22 hours ago
7ኛው ሀገራዊ የሳይበር ደኅንነት ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር በይፋ ተጀመረ!
ኩባንያችን ኢትዮ ቴሌኮም በዋና ስፖንሰርነት (Title Sponsor) የተሳተፈበት 7ኛው ሀገራዊ የሳይበር ደኅንነት ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር “ንቁ ዜጋ ደኅንነቷ ለተጠበቀ ሀገር” በሚል መሪ ቃል በይፋ ተጀምሯል።
የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ራዕይን ለማሳካት ተቋማችን የብዙ-ደረጃ መከላከያ (Defense-in-Depth) እና የዜሮ-ትረስት (Zero Trust Architecture) ደኅንነት ስትራቴጂዎችን ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል። ከዚህም ባሻገር ከኢንፎርሜሽን መረብ ደኀንነት አስተዳደር (INSA) ጋር በመተባበር የህፃናትን ኦንላይን ደኅንነት ለማስጠበቅ የሚያስችሉ እንደ Child-Safe SIMs፣ የመኖሪያ ቤት የብሮድባንድ DNS Filtering እና Deep Packet Inspection (DPI) ያሉ የላቁ የቴክኖሎጂ መፍትሔዎችን በመተግበር ላይ እንገኛለን።
የሳይበር ደኅንነት የመንግሥት አካላት፣ የቴሌኮም ኦፕሬተሮች፣ የትምህርት ተቋማትና የእያንዳንዱ ዜጋ የተቀናጀ የጋራ ኃላፊነት እንደመሆኑ ያልተረጋገጡ ሊንኮችን ባለመክፈት፣ ጠንካራ የይለፍ ቃላትን በመጠቀምና የህፃናትን ኦንላይን ደኅንነት በጥንቃቄ በመጠበቅ የሳይበር ጥንቃቄን የዘወትር ልማዳችን እንድናደርግ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
#cybersecuritymonth #ethiotelecom #insa #securebyhabit #childonlinesafety #cybersecurity #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia

Comments