2 months ago
የነፍስ ተናፋቂው ጥሪ፤ ሐጅ የሙስሊሞች የሕይወት ዘመን ታላቅ መንፈሳዊ ሕልምና የዒባዳ ማዕዘን
#ethiopia | ሐጅ... የአላህ (ሱ.ወ) ቤት ወደሆነችውና የሙዕሚኖች ልብ ዘወትር ወደምትናፍቃት ቅድስት መካ የሚደረግ፣ በአካል ለቻለና አቅም ላለው ሙስሊም ሁሉ በሕይወት ዘመን አንድ ጊዜ የመፈጸም ግዴታ ያለበት አምስተኛው የእስልምና ማዕዘን ነው።
ይህ ታላቅ ጉዞ የግል መንፈሳዊ ጥንካሬን ማደሻ ብቻ ሳይሆን፣ የታማኝነት እና የዓለም አቀፋዊ የእስልምና አንድነት ከፍተኛ መገለጫ ተደርጎ ይወሰዳል።
በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ምድራዊ ማዕረግና የሀብት ልዩነትን ሁሉ አውልቀው፣ ተመሳሳይ ነጭ ኢሕራም ለብሰው በአንድነት ሲቆሙ ፍጹም የእኩልነት እና የወንድማማችነት ትርጉም በተግባር ይገለጻል።
ይህ ሥርዓት ከዘመናት በፊት ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ያስተማሩትን መንገዶች በመከተል የሚከናወን ሲሆን፣ እያንዳንዱ ተግባር ከነቢዩ ኢብራሂምና (ረ.ወ) ከነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ታሪክ ጋር የተያያዘ ጥልቅ መንፈሳዊ ትርጉም አለው።
ጉዞው በእስልምና የጨረቃ አቆጣጠር 12ኛው ወር "ዙል-ሒጃ" ላይ የሚፈጸም ሲሆን፣ የጨረቃ አቆጣጠር ከግሪጎሪያን አቆጣጠር ጋር ሲነጻጸር በየዓመቱ ወደ 11 ቀናት ገደማ ወደ ኋላ ስለሚሽከረከር የሐጅ ወቅት በተለያዩ የአየር ንብረቶች (በበጋ፣ በክረምትና በጸደይ) ላይ እንዲያርፍ ያደርገዋል።
የዚህ ታላቅ የሐጅ ሥርዓት ማጠናቀቂያ በመላው ዓለም በታላቅ ድምቀት በሚከበረው ዒድ አል-አድሃ (የአረፋ በዓል) ላይ ይደርሳል።
አማኞች መስዋዕት በማቅረብ፣ ያረዱትን አንድ ሦስተኛ ለቤተሰቦቻቸው፣ አንድ ሦስተኛ ለጎረቤቶቻቸው እንዲሁም ቀሪውን አንድ ሦስተኛ ለድሆች በማካፈል አጋርነታቸውንና እስላማዊ ፍቅራቸውን ይገልጻሉ።
በአካል ደክሞ በመንፈስ ታድሶ የሚመለስበት ሐጅ የትዕግስት፣ የትሕትናና የአንድነት ትምህርት ቤት ነው። አላህ (ሱ.ወ) ለሁላችንም ይህንን የአላህን ምሕረትና በረከት የምንቀበልበትን ልዩ የሕይወት አጋጣሚ ይወፍቀን።
በኢቲሃድ አብራር(ebc)
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #hajj #makkah #eidaladha #islam #muslimummah #faith

Comments