2 hours ago
እንኳን ለ19ኛው የብሔራዊ ሰንደቅ ዓለማ ቀን አደረሳችሁ-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
#ethiopia #ebc #nationalpride #ethiopianflagday #የመደመርመንግሥት
17 hours ago
ከማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋት እስከ ዘላቂ ዕድገት፡ የኢትዮጵያ የሁለንተናዊ ብልጽግና ጉዞ
**********
የማንኛውም ሀገር ዘላቂ ደህንነት እና ሉዓላዊነት በጠንካራ ኢኮኖሚ ላይ የተመሠረተ ነው። የመደመር መንግሥት የሀገር ግንባታን ሁለንተናዊ ለማድረግ በያዘው ስትራቴጂያዊ ርዕይ ውስጥ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሥራዎች የለውጡ ማዕከላዊ አንቀሳቃሽ ሞተር ሆነው ይገኛሉ። ፖለቲካዊ ሰላም፣ ማህበራዊ ትስስር እና ኢኮኖሚያዊ ነፃነት ተደጋግፈው ሢሠሩ፣ ሀገርን ወደ ላቀ የብልጽግና ከፍታ ማሸጋገር ይቻላል።
የመደመር መንግሥት ተግባራዊ ያደረገው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ የሀገራችንን እምቅ ሀብት በአግባቡ ለመጠቀም፣ የምርት እና ምርታማነት አቅምን ለማሳደግ እና የግሉን ዘርፍ በስፋት ለማሳተፍ ያስቻለ ትልቅ እርምጃ ናቸው።
ግብርናን በቴክኖሎጂ ማዘመን፣ ክረምትና በጋን ማስተሳሰር፣ የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ፣ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ እና የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን የሚስቡ ምቹ የንግድ አሠራሮችን መዘርጋት የዚህ ሁለንተናዊ ለውጥ ማሳያዎች ናቸው።
የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋትን ለማረጋገጥ፣ የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር እና የውጭ ምንዛሪ አቅርቦትን ለማሻሻል የተወሰዱት የፖሊሲ እርምጃዎች የኢኮኖሚውን አቅም ወደ ላቀ ደረጃ እያሸጋገሩት ይገኛሉ።
የመደመር መንግሥት የገበያ ሥርዓቱን ፍትሐዊ፣ ተወዳዳሪ እና አሳታፊ በማድረግ ረገድ የወሰዳቸው እርምጃዎች የሀገራችንን የንግድ እና ኢንቨስትመንት ከባቢ በከፍተኛ ደረጃ ለውጠውታል።
በባንክ አገልግሎቶች፣ በፋይናንስ ተደራሽነት እና በካፒታል ገበያ ግንባታ የተከናወኑ ሥራዎችም የኢኮኖሚውን አጠቃላይ አቅም አጎልብተውታል።
ከዚህ በተጨማሪ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማስፋት የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታን እውን ለማድረግ የተሠሩ ሰፋፊ ሥራዎች የገበያውን ተወዳዳሪነት አጠናክረውታል።
እነዚህ ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ዜጎች በፈጠራ ሥራዎች እንዲሰማሩ፣ ሥራ አጥነት እንዲቀነስ እና ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል እንዲሰፍን ምቹ ሁኔታ ፈጥረዋል።
የሰላም እና የልማት ትስስር ተጠናክሮ ሲቀጥል፣ ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና የኢኮኖሚ ማዕከል ሆና የምትወጣበት አቅሟ በይበልጥ እየተረጋገጠ ይመጣል።
በሔዋን ጌታቸው
#የመደመርመንግሥት
#ethiopia #economy #homegrowneconomicreform #digitaleconomy #medemer #prosperity #ethiopiatamirt #ebc

19 hours ago
ሰንደቅ ዓላማ፦ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት እና ለገዢ ትርክት
***************
የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ከትውልድ ትውልድ የተሸጋገረ፣ በአባቶች የደም ቀለም የተጻፈ፣ የጀግኖች አባቶች የደማቸው ፍሳሽ እና የመሥዋዕትነት ውጤት የድል ዓርማ በመሆኑ ከሀገር ሕልውና ጋር ተያይዞ የሚታይ ነው።
የዘንድሮው የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባት እና ለአንድነታችን” በሚል መሪ ቃል ሲከበር፣ ዜጎች በሰንደቁ ፊት ቆመው ቃለ መሐላ በመፈጸም ለሀገራቸው ያላቸውን የማይነጥፍ ፍቅር እና ክብር የሚያረጋግጡበት ታላቅ አውድ ይፈጥራል።
በአዋጅ ቁጥር 654/2001 ዓ.ም መሠረት የሰንደቁ ቀለማት ሕጋዊ ትርጉም አግኝተዋል፤ አረንጓዴ የሥራ፣ የልምላሜ እና የዕድገት፣ ቢጫ የተስፋ፣ የፍትሕ እና የእኩልነት፣ ቀይ ደግሞ ለነፃነት እና ለእኩልነት መስፈን የሚደረግ የመሥዋዕትነት እና የጀግንነት ምልክት ናቸው።
ሰንደቁን ከሚወክሉት መገለጫዎች አንዱ የሆነው ብሔራዊ ዓርማ፣ የሕዝቦች አጠቃላይ ፍልስፍና እና የርዕዮተ ዓለም አቅጣጫን በግልጽ ይጠቁማል። በሰንደቁ መሐል ላይ የሚያርፈው ዓርማ ቀጥታ እና እኩል የሆኑ መስመሮች የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች እንዲሁም የሃይማኖቶች እኩልነትን የሚያሳዩ ሲሆን፣ ከመስመሮቹ የተዋቀረው ኮከብ በመፈቃቀድ የመሠረቱትን ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ይወክላል። ቢጫው ጨረር ደግሞ ለሁሉም አቅጣጫ የፈነጠቀውን ብሩህ ተስፋ ይጠቁማል።
የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ታሪክ ከቅኝ ገዥዎች ነፃ ከወጣችበት ሐቅ ጋር የተቆራኘ ነው። የዓድዋ ድል በሰንደቃችን ሥር ተሰባስበን ለክብራችን መዋደቃችን ዐቢይ አብነት በመሆኑ፣ የድል አድራጊነት ከፍታ እና የጋራ ገዢ ትርክት ግንባታ መሠረት ሆኗል።
የኢትዮጵያ ሰንደቅ የረዥም ዘመናት የነፃነት ተምሳሌት በመሆን ለአፍሪካ እና ለዓለም ሕዝቦች የነፃነት ፋና ወጊ እና የድል ብርሃን ፈንጣቂ ሆኖ አገልግሏል። በቅኝ ግዛት የተጨቆኑ አፍሪካውያን ሀገራት ነፃ ሲወጡ የሰንደቃችንን ቀለማት መሠረት በማድረግ የራሳቸውን ዓርማዎች መምረጣቸው፣ ሰንደቁ የአህጉር፣ የዘር እና የነፃነት የጋራ ቋንቋ መሆኑን በውል ያሳያል።
ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ እና ታላቅ ርዕይ ያላት ኢትዮጵያ፣ ዛሬ ላይ ሉዓላዊነቷ በዘላቂነት ሊረጋገጥ የሚችለው ሀገርን ከልመና እና ጥገኝነት ነፃ በማውጣት ሁለንተናዊ ብልጽግናን ስናረጋግጥ ነው።
በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እና ሌሎች ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች የተበሰሩ ስኬቶች ሀገራችን ብሔራዊ ጥቅሟን እንድታስከብር እና የውኃ ሀብት ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን እንድታረጋግጥ የሚያስችሉ ናቸው።
ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን አጽንተን የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በከፍታ እናውለበልባለን በሚል መንፈስ፣ ዜጎች በየተሰማሩበት ዘርፍ ሁሉ ሁለንተናዊ ብልጽግናን በማረጋገጥ ለሰንደቁ ልዕልና እና ለሀገር ከፍታ ዘብ መቆም ይጠበቅባቸዋል።
በሰለሞን ገዳ
#የመደመርመንግሥት
#ethiopia #ebc #nationalflagday #medemer #medemergovernment

24 hours ago
ጥሬ ሀብትን ወደ እሴት፡ የኢትዮጵያ የወርቅ እና ማዕድን ዘርፍ አዲስ ምዕራፍ
*******************
ኢትዮጵያ በከርሰ ምድሯ በርካታ ያልተነኩ ውድ የተፈጥሮ ሀብቶችን ይዛ የምትገኝ ሀገር ነች።
ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ ባሉ ሰፋፊ ቀጣናዎች ሥር የሚገኙት የወርቅ፣ የከበሩ ድንጋዮች፣ የብረት፣ የታንታለም፣ የሊቲየም እና የፖታሽ ክምችቶች የዚህ ታላቅ በረከት ማሳያዎች ናቸው።
ላለፉት በርካታ ዘመናት ይህንን የተፈጥሮ ጸጋ በባህላዊ ማውጣት ዘዴዎች ብቻ በመጠቀም ዘርፉ ሊሰጥ የሚችለውን ያህል ጥቅም ሳናገኝበት ቆይተናል።
አሁን ላይ ግን የተወሰዱ የፖሊሲ እና የአሠራር ማሻሻያዎች ዘርፉን አዲስ ወደሆነ የኢኮኖሚ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ዋና የልማት ምሶሶ እያደረጉት ይገኛሉ።
የማዕድን ዘርፉ ትልቁ መዋቅራዊ ሽግግር የሚጀምረው ከፖሊሲ አቅጣጫ ለውጥ ነው። ቀደም ሲል ጥሬ ወርቅን እና ሌሎች ማዕድናትን ያለ ምንም ተጨማሪ እሴት በቀጥታ ወደ ውጭ መላክ የተለመደ አሠራር ነበር።
ይህም ኢትዮጵያ ማግኘት የሚገባትን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና ከዘርፉ የምታገኘውን ዋጋ እንድታጣ አድርጓታል።
አሁን የተያዘው ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ ግን ጥሬ ሀብትን በቀጥታ ከመሸጥ ይልቅ በሀገር ውስጥ የማጣራት፣ እሴት የመጨመር እና ምርቶቹን ወደ ተጠናቀቁ የኢንዱስትሪ ውጤቶች የመቀየር ግብ ላይ ያተኮረ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በይፋ ሥራ ያስጀመሩት የቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ የዚህ አዲስ ሀገራዊ አቅጣጫ ግልጽ ማሳያ ነው።
ይህ ታላቅ የኢንዱስትሪ አቅም የተፈጥሮ ሀብትን ከዘመናዊ ማኑፋክቸሪንግ ጋር በማስተሳሰር የወጪ ንግድ ገቢን ለማሳደግ፣ ሰፊ የሥራ ዕድል ለመፍጠር እና የሀገር ውስጥ የጌጣጌጥ ኢንዱስትሪን መሠረት ለማጠናከር አልሞ የተገነባ ነው።
ይህም ግልጽ እና ተወዳዳሪ የሆነ የወርቅ እሴት ሰንሰለት በመገንባት ዘላቂ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታን ለመፍጠር እየተሠራ መሆኑን ማረጋገጫ ነው።
ከማዕድን ማውጣት እስከ ኤክስፖርት ድረስ ያለው ይህ አጠቃላይ የላቀ እሴት የመፍጠር ሂደት ኢትዮጵያን በምሥራቅ አፍሪካ የቀጣናው ዋና የማዕድን ማጣሪያ እና የንግድ ማዕከል የማድረግ ሰፊ ራዕይ አካል ነው።
አሠራሩ የውጭ ምንዛሬ ገቢን ከማሳደጉ ባሻገር ቀደም ሲል በኮንትሮባንድ እና በሕገ-ወጥ ንግድ መስመር ይባክን የነበረውን አቅም ወደ ሕጋዊ እና ግልጽ የፋይናንስ ሥርዓት በማስገባት የተፈጥሮ ሀብቱን ለትውልድ የሚሻገር ዘላቂ የኢኮኖሚ ጉልበት ያደርገዋል።
#የመደመርመንግሥት
በሔዋን ጌታቸው
#ethiopia #ebc #goldrefinery #valueaddition #mining

1 day ago
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቐለ ከተማ የሚያደርገውን በረራ ጀመረ
************
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ዛሬ ጀምሯል።
የአየር መንገዱ አውሮፕላን ዛሬ ማለዳ መቐለ ከተማ ማረፉን እና አየር መንገዱ ወደ ትግራይ ክልል በረራ መጀመሩን ተከትሎ የከተማዋ ነዋሪዎች በአሉላ አባነጋ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ደስታቸውን እየገለጹ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቐለ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ የሚጀምር መሆኑን መግለጹ ይታወቃል።
#የመደመርመንግሥት
#ethiopia #ebc #medemer #medemergovernment #ethiopianairlines #mekelle

2 days ago
የመደመር መንግሥት ታሪክን በዘመናዊነት የማደስ ጥበብ
***********
የታላቅ ህዝብ ታሪካዊ ቅርስ እና ድል የዛሬዋ ኢትዮጵያ ወደ ዘመናዊ የብልፅግና ምዕራፍ የምታደርገው ጉዞ መሰረትና ህያው ምስክር ነው።
ጥንታዊ ቅርሶቻችንን በመጠበቅ፣ የታሪክ አደራችንን በዘመናዊ መልክ በማደስ እና ለትውልድ የሚሻገር አዲስ እሴት በመፍጠር ረገድ ባለፉት ዓመታት የተሰሩ ታላላቅ ስራዎች ሀገራዊ ፍቅራችንን እና የጥበብ ጥጋችንን በተግባር ያሳዩ ናቸው።
የሀገራችን የነጻነትና የድል ምልክት የሆነውን የጀግኖች ህዝቦችን ኩራት የዓድዋ ድል ክብር የሚገልፅ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በዘመናዊ የሙዚየም ንድፍና ቴክኖሎጂ ግብዓት ተገንብቶ ለአገልግሎት በቅቷል።
ይህም የቀደሙ አባቶቻችንን ገድል ለትውልድ ከማስተላለፉም በላይ፣ ከውጭ ሀገራት የተመለሱና የተሰበሰቡ ታሪካዊ ቅርሶችን በደህንነት አቃፎ የያዘ ታላቅ የመዘክር ማዕከል ለመሆን በቅቷል።
ከዚሁ ጎን ለጎን በገበታ ለሀገር፣ በገበታ ለትውልድ እና በሸገር ማስዋብ ፕሮጀክቶች አማካኝነት የመንግስትና የህዝብ ቅንጅት ያሳዩ በርካታ የቱሪዝምና የቅርስ እድሳት ስራዎች ተከናውነዋል።
በጎንደር የአፄ ፋሲል ቤተ-መንግስትና አካባቢው ጥንታዊ ውበቱ ሳይጎዳ ታድሶ ለጎብኚዎች ምቹ በሆነ መልኩ ተዘጋጅቷል፤ በባሌ የተፈጥሮና የባህል ሃብቶችን አጣምረው የያዙ ማዕከላት በዘመናዊ መልክ ተገንብተዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ በተለየም በአርባምንጭ ተንሳፋፊ ሪዞርት በመስራት አርባ ምንጭ የ40 ምንጮች መገኛ መሆኗን ያስመሰከረ ሆኗል።
እንዲሁም በአፋርና በሶማሌ ክልሎች የነበሩ ታሪካዊና ተፈጥሯዊ መስህቦች የገበታ ለትውልድ አካል በመሆን በዘመናዊ ዲዛይን ታድሰውና አዲስ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ተደርጎላቸው ለክልሎቹ አዲስ የኢኮኖሚና የቱሪዝም ህይወት ዘርተዋል።
በተጨማሪም በመዲናችን አዲስ አበባ የተሰሩት የሸገር ማስዋብና፣ የአንድነት ፓርክ፣ የሳይንስ ሙዚየምና የወንዞች ዳርቻ ልማት ፕሮጀክቶች መዲናዋን የዘመናዊነትና የተፈጥሮ ውበት መገናኛ አድርገዋታል።
እነዚህ ስራዎች በሙሉ ኢትዮጵያ የታላቅ ታሪክ ባለቤት ብቻ ሳትሆን፣ ያንን ታሪክና ቅርስ በዘመናዊ እይታ አድሳና አስውባ ለቀጣዩ ትውልድ ለማስረከብ ያላትን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጡ ህያው ማረጋገጫዎች ናቸው።
በልዩ እሸቱ
#የመደመርመንግሥት #ethiopia #ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ

የካይሮ የሴራ እንቅስቃሴ እና የኢትዮጵያ የማይናወጥ የከፍታ ጉዞ
******************
የታሪክ የሉዓላዊነትና የነፃነት ተምሳሌት የሆነችው ኢትዮጵያ ከውስጥና ከውጭ የሚሰነዘሩባትን ሁለገብ ተፅእኖዎችና መሰናክሎች አልፋ የብልፅግና ጉዞዋን በፅናት እያስቀጠለች ትገኛለች።
ሀገራችን ያላትን ሰፊ ለም መሬት፣ የተትረፈረፈ የውሃና የማዕድን ሀብት እንዲሁም ታላቅ የሰው ሀይል ከህዝቧ የኑሮ ደረጃ ጋር ለማጣጣምና ድህነትን ታሪክ ለማድረግ በፈጣን የልማት ሂደት ላይ ትገኛለች።
ይሁን እንጂ የኢትዮጵያን ሰላምና እድገት ለማጨናገፍ ከታሪካዊ ጠላቶችና ከእነሱ ጋር ከተሰለፉ የውስጥ ከዳተኞች የሚሰነዘሩት ትንኮሳዎችና የጥፋት እንቅስቃሴዎች ዛሬም የሀገራችንን ሉአላዊነት ለመሸርሸር ያለሙ መሆናቸው ይታወቃል።
የዓባይ ወንዝን ፍሰትና ፍትሃዊ ጥቅም በተመለከተ የካይሮ መንግስት የሚከተለው ፖሊሲ የኢትዮጵያን የመልማት መብት ለመገደብ ያለመና በቅኝ ግዛት ዘመን የቆዩ ጊዜያቸው ያለፈባቸውን ውሎች በማንሳት ላይ የተመሰረተ ነው።
እነዚህ ጠላቶች ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ከመጀመሪያው አንስቶ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በዲፕሎማሲ መስኮች ለማደናቀፍ የውስጥ ተላላኪዎችን በመሳሪያነት በመጠቀም ቀጠናው ሰላም እንዳያገኝ ሲጥሩ ቆይተዋል።
ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ የናይል ወንዝን በፍትሃዊ፣ ምክንያታዊና በታችኞቹ የተፋሰስ ሀገራት ላይ ጉዳት በማያደርስ መርኋ መሰረት ውሃውን ለልማቷ እያዋለች ትገኛለች።
ታላቁ የህዳሴ ግድብ የደለል ክምችትን በመቀነስ የጎርፍ አደጋን በመከላከልና ንፁህ የኤሌክትሪክ ኃይል ለጎረቤት ሀገራት በማቅረብ የምስራቅ አፍሪካን የኃይል እጥረት የሚቀርፍና እውነተኛ ቀጠናዊ የኢኮኖሚ ትስስርን የሚያረጋግጥ ዘመናዊ መሰረተ ልማት መሆኑ በተግባር ተረጋገጧል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዲሱ የመደመር መንግስት ምስረታ ወቅት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር፤ እንደ ሀገር ቀድሞ አለመዘጋጀት የሚያስከፍለውን ዋጋ ለመገንዘብ የጣሊያን ዳግም ወረራን መለስ ብሎ መቃኘት አስፈላጊ መሆኑን ገልፀው፤ ኢትዮጵያ ያሰበችውን ታሳካለች ጠላቶቿንም አስወግዳ ጉዞዋን በፍጥነት ትቀጥላለች ሲሉ አስምረውበታል።
አክለውም ኢትዮጵያ የዓባይን ወንዝ የምትጠቀመው የሌሎችን ድርሻ ለመጋፋት ሳይሆን ህዝቧን ከጨለማ ለማውጣትና ከጎረቤቶቿ ጋር በጋራ ለማደግ መሆኑን ገልፀዋል።
በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ በጠንካራና ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በተገነባ መከላከያ ሰራዊት በፈጣን ኢኮኖሚያዊ እድገት በዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምና እንደ ታላቁ ህዳሴ ግድብ የከተሞች ኮሪደር ልማትና በግብርና እራስን የመቻል እንቅስቃሴ ባሉ ታላላቅ ሜጋ ፕሮጀክቶች የቀጠናውን መሪነቷን አጠናክራለች።
ከአፍሪካ ሁለተኛ ባለ ብዙ ቁጥር ህዝብ ያላት ሀገር እንደመሆኗ በቀጠናው ዘላቂ ሰላምና የጋራ ብልፅግና ለማረጋገጥ በታሪካዊ ስህተት ያጣችውን የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ በሰላማዊና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ በሰጥቶ መቀበል መርህ እውን ለማድረግ ብሄራዊ አጀንዳ አድርጋ እየሰራች ሲሆን ጥያቄውም በአለም አቀፍ ደረጃ ድጋፍ በማግኘት ላይ ይገኛል።
እንደ ዓድዋ ድል ሁሉ የባህር በር ማግኘት ለዛሬው ትውልድ የህልውናና የሁለተኛው ትውልድ የመልማት የመበልፀግና የሀገር ፍቅር ንቅናቄ ጉዳይ መሆኑ የውጭ ጫናዎችና ጂኦፖለቲካዊ ተቃውሞዎች የህዝቡን አንድነት የበለጠ የሚያጠናክሩት በመሆናቸው ኢትዮጵያውያን በጋራ በመቆም ለቀጣዩ ትውልድ የበለፀገች ሀገር የማስረከብ አርበኝነትን በተግባር መወጣት ይገባናል።
በብሌን ደምበሎ
#ethiopia #የመደመርመንግሥት #ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ

Sponsored by
Surafel
2 days ago
በፈተናዎች ውስጥ የበረታችው ኢትዮጵያ
***************
ኢትዮጵያ በታሪኳ ፈተናዎችን በጽናት በመሻገር ያሸበረቀች የጥንካሬ ምሳሌ ናት።
በየዘመናቱ ጠላቶቿና ተቀናቃኞቿ ወድቀቷን፣ ድክመቷንና መበታተኗን አጥብቀው በሚመኙበት በዚያው ወቅት፣ እሷ ግን በተቃራኒው ይበልጥ ክንዷን አበርትታና አጠናክራ የምትገነባ ሀገር መሆኗን በተግባር አስመስክራለች።
ይህ የጽናት ጉዞ ከጥንት ጀምሮ ዓለም ፊቱን ባዞረብንና በብቸኝነት በቆምንበት ወቅት፣ እንዲሁም በዓድዋ ዘመቻ ጊዜ በዲፕሎማሲና በሴራ ሊያጠቁን ሲሞክሩ ኢትዮጵያውያን በተባበረ ክንድ ፈተናውን መክተው ታሪክ ሰርተዋል።
በቅርብ ጊዜ ደግሞ ዓለም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ተዘጋግቶ ተስፋ በቆረጠበት ወቅት፣ ኢትዮጵያ እጅ ሳትሰጥና ሽብርክ ሳትል በተገቢው የጤና ጥንቃቄና በህዝባዊ ትብብር በመዚቃ፣ በቲያትር መማነቃቃት ወረርሽኙን ተቋቁማ ማለፍ ችላለች።
ሀገራችን የተለያዩ ዘመቻዎች ተከፍተውባት፣ ዓለም ጀርባውን ባዞረባትና ፍርደ-ገምድልነቱን ደጋግሞ ባሳያትም ጊዜ ለአንዲት ሰከንድ እንኳ አንገቷን አልደፋችም።
በመደመር መንግስት ምስረታ ጉባኤ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በግልፅ እንዳስቀመጡትም፤ በተፈጥሮ ሀብታችንና በወንዛችን የመጠቀም መብታችንን ለማስከበር ደፋ ቀና ስንል፣ የታላቁ ህዳሴ ግድባችንን ፍጻሜ ለማደናቀፍ በረጅም ገመድ አስረው ወደኋላ ሊጎትቱን ቢሞክሩም ተንገዳገድን እንጂ አልወደቅንም፤ ከእንግዲህም ቢሆን በፍጹም አንወድቅም ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተናገሩት በዚህ ጥልቅ ሃሳብ ላይ እንደሚንጸባረቀው፣ ኢትዮጵያ ከአያት ቅድመ-አያቶቿ የወረሰችውን የማይበገር የማሸነፍ መንፈስ ሰንቃ በርካታ ውጫዊና ውስጣዊ ጫናዎችን ተቋቁማ አልፋለች።
ይህ ታሪክ ደግሞ ወደፊትም ሀገራችን በማንኛውም ፈተና ውስጥ አልፋ የምትገነባ ጽኑ ሀገር መሆኗን ህያው ምስክር ሆኖ ይኖራል።
በልዩ እሸቱ
#የመደመርመንግሥት #ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ

የኢትዮጵያ የውጭ ፖሊሲ የሽግግር ምዕራፍ
**************
የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ታሪክ በዓለም አቀፍ ደረጃ ነጻነቷንና ሉዓላዊነቷን ከማስከበር ባለፈ በባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ውስጥ ቀደምትና ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የሚታወቅ ቢሆንም፣ በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች የሀገራችን የውጭ ፖሊሲ ከውስጣዊ ደኅንነትና ሉዓላዊነትን ከማስከበር ባሻገር ተጽዕኖ ፈጣሪነቷን በሙሉ አቅም ለመጠቀም ውስንነቶች ነበሩበት።
በንጉሠ ነገሥቱ ዘመን የውጭ ፖሊሲው በዋናነት የምዕራባውያንን ድጋፍ በማጠናከርና ሉዓላዊነትን በማስከበር ላይ የተመሠረተ ሲሆን፣ በደርግ ዘመን ደግሞ የሶቭየት ኅብረትን የርዕዮተ-ዓለም ካምፕ በመከተል በደኅንነትና የወታደራዊ ትስስር ላይ ያተኮረ አካሄድን ይከተል ነበር።
ከ1983 ዓ.ም በኋላ የወጣው ፖሊሲ ደግሞ ድህነትን መዋጋትን ዋና መሠረት በማድረግ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲንና የጎረቤቶች ሰላምን ማዕከል ያደረገ ቢሆንም፣ የዓለም አቀፍ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች መለወጥ፣ የጂኦ-ፖለቲካ ፉክክር መጨመር እና የሀገር ውስጥና የአካባቢው ለውጦች ፖሊሲውን ማሻሻልና ማሳደግ አስፈላጊ አድርገውታል።
በቅርብ ዓመታት ደግሞ የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ በቀጥታ ከዓለም አቀፍ ተቀባይነት ፍለጋ በመውጣት፣ በክልላዊና ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ንቁ አጀንዳ ሰጭነት እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ዲፕሎማሲያዊ ሚና ወደ መጫወት ተሸጋግሯል።
ዓለም ከአንድ ወገን የበላይነት ወደ ባለብዙ ወገን መሸጋገሯ ኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ አቅጣጫዎቿን እንድታሰፋና የፖሊሲ አማራጮቿን እንድታበዛ ያስገደዳት ሲሆን፣ የሀገር ውስጥ የኢኮኖሚ ፍላጎትን ለማሟላት፣ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለማሳደግና የኃይል ሽያጭን ጨምሮ ክልላዊ የኢኮኖሚ ትስስርን ለማጠናከር አዲስ አቀራረብ ተከትላለች።
በዚህም መሠረት ቀደም ሲል ከነበራት በተወሰኑ ምዕራባውያን ወይም ታላላቅ ኃይሎች ላይ የተመሠረተ ግንኙነት በመውጣት፣ ከሁሉም ጋር በጋራ ጥቅም ላይ የተመሠረተ ተግባራዊ የዲፕሎማሲ አቅጣጫ መከተል ጀምራለች።
የዚህ የውጭ ፖሊሲ ትልቁ የስኬት ማሳያ ሀገራችን የብሪክስ አባል መሆኗ ሲሆን፣ ይህም በዓለም አቀፍ የፋይናንስና የንግድ ሥርዓት ውስጥ ድምጿ እንዲሰማ፣ ከአስደናቂ የኢኮኖሚ ዕድገት ባለቤቶች እንደ ቻይና፣ ህንድ፣ ብራዚልና ሩሲያ ጋር ያላትን ትስስር እንድታጠናክርና አማራጭ የልማት ፋይናንስ ምንጮችን እንድታገኝ በር ከፍቷል።
በሌላ በኩል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅና ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀንድ የንጹሕ ኃይል አቅርቦት ማዕከል ያደረጋት ሲሆን፣ ለሱዳን፣ ጂቡቲ እና ኬንያ እየቀረበ ያለው የኤሌክትሪክ ኃይል የቀጣናውን የኢኮኖሚ ትስስር ማጠናከሩ ብቻ ሳይሆን በጎረቤት ሀገራት ዘንድ ያላትን ስትራቴጂካዊ አስፈላጊነት አሳድጎታል።
በአጠቃላይ ኢትዮጵያ የተመጣጠነና የብዙ ወገን ዲፕሎማሲ በመከተል በታላላቅ ኃይሎች ፉክክር ውስጥ ገለልተኝነቷንና ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ እየሠራች ትገኛለች።
የብሪክስ አባልነት፣ የኢኮኖሚና የኃይል ዲፕሎማሲ እንዲሁም በቀጣናው የሚደረጉ የሰላም ማስከበር እንቅስቃሴዎችም ብሔራዊ ጥቅሟን ከቀጣናዊ ትስስር እና ከዓለም አቀፍ ትብብር ጋር አጣጥማ በመጓዝ የጀመረችውን የአጀንዳ ሰጭነት ሚና አጠናክራ እንድትቀጥል የሚያስችሏት ናቸው።
በአድማሱ አራጋው
#ethiopianbroadcastingcorporation #ethiopianforeignpolicy #brics #gerd #የመደመርመንግሥት

ሀገር አቀፍ የህግ ተርጓሚዎች ጉባኤ በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው
*****************
የፌዴራል እና የክልል ፍርድ ቤቶች ለፍትህ ሥርዓቱ መጠናከር በጋራ እንዲሠሩ የሚያስችል ሀገር አቀፍ የህግ ተርጓሚዎች ጉባኤ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አዘጋጅነት በባሕር ዳር ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትና የህግ ተርጓሚዎች ጉባኤ ሰብሳቢ አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በመድረኩ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ጉባኤው ፍርድ ቤቶች በአደረጃጀታቸውና በሥልጣን ወሰናቸው ያደረጓቸውን እንቅስቃሴዎች በመፈተሽ ከስኬቶችና ከክፍተቶች ተሞክሮ ለመጋራት እንደሚያስችል አስታውቀዋል።
ተገልጋዮችን እርካታ የሚያረጋግጥ ተቀራራቢ የህግ አተረጓጎም እና አተገባበር እንዲኖር ትልቅ ፋይዳ እንዳለውም ገልጸዋል።
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ አለምአንተ አግደው በበኩላቸው፣ የፌዴራልና የክልል ፍርድ ቤቶች በህግ ትርጓሜ ላይ በመቀናጀት የሚሠሩት አሠራር ድምበር የለሽ የሆነውን የፍትህ አገልግሎት ለማሳለጥ የሚያግዝ መሆኑን ጠቁመዋል።
የዳኝነት አገልግሎት ዘርፍ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ፣ ሰብአዊ መብቶችንና ነፃነቶችን ለማስከበር እንዲሁም ለንግድና ኢንቨስትመንት መሳለጥ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
ይህን ተልዕኮ ለማሳካት በአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች የተጀመሩ የለውጥ ሥራዎች ተጨባጭ ውጤት እያስገኙ መሆናቸውን ገልጸው፣ ጉባኤው ለለውጥ ሥራው የላቀ ስኬት አስተዋጽኦ እንዳለው እምነታቸውን ገልጸዋል።
በጉባኤው ላይ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትን ጨምሮ የሁሉም ክልሎች ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች እና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች ፕሬዚዳንቶች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
በራሔል ፍሬው
#ethiopia #ebc #justice #የመደመርመንግሥት #courtoffice

3 days ago
አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ - በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አስተባባሪ
#ethiopia #ኢትዮጵያ #የኢፌዴሪየመደመርመንግሥት #pmoethiopia #ebc
#ethiopia #ኢትዮጵያ #የኢፌዴሪየመደመርመንግሥት #pmoethiopia #ebc
3 days ago
ዶ/ር ደረጀ ድጉማ - በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አስተባባሪ
#ethiopia #ኢትዮጵያ #የኢፌዴሪየመደመርመንግሥት #pmoethiopia #ebc
#ethiopia #ኢትዮጵያ #የኢፌዴሪየመደመርመንግሥት #pmoethiopia #ebc
3 days ago
አቶ ፍሰሃ ደሳለኝ - በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አስተባባሪ
#ethiopia #ኢትዮጵያ #የኢፌዴሪየመደመርመንግሥት #pmoethiopia #ebc
#ethiopia #ኢትዮጵያ #የኢፌዴሪየመደመርመንግሥት #pmoethiopia #ebc
Sponsored by
Surafel
3 days ago
ይህ ሳምንት ቁልፍ የአመራር ሹመቶች እና ለቀጣዩ የአስተዳደር ምዕራፍ የሚደረጉ ዝግጅቶች የተከናወኑበት፣ የመደመር መንግሥት ምስረታ ሳምንት ነበር።
#pmoethiopia
#የመደመርመንግሥት
4 days ago
ከቤት ደጃፍ እስከ አፍሪካ ክብር፤ የኢትዮጵያ ቡና ዓለም አቀፍ ከፍታ
****************
“ኑ ቡና ጠጡ፣ ቡና ፈልቷል” የሚለው ጥሪ በኢትዮጵያውያን የዘወትር ሕይወት ውስጥ ትልቅ የፍቅርና የእንግዳ ተቀባይነት ግብዣ ነው።
በዚሁ የቡና አፈላል ሥነ-ሥርዓት ወቅት ማኅበራዊ ውይይቶች ይካሄዳሉ፤ ጥልቅ ትስስር ይፈጠራል።
የኢትዮጵያዊነት አንዱ መገለጫ የሆነው የቡና ስነ ስርዓት ከእርሻ ማሳዎች እስከ ሲኒያችን ድረስ የአርሶ አደሩ እጅ ቤተሰብንና ማኅበረሰብን የሚደግፍ ታላቅ እሴት ነው።
ይህ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲሸጋገር የመጣ የቡና ባህል በቤትና በማኅበረሰብ ደረጃ ብቻ ተወሰኖ አልቀረም።
ዛሬ የኢትዮጵያ ቡና ሌላ አዲስ የክብር ገጽታውን ለአፍሪካና ለዓለም አሳይቷል።
በአንድ ቀን 10 ሺህ ሲኒ ቡና በአንድ ሥፍራ በማቅረብ፣ ባህላዊ የቡና አፈላል ሥርዓቱ በአፍሪካ የድንቃድንቅ መዝገብ ውስጥ ዕውቅና አግኝቷል።
በመሆኑም “ኑ ቡና ጠጡ” የሚለው ጥሪ ከቤት ደጃፍ አልፎ በአህጉራዊ የክብር መዝገብ ውስጥ በመግባት፣ ከ“ኑ ቡና ጠጡ” ወደ “የኢትዮጵያን ባህልና አብሮነት ይዩ” ወደሚል ሰፊ አህጉራዊ ጥሪ ተሸጋግሯል።
ኢትዮጵያ የአረቢካ ቡና መገኛ እና የአፍሪካ ቀዳሚ ቡና አምራች ሀገር ስትሆን፣ የመጀመሪያው የቡና ፍሬ ተለቅሞና ተሰብስቦ ለዓለም የተበረከተው እዚሁ በኢትዮጵያ ምድር ነው።
ሀገራችን በ2018 በጀት ዓመት ከቡና ወጪ ንግድ ከ3.1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማስመዝገብ ችላለች።
ይህም ኢትዮጵያ ባለፉት 17 ዓመታት በአጠቃላይ ካገኘችው 3.3 ቢሊዮን ዶላር የገቢ መጠን ጋር የሚቀራረብ ነው።
በተጨማሪም በየዓመቱ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞች በሚተከሉበት የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር ውስጥ ሰፊውን ቁጥር የሚይዙት የቡና ችግኞች ናቸው።
ይህም ደኖችን መልሶ ለማቋቋም፣ ሥነ-ምህዳርን ለመጠበቅ እና የቡና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስፈልገውን አየር ንብረት ለመፍጠር አስችሏል።
ከዚህ ዕድገት ጎን ለጎን ኢትዮጵያ የቡና በሽታን ለመለየትና ለማከም የሚያስችሉ አዳዲስ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂዎችን እና ምርምሮችን በማሳደግ ላይ ትገኛለች።
በልዩ እሸቱ
#የመደመርመንግሥት
#ethiopia #ebc #medemer #ethiopiancoffee #coffeeculture

የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ
****************
የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራህማንያም ጃይሻንካር (ዶ/ር) ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ ገብተዋል።
ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ፤ ጉብኝቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ዘመናት የተሻገረና ሁለንተናዊ የሁለትዮሽ አጋርነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩ ውጤታማ ውይይቶች የሚካሄዱበት እንደሚሆን ገልፀዋል።
ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽ፣ በቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማ ምክክር ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።
#የመደመርመንግሥት
#ethiopia #ebc #medemer #india #diplomacy

በናይጄሪያ ምክትል ፕሬዝዳንት የተመራው ልዑክ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎበኘ
*****************
በናይጄሪያው ምክትል ፕሬዝዳንት ካሺም ሼቲማ የተመራው ከፍተኛ ልዑክ በኦሮሚያ ክልል የተሰሩ የተለያዩ የልማት ስራዎችን በመጎብኘት የልምድ ልውውጥ አድርጓል፡፡
ከፍተኛ ልዑኩ በኦሮሚያ ክልል ያደረገው የመስክ ምልከታና የልምድ ልውውጥ ከስንዴ ክላስተር እስከ ማኑፋክቸሪንግ ባሉ ስትራቴጂካዊ የልማት መስኮች ላይ ያተኮረ እንደነበረ ተገልጿል፡፡
ልዑኩ በጉብኝቱ የኩቃ ዓሳ እርባታና የሉሚ እርሻ ኩርፊሳ ፕሮጀክትን፣ የ'ባሃሪ' አትክልት ልማት ኢኒሼቲቪን እንዲሁም የጃቡዱ ሞተርስ የጋራ አክሲዮን ኩባንያ ያሉ የልማት ስራዎችን ተዘዋውሮ ተመልክቷል፡፡
የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ጉብኝቱ በከተሞች መስፋፋት፣ በግብርናና ገጠር ሽግግር፣ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥና የሥራ ዕድሎችን በመፍጠር ዙሪያ ያተኮረ እንደነበር ገልጸዋል።
በክልሉ የተካሄዱት የመስክ ምልከታዎችም የግብርና ሽግግር እንቅስቃሴና የሕዝቡን የኑሮ ለውጥ በተግባር ያሳዩ እንደነበርም ጠቁመዋል።
በክልሉ ግብርናን ማዘመን የኢኮኖሚ ሽግግር መነሻ እንጂ የመጨረሻ ግብ አይደለም ያሉት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፤ ዋናው ዓላማ ሕዝቡን ከልማት ተመልካችነት ወደ ለውጥ ባለቤትነት ያሸጋገረ፣ ሀብት የሚያፈራና የተመጣጠነ ምግብ የሚያገኝ አምራች ገበሬ መገንባት መሆኑን አብራርተዋል።
በልዩ እሸቱ
#የመደመርመንግሥት
#ethiopia #ebc #medemer #nigeria #agriculture

የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ያለ ባሕር በር እውን ሊሆን አይችልም!
*******************
ከጥንታዊቷ እስከ ዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ቀይ ባህር የግዛቷ አካል ሆኖ መርከቦቿ ሲጠቀሙበት የኖሩ ሲሆን ጥንታዊት ኢትዮጵያን በአለም ላይ ከነበሩት ታላላቅ ሀይሎች አንዷ እንድትሆን ያደረጓት በወቅቱ ታስተዳድራቸው የነበሩት ወደቦቿ፣ የንግድ ትስስሮቿ እና "ባህረ ነጋሽ" የሚለው የማእረግ መጠሪያ ስያሜ እንደነበሩ ይታወቃል።
ሆኖም ሀገራችን በታሪክ አጋጣሚዎች እና በተደረጉባት እኩይ ሴራዎች ምክንያት ከሶስት አስርት አመታት በላይ የባህር በር አልባ ሆና በመቆየቷ ለከፍተኛ የኢኮኖሚ የጂኦ ፖለቲካ እና የብሄራዊ ደህንነት ማነቆዎች ተዳርጋ ኖራለች።
በተባበሩት መንግስታት የንግድና ልማት ጉባኤ መረጃ መሰረትም የባህር በር የሌላቸው ሀገራት ከአለም አማካይ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ወጪ በላይ ተጨማሪ ክፍያ ለማውጣት የሚገደዱ በመሆኑ ይህ ተፅእኖ በዜጎች እለታዊ የሸመታ አቅም፣ በሀገራችን የኢንቨስትመንት እድሎች እንዲሁም በአለም አቀፍ ደረጃ ከ95 በመቶ በላይ የሚሆነውን የዲጂታል መረጃ በሚያስተላልፉት ከባህር በታች ያሉ የፋይበር ኦፕቲክስ መስመሮች ተጠቃሚነት ላይ ከፍተኛ ጫና ሲፈጥር ቆይቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመደመር መንግስት ምስረታ ወቅት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደገለፁት የኢትዮጵያ ስልጣኔ ያለ ባህር በር እውን ሊሆን አይችልም፡፡
በመሆኑም በሰጥቶ መቀበል መርህ ኢትዮጵያ ወጥቶ መግቢያ በር እንዲኖራት አጥብቀን እንሰራለን ያሉም ሲሆን፤ ይህንን ታሪካዊ ስህተት እና የትውልድ ቁጭት ለመቅረፍ "የመደመር መንግስት" የባህር በር ጥያቄን ከወቅታዊ ፖለቲካ እና ከፓርቲ ወገንተኝነት በላይ በሆነ ትውልድ ተሻጋሪ ብሄራዊ አጀንዳ አድርጎ እንደሚሰራበት ተናግረዋል።
የመደመር መንግስት በያዘዉ ጠንካራ አቋም የኢትዮጵያ ስልጣኔና እድገት ያለ ባህር በር እውን ሊሆን ስለማይችል ሀገራችን በሰጥቶ መቀበል በጋራ ተጠቃሚነት እና በሰላማዊ ዲፕሎማሲ መርህ ወደ አለም የምትወጣበትን መስመር የማረጋገጥ ጉዞዋ ተጠናክሮ ይቀጥላል።
እውነተኛ ብሄራዊ ደህንነትና ሉአላዊነት የሚረጋገጠው ስትራቴጂካዊ ቁሳቁሶች ያለ ምንም የውጭ ጫና እገዳ ወይም የጎረቤት ሀገራት በጎ ፈቃድ በቀጥታ ወደ ሀገር ውስጥ መግባት ሲችሉ እንደመሆኑ መጠን ቀጥተኛ የባህር በር ማግኘት የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት እድሎችን በመክፈት የወጣቶችን ስራ አጥነት ከመቅረፉ ባሻገር ኢትዮጵያ በቀይ ባህር እና በስትራቴጂካዊ የውሃ አካላት ቀጠናዊ ውሳኔዎች ላይ ያላትን የዲፕሎማሲና የፖለቲካ ተሰሚነት ከፍ ያደርገዋል።
በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ተፈጥሯዊ እና ታሪካዊ አካል እንጂ ከሩቅ የመጣች እንግዳ እንዳልሆነችና በጂኦ ፖለቲካዊ ሴራዎች የባህር በር አልባ እንድትሆን መደረጓን ለአለም እያስረዳች ትገኛለች።
ኢትዮጵያ ቀይ ባህር ላይ እግሯን እንዳትተክል የሚደረጉ የተለያዩ የፖለቲካ የዲፕሎማሲ እና የፕሮፓጋንዳ ሸፍጦች አልቆሙም እነዚህን ሸፍጦች ሲጠነስሱ እንቅልፍ አጥተው የሚያድሩ አካላት መፍጨርጨራቸው ባይገታም ኢትዮጵያን በዘላቂነት ሊያግዷት አይችሉም።
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ የሰላም እና የአካባቢያዊ ትስስር ዋና ምሰሶ እንደመሆኗ የባህር በር ማግኘቷ ለአካባቢው ሀገራትም ቢሆን ትልቅ የኢኮኖሚ ጥቅም የሚያስገኝ በመሆኑ በቅርብም በሩቅም ያሉ ሀገራት ለኢትዮጵያ ቀና ምላሽ በመስጠት በጋራ መስራትን ተመራጭ ያደርጋሉ።
ፈጣን እድገት እያስመዘገበ ያለው ኢኮኖሚና ትልቅ ህዝብ ያላት ሀገር መሆኗም ይህን ግስጋሴ የሚያስተናግድ የባህር በር የማግኘት ትልሟን እውን ለማድረግ ትልቅ አቅም ይሆናታል።
በአጠቃላይ የታሪክ እውነታ የህግ መብት እና የህልውና ጥያቄ የኢትዮጵያን የባህር በር ባለቤትነት ጉዳይ አይቀሬ ያደርጉታል።
ይህንን አገራዊና ታሪካዊ ሀላፊነት ከግብ ለማድረስ የውስጥ አንድነትን ማፅናትና ደህንነትን ማረጋገጥ የሃሳብ ፖለቲካን ማጠናከር እና በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ሀገራዊ መግባባትን መፍጠር ወሳኝ መፍትሄ ነው።
በአለም አቀፍ የባህር ህግጋት እና በዲፕሎማሲያዊ አማራጮች የታገዘው ይህ ጥረት የመጪውን ትውልድ መብትና እድል የማስከበር የታሪክ ጥሪም ሲሆን ኢትዮጵያን በጠንካራ መሰረት ላይ ገንብቶ ለዘላቂ ብልፅግና የሚያሸጋግር ጨዋታ ቀያሪ ምእራፍ ነው።
ዛሬ ብርቱዋ ኢትዮጵያ ለሶስት አስርት አመታት ካቀረቀረችበት ቀና ብላለች የቀይ ባህር ተጋሪነቷን ለማደናቀፍ የሚደረጉ ማናቸውም ሸፍጦች ጊዜያዊ እንቅፋት ሊሆኑ ይችላሉ እንጂ የህዝቧን የታሪክ እና የተፈጥሮ መብት ሊያጠፉ አይችሉም።
ኢትዮጵያ አትቆምም የጂኦ-ፖለቲካ ሴራዎችን ሁሉ በጣጥሳ ከባህሩ ትደርሳለች ባህር ሀይሏና መርከቦቿም በቀይ ባህር ዳግም ይጓዛሉ።
በብሌን ደምበሎ
#የመደመርመንግሥት
#ethiopia #ebc #medemer #seaaccess #redsea #diplomacy

አዲስ የታሰረ የቃል ኪዳን ተስፋ በኢትዮጵያ ሰማይ ሥር
****************
ኢትዮጵያ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በስኬት ማካሄዷን ተከትሎ፣ አዲሱ የመደመር መንግሥት መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም በይፋ ተመስርቷል።
ይህ ዕለት የኢትዮጵያ አዲስ የተስፋ አድማስ የተበሰረበትና የሕዝቡ ዲሞክራሲያዊ ውሳኔ ዕውን የሆነበት ታሪካዊ ምዕራፍ ነው።
አዲሱ የመደመር መንግሥት ምስረታ ላለፉት ዓመታት የተጣሉትን የዕድገትና የተስፋ መሠረቶች አጠናክሮ በማስቀጠል፣ የሀገራችንን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ ያለመ ነው።
የመደመር እይታ ያለፉ ስኬቶችን በማስቀጠል፣ ክፍተቶችን በመሙላትና የቀጣይ ትውልድን ተስፋ በማገናኘት ሀገራዊ አንድነትንና ትብብርን ማዕከል ያደረገ አሰራርን ይዞ ይመጣል ተብሎ ይጠበቃል።
ላለፉት ዓመታት በመደመር መንግሥት ከተከናወኑ አበይት ተግባራት መካከል በቴክኖሎጂ፣ በኢንዱስትሪ፣ በማኅበራዊና ፖለቲካዊ ዘርፎች፣ በምግብ ሉዓላዊነት፣ በከተማ ልማት እንዲሁም በዲፕሎማሲ የተመዘገቡት ስኬቶች በዋናነት ይጠቀሳሉ።
በተጨማሪም የሕዳሴ ግድብን ማጠናቀቅና የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ራዕይ ሌሎች ማሳያዎች ናቸው።
አዲሱ የመደመር መንግሥት በተመሰረተበት የሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ የ2019 ዓ.ም የመደመር መንግሥት ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎችንና ግቦችን አብራርተዋል።
ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው፤ በሀገራችን ዘላቂ ሰላምን፣ ኅብረትንና ትብብርን ማስፈን፣ ጥራትን መሠረት ያደረገ መዋቅራዊ ሽግግር ማድረግ እንዲሁም የትምህርት፣ የጤና እና የማኅበራዊ ጥበቃ አገልግሎቶችን በጥራት ማሳደግ ዋነኛ ትኩረቶች መሆናቸውን ገልጸዋል።
በተጨማሪም የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ወደ 65 በመቶ፣ የጤና መድኅን ሽፋንን ወደ 85 በመቶ፣ እንዲሁም የተማሪዎች የምገባ ሽፋን ወደ 70 በመቶ ማሳደግ የተያዙ አበይት ግቦች መሆናቸውን አንሥተዋል።
በመሆኑም የመደመር መንግሥት ምስረታ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር፣ የሕግ የበላይነትን በማስከበርና የሕዝቦችን አብሮነት በማጠናከር ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ የሰላም፣ የፍትሕና የልማት ምዕራፍ የሚያሸጋግር አዲስ የቃል ኪዳን መስመር ይከፍታል።
በልዩ እሸቱ
#የመደመርመንግሥት
#ethiopia #ebc #medemer #medemergovernment #statebuilding

5 days ago
ጅማ አዌቱ አጠቃላይ ሆስፒታል ለመላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ለመደመር መንግሥት ምስረታ አደረሳችሁ ሲል መልዕክቱን ያስተላልፋል
#ethiopia #houseofpeoplesrepresentatives #houseoffederation #ትልቅ_ሀገር ! #ትልቅ_ሕዝብ ! #ታላቅ_ርዕይ ! #ethiopia #ebc #medemer #የመደመርመንግሥት
Sponsored by
Surafel
6 days ago
የኢትዮጵያ ምግብ መድሐኒት ባለስልጣን ለመላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ለመደመር መንግሥት ምስረታ አደረሳችሁ ሲል መልእክቱን ያስተላልፋል
#ethiopia #houseofpeoplesrepresentatives #houseoffederation #ትልቅ_ሀገር ! #ትልቅ_ሕዝብ ! #ታላቅ_ርዕይ ! #ethiopia #ebc #medemer #የመደመርመንግሥት
6 days ago
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ለመደመር መንግሥት ምስረታ አደረሳችሁ ሲል መልእክቱን ያስተላልፋል #ethiopia #houseofpeoplesrepresentatives #houseoffederation #ትልቅ_ሀገር ! #ትልቅ_ሕዝብ ! #ታላቅ_ርዕይ ! #ethiopia #ebc #medemer #የመደመርመንግሥት
6 days ago
"በሌሎች እሳቤ ኢትዮጵያን ከመቀየር ይልቅ ለኢትዮጵያ ሲባል የሌሎችን እሳቤ አቃንቶ መቀበል ተገቢ አካሄድ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
#የመደመርመንግሥት
#ethiopia #ebc #pmabiyahmed
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
#የመደመርመንግሥት
#ethiopia #ebc #pmabiyahmed
6 days ago
ግብርና ሚኒስትር ለመላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ለመደመር መንግሥት ምስረታ
አደረሳችሁ ሲል መልእክቱን ያስተላልፋል
#ethiopia #houseofpeoplesrepresentatives #houseoffederation #ትልቅ_ሀገር ! #ትልቅ_ሕዝብ ! #ታላቅ_ርዕይ ! #ethiopia #ebc #medemer #የመደመርመንግሥት
6 days ago
የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን
ለመላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ለመደመር መንግሥት ምስረታ
አደረሳችሁ ሲል መልእክቱን ያስተላልፋል #ethiopia #houseofpeoplesrepresentatives #houseoffederation #ትልቅ_ሀገር ! #ትልቅ_ሕዝብ ! #ታላቅ_ርዕይ ! #ethiopia #ebc #medemer #የመደመርመንግሥት
6 days ago
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

ጊፍት ሪልስቴት

Comments