መሳሪያ ሙከራ ያከናወነችው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በደቡብ ኮሪያ የጎበኙበትን ጊዜ በመምረጥ የግልጽ ተቃውሞና ንቀት ለማሳየት ነው። የሰሜን ኮሪያ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለሥልጣን ፓክ ጆንግ ቾን እንደተናገሩት፣ ሙከራው የተካሄደው የሀገሪቱን የጦርነት መከላከያ አቅም የሚያሳድገውን "የኑክሌር ኃይል" በተግባር ላይ በማዋል፣ በጠላቶች ላይ ወታደራዊ ችሎታን ለማሳየት እና አስተማማኝነታቸውን ለመፈተሽ ነው። ይህ ተግባር በ2019 ዓ.ም በትራምፕ እና በኪም ጆንግ ኡን መካከል የተጀመረው የኒውክሌር ድርድር ከተበተነ በኋላ በዋሽንግተን ላይ የተሰነዘረ ሌላ ወታደራዊ ማስጠንቀቂያ እንደሆነ ተገልጿል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የደቡብ ኮሪያ የጋራ ኤታማዦር ሹሞች (JCS) ሚሳኤል ማስወንጨፉን መለየታቸውን አረጋግጠው፣ ዝርዝር ትንተና በማድረግ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል። በበኩላቸው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ግን ከጃፓን ወደ ደቡብ ኮሪያ በሚያደርጉት የበረራ ጉዞ ላይ ሳሉ ስለ ማስወንጨፉ ተጠይቀው አቅልለው ተመልክተዉታል። "እሱ (ኪም ጆንግ ኡን) ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሚሳኤሎችን ሲያስወንጭፍ ቆይቷል አይደል?" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። አክለውም፣ ኪም ጆንግ ኡንን ለመገናኘት አሁንም ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።
በአጠቃላይ፣ የሰሜን ኮሪያ ድርጊት አሜሪካ እና ቻይና በፓስፊክ ክልል የንግድ እና የደኅንነት ውጥረቶችን ለመፍታት ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችን በሚያደርጉበት ወቅት መፈጸሙ፣ በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ የፒዮንግያንግን ጉልህ ስፍራ እንዲይዝ ማድረጉን ታዛቢዎች ይገልጻሉ ሲል የዘገበው መናኸሪያ ኤፍ ኤም ነው።

12 months ago
ሰሜን ኮሪያ የተሳካ የሃይፐርሶኒክ ሚሳኤል ሙከራ አደረገች
#ethiopia | ሰሜን ኮሪያ የተሳካ የሃይፐርሶኒክ ሚሳኤል ሙከራ ማድረጓን አስታወቀች።
ሀገሪቱ ያደረገችው የሃይፐርሶኒክ ሚሳኤል ሙከራ እራሷን የመከላከል ቴክኒካል አቅሟን እያሳደገች ስለመሆኑ ግልጽ ማስረጃ መሆኑን አረጋግጣለች።
በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮሪያ በሚሳኤል አስተዳደር የተካሄደውን ሙከራ፣ የኮሪያ የሰራተኞች ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ፀሃፊ ፓክ ጆንግ ቾን፣ የሰሜን ኮሪያ የሚሳኤል አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ጃንግ ቻንግ ሃ መምራታቸውን የኮሪያ ማዕከላዊ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።
አዲሱ የጦር መሣሪያ ስርዓት ከጠላት ሊሰነዘሩ የሚችሉ ስትራቴጂካዊ ጥቃቶችን በዘላቂነት እና ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመመከት እንደሚያስችል ተነግሯል።
የፒዮንግያንግ እንቅስቃሴ ጦርነትን ቀድሞ ለማስቀረት ያለመና ዓላማው ራስን መከላከል ብቻ መሆኑን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ተናግረዋል።
የደቡብ ኮሪያ ጦር ፒዮንግያንግ በርካታ የአጭር ርቀት ባለስቲክ ሚሳኤሎችን ወደ ምስራቅ ባህር መተኮሷን አስታውቋል።
አሜሪካ ሙከራው ህገ-ወጥ እና የቀጠናውን መረጋጋት የሚረብሽ ነው በማለት ያወገዘች ሲሆን፤ ሰሜን ኮሪያ የተለያዩ የሰላም ስምምነቶችን ከሚጥሱ ተጨማሪ ድርጊቶች እንዲትተቀብ ጠይቃለች።
በክብረአብ በላቸው #ጋዜጣፕላስ #ዓለምዓቀፍ #ሰሜንኮሪያ #ደቡብኮሪያ

የአሜሪካ አዛዥ ናዛዥነት ከእንግዲህ አክትሟል ! /ኪም ጆንግ ኡን/
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን በሚቀጥሉት ሳምንታት ሊሞክረው ይችላል ብለው የሚያምኑትን አዲስ አህጉር አቀፍ ባሊስቲክ ሚሳኤልን በዛሬው እለት በፒዮንግያንግ አደባባዮች ማሳየታቸው ተነገረ ።
የኮሪያ የሰራተኞች ፓርቲ የተመሰረተበትን 80ኛ አመት በዓል ተከትሎ በፒዮንግያንግ አደባባይ በተዘጋጀው ትርኢት ሰሜን ኮሪያ የላቀውን Hwasong-20 አቋራጭ ባሊስቲክ ሚሳኤልን አሳይታለች ሲል የመንግስት ሚዲያ KCNA ዘግቧል።
አሁን ባሉት የአሜሪካ ሚሳኤል መከላከያ ስርዓቶች ላይ ጭንቀትን ይጨምራሉ የተባለለትን አህጉር አቀፍ ባሊስቲክ ሚሳኤል ባሳዩበት ትልቅ ወታደራዊ ሰልፍ የቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ፣ የቀድሞ የሩሲያ ፕሬዚዳንት ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ እና የቬትናም ኮሚኒስት ፓርቲ መሪ ቶ ላም ተገኝተዋል ተብሏል ።
በሰልፉ ላይ ባደረጉት ንግግር ኪም በውጭ አገር ለሚያገለግሉት የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች በተለይም በሩሲያ የዩክሬን ጦርነት ውስጥ “ሞቅ ያለ ማበረታቻ” አቅርበዋል፣ ጀግንነታቸው ከአገር መከላከያ አልፎ “ከሶሻሊስት ግንባታ” ታላቅ አስተዋጽኦ እንዳለዉ መግለፃቸውን ኬሲኤንኤን ዘግቧል።
ሀገራቸው “ከአሜሪካ ኢምፔሪያሊስቶች እየተባባሰ የመጣውን የኒውክሌር ጦርነት ስጋት” ለመከላከል የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ልማቷን እና ኢኮኖሚዋን በአንድ ጊዜ እያራመደች ነው ብለዋል።
“ፓርቲያችን እና መንግስታችን አሁንም ጠንከር ያሉ ፖሊሲዎችን በመቀበል፣ ጠንካራ መርሆችን በማክበር እና ደፋር የመከላከያ እርምጃዎችን በመውሰድ የጠላቶቻችንን ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ እርምጃዎችን እየታገለ ነው” ሲል ኪም ተናግሯል።
የላቀውን Hwasong-20 አቋራጭ ባሊስቲክ ሚሳኤልን KCNA የሀገሪቱ “ጠንካራው የኒውክሌር ስትራቴጂካዊ የጦር መሳሪያ ስርዓት” በማለት ገልጿል።
የHwasong ICBM ሰሜን ኮሪያ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የትኛውም ቦታ ላይ እንድትመታ ሊያስችላት ይችላል የተባለ ሲሆን
ለማረጋገጥ ግን ከዚህ አመት መጨረሻ በፊት ሲፈተሽ ለማየት መጠበቅ አለብን "በዩኤስ የተመሰረተው ካርኔጊ ኢንዶውመንት ለአለም አቀፍ ሰላም አንኪት ፓንዳ ተናግረዋል።
የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ

"ሁዋሶንግ-20" አስፈሪው የሰሜን ኮሪያ ባሊስቲክ ሚሳዔል
#ethiopia | ሰሜን ኮሪያ በ80ኛ ዓመቱ የሰራተኞች ፓርቲ ምስረታ በዓል ላይ እጅግ ኃይለኛ የተባለውን አህጉር አቋራጭ ባሊስቲክ ሚሳዔል ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ አደረገች፡፡
ሁዋሶንግ -20 አይ ሲ ቢ ኤምን በወታደራዊ ትዕይንቱ ላይ ያስመለከቱት ኪም ጆንግ ኡን በኩራት አስመልክተውታልም ተብሏል ፡፡
እጅጉን አውዳሚውን የጦር መሳሪያ ለዓለም ማስተዋወቃቸው ተሰምቷል ኪም ጆንግ ኡን፡፡
የሰሜን ኮሪያ ማዕከላዊ የዜና ወኪል ኪም ጆንግ ኡን ባሊስቲክ ሚሳዔሉን በወታዳራዊ ትዕይንቱ ላይ ተመልክተውታል ፤ሁዋሲንግ-20 በሄራዊ ኩራት ነውም ሲልም ዘግቧል ፡፡
ፒዮንግያንግ ሁዋሶንግ-20 ባሊስቲክ ሚሳዔልን ይፋ ስታደርግ በዓለም አደባባይ ላይ ወታደራዊ ጡንቻዬን ዕወቁልኝ ስትል ነው በሚልም ምዕራቡ ዓለም ተችቷታል ፡፡
ሁዋሶንግ -20 በአሁኑ ሰዓት ሰሜን ኮሪያ የረዥም ርቀት ተወንጫፊ የኑክሌር ጦር መሳሪያ ስርዓት አቅሟ ምን ላይ እንደደረሰ እንዲሁም ፍላጎቷን የሚያሳይ ነው ፡፡
ተከታታይ የሁዋሶንግ ባሊስቲክ ሚሳዔል ምርት ላይ ያተኮረችው የኪሞቹ አገር አህጉር አቋርጦ ማውደም የሚችል የጦር መሳሪያ ስርዓት ባለቤት መሆኗን የሚጠቁም አድርጎላታል ፡፡
ሁዋሶንግ-20 በርካታ የኑክሌር አረር ጫፎችን በተመሳሳይ ሰዓት እንዲሸከም ተደርጎ የተሰራ ሳይሆን አይቀርም በሚልም ወታደራዊ አዋቂዎች ሀሳባቸውን በማጋራት ላይ ይገኛሉ፡፡
ሁዋሶንግ-18ን ቀደም ሲል ፒዮንግያንግ ማምረቷም የሚዘነጋ አይደለም ፡፡NBC

1 year ago
ሰሜን ኮርያን እና ሩሲያን የሚለያይ ምድራዊ ሃይል የለም ! /ኪም ጆንግ ኡን/
የሰሜን ኮርያው ሁለንተናዊ መሪ ኪም ጆንግ ከሞስኮ ጋር ያላቸው ወዳጅነት ከብረት የጠነከረ በከፍታም በዝቅታም የማይናወጥ መሆኑን መናገራቸው ተሰማ ።
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ለሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እንደተናገሩት ጥምረታቸው "ትላንትም ዛሬም ወደፊትም ሁልጊዜም የሚቀጥል ይሆናል" ሲሉ ፒዮንግያንግ እና ሞስኮ ሩሲያ ከዩክሬን ጋር እያደረገችዉ በሚገኘዉ ጦርነት ወታደራዊ ትብብርን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል ።
ኪም ይህን ያሉት የሩሲያውን መሪ በልደታቸው ቀን እንኳን ደስ ያላችሁ በማለት ለፑቲን በላኩት ደብዳቤ ነው ሲል የሰሜን ኮሪያ ማዕከላዊ የዜና አገልግሎት (KCNA) ዘግቧል።
"ታላቁን የድል ቀን የተቀበሉት የሁለቱ ሀገራት የትብብር ግንኙነት ወደ ፊት ወደፊት እንደሚቀጥል አልጠራጠርም ። በመካከላችን ላለው ሞቅ ያለ ወዳጅነት እና የቅርብ ወዳጃዊ ግንኙነት ምስጋና ይግባውና የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን ሁለንተናዊ እድገት በሃይል ለማስፋፋት እና ፍትሃዊ እና ባለብዙ-ፖላራይዝድ የአለም ስርአት እንዲፈጠር ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት አልጠራጠርም ሲል ኪም ለፑቲን ተናግረዋል ።
ካለፈው አመት ጥቅምት ወር ጀምሮ ሰሜን ኮሪያ 15,000 የሚጠጉ ወታደሮችን እና የጦር መሳሪያዎችን ለሩሲያ በመላክ የጦርነት ጥምረቷን እያሳየች ነዉ ሲል የደቡብ ኮሪያ የስለላ ድርጅት አስታውቋል።
በደብዳቤው ላይ ኪም ሩሲያ ብሄራዊ ሉዓላዊነቷን ለማስጠበቅ የምታደርገውን “ፍትሃዊ ትግል” ሙሉ በሙሉ እንደሚደግፉ ገልፀው ሞስኮ ከዩክሬንና ከኔቶ ጋር የገባችበትን ጦርነት እንዲያሸንፉ እያገዙ ነዉ ሲል ዮንሃፕ የዜና አገልግሎት ዘግቧል።
ቀደም ብሎ በነሀሴ 13 የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በስልክ ባደረጉት ውይይት ሁለቱ ሀገራት ወታደራዊ ትብብር እያሳደጉ በመሆናቸው ለሩሲያ ያላቸውን "ሙሉ ድጋፍ" ገልፀው ነበር። በማለት ከሰሞኑን የአዉሮጳ ህብረት አባለ ሀገራት ሞስኮን በኢኮኖሚ በአቅርቦት በወታደራዊ የበላይነት ለመዉሰድ የጀመሩትን ትብብር ለማክሸፍና አሸናፊ ለመሆን ኪም እና ፑቲን የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን ኬሲኤንኤ ዘግቧል።

Comments