ፕሬዚዳንት ታዬ በኢትዮ-ኢስታንቡል ሆስፒታል ነጻ የቀዶ ህክምና ያገኙ የልብ ህሙማን ህጻናትን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በኢትዮ-ኢስታንቡል ሆስፒታል ነጻ የቀዶ ህክምና ያገኙ የልብ ህሙማን ህጻናትን ጎብኝተዋል።
የጣሊያኑ የ"ፔድሬ ፓዮ" የሕክምና ቡድን ከኢትዮ ኢስታንቡል ሆስፒታል ባለሙያዎች ጋር በመሆን በ12 ቀናት በአዲስ አበባ 58 በጅግጅጋ 16 በድምሩ ለ74 ሕፃናት የልብ ቀዶ ህክምና አገልግሎት ሰጥቷል።
"ኸርት ቱ ኸርት ችልድረን’ስ ኤይድ ፋውንዴሽን’ ካሰባሰበው የእርዳታ ገንዘብ እና ኢትዮ-ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል ባደረገው ድጋፍ ነው አገልግሎቱ የተሰጠው።
ፕሬዚዳንቱ በጉብኝታቸው ወቅት እንዳሉት፤ ሆስፒታሉ የሚያከናውነው ዘመናዊ የሕክምና አገልግሎትና የበጎ አድራጎት ሥራ በኢትዮጵያ የሕክምና ዘርፍ ወደ አዲስ ምዕራፍ መሸጋገሩን ያሳያል።
ያስተማረንን ሕዝብ ማስታወስ ትልቅ በረከት ነው ያሉት ፕሬዚዳንት ታዬ፤ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ሀገራቸውን ማገልገል እንዳለባቸው አመላክተዋል።
በሆስፒታሉ የሚሰጠው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እና ዘመናዊ ህክምና ለህክምና ወደ ውጭ ሀገር የሚደረገውን ጉዞ የማስቀረት ተስፋ እንዳለ የሚጠቁም መሆኑን ገልጸዋል።
ለህጻናቱ ነጻ የህክምና አገልግሎት የሰጠው ፔድሬ ፓዮ የህክምና ቡድን ለህፃናቱ እና ለቤተሰቦቻቸው የተስፋ ብርሃን መፈንጠቁን ገልጸው፤ አገልግሎቱ የኢትዮጵያ እና የጣሊያን ግንኙነትን ይበልጥ ለማጠናከር አስተዋጽኦ እንዳለው ጠቁመዋል።
የኢትዮ-ኢስታንቡል ሆስፒታል መስራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃን ተድላ በበኩላቸው፤ ባለፉት ሁለት ዓመታት ለ184 ሕፃናት 120 ሚሊየን ብር በሚገመት ወጪ ነፃ ሕክምና ሰጥቷል ብለዋል።
ሆስፒታሉ ውስብስብ የልብ፣ የካንሰር፣ የደም ስር የጭንቅላት የህብለሰረስና የአጥንት ቀዶ ህክምናን ጨምሮ ሌሎችም አገልግሎቶች እየሰጠ መሆኑን ገልጸዋል።
ነጻ የቀዶ ህክምና ያገኙ የልብ ህሙማን ህጻናት ቤተሰቦች ወጪ በመሸፈን ልጆቻቸውን ማሳከም ባለመቻላቸው ለዓመታት ሲሰቃዩ መቆየታቸውን አስታውሰው፤ ባገኙት ነፃ የህክምና አገልግሎት እፎይታ ማግኘታቸውን ተናግረዋል።
የህፃናት ነፃ የልብ ሕክምና አገልግሎቱ በቀጣይ ወደ ኦሮሚያ፣ አማራ፣ ትግራይ፣ ሲዳማ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ እና ሌሎች ክልሎች የሚቀጥል መሆኑ ተጠቁሟል።
#የተከፈለበት

1 month ago