25 days ago
ፈተናዎችን ያለፈው የሀላባ እግር ኳስ ለታሪክ ሰሪዎቹ የመሬትና የገንዘብ ሽልማት ተበረከተላቸው
***********************
በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ክለቡን ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ማሳደግ ለቻሉት የሀላባ ከተማ እግር ኳስ ቡድን አባላት፣ ዛሬ በሀላባ ዓለም አቀፍ ስታዲየም በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ደጋፊዎች በተገኙበት ደማቅ ሕዝባዊ አቀባበልና የሽልማት ሥነ-ሥርዓት ተከናውኗል።
በ2018 የውድድር ዘመን የከፍተኛ ሊጉ አሸናፊ በመሆን ወደ 2019 የሲቢኢ (CBE) ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊነቱን ያረጋገጠው ክለቡ፣ በዛሬው ዕለት ከዞኑ አስተዳደር ለእያንዳንዱ የቡድኑ አባል የ120 ካሬ ሜትር የመሬት ስጦታና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶለታል።
በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙህዲን ሁሴን፣ ይህ ወቅት የሀላባ ስፖርት ጮራው የፈነጠቀበት ወርቃማ ጊዜ መሆኑን ገልጸው፤ የዘመናችን ጀግንነት እንደ ሀላባ ከነማ በብዙ መሰናክሎች ውስጥ አልፎ ስኬት ማስመዝገብ መሆኑን አብራርተዋል።
በተያያዘም የሀላባ ከተማ ከንቲባና የክለቡ ፕሬዚዳንት አቶ ገመዳ መሐመድ የሀላባ እግር ኳስ የሕይወት መስዋዕትነት ጭምር የተከፈለበት ታሪካዊ ስፖርት መሆኑን አስታውሰዋል።
ለዚህም ማሳያ እንዲሆን፣ ከዚህ ቀደም ቡድኑን ለመደገፍ ወደ ድሬዳዋ ሲጓዙ በመኪና አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦችና አደጋ የደረሰባቸው ደጋፊዎች የዞኑ አስተዳደር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።
ይህ በድል የታጀበው ታሪካዊ ጉዞ እግር ኳስ ወዳዱን የሀላባ ሕዝብ ከማስደሰት ባለፈ፣ ከተማዋን የዓለም አቀፍ ስታዲየም ባለቤት ለማድረግና በሀገሪቱ እግር ኳስ ውስጥ ጠንካራ ተወዳዳሪ ቡድን ለመገንባት ለሚደረገው ጥረት ትልቅ መነቃቃት ፈጥሯል።
ሀላባ ከተማ ወደ ከፍተኛው የሊግ እርከን መመለሱ፣ በቀጣዩ ዓመት በፕሪሚየር ሊጉ ላይ አዲስና ብርቱ የፉክክር መንፈስ ይዞ እንደሚመጣ የስፖርት ቤተሰቡ በታላቅ ተስፋ እየጠበቀው ይገኛል።
በአብርሃም አድማሱ
#halabacity #ethiopianpremierleague #ethiopianfootball #victory #cbepremierleague

1 month ago
ስኬት ባንክ የሠራተኞች ቀንን አከበረ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ስኬት ባንክ “ሠራተኞቻችን የስኬታችን መሰረት ናቸው” በሚል መሪ ሃሳብ የሠራተኞች ቀንን በድምቀት አክብሯል።
በአራዳ ፓርክ በተለያዩ ዝግጅቶች በደማቅ ስነ-ስርዓት በተከበረው በዚህ በመርሐ ግብር ላይ የባንኩ የቦርድ አመራር አባላት፣ ከፍተኛ አመራሮች እና ሠራተኞች ተገኝተዋል።
ባንኩ በዘርፉ የበኩሉን አስተዋፅዖ በመወጣት ከመደበኛው የባንክ አገልግሎት በተጨማሪ የደንበኞቹን ፍላጎት ማዕከል ያደረጉ የተለያዩ የዲጂታልና ዓለም አቀፍ አገልግሎቶችን እየሰጠ መሆኑ ተገልጿል።
በተጨማሪም ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ መሆኑም ተነስቷል።
#የተከፈለበት

ፕሬዚዳንት ታዬ በኢትዮ-ኢስታንቡል ሆስፒታል ነጻ የቀዶ ህክምና ያገኙ የልብ ህሙማን ህጻናትን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በኢትዮ-ኢስታንቡል ሆስፒታል ነጻ የቀዶ ህክምና ያገኙ የልብ ህሙማን ህጻናትን ጎብኝተዋል።
የጣሊያኑ የ"ፔድሬ ፓዮ" የሕክምና ቡድን ከኢትዮ ኢስታንቡል ሆስፒታል ባለሙያዎች ጋር በመሆን በ12 ቀናት በአዲስ አበባ 58 በጅግጅጋ 16 በድምሩ ለ74 ሕፃናት የልብ ቀዶ ህክምና አገልግሎት ሰጥቷል።
"ኸርት ቱ ኸርት ችልድረን’ስ ኤይድ ፋውንዴሽን’ ካሰባሰበው የእርዳታ ገንዘብ እና ኢትዮ-ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል ባደረገው ድጋፍ ነው አገልግሎቱ የተሰጠው።
ፕሬዚዳንቱ በጉብኝታቸው ወቅት እንዳሉት፤ ሆስፒታሉ የሚያከናውነው ዘመናዊ የሕክምና አገልግሎትና የበጎ አድራጎት ሥራ በኢትዮጵያ የሕክምና ዘርፍ ወደ አዲስ ምዕራፍ መሸጋገሩን ያሳያል።
ያስተማረንን ሕዝብ ማስታወስ ትልቅ በረከት ነው ያሉት ፕሬዚዳንት ታዬ፤ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ሀገራቸውን ማገልገል እንዳለባቸው አመላክተዋል።
በሆስፒታሉ የሚሰጠው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እና ዘመናዊ ህክምና ለህክምና ወደ ውጭ ሀገር የሚደረገውን ጉዞ የማስቀረት ተስፋ እንዳለ የሚጠቁም መሆኑን ገልጸዋል።
ለህጻናቱ ነጻ የህክምና አገልግሎት የሰጠው ፔድሬ ፓዮ የህክምና ቡድን ለህፃናቱ እና ለቤተሰቦቻቸው የተስፋ ብርሃን መፈንጠቁን ገልጸው፤ አገልግሎቱ የኢትዮጵያ እና የጣሊያን ግንኙነትን ይበልጥ ለማጠናከር አስተዋጽኦ እንዳለው ጠቁመዋል።
የኢትዮ-ኢስታንቡል ሆስፒታል መስራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃን ተድላ በበኩላቸው፤ ባለፉት ሁለት ዓመታት ለ184 ሕፃናት 120 ሚሊየን ብር በሚገመት ወጪ ነፃ ሕክምና ሰጥቷል ብለዋል።
ሆስፒታሉ ውስብስብ የልብ፣ የካንሰር፣ የደም ስር የጭንቅላት የህብለሰረስና የአጥንት ቀዶ ህክምናን ጨምሮ ሌሎችም አገልግሎቶች እየሰጠ መሆኑን ገልጸዋል።
ነጻ የቀዶ ህክምና ያገኙ የልብ ህሙማን ህጻናት ቤተሰቦች ወጪ በመሸፈን ልጆቻቸውን ማሳከም ባለመቻላቸው ለዓመታት ሲሰቃዩ መቆየታቸውን አስታውሰው፤ ባገኙት ነፃ የህክምና አገልግሎት እፎይታ ማግኘታቸውን ተናግረዋል።
የህፃናት ነፃ የልብ ሕክምና አገልግሎቱ በቀጣይ ወደ ኦሮሚያ፣ አማራ፣ ትግራይ፣ ሲዳማ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ እና ሌሎች ክልሎች የሚቀጥል መሆኑ ተጠቁሟል።

5 months ago
ነይ እንሂድ‼️
#ethiopia | ብዙ አሳልፈዋል፤ የትምህርት ቤት ትውውቅ ወደ ፍቅር አድጎ በትዳር እስከመጣመር አድርሷቸዋል፤ ለአመታት ደስታና ሀዘን፥ ሳቅና ለቅሶ ተጋርተዋል፤ ሁለት ስም፥ ሁለት አካል ቢኖራቸውም አንድ ልብ ተላብሰዋል፤ በፅኑ ፍቅር ተጋምደዋል፤ ጓዳቸው ሙሉ ነው፤ በጋራ የሚመሩት የንግድ ተቋም አላቸው፤ ለሌላው ይተርፋሉ፤ ልጅ ግን የላቸውም፤ እስካሁን ፍሬያቸውን አላዩም፤ አቅፎ ለመሳም አልታደሉም፤ የቤተሰብ ጫና ተጨምሮባቸዋል፤ የዘመድ አዝማድ ግፊት በዝቶባቸዋል፤ የጓደኛና ጎረቤት ምላስ ተዘርግቶባቸዋል፤ ይህንን ሁሉ መቋቋም አቅቷቸዋል፤ ብን ብሎ መጥፋትን፥ ርቆ መኖርን ተመኝተዋል፤ እናም 'ነይ' እያለ ልብን በመሪነት ሾሞ መንገድ እንጀምር ይላታል፦
"ነይ እንድረስ ከአድማስ ወዲያ
አይ ልባችን ይምራንና
ነይ እንጥፋ እንሻገር
አላማረም የእኛ ነገር..."
ብቻውን አይሆንለትም፤ አልባሽ አጉራሹ፥ የልጅነት ፍቅሩ የህይወት አጋሩ፥ ግራ ጎኑ ቃልኪዳኑ፥ የሰማንያ ሚስቱ ምርኩዝ ብርታቱ፥ እሷ ነችና እጇን ይዞ ይህን ክፉ ቀን ራቅ ብለን እናሳልፍ ይላታል፤ የጉዞ ትጥቁ 'እምነቱ' የመንገድ ስንቁ 'ፍቅሩ' ብቻ ናቸው፤ ተስፋውን ሸክፎ ይማፀናታል፦
"ነይ እንሂድ
ፍቅር አለን የሚያነሳ
ነይ እንሂድ
እንነሳ...."
አለሜ የሚላት ሚስቱ ስለ ፍቅር ብላ ብዙ ችላለች፤ የዘመድ አዝማድና የጎረቤት ምላስ ደጋግሞ ገርፏታል፤ ማህፀነ ደረቅ ተብላለች፤ አጥንት በሚሰብሩ ቃላት በማያገባቸው በገቡ አለሜዎች የእሱ አለም እልፍ ጊዜ ታማለች፤ በልደትና ክርስትና፥ በለቅሶና ሰርግ በሽሙጥ ጦር ተወግታለች፤ ህመሟ ህመሙ ነውና ከዚህ በላይ ስቃይ ይብቃ፥ ብንሄድ ይሻላል እያላት ነው፦
"አንቺም ለኔ እንደሆንሽው እኔም ላንቺ
አለሜ አትንገላቺ
ከሚገርፈው ከውርጩ ከወረት አለም
አይ እንሂድ... እንሂድ ተይ አንታመም..."
እሱም ብዙ ደርሶበታል፤ ተዋትና ሌላ አግባ፥ ወላድ በድባብ ትሂድ የሚሉ የአንድ ልብ ሰንጣቂዎች ዘምተውበታል፤ አቋሙ ግን ፅኑ ነው፤ ጅማሬዬ እሷ ነበረች፤ ፍፃሜዬም እሷ ትሆናለች ይላቸዋል፤ የእኔ ማለዳ፥ የልቤ ሰሌዳ፥ ሀገሬ፥ ፍቅሬ፥ አለሜ ነች ብሎ ይመሰክርላታል
"እንደፈረስ ለጋሪው እንግዳ
በቤቱ ባይተዋር ተይ አንሁን እዳ
ብድርሽ ብድሬ ሀገርሽ ሀገሬ
በሬም አለ... ከበደኝ ቀንበሬ..."
በሰኔ ዝናብ እጦት እንደቆዘመ ገበሬ፥ በፀሎትና በምልጃ የደመናን ማርገዝ እንደሚለምን አርሶ አደር እነሱም ፍሬያቸውን ለብዙ ሰኔዎች ጠብቀዋል፤ በእንባ ጠይቀዋል፤ ምድራዊው ሃኪም ሁለቱም መውለድ እንደሚችሉ ነግሯቸዋል፤ የምድርና የሰማይ አምላካቸውን መለመናቸውን ቀጥለዋል፤ ሆኖም ተስፋ አስቆራጩ በዛባቸው፤ እናም ከእሱም ከእሷም ቤተሰብንና ከዘመድ አዝማዱ ጨለማዊ አመለካከት መሸሽን መርጠዋል፤ እስኪነጋ ድረስ ከአድማስ ወዲያን ለመመኘት ተገደዋል፤ ፍቅር ብቻ ያለበት ፀጥ ያለ ሰላማዊ ቦታን ናፍቀዋል
"እንደ ሰኔ ደመና እንደራቀው
እንደከፋው ገበሬ ተይ አንታመመው
እንሂድ እንሂድ ፀጥ ካለው ስፍራ
ተይ እንሁን ሰላም መኖርን ሳንፈራ...."
ነይ እንሂድ፥ ነይ እንጥፋ፥ ነይ እንሻገር፥ ነይ እንነሳ ይላታል
ሽሽቱ ሰላምን ፍለጋ ነው፤ ስደቱ መስዕዋት የተከፈለበትን ፍቅር ለማፅናት ነው፤ መንገዱ በፀጥታ ለመኖር ነው፤ መሪው ደግሞ ልብ!
ማስታወሻ፦ ( 'ነይ እንሂድ' በድምፃዊ ሮቤል ሚደቅሳ አልበም ውስጥ የሚገኝ ልብ ሰርሳሪ ሙዚቃ ነው፤ የፃፍኩት ደግሞ የማውቃቸውን ጥንዶች ታሪክ ነው፤ ሙሉ ሙዚቃው በመጀመሪያው አስተያየት መስጫ ላይ ይገኛል)
(ታምሩ ዓለሙ)

Sponsored by
Surafel
8 months ago
የከቴ ቤተሰቦች እንኳን ደስ አላችሁ
#ethiopia | ዋጋ የተከፈለበት ሸንፈትን የማይወደው የብዙሃን መግለጫ የሆነው የኛ አዲስ ከቴ እግር ኳስ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ እግር ኳስ ሊግ አንድ ማደጉ ይታወሳል።
ሰላም ሰለም እንዴት ከረማቹ የኛ አዲስ ከቴ ቤተሰቦች ቡድናችን ለ2018 ዓም ወደ ሊግ አንድ ለማድግ ወደ ጂንካ ከተማ ተጎዞ 36 ክለቦች የተካተቱበት የክልል ክለቦች ውድድር ላይ መሳተፉ ይታወሳል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ ቡድናች በውድድሩ ከላፉት ሰባት ዓመታት እንዲሁም ካሰቀመጠው ዓላማ አንፃር ከፍተኛ ውጤት ያመጣበት በተጨማሪም ወደ አንደኛ ሊግ ያደገበት እና ዓላማችን ያሳካንበት ውድድር ሆኗል።
በመሆኑም የተከበራቹ የከቴ ቤተሰቦች እንኳን ደስ አላችሁ።
እንኳን ደሰ አለን እያልን በቀጣይ ቡድናችን በሊግ አንድ ለመሳተፍ ከምንጊዜውም በበለጠ የማህበረሰቡ ድጋፍ እንደሚያሰፈልገው ከወዲሁ ለማሳሰብ እንወዳለን።
ሰለዚህ የከቴ ቤተሰቦች የመሰባሰባችን መለያ የሆነው ቡድናችን በአዲሱ የውድድር መድረክ እንዲሳተፍ ብሎም የተሻለ ውጤት እንዲያመጣ የበኩላቹን እንድታደርጉ ሰንል በአክብሮት እንጠይቃለን ።
ከዚህ ጋር በተያያዘ የኛ ከቴ በሊግ አንድ ለመሳተፍ ከዚህ ቀደም ከነበረው የውድድር ቅርፅ በተለየ ሁኔታ ከአዲስ አበበ ውጪ ጨዋታዎችን ያከናውናል። ለዚህም ከፍተኛ የገንዘብ በጀት ያሰፈልገዋል።
በመሆኑም ቡድናችን በሊጉ እንዲሳተፍ ብሉም የተሻለ ውጤት እንዲያመጣ መላው የእግር ኳስ ቤተሰብ የገንዘብ እንዲያደረጉለት መላው የኮሚቴ አባላት በአክብሮት ይጠይቃሉ።
ከሰላምታ ጋር
የተሻለ ነገር ለከቴ ይሁን!
ኮሚቴው

9 months ago
የሜሮን ጌትነት "ሌላ ዕውነት የለኝም" ታተመ
(ከዕዝራ እጅጉ)
ከ80 በላይ ግጥሞችን የያዘውና 134 ገፆች ያሉት "ሌላ ዕውነት የለኝም" የተሰኘው የሜሮን ጌትነት መፅሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው።
ሜሮን በተለያየ ጊዜ የጻፈቻቸውን ግጥሞች በአንድ ላይ አድርጋ ለሕትመት ያበቃች ሲሆን ግጥሞቹም በግላዊ ገጠመኝና ዕይታ ላይ ትኩረታቸውን ያደርጋሉ።
ለ 10 ዓመታት መኖሪያዋን ባህር ማዶ አድርጋ የነበረችው የኪነ- ጥበብ ሰው ሜሮን ጌትነት ለጥቂት ዓመታት ከጥበቡ ዓለም ራቅ ብላ መቆየቷ ይታወቃል።
ለሥነ- ግጥም ልዩ አክብሮት አለኝ የምትለው ሜሮን በአዲሱ መፅሐፏ የሚሰማትን ገልጻለች።
"ሌላ እውነት የለኝም በተለያየ ጊዜ፣ ቦታ እና ሁኔታ ውስጥ ሆኜ የፃፍኳቸው ግጥሞች ስብስብ ነው። ግላዊ ስሜቶች፣ እውነቶችና በህይወት መስመር ላይ ያስተዋልኳቸው ማህበራዊ ሁነቶች ከጫሩብኝ ሀሳቦች ተነስቼ የከተብኳቸው ናቸው ትወዷቸዋላችሁ።"ስትል ሜሮን ሀሣቧን ለተወዳጅ ሚድያ ትገልጻለች።
ሜሮን ጌትነት፣ የህይወት ታሪኳ በአማርኛ ኢንሳይክሎፒዲያ መዝገበ አእምሮ ላይ የተሰነደ ሲሆን ከግጥም ባሻገርም ቴአትር ፍቅር አላት።
ሜሮን ጌትነት በምሥራቅ ሀረርጌ አሰበ ተፈሪ /ጭሮ/ ከተማ ሰኔ 10 ቀን 1975 ዓ.ም የተወለደች ሲሆን በወላጆችዋ የሥራ ዝውውር ምክንያት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቷን በተለያዩ የሃገሪቷ ከተሞች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ተዘዋውራ የተማረች ሲሆን ይህም 1ኛ ክፍልን ወለጋ ሻምቡ አንደኛ ደረጃ፤ 2ኛ እና 3ኛ ክፍልን በአዲስ አበባ ህብረት በልጅነት፤ 4ኛ ክፍል በአራት ኪሎ ቅድስት ስላሴ፤ 5 ኛ ክፍልን በጠመንጃ ያዥ፤ 6ኛ ክፍል በአሰበ ተፈሪ ቁጥር አንድ፣ 7ኛ እና 8ኛ ክፍል በእውቀት ፋና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሲሆን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን በአብዮት ቅርስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠናቃለች።
ከዚያም በዩኒቲ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ በማርኬቲንግ ክፍል በዲፕሎማ እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር ጥበባት ትምህርት ክፍል በዲግሪ የተመረቀች ሲሆን የሁለተኛ ዲግሪዋንም በዚሁ ትምህርት ክፍል በቴአትር ለልማት /Theatre for Development/ ተከታትላለች።
ይህ በተለያዩ አካባቢዎች የማደግና የመማር አጋጣሚ ከሰዎች ጋር በቶሎ የመግባባትና ወዳጅነት የመፍጠር እንዲሁም ከአካባቢና ሁኔታዎች ጋር በፍጥነት መላመድ እንድትችል ያገዛት ሲሆን ለኪነጥበባዊ ምልከታዎቿና ለፈጠራ ዝንባሌዋ መሰረት ሆኗታል።
የኪነጥበበ ጉዞዋን የጀመረችው ሜሮን የአስራ አንደኛ ክፍል ተማሪ በነበረችበት ወቅት በጋሽ አበራ ሞላ የወጣቶች ፕሮጀክት አማካኝነት የኢትዮጵያንና የጃፓንን ግንኙነት በሙዚቃ ለማጠናከር በተደረገ ውድድር ተመርጣ ወደ ጃፓን ተጉዛለች። በቆይታዋም ቶኪዮ በሚገኝ የሙዚቃ ት/ቤት የድምጽ ስልጠና በመውሰድ በጃፓንኛ ያቀነቀነች ሲሆን ከዝነኛ የጃፓን ድምጻዊ ጋር በመሆን ዝግጅቷን በተለያዩ ከተሞች ተዘርዋውራ ስታቀርብ ከመቆየቷም በተጨማሪ በጃፓንኛ ነጠላ ዜማ ሰርታለች። ቲቪ አሳሂ በተባለ የቴሌቭዥን ጣቢያም ለአራት ወራት ያህል የተላለፈ አጠቃላይ ጉዞዋን የተመለከተ ሳምንታዊ ፕሮግራም ሰርታለች። “ይህ አጋጣሚ መክሊቴን ፍለጋ ከቆፈርኩባቸው ቦታዎች አንዱና የልጅነት ጀብዱዬ ብቻ ሆኖ እንዳይቀር ሌላ ታላቅ አጋጣሚ ፈጥሮልኝ አልፏል” ትላለች።
ሜሮን ግጥሞቿን በበርካታ መድረኮች፣ መገናኛ ብዙሃንና ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከማቅረብ ባሻገር በ1999 ዓ.ም “ዙረት” የተሰኘ የግጥም መድበል አሳትማ ለንባብ አብቅታለች። በኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ውክልናም የኢትዮጵያ ሚሊኒየም ወጣት ጀግኖች ተሸላሚ በመሆን በወቅቱ የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት ከነበሩት ከክቡር ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ እጅ የሜዳሊያ ሽልማት ተቀብላለች።
ሜሮን ከሁለት እስከ አምስት አመታት ያህል በመድረክ ላይ በቆዩ የሙሉ ሰአት ቴአትሮች ላይ በመሪ ተዋናይነት ሰርታለች። እነዚህም
ፍሬሽማን፣ ትሩፋልዲኖ፣ መስተፋቅር፣ ሰማያዊ ዓይን በሃገር ፍቅር ቴአትር፤ እልባት በአዲስ አበባ ባህልና ቴአትር አዳራሽ፤
ቅጥልጥል ኮከቦች በብሄራዊ ቴአትር ናቸው። በአንድ ቀን ሁለት የተለያዩ ቴአትሮችን በሁለት ተለያዩ መድረኮች ላይ ለአመታት የተጫወተች ሲሆን በ2ኛው የተስፋ ኢንተርፕራይዝ ሃገር አቀፍ የቴአትር ፌስቲቫል የሴት ኮከብ ተዋናይት ዘርፍ ተሸላሚ ሆናለች። በአሜሪካም በሚኔሶታ ግዛት የፍሪንጅ ቴአትር ፌስቲቫል ላይ ተሳትፋ ኢትዮጲያዊት ገጸ ባህሪ ወክላ በመጫወት የሀገሯን ባህል አስተዋውቃለች።
“የቴሌቭዥን ድራማዎች ከተመልካች ጋር የበለጠ እንድተዋወቅ አድርገውኛል” የምትለው ሜሮን ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2006 ዓ.ም በተከታታይነት በኢትዮጲያ ቴሌቭዥን ሲተላለፉ በቆዩ ገመና አንድ፣ ገመና ሁለትና ዳና በተሰኙ ሳምንታዊ ድራማዎች ላይ ተወዳጅ ገጸ ባህሪያትን ወክላ በመጫወት ትታወቃለች።
አንድ ዕድል፣ ፊደል አዳኝ፣ ኤልዛቤል፣ የእግር ዕጣ፣ ዱካ፣ ይሉኝታ፣ቤተልሄም፣ ሄሎ ኢትዮጵያ፣ ዲፕሎማት፣ ጊዜ ግዙን፣ የተከፈለበት፣ ትራፊኳ እና ድፍረት የተወነችባቸው ፊልሞች ሲሆኑ የተከፈለበት በድርሰት፣ በዝግጅትና በፕሮዲውሰርነት ተሳትፋለች። በዚህም በኢትዮጲያ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል የተመልካች ምርጫ ፊልም አሸናፊ እንዲሁም በቤተልሄም ምርጥ ረዳት ሴት ተዋናይት ዘርፍ ተሸላሚ ሆናለች። ከሃገር ወጪም በጀርመን የበርሊን ፊልም ፌስቲቫልና በአሜሪካ የሰንዳንስ ፊልም ፌስቲቫሎች ላይ ተገኝታ በድፍረት ፊልም “የ2014 መታየት ያለባቸው የተመረጡ ተዋንያን” ዝርዝር ውስጥ ተካታለች።
በሬዲዮ ድራማ የዘመን ችግኞች እና ቀጭን ፍቅር በተሰኙ ተከታታይ ድራማዎች ላይ በትወና፤ ቃና ዜማ የተሰኘ ሳምንታዊ የመዝናኛ ፕሮግራም (ራዲዮ ፋና) በአዘጋጅና አቅራቢነት ለ2 ዓመታት ሠርታለች።

#ethiopia | ከ80 በላይ ግጥሞችን የያዘውና 134 ገፆች ያሉት "ሌላ ዕውነት የለኝም" የተሰኘው የሜሮን ጌትነት መፅሐፍ ለንባብ ሊበቃ ነው።

ፍሬሽማን፣ ትሩፋልዲኖ፣ መስተፋቅር፣ ሰማያዊ ዓይን በሃገር ፍቅር ቴአትር፤
እልባት በአዲስ አበባ ባህልና ቴአትር አዳራሽ፤

"ኢትዮጵያ ችላለች ፣ ኢትዮጵያ አድርጋች ፣ ኢትዮጵያ አሳክታለች"
አርቲስት ጥላሁን ጉግሳ
#ethiopia | በኢትዮጵያ የኪነጥበብ ዘርፍ ስማቸው በጉልህ ከሚነሱ ከያኒያን እውቁና አንጋፋው ጥላሁን ጉግሳ ከግንባር ቀደሞቹ ይጠቀሳል። ይህ የኪነጥበብ ሰው በስፋት የሚታወቀው በመድረክ ቴአትሮች ፣ በቤቶች ድራማና በማስታወቂያ ስራው ነው።
አርቲስት ጥላሁን ጉግሣ የህዳሴ ግድብ መጠናቀቁን አስመልክቶ የግድቡ ስፍራ ድረስ በማምራት የግድቡን መጠነቃቅ ከጎበኙ ከያኒያን መካከል ሲሆን የተሰማውን ደስታ ለኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ሙዚቃ ፕላስ መሰናዶ አጋርቷል።
አርቲስቱ በቆይታው የህዳሴ ግድብ በመጠናቀቁ ደስታውን ገልፆ ግድቡ ኢትዮጵያን እንደ ሃገር ትልቅ ሃገር ያደረገ ፣ በማህበራዊና በምጣኔ ሃብት ሀገርን የሚያገዝፍ ድንቅ ስራ ሲል አድናቆቱን ገልጿል።
"ኢትዮጵያ ችላለች ፣ ኢትዮጵያ አድርጋች ፣ ኢትዮጵያ አሳክታለች" የሚለው አርቲስቱ ኢትዮጵያ እንደምትችል፣ ኢትዮጵያ ጀምራ እንደምትጨርስ ማሳያ የሆነ ግድብ እንደሆነም አክሏል።
አርቲስት ጥላሁን ጉግሣ አያይዞም "ኢትዮጵያውያን ከተባበርን፣ ኢትዮጵያውያን እንድነታችንን ከጠበቅን የፈለግነውን ማድረግ እንደምንችል የህዳሴ ግድብ ትልቅ ማሳያ ነው" በማለት ተናግሯል።
ግድቡ ብዙ ዋጋ የተከፈለበትና የኢትዮጵያ ህዝብም በእኔነት ስሜት እስከ መጨረሻው የለፋበት እንዲሁም እንደ ሃገርም እንደ ህዝብም ታላቁን ስራ የሰራንበት እንደመሆኑ በቀጣይም እንቆማለን ብዬ አላስብም በማለት ተስፋውን ገልጿል።
በመጨረሻም አርቲስት ጥላሁን "ይሄንን አንድነት እንደጠበቅን ልዩነቶቻችን በማጥበብ ለቀጣይ ስራችን እንድንነሳሳ የሚያደርግ ግድብ ነው። እንኳን ደስ አላችሁ" በማለት ሃሳብን አጠቃሏል።#fm Addis

10 months ago
ምረቃው የተሰረዘው ሎጎ
600 ሚሊየን ብር የተከፈለበትና ይፋ ሊደረግ በመጨረሻ ሰዓት ላይ በጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አህመድ የምረቃ ስነስርዓቱ እንዲሰረዝ የተደረገው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ ሎጎ ከላይ በምስሉ ተያይዟል።
Seledadotio