5 months ago
የነፍስ ተናፋቂው ጥሪ፤ ሐጅ የሙስሊሞች የሕይወት ዘመን ታላቅ መንፈሳዊ ሕልምና የዒባዳ ማዕዘን
#ethiopia | ሐጅ... የአላህ (ሱ.ወ) ቤት ወደሆነችውና የሙዕሚኖች ልብ ዘወትር ወደምትናፍቃት ቅድስት መካ የሚደረግ፣ በአካል ለቻለና አቅም ላለው ሙስሊም ሁሉ በሕይወት ዘመን አንድ ጊዜ የመፈጸም ግዴታ ያለበት አምስተኛው የእስልምና ማዕዘን ነው።
ይህ ታላቅ ጉዞ የግል መንፈሳዊ ጥንካሬን ማደሻ ብቻ ሳይሆን፣ የታማኝነት እና የዓለም አቀፋዊ የእስልምና አንድነት ከፍተኛ መገለጫ ተደርጎ ይወሰዳል።
በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ምድራዊ ማዕረግና የሀብት ልዩነትን ሁሉ አውልቀው፣ ተመሳሳይ ነጭ ኢሕራም ለብሰው በአንድነት ሲቆሙ ፍጹም የእኩልነት እና የወንድማማችነት ትርጉም በተግባር ይገለጻል።
ይህ ሥርዓት ከዘመናት በፊት ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ያስተማሩትን መንገዶች በመከተል የሚከናወን ሲሆን፣ እያንዳንዱ ተግባር ከነቢዩ ኢብራሂምና (ረ.ወ) ከነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ታሪክ ጋር የተያያዘ ጥልቅ መንፈሳዊ ትርጉም አለው።
ጉዞው በእስልምና የጨረቃ አቆጣጠር 12ኛው ወር "ዙል-ሒጃ" ላይ የሚፈጸም ሲሆን፣ የጨረቃ አቆጣጠር ከግሪጎሪያን አቆጣጠር ጋር ሲነጻጸር በየዓመቱ ወደ 11 ቀናት ገደማ ወደ ኋላ ስለሚሽከረከር የሐጅ ወቅት በተለያዩ የአየር ንብረቶች (በበጋ፣ በክረምትና በጸደይ) ላይ እንዲያርፍ ያደርገዋል።
የዚህ ታላቅ የሐጅ ሥርዓት ማጠናቀቂያ በመላው ዓለም በታላቅ ድምቀት በሚከበረው ዒድ አል-አድሃ (የአረፋ በዓል) ላይ ይደርሳል።
አማኞች መስዋዕት በማቅረብ፣ ያረዱትን አንድ ሦስተኛ ለቤተሰቦቻቸው፣ አንድ ሦስተኛ ለጎረቤቶቻቸው እንዲሁም ቀሪውን አንድ ሦስተኛ ለድሆች በማካፈል አጋርነታቸውንና እስላማዊ ፍቅራቸውን ይገልጻሉ።
በአካል ደክሞ በመንፈስ ታድሶ የሚመለስበት ሐጅ የትዕግስት፣ የትሕትናና የአንድነት ትምህርት ቤት ነው። አላህ (ሱ.ወ) ለሁላችንም ይህንን የአላህን ምሕረትና በረከት የምንቀበልበትን ልዩ የሕይወት አጋጣሚ ይወፍቀን።
በኢቲሃድ አብራር(ebc)
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #hajj #makkah #eidaladha #islam #muslimummah #faith

ከግማሽ ክፍለ ዘመን ( ከ 50 ዓመታት ) በላይ በታማኝነት ያገለገሉት መልአከ ገነት ቆሞስ አባ ተስፋ ማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
#rthiopia | በቦሬ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንደ ጽኑ ዋርካ በመሆን ለሃምሳ ዓመታት ያህል ያለመታከትና በታላቅ ፍቅር ሕዝበ ክርስቲያንን ሲያገለግሉ የኖሩት ታላቁ አባት መልአከ ገነት ቆሞስ አባ ተስፋ ማርያም ሕይወታቸው አልፏል።
አባታችን ለምዕመናን የእምነት ምሰሶ እና የትሕትና ትልቅ አርአያ ነበሩ።
በቅዱስ ሥፍራው ያሳለፏቸው ረጅም ዘመናት ለሥልጣን ወይም ለምድራዊ ዝና ሳይሆን ለእውነተኛ መንፈሳዊ አገልግሎት የተሰጡ ነበሩ።
ማንኛውንም ዓይነት ፈተናና የሕይወት መከራ ሳይበግራቸው እምነታቸውን ጠብቀው ሐዋርያዊ ሩጫቸውን በድል አጠናቀዋል።
አባታችን በ1977 ዓ.ም መልአከ ገነት የሚለውን የማዕረግ ስም ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ኃይማኖት በብፁዕ አቡነ በርተሎሚዎስ አቅራቢነት አግኝተዋል።
ታላቁ አባት በቀድሞው የሲዳሞ ክፍለ ሀገር ውስጥ በይርጋዓለም፣ በጀምጀም፣ በሻኪሶ፣ በነጌሌ ቦረና፣ በዲላ፣ በይርጋጨፌ፣ በአለታ ወንዶ፣ በቦሬ ቅድስት ማርያም እና በይርባ ሙዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሳይቀሩ ቅዱስ ወንጌልን በመስበክና የሰንበት ትምህርት ቤቶችን በማደራጀት ከልጅነት እስከ እውቀት የደከሙ ታላቅ ሐዋርያ ነበሩ።
ለቤተ ክርስቲያን ካበረከቷቸውና ሁልጊዜም በታሪክ ከሚታወሱት ተግባሮቻቸው መካከል
አንደኛው ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ያሳዩት ጽናትና ታማኝነት ሲሆን፣ ቅዱስ ስፍራውን ሳይለቁ በቅድስና መኖር የሚቻለው በእግዚአብሔር ጸጋ መሆኑን በተግባር አሳይተዋል።
ሁለተኛው ዕድሜያቸው ቢገፋም መንፈሳቸው እየታደሰ ለምዕመናን መጽናናትና ለአገልግሎት ራሳቸውን አሳልፈው መስጠታቸው ነው።
ሦስተኛው ደግሞ ያከናወኑት መንፈሳዊ ተጋድሎ ሁሉ ያለ ምንም ምድራዊ ጥቅም፣ በቅንነትና በንጹሕ ልብ የተመራ መሆኑ ነው።
በአሁኑ ወቅት አባታችን ከዚህ ዓለም ድካምና መከራ አርፈው ወደማያልፈው የቅዱሳን ማረፊያ ተሻግረዋል።
ምንም እንኳ የአካል መለያየታቸው፣ ያሳደገን፣ የመከረንና ያስተማረን ጣፋጭ ምክራቸውን ማጣታችን ልብን የሚነካ ቢሆንም፣ የሠሩት መልካም ሥራ ግን ሁልጊዜም ሕያው ሆኖ ይኖራል።
ያገለገሏት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንና ሕዝበ ክርስቲያኑ የአባታችንን ጸሎትና በረከት እንዲያገኙ እየተመኘን፣ ለእናት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን፣ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለመላው የቦሬ ከተማና የገጠር ሕዝብ መጽናናትን እንመኛለን።
#church #ethiopianorthodox #christianity #memorial #bore #sidamo #orthodox #faith #clergy #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

6 months ago
#የልህቀትና #የትሕትና ##ተምሳሌት# #ዶክተር #ዋቆ #ገዳ !
#ethiopia | በዓል ማለት ለብዙዎቻችን ከቤተሰብ ጋር መሰብሰብ ፣ በሞቀው ማዕድ ዙሪያ መሳቅና መጫወት ማለት ነው ።
እንዲያውም አንድ የቢሮ ሰራተኛ እንኳን ቀኑን ከቤቱ ውጪ ለማሳለፍ በማይፈቅድበት ፣ ትልቁ የፋሲካ ዕለት ነገር ግን ለየት ያሉ መሪዎች "ቤተሰብ" የሚለውን ትርጓሜ ከገዛ ቤታቸው አጥር አሻግረው ያዩታል ።
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ አንድ ታላቅ የታሪክ ምዕራፍ ተፅፏል ።
የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዴንት ዶክተር ዋቆ ገዳ ፣ የፋሲካን ዕለት ከገዛ ቤተሰባቸው ጋር ከማሳለፍ ይልቅ ፣ "ቤተሰቦቼ ናቸው" የሚሏቸውን ተማሪዎቻቸውን በማሰብ በዩኒቨርስቲው ቅጥር ግቢ ተገኝተው በዓሉን አብረው አሳልፈዋል ።
ይህ ተግባር እንዲሁ በቀላሉ የመገኘት ጉዳይ ፤ ሳይሆን የእውነተኛ የመሪነት መገለጫ ፣ አመራር ከቢሮ ወንበር በላይ መሆኑን ያሳየ ፤ የአባትነት ፍቅር ፣ ተማሪዎቹ ከቤተሰቦቻቸው ርቀው ባሉበት ወቅት ባይተዋርነት እንዳይሰማቸው ያደረገ ፤ የትሕትና ልክ ፣ ከፍተኛ የኃላፊነት ደረጃ ላይ ሆኖ ራስን ዝቅ አድርጎ ከተማሪዎች ጋር መሳተፍ ለሌሎች አመራሮችም ትልቅ ትምህርት ነው ።
ዶክተር ዋቆ ገዳ ፣ ተማሪዎችን እንደ ወንድም ፣ እንደ እህትና እንደ ልጅ ተመልክቶ በበዓል ዕለት አብሮ በመሆን የመጀመሪያው ከፍተኛ አመራርና ፕሬዚዴንት በመሆን በታሪክ መዝገብ ላይ ስማቸውን በወርቅ ቀለም ፅፈዋል ።
ለዚህ ድንቅ መሪና ፕሬዚዴንት ፣ ለዚህ ትሁት አገልጋይና ለዚህ የለውጥ ሰው ያለንን ከፍ ያለ አክብሮትና ምስጋና እንገልጻለን ‼️
ኢትዮጵያ እንደ ዶክተር ዋቆ ያሉ ፣ የሕዝባቸውን የልብ ትርታ የሚያዳምጡ መሪዎች ያስፈልጓታል ።
ክብር ለሚገባቸው ክብር እንስጥ! 👏🙌
ጌታቸው ባይባ ሚዛን አማን !
#mizantepiuniversity #leadership #inspiration #drwakogeda #ethiopia #serviceaboveself

በዓለሙ የተጠላውን ነገር ወደ ቤተክርስቲያን?
“አንተ ግን ምጽዋት ስታደርግ ምጽዋትህ በስውር እንዲሆን ቀኝህ የሚሰራውን ግራህ አይወቅ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።”
( ማቴዎስ 6፥3-4 )
ምጽዋትን በካሜራ እያሳዩ የመስጠት ልምድ ከቅዱስ ወንጌል መሠረታዊ መመሪያ ጋር በእጅጉ የሚጋጭ ነው።
በተለይም የቤተክርስቲያን አባቶችና አገልጋዮች የክርስቶስን ትሕትናና ትእዛዝ ለሕዝቡ በተግባር ማሳየት ሲገባቸው ድርጊቱ ለታይታ የቀረበ "መንፈሳዊ ትርኢት" መስሎ መታየቱ እጅግ ያሳዝናል።
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአንቀጸ ብፁዓን ትምህርቱ ላይ “ቀኝህ የሚሠራውን ግራህ አይወቅ” (ማቴ. 6፥3) በማለት ምጽዋት በፍጹም ምስጢራዊነት ሊከናወን እንደሚገባ አዝዟል።
ዓላማውም ሰጪው ክብሩን ከእግዚአብሔር እንጂ ከሰው እንዳይፈልግ ነው።
ካሜራ ፊት ቆሞ መመጽወት ግን የሰማያዊውን ዋጋ በምድራዊ ጭብጨባ መለወጥ ነው
ምጽዋት የሚቀበሉ ወገኖች በችግራቸው ምክንያት እርዳታ የሚሹ እንጂ ለሌላው ሰው የዝና መወጣጫ ሊሆኑ አይገባም። የሰውን ልጅ ችግር ለፎቶግራፍና ለቪዲዮ ማድመቂያ መጠቀም የተቀባዩን ሰብአዊ ክብር ይነካል ተቀባዩ በካሜራ ፊት እንዲሸማቀቅ ያደርጋል ርኅራኄን ወደ ሕዝብ ግንኙነት (PR) ሥራ ይለውጠዋል።
ቤተክርስቲያን የድሆች መጠጊያና የትሕትና መገኛ ናት እንዲህ ያሉ ድርጊቶች ግን ቤተክርስቲያን እንደ ማንኛውም ዓለማዊ ግብረ-ሰናይ ድርጅት ለታይታ ትሠራለች የሚል የተሳሳተ ትችት እንዲሰነዘርባት በር ይከፍታሉ።
በዓለሙ ዘንድ የተጠላውን "ራስን የማስታወቅ" (Self-promotion) አባዜ ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን ማምጣት መንፈሳዊነቱን ያጎድለዋል።
እውነተኛ ምጽዋት የሚለካው በገንዘቡ ብዛት ወይም በፎቶው ጥራት ሳይሆን በልቡና ቅንነት ነው። በስውር የሚሰጥ እጅ በእግዚአብሔር ዘንድ የተባረከ ነው።
አገልጋዮች አርአያነታቸው በትሕትና ሊሆን ይገባል ምእመናንም ቢሆኑ ሰብአዊነትንና ወንጌላዊ ሥርዓትን በጠበቀ መልኩ በስውር መርዳትን ልምድ ሊያደርጉ ይገባል።
መታየት ለሚፈልጉ ሹመትና ክብር ይበቃቸዋል በስውር ለሚሠሩ ግን የእግዚአብሔር መንግሥት ትጠብቃቸዋለች።

የጸሎተ ሐሙስ በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ተከበረ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የሕጽበተ እግርና የጸሎተ ሐሙስ በዓልን በፒያሳ በሚገኘው የልደታ ማርያም ካቴድራል በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች አክብራ ውላለች።
በዚህ ታላቅ መንፈሳዊ መርሐ ግብር ላይ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ ተገኝተው የሕጽበተ እግር ሥርዓቱን መርተዋል።
ብፁዕነታቸው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ እግር በማጠብ ያሳየውን የትሕትና እና የአገልግሎት ምሳሌነት በማሰብ የምእመናንን እግር አጥበዋል።
በዕለቱ በተከናወነው የቅዳሴ ጸሎትና ልዩ ልዩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች ላይ በርካታ ምእመናን የተገኙ ሲሆን፣ የክርስቶስን ሕማማትና የመጨረሻውን የእራት ግብዣ የሚያዘክሩ ጸሎቶችም በጋራ ቀርበዋል።
ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ ለምእመናኑ ባስተላለፉት መልእክት የጸሎተ ሐሙስን መንፈሳዊ ትርጉምና የእርስ በእርስ መዋደድን አስፈላጊነት አጽንኦት ሰጥተው አብራርተዋል።
ጌትነት ተመስገን
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
📷 EBC

ጸሎተ ሐሙስ
የትሕትናና የአዲስ ኪዳን ብስራት
ዛሬ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ "ጸሎተ ሐሙስ" ወይም "ሕጽበተ እግር" ተብሎ የሚታሰበው ታላቅ ዕለት ነው። ይህ ቀን ስድስት የተለያዩ መጠሪያዎችና ጥልቅ ትርጉሞች አሉት፦
ጸሎተ ሐሙስ
ጌታ በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ የጸለየበት በመሆኑ።
ሕጽበተ እግር
የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠብ ትሕትናን ያስተማረበት።
ምሴተ ሐሙስ
የጌታ እራት ወይም ቅዱስ ቁርባን የተመሰረተበት።
የነጻነት ሐሙስ
የሰው ልጅ ከኃጢአት ባርነት ነጻ መውጣቱ የታወጀበት።
የአዲስ ኪዳን ሐሙስ
የጥላው (የብሉይ ኪዳን) አልፎ የእውነቱ (የአዲስ ኪዳን) መሥዋዕት የተጀመረበት።
የአይሁድ ፋሲካ
አይሁድ የመሻገሪያ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ዕለት።
"እኔ ጌታና መምህር ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ፣ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባችኋል።" (ዮሐ 13:14)
#getu #holythursday #maundythursday #humility #ethiopianorthodox #passionweek #lastsupper #newcovenant #ሕማማት #ጸሎተሐሙስ #ሕጽበተእግር #ትሕትና #ጌጡተመስገን #getutemesgen

7 months ago
የከተማው መናኝ፦ የመምህር ዘላለም ወንድሙ የምድር ስንብትና የክብር ጉዞ
👉ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከእውነተኛ ጠበቃዎቿ መሀል አንዱን አጥታለች!!
ከወንጌል ውጭ ስለ ግል ታሪኩ ምንም እንዲነገር የማይፈልገው መምህር በመጨረሻም በስጋ እረፍቱ በኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ ዘንድ ስለ እሱ ነው የሚያወራው።
ፊደል ፖስት ይሄን ፅሁፍ ለማዘጋጀት የግል ህይወቱን በተመለከተ የቅርብ ወዳጆቹ ጋር ደውሎ ሲጠይቅ "ዘላለም እኮ ወንጌል ሰባኪ ሆኜ የግል ህይወቴን መንገር ወንጌልን ክብር ማሳጣት ነው ስለሚል ስለ ግል ህይወቱ አናውቅም" የሚል መልስ ነው በአብዛኛው ያገኘው።
በአዲስ አበባ ጎዳናዎችና በታላላቅ ደብራት ግቢ ውስጥ ሲያድግ፣ ልቡን ለወንጌል የሰጠው ገና በጠዋቱ ነበር። እድገቱ የትሕትናና የጽናት ተምሳሌት ሲሆን፣ በተግባረ ዕድ በቴክኒክ ሙያ ሰልጥኖ በአውራ ጎዳና ባለሥልጣን ውስጥ ሲያገለግልም፣ የዕለት እንጀራውን በላቡ እየፈለገ ለቤተክርስቲያኑ ግን በነጻ የሚገዛ ድንቅ ወጣት ሆኖ ተገኘ።
ይህ በሥራና በጸሎት የታጀበ የልጅነት መሠረት ነው ዛሬ የምናየውን ታላቅ መምህር የፈጠረው።
ከ30 ዓመታት በፊት በአዲስ አበባ አድማስ ላይ ድምፁ መሰማት ሲጀምር፣ መመሪያው የነበረው የቅዱስ ጳውሎስ ቃል ነበር፦ "ከውሾች ተጠበቁ፤ ከክፉዎችም ሠራተኞች ተጠበቁ" (ፊልጵ. 3:2 ይህ ድምፅ ለሦስት አሥርተ ዓመታት ሳይከስም፣ ለሥልጣን ሳይላላጥና ለገንዘብ ሳይሸጥ ቆይቶ ዛሬ በዝምታ ተዋጠ።
ባጋጠመው ድንገተኛ ሕመም ከዚህ ዓለም በሥጋ መለየቱ፣ በቅዱስ ፓትርያርኩ አቡነ ማትያስ አንደበት "ታላቅ ድንጋጤ" ተብሎ ተገልጿል። ይህ ድንጋጤ የመነጨው መምህሩ ለሦስት አሥርተ ዓመታት የኖረበት የቅድስና ሕይወት፣ ያሳየው ትሕትና እና ያፈራው መንፈሳዊ ፍሬ በብዙዎች ልብ ውስጥ የገነባው ፍቅር በመኖሩ ነው።
እርሱ በቃላት የሚደረድር ሰባኪ ሳይሆን፣ በሕይወቱ የሚሰብክ ሐዋርያ በመሆኑ፣ ሕልፈቱ የቃላት ድርቅ ሳይሆን የብርሃን መጥፋት ሆኖ ተሰምቷል።
ከሃያ ዓመታት በፊት በአዲስ አበባ በአንድ ደብር ላይ ምዕመናን እርሱን ፍለጋ ቤተክርስቲያኑን ጥለው ሊወጡ ሲሉ፣ በተተኪው መምህር እግር ሥር ተቀምጦ ማዳመጡና በኋላም "ወንጌልን ነው ወይስ ሰውን የምትከተሉት?" ብሎ መገሰጹ፣ ዛሬ ላለንበት ለብዚ ሰው ተከታይ ሰው ትልቅ ትምህርት ነው።
መምህሩ ራሱን ዝቅ አድርጎ ክርስቶስን ከፍ ያደረገ፣ ለስሙ ዝና ሳይሆን ለነፍሳት ድነት የቆመ እውነተኛ የቤተክርስቲያን ጠበቃ ነበር። ይህ የትሕትናው መጀመሪያ እንጂ መጨረሻ አልነበረም፤ ሕይወቱ በሙሉ በዝምታና በሥራ የታጀበ ድንቅ ጉዞ ነበር።
መምህር ዘላለም "የከተማው መናኝ" የሚል ስያሜ የተሰጠው ያለ ምክንያት አይደለም። በአዲስ አበባ ግርግርና ጩኸት ውስጥ እየኖረ፣ ልቡ ግን ከምድራዊ ምቾት የተለየ ነበር። እርሱ ለሥልጣን ሳይላላጥ፣ ለገንዘብ ሳይሸጥና ለጊዜያዊ ጥቅሞች ሳይንበረከክ ለሦስት አሥርተ ዓመታት እንደ ጽኑ ዓለት ቆሟል።
እንደ ቅዱስ ጳውሎስ "ከውሾችና ከክፉዎች ሠራተኞች ተጠበቁ" እያለ ሲያስጠነቅቅ፣ ራሱ ከዓለማዊ ረክስና የራቀ ንጹሕ ሕይወት ይመራ ነበር። በከተማው መሃል ሆኖ በዋልድባና በደብረ ሊባኖስ እንደሚኖሩ መናንያን ራሱን ለእግዚአብሔር የቀደሰ፣ ለጽድቅ ናፋቂዎች ደግሞ የጽናታቸው ምንጭ የነበረ እንቁ አገልጋይ ነበር።
በማህበራዊ ሚዲያ ግን አማኙ ቀኝ እጁን የተቆረጠበት ያህል ተሰምቶታል። "ሞት እኛን አያስፈራራንም ። ነገር ግን በመመህር በዘላለም ሞት ተበቀለን " የሚሉ ድምፆች አሁን ድረስ ያስተጋባሉ።
ከአባቶች ስር ወንጌል የተማረው መምህር ዘላለም በሃምሳዎቹ እድሜ መጨረሻ ላይ ቢገኝም፣ በምድራዊ ሕይወት ሚስት አላገባም፣ ልጅም አልወለደም።
ለጠየቁት ሁሉ የሚሰጠው መልስ አንድ ነበር፦ "ትዳሬ ወንጌሌ ነው!" እርሱ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ "ያላገባው ጌታን እንዴት ደስ እንደሚያሰኘው የጌታን ነገር ያስባል" (1ኛ ቆሮ. 7:32) የሚለውን ቃል በተግባር የኖረ ምስክር ነበር።
ካህናት እና ምዕመናን በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል እንደ በግ ሲታረዱ ይህ መምህር ድምፅ ሆኗል። ግፍንም እያለቀሰ ማንንም ሳይፈራ በጠንካራ ድምፅ ተቃዉሟል።
ከአቡነ ጳውሎስ ጀምሮ አስከ አሁን ድረስ በቤተክርስቲያን ላይ ብልሹ አሰራር ሲያይ ካህናት ፣ጳጳሳት ፣ቄስ ፣ዳቆን ፣ዘማሪ... ሳይል ፊት ለፊት "የበግ ለምድ ለብሳቹ በተኩላ ስጋ አትምጡ! በማለት ወቀሳ እና ትችት አቅርቧል። የታሰረበትም ጊዜያቶች ነበሩ።
መንፋሳዊ መፅሀፍት ማንበብ ለልክ በላይ የሚወደው ሰው የቤተክርስቲያን ስታለቅስ ከልብ የሚያለቅስ ሰው ነበር።
ከልጅነቱ ጀምሮ ለዓለማዊ ግርግር ግድ የሌለው፣ ይልቁንም በቅዱሳት መጻሕፍትና በዜማ መሣሪያዎች የታጀበ መንፈሳዊ ጥም የነበረው ሕፃን ነበር።
ዛሬ ማኅበራዊ ሚዲያው በእርሱ ፎቶዎች ተጥለቅልቋል። "ደፋር ነበር!" "ማሽሞንሞን አያውቅም!" "ጊዜና ሀብት ለእርሱ ቆሻሻ ነበሩ!" የሚሉ ምስክሮች ከዳር እስከ ዳር እየሰሙ ነው። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ምዕመናን በመምህሩ ዕረፍት ልባቸው ተሰብሯል። ሁሉም በየፊናው ያደረገለትን መልካም ነገር እያነሳ ይናፍቀዋል።
ዛሬ ዕድሜያቸው አርባ የተሻገረ ከዛም በላይ እና በታች ያሉ አማኞች ከልጅነታቸው ጀምሮ የሚያውቁት መምህር በስጋ መለየቱ አሳዝኗቸዋል።
ወንጌልን ማስተማር "ሀ "ብሎ የጀመረባቸው ቅዱስ እስጢፋኖስ እና መርካቶ ያለው ተክሃይማኖት ቤተክርስቲያን አካባቢ ነዋሪ አማኞች አዝነዋል።
የአማኑኤል ፣ገነት ፅጌ መናገሻ ቅዱስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ወልደ ነገድጓድ ቅዱስ ዩሃንስ ፣ ቅዱስ አማኑኤል፣ ቅዱስ ሩፋኤል ፣ጎላ እና አዲስ ሚካኤል ፣ ቅዱስ ኡራኤል ፣ ቅድስት ልደታ ማሪያም... ቤተክርስቲያን አምለኮ የሚፈፅሙ አማኞች... የወንጌል መምህራችን... በማለት ሀዘናቸውን ገልፀዋል።
እርሱ በግሸን ደብረ ከርቤ ዓመታዊ በዓል ላይ ሕዝቡን ሲመግብ የነበረው መንፈሳዊ ቃል፣ ዛሬ በዝምታ ተተክቷል። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ምዕመናን በመምህሩ ዕረፍት ልባቸው ተሰብሯል። ሁሉም በየፊናው ያደረገለትን መልካም ነገር እያነሳ ይናፍቀዋል።
ለስብከት አገልግሎት ክፍያ መቀበልን አጥብቆ ይቃወም ነበር። ይልቁንም ከመንግሥት ደመወዙ ኋላም ከሚተዳደርበት የግል ንግድ ስራ ገንዘብቀንሶ ለችግረኞች የሚሰጥ እውነተኛ ደግ ሰው ነበር።
በውጭ እና በገጠር ላሉ ለምዕመናን እንዲዳረስ ተብሎ ሲያስተምር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቪዲዮ መቀረፅ ጀመረ እንጂ ሲያስተምር ቪዲዮ የሚቀርፅ ሰው ካለ ያስቆም ነበር።
መምህር ዘላለም "ጎጠኝነት" ሲነሳ ፊቱ ይለዋወጣል። ክርስቶስ በአንድነቱ የሰበሰባትን ቤተክርስቲያን በዘርና በጎሳ የሚከፋፍሉትን እንደ መጽሐፍ ቅዱሱ ነቢይ እንደ ኤልያስ ይገስጻቸዋል። "ሌብነትና ግፍ" ደግሞ በእርሱ ዘንድ ፍጹም ፅዩፍ ነበሩ። በቤተክርስቲያን መድረክ ላይ ቆሞ ባለሥልጣን ሳይፈራ፣ ለሹመት ሳይደለል፣ "ጽድቅን ተከተሉ" እያለ ይጮኻል።
እርሱ ስለ ትሕትና ሲሰብክ ዝቅ ብሎ ነው፤ ስለ መስጠት ሲሰብክ ባዶ እጁን ሆኖ ነው። እዩኝ እዩኝ የማይለው፣ ሕፃን አዋቂ ሳይል ለሁሉ ትሁት የሆነ እንቁ የኦርቶዶክስ መምህር በመሆኑ በሁሉም ዘንድ ይወደዳል።

Sponsored by
Surafel
9 months ago
በዓለ ጥምቀት
“ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር ዘያአትት ወያሴስል ኃጢአተ ዓለም፦እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ።” (ዮሐ. 1፡29)
#ethiopia | ጌታችን፣ አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዘመነ ሥጋዌው ካከናወናቸው ታላላቅ የትሕትና ተግባራት አንዱ በጥምቀቱ የተገለጠው ነው ። እርሱ መጠመቅ የሚያስፈልገው ሆኖ ሳይሆን የእኛን ጥምቀት ለመባረክና ትሕትናን ሊያስተምረን ወደ ባሕረ ዮርዳኖስ ገሰገሰ፤ ከባሪያው እጅም ተጠመቀ፤ በዚህም ትሕትና ማለት የበላይን ሳይሆን የበታችን ማክበር መሆኑን አስተማረን ። ኃጢአት ወደዚህ ዓለም የገባው በትዕቢት ነበር፤ ጌታችን በትሕትና የጽድቅን መንገድ ከፈተልን ።
ትዕቢት ከገነት ጀምሮ የሰው ልጆች የመውደቂያ ገደል ሁኖ ነበር፤ ቃየን ወንድሙ አቤልን በቅናት ተነሣሥቶ ቢገድለውም የሚፈርድ አምላክን መዘንጋቱ ግን ትዕቢት ነበር፤ ጥቅመ ሰናዖር በጅምር የቀረው በትዕቢት ምክንያት ነበር ። የትኛውም ከፍታ ወደ ዝቅታ የሚለወጠው በትዕቢት ሲሆን ታላላቅ ሥልጣኔዎች ዕድሜ የሚኖራቸው በትሕትና ነው፤ ካልሆነ ግን የሰው ልጆች ስጋት ለመሆን ወዲያው ወደ አውዳሚነት ይቀየራሉ ። ሰዎችን ለመርዳት የመጀመሪያው አቅም ትሕትና ነው ። ትሕትና:- መቆም ፣ ማዳመጥ ፣ ዝቅ ብሎ የሌሎችን ሕመም ማየት ፣ የራስን መውደቂያ በማሰብ ድጋፍ ማድረግ ነው ። ሙሴ በበረሃ የቀረው ትዕቢት የሚመስል ነገር በመናገሩ ነው ። ራስን ከእግዚአብሔር ጋር ማነጻጸር፣ በጸጋ የተቀበሉትን በድካም እንዳገኙ አድርጎ መቍጠር፣ ‹‹እንዴት ሌሎች ይህን ያጣሉ?›› ብሎ መመጻደቅ፣ ተቀብሎ ለመስጠት መሰሰትና የመሳሰሉት በትዕቢት መደብ ላይ ሲገኙ ከሁሉም በላይ አምልኮተ እግዚአብሔርን ማጓደል፣ የፈጣሪን ክብር ለማይገባው መስጠት ደግሞ የትዕቢት አውራ ነው ።
ንጉሥ ዖዝያን ሀብተ መንግሥት ተሰጥቶት ሳለ በትዕቢት ምክንያት ‹‹ሀብተ ክህነቱንስ ማን ይከለክለኛል›› በማለቱና ዕጣን ሊያጥን ወደ መቅደስ በመግባቱ በለምፅ ተቀጣ ። እግዚአብሔር ከብርቱ ንጉሥ ይልቅ ደካማውን ካህን ይወዳል ። ደግሞም ክብራችን ያለው በተሰጠን በመገኘት እንጂ ያልተሰጠንን መፈለግ ትዕቢት ነው ። ክብረ ክህነት በተቃለለበት፣ ካህናት በልጆቻቸው በሚሰደቡበት፣ መስቀልን ቀምቶ አባቶችን ለማባረር በሚመከርበት በዚህ ዘመን የዖዝያን ተግሣጽ ትዝ ሊለን ይገባል ።
ጌታችን ዮሐንስን መጥተህ አጥምቀኝ ቢል ይቻለዋል፤ ነገር ግን በቀጣይ የሚነሡ ነገሥታት መጥታችሁ አጥምቁን ብለው ካህናትን እንዳያዝዙ መሠረት ጣለልን ። የንጉሥ ልጅ ልዑልና ልዕልትም ወደቤተ ክርስቲያን ሄደው ይጠመቃሉና ጥምቀት የትሕትና ትምህርት ቤት ነው ። ትዕቢት መራራቅ ፣ በርቀት መተኮስ ፣ በግምትና በሐሰት የሰውን ስምና ክብር ማርከስ ነው። ትሕትና ግን መሄድ ፣ ቀርቦ ማገዝ ፣ ለወንድምም የስሙ ጠባቂ መሆን ነው ።
ዓለማችን በልዩ ልዩ ጦርነቶች እየታወከች፤ ኃያላን ሲጋፉም ደካማ አገራት እየደቀቁ እንደሆነ እናውቃለን፤ ሰዎች ከምድር ጨርሰው ጨረቃ ላይ ውድድር ከገቡ አንድ ክፍለ ዘመን ሊያስቆጥር ቢቃረብም የጦር መሣሪያው ሳይንስ በየጊዜው እየረቀቀ ነው፤ ውጤቱ ግን ሰው ራሱን የሚያወድምበት ዘመን መቃረቡን የሚናገር ነው ። ይህች ዓለም በትዕቢት ምክንያት ክፉኛ ተጨንቃ ምጥ እንደ ያዛት ሴት እየጮኸች ሲሆን እግዚአብሔር አምላክ መሪዎችን አባት ፣ ቤተ ክርስቲያንን እናት አድርጎ ለዚህች ዓለም ሰጥቷልና ለሰዎች ማረፍ ተግተን መሥራት ይጠበቅብናል ።
ጌታችን ለመጠመቅ ወደ ዮሐንስ በሄደ ጊዜ ኃጢአታቸውን እየተናዘዙ የሚጠመቁ ሰዎች ረጅም ሰልፍ ይዘው ስለነበር ‹‹እኔ ጻድቅ ነኝ ልቅደም›› አላለም፤ ደግሞም ‹‹እንዴት በረከሱ መካከል እገኛለሁ?›› አላለም፤ ይልቁንም አዲሱ ሊቀ ካህናት ወደ ብሉይ ኪዳኑ ካህን ጋር እስከሚደርስ ወረፋውን በትዕግሥት ጠበቀ ። ከዚህ ታሪክ ዓለም ብዙ መማር ይችላል፤ እውነተኛ ቅድስና ያለው ሰው ሌላው እንዲቀደስለት ባልንጀራ ለማብዛት ይጥራል እንጂ እንደ ርኵስ አይጸየፍም ። ይልቁንም ወገኖቹን ከእሳት ነጥቆ በማውጣት ለርስተ መንግሥተ ሰማያት ያበቃል።
ሰዎችን ለመርዳት በሰዎች መካከል መሆን አስፈላጊ ነው ። ጌታችን ኃጢአታቸውን ተሸክሞ መሥዋዕት የሚሆንላቸውን ኃጢአተኞች በመካከላቸው ሆኖ የልባቸውን ትርታ፣ የእርስ በርስ የፍርሃት ድምፃቸውን ይሰማ ነበር ። ወደ እውነተኛ ንስሐ ብትመጡ በመካከላችሁ እሆናለሁ ሲለን ይህን አደረገ ። የታደለው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስም፡- በተመለከተው ጊዜ “እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ” በማለት አስተዋወቀው (ዮሐ. 1፡29) ። ዮሐንስ ስርየትን ያውጅ የነበረው የጥንቱን በግና ፍየል በመሠዋት ሳይሆን እየቀረበ ያለውን የእግዚአብሔር በግ በማሰብ ነበር ። በብሉይ ኪዳን ሰዎች በሚሊየን የሚቆጠሩ በጎችን ቢያቀርቡም መፍትሔ አልተገኘም፤ አንዱ በግ ክርስቶስ ግን ከኃጢአታችን አዳነን ። የሰዎች መላ ችግርን ያዳፍን ይሆናል፣ ችግርን የሚያስወግደው እግዚአብሔር የሚሰጠን መፍትሔ ነው ። በየትኛውም የአገልግሎት መስክ ላይ ሰዎች እንደ አመጣጣቸው መስተናገድ አለባቸው፤ በዕድሜ የሚበልጡንን የምናከብረው በሰውነት ብቻ ሳይሆን በመኖር ስለሚቀድሙን ጭምር ነው ። የሚያየውን አባቱን ያላከበረ የማያየውን አምላክ አከብራለሁ ቢል ይዋሻልና የሚከተሉት የሚቀድሙትን ካላከበሩ እውነተኛ አምልኮ ሊኖር አይችልም ።
መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ የሰዎችን ኃጢአት ሲሰማ እየዋለ ግለሰቦች የከበዳቸውን ሸክም ለእርሱ ያሸክሙት ስለነበር በአገልግሎት ብዛት ደክሟልና ጌታችንን ባየ ጊዜ ማረፍንና በጌታ እጅ የሚጠመቅ የመጨረሻው ተጠማቂ ለመሆን ተመኘ ። ጌታችን ግን ዮርዳኖስ የትሕትና ትምህርት ቤት ስለሆነች ከለከለው ። የጌቶች ጌታ ሲሆን በባሪያ እጅ፣ አምላክ ሲሆን በፍጡሩ እጅ ተጠመቀ። የመስቀሉን መልክ አንድም ቀን ትቶት አያውቅምና በዮርዳኖስ ቅዱስ ዮሐንስ በቀኙ ፣ በደለኞች ተነሣሕያን ደግሞ በግራው ይታያሉ፤ እርሱም በመካከላቸው ሆኖ ወደ ራሱ ይስባቸዋል ። በደሉን ላመነ በእግዚአብሔር ዘንድ የበደል እስራት የሚቆረጥበት ምሕረት አለና ትልቁ በደል ንስሐ አለመግባት ነው ።
የናዝሬት ነዋሪዎች አምላክነቱን ቢሰውርባቸው አናጢ አድርገው ስለውት ነበር፤ በዮርዳኖስ ግን መሥዋዕት አቅራቢው ሊቀ ካህናት፣ የአለምን ኃጢአት የሚያስወግደው የእግዚአብሔር በግ፣ ተወካፌ መሥዋዕትም እርሱ መሆኑ ተገለጠ ። በናዝሬት በእናቱ ቤት ቢሸሸግ ዕለተ ሞቱ ዘገየ፣ በባሕረ ዮርዳኖስ ግን በዮሐንስ ስብከት፤ እግዚአብሔር አብ ከሰማያት ሆኖ ‹‹የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት›› ብሎ ባሰማው ምስክርነት፤ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል በራሱ ላይ ከታየ በኋላ የቀራንዮ ጉዞው ፈጠነ ። በዚህም በተገለጥን ቍጥር መሥዋዕትነት ቅርብ መሆኑን አስተማረን!
ጥምቀት ጅምሩም ወራጁም የድሀ ሀብት ተደርጎ በሚታሰበው ውኃ የሚከናወን ነው ። ጥምቀት ትሕትና ነውና ዝቅ ብለው በሚቀዱት ውኃ መከናወን አለበት ። ሁሉም ሊያገኘው በሚችል ውኃ ምሥጢረ ጥምቀት መመሥረቱም ማንም ሰው በሰበብ እንዳይቀር ለማድረግ ነው። ባለቤቱ በቃልም በተግባርም የቀደሰውንና ያዘዘውን ጥምቀት መናቅ ከድኅነት መጉደልን ያስከትላል ። ዛሬ ቤተ ክርስቲያን ታቦተ ምሥዋዕን አክብራ ወደ ባሕረ ጥምቀት የምትወርደው መሠዊያውና መሥዋዕቱ አይለያዩምና የእግዚአብሔር በግ የሆነው ክርስቶስን ለዓለም ለመስበክ ነው። ስለሆነም በጉ ኃጢአትን ሊያስወግድ መጥቷልና የጥምቀት በዓላችን ምንም ዓይነት የኃጢአት ነቁጥ የማይታይበት፤ ዘፈንና ሥጋዊ መሻት ሁሉ የሚወገድበት በዓል ሊሆን ይገባል ። ኃጢአተኞች ኃጢአተኛን ይገድላሉ፣ በዚህም እግዚአብሔር እንደ እነርሱ መስሎአቸው አበጀህ የሚል ሽልማትን ከአምላክ በመጠበቅ ይስታሉ፤ ጻድቁ ግን ኃጢአትን ይገድላል፤ ለኃጢአተኛውም ይጸልያል፤ በበደል ሸፋኝነትም አምላኩን ይመስላል ።
ማጠቃለያ
በዓለ ጥምቀት በመላው ዓለም በድምቀት የሚከበር ቢሆንም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ግን ዓበይት ተብለው ከተሰየሙት በዓላተ እግዚእ መካከል በመቶ ሚሊየን የሚቆጠሩ አገልጋዮችና ምእመናን በአደባባይ ወጥተው የሚዘክሩት ታላቅ በዓል ነው ። የ2018 ዓ.ም. የጥምቀት በዓልን ስናከብርም ትሕትናን ገንዘብ አድርገን፤ ክህደትን በሃይማኖት፣ ጦርነትን በሰላም፣ መርዶን በብሥራት፣ ኀዘንን በደስታ ለመለወጥ ጠንክረን መሥራት ይጠበቅብናል የሚለው የዘመኑ የቤተ ክርስቲያናችን መልእክት ነው ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!
አሜን፡፡
መልአከ ሕይወት አባ ኃይለ ገብርኤል ነጋሽ (ቆሞስ)
የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጸሓፊ
ጥር 11 ቀን 2018 ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

Comments