ነይ እንሂድ‼️
#ethiopia | ብዙ አሳልፈዋል፤ የትምህርት ቤት ትውውቅ ወደ ፍቅር አድጎ በትዳር እስከመጣመር አድርሷቸዋል፤ ለአመታት ደስታና ሀዘን፥ ሳቅና ለቅሶ ተጋርተዋል፤ ሁለት ስም፥ ሁለት አካል ቢኖራቸውም አንድ ልብ ተላብሰዋል፤ በፅኑ ፍቅር ተጋምደዋል፤ ጓዳቸው ሙሉ ነው፤ በጋራ የሚመሩት የንግድ ተቋም አላቸው፤ ለሌላው ይተርፋሉ፤ ልጅ ግን የላቸውም፤ እስካሁን ፍሬያቸውን አላዩም፤ አቅፎ ለመሳም አልታደሉም፤ የቤተሰብ ጫና ተጨምሮባቸዋል፤ የዘመድ አዝማድ ግፊት በዝቶባቸዋል፤ የጓደኛና ጎረቤት ምላስ ተዘርግቶባቸዋል፤ ይህንን ሁሉ መቋቋም አቅቷቸዋል፤ ብን ብሎ መጥፋትን፥ ርቆ መኖርን ተመኝተዋል፤ እናም 'ነይ' እያለ ልብን በመሪነት ሾሞ መንገድ እንጀምር ይላታል፦
"ነይ እንድረስ ከአድማስ ወዲያ
አይ ልባችን ይምራንና
ነይ እንጥፋ እንሻገር
አላማረም የእኛ ነገር..."
ብቻውን አይሆንለትም፤ አልባሽ አጉራሹ፥ የልጅነት ፍቅሩ የህይወት አጋሩ፥ ግራ ጎኑ ቃልኪዳኑ፥ የሰማንያ ሚስቱ ምርኩዝ ብርታቱ፥ እሷ ነችና እጇን ይዞ ይህን ክፉ ቀን ራቅ ብለን እናሳልፍ ይላታል፤ የጉዞ ትጥቁ 'እምነቱ' የመንገድ ስንቁ 'ፍቅሩ' ብቻ ናቸው፤ ተስፋውን ሸክፎ ይማፀናታል፦
"ነይ እንሂድ
ፍቅር አለን የሚያነሳ
ነይ እንሂድ
እንነሳ...."
አለሜ የሚላት ሚስቱ ስለ ፍቅር ብላ ብዙ ችላለች፤ የዘመድ አዝማድና የጎረቤት ምላስ ደጋግሞ ገርፏታል፤ ማህፀነ ደረቅ ተብላለች፤ አጥንት በሚሰብሩ ቃላት በማያገባቸው በገቡ አለሜዎች የእሱ አለም እልፍ ጊዜ ታማለች፤ በልደትና ክርስትና፥ በለቅሶና ሰርግ በሽሙጥ ጦር ተወግታለች፤ ህመሟ ህመሙ ነውና ከዚህ በላይ ስቃይ ይብቃ፥ ብንሄድ ይሻላል እያላት ነው፦
"አንቺም ለኔ እንደሆንሽው እኔም ላንቺ
አለሜ አትንገላቺ
ከሚገርፈው ከውርጩ ከወረት አለም
አይ እንሂድ... እንሂድ ተይ አንታመም..."
እሱም ብዙ ደርሶበታል፤ ተዋትና ሌላ አግባ፥ ወላድ በድባብ ትሂድ የሚሉ የአንድ ልብ ሰንጣቂዎች ዘምተውበታል፤ አቋሙ ግን ፅኑ ነው፤ ጅማሬዬ እሷ ነበረች፤ ፍፃሜዬም እሷ ትሆናለች ይላቸዋል፤ የእኔ ማለዳ፥ የልቤ ሰሌዳ፥ ሀገሬ፥ ፍቅሬ፥ አለሜ ነች ብሎ ይመሰክርላታል
"እንደፈረስ ለጋሪው እንግዳ
በቤቱ ባይተዋር ተይ አንሁን እዳ
ብድርሽ ብድሬ ሀገርሽ ሀገሬ
በሬም አለ... ከበደኝ ቀንበሬ..."
በሰኔ ዝናብ እጦት እንደቆዘመ ገበሬ፥ በፀሎትና በምልጃ የደመናን ማርገዝ እንደሚለምን አርሶ አደር እነሱም ፍሬያቸውን ለብዙ ሰኔዎች ጠብቀዋል፤ በእንባ ጠይቀዋል፤ ምድራዊው ሃኪም ሁለቱም መውለድ እንደሚችሉ ነግሯቸዋል፤ የምድርና የሰማይ አምላካቸውን መለመናቸውን ቀጥለዋል፤ ሆኖም ተስፋ አስቆራጩ በዛባቸው፤ እናም ከእሱም ከእሷም ቤተሰብንና ከዘመድ አዝማዱ ጨለማዊ አመለካከት መሸሽን መርጠዋል፤ እስኪነጋ ድረስ ከአድማስ ወዲያን ለመመኘት ተገደዋል፤ ፍቅር ብቻ ያለበት ፀጥ ያለ ሰላማዊ ቦታን ናፍቀዋል
"እንደ ሰኔ ደመና እንደራቀው
እንደከፋው ገበሬ ተይ አንታመመው
እንሂድ እንሂድ ፀጥ ካለው ስፍራ
ተይ እንሁን ሰላም መኖርን ሳንፈራ...."
ነይ እንሂድ፥ ነይ እንጥፋ፥ ነይ እንሻገር፥ ነይ እንነሳ ይላታል
ሽሽቱ ሰላምን ፍለጋ ነው፤ ስደቱ መስዕዋት የተከፈለበትን ፍቅር ለማፅናት ነው፤ መንገዱ በፀጥታ ለመኖር ነው፤ መሪው ደግሞ ልብ!
ማስታወሻ፦ ( 'ነይ እንሂድ' በድምፃዊ ሮቤል ሚደቅሳ አልበም ውስጥ የሚገኝ ልብ ሰርሳሪ ሙዚቃ ነው፤ የፃፍኩት ደግሞ የማውቃቸውን ጥንዶች ታሪክ ነው፤ ሙሉ ሙዚቃው በመጀመሪያው አስተያየት መስጫ ላይ ይገኛል)
(ታምሩ ዓለሙ)

5 months ago