22 days ago
"ከአሁን በኋላ መንገድ ላይ ጉድጓድ
ካየሁ ኮንትራክተሩ ያልቅለታል!"
የኡጋንዳው ታዋቂ ጄኔራል ሙሆዚ ካይነሩጋባ በሙስና በተዘፈቁ የመንገድ ተቋራጮች ላይ ጠንካራ እርምጃ እንደሚወስዱ ዝተዋል። "የመንገድ ግንባታ ክፍያ ከፍለን ካበቃን በኋላ በመንገዱ ላይ አንድም ጉድጓድ ካየሁ፣ ያ ኮንትራክተር በህይወቱ ይከፍላል" ሲሉ ባለሙሉ ስልጣኑ ጄኔራል በይፋ አስታውቀዋል።
seledadotio

4 months ago
ደቡብ ሱዳን ያልወጡ ወርቆቿን አሲዛ የመንገድ ፕሮጀክቶችን ልትጀምር ነው
#ethiopia | የደቡብ ሱዳን መንግሥት የሀገሪቱን የተፈጥሮ ሀብት ለልማት ለማዋል ባደረገው አዲስ ውሳኔ፣ የወርቅ ክምችቷን ዋስትና በማስያዝ የ2 ቢሊየን ዶላር የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን ሊያከናውን መሆኑን አስታወቀ።
የሀገሪቱ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት፣ በጠቅላላው 1,031 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ያላቸውን መንገዶች ለመገንባትና ደረጃቸውን ለማሻሻል "ሻምሮክ ግሎባል ግሩፕ" (Shamrock Global Group) ከተሰኘ ተቋም ጋር ስምምነት ላይ ተደርሷል። ለዚህም ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ ይሆን ዘንድ የሀገሪቱ የወርቅ ክምችት በዋስትናነት እንዲያዝ ተወስኗል።
የደቡብ ሱዳን የማስታወቂያ ሚኒስትር አቴኒ ዌክ እንደገለጹት፦
* ለፕሮጀክቱ አጠቃላይ 2 ቢሊየን ዶላር ወጪ ይደረጋል።
* በአማካይ ለአንድ ኪሎ ሜትር መንገድ ግንባታ 2.3 ሚሊየን ዶላር ይፈጃል።
ይህ ግዙፍ የኢንፍራስትራክቸር ዕቅድ የሀገሪቱን የትራንስፖርት ትስስር በማጠናከር ለኢኮኖሚ እድገት ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል። ደቡብ ሱዳን ከነዳጅ ውጪ ያሉ የተፈጥሮ ሀብቶቿን ለልማት ዋስትና ስትጠቀም ይህ የመጀመሪያው ባይሆንም፣ በወርቅ ክምችት ላይ የተመሰረተው የዘንድሮው ስምምነት ግን በስፋቱና በወጪው ከፍተኛ ተጠቃሽ ሆኗል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ደቡብ_ሱዳን #የመንገድ_ግንባታ #ወርቅ #አፍሪካ #ኢኮኖሚ #southsudan #infrastructure #goldreserve

የጎፋ ካምፕ - መብራት ኃይል - ኖክ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ በጥሩ ፍጥነት ላይ ይገኛል! 🚧✨
#ethiopia | የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን የትራፊክ ፍሰቱን ለማሳለጥና የአካባቢውን ማህበረሰብ የትራንስፖርት እንግልት ለመቀነስ የጀመረውን የጎፋ ካምፕ - መብራት ኃይል ኮንዶሚኒየም - ኖክ የመንገድ ግንባታ በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ በትጋት እየሰራ ነው።
የፕሮጀክቱ ቁልፍ መረጃዎች፦
📏 ልኬት፦
መንገዱ 988 ሜትር ርዝመት እና 20 ሜትር የጎን ስፋት አለው።
🏗️ አሁናዊ ሁኔታ፦
በአሁኑ ወቅት የገረጋንቲ ሙሌት፣ የከርቭስቶን ስራ እና የሰቤዝ (Sub-base) ግንባታዎች በከፍተኛ ፍጥነት እየተከናወኑ ይገኛሉ።
🔄 የለውጥ እርምጃ፦
ግንባታው ቀደም ሲል በሀገር በቀል ተቋራጭ ተጀምሮ የነበረ ቢሆንም፣ በመዘግየቱ ምክንያት ውሉ ተቋርጦ አሁን በባለሥልጣኑ የራስ ኃይል (ደቡብ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት) እየተገነባ ይገኛል።
የመንገዱ ፋይዳ፦
ይህ መንገድ ሲጠናቀቅ ከጎፋ ካምፕ በመብራት ኃይል ኮንዶሚኒየም በኩል ወደ ጎፋ ገብርኤል፣ ላፍቶ እና ተቃራኒ አቅጣጫዎች የሚደረገውን የትራፊክ ፍሰት በአቋራጭ በማሳለጥ የነዋሪውን እንግልት በእጅጉ ይቀንሳል።
#addisababaroads #infrastructure #gofacamp #roadconstruction #ethiopia #addisababa #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

5 months ago
በአዲስ አበባ አንዳንድ መንገዶች ላይ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ተከለከለ
የአዲስ አበባ ፖሊስ በከተማዋ እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማትና የመንገድ ግንባታ ስራ ለማፋጠን እንዲቻል፣ በተወሰኑ መስመሮች ላይ ተሽከርካሪዎችን አቁሞ መሄድ (Parking) ሙሉ በሙሉ መከልከሉን አስታውቋል።
📍 ክልከላው የተጣለባቸው ዋና ዋና መስመሮች፦
ከቅዱስ ኡራኤል — በአትላስ ሆቴል (ኤድሞል) በኩል እስከ ቦሌ ብራስ።
በአደይ አበባ ስታዲየም ዙሪያ ያሉ መንገዶች።
🚧 የክልከላው ምክንያት፦
በእነዚህ ቀጠናዎች የሚቆሙ ተሽከርካሪዎች በግንባታው ሂደት ላይ እንቅፋት እየፈጠሩ በመሆኑና የልማት ስራው የሚጠቀማቸው ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ እንዳይገደብ ለማድረግ ነው።
⚠️ ለአሽከርካሪዎች የተላለፈ ጥብቅ ማሳሰቢያ፦
ክልከላው ከዛሬ ጥር 04 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ሆኗል።
በስራው ላይ ከተሰማሩ ተሽከርካሪዎች ውጭ ማንኛውም የግልም ሆነ የህዝብ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት የተከለከለ ነው።
አሽከርካሪዎች አማራጭ የመኪና ማቆሚያ ቦታዎችን በመጠቀም ከአላስፈላጊ ቅጣትና እንግልት ራሳቸውን እንዲጠብቁ ፖሊስ አሳስቧል።

Sponsored by
Surafel
5 months ago
የመንገድ ግንባታ በሚደረግባቸው ቦታዎች ተሽከርካሪዎችን አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማትና የመንገድ ግንባታ በሚደረግባቸው ከቅዱስ ኡራኤል፣ በአትላስ ሆቴል ኤድሞል እስከ ቦሌ ብራስ ድረስ፣ እንዲሁም አደይ አበባ ስታዲየም፣ አካባቢዎች የሚቆሙ ተሽከርካሪዎች በመንገድ ስራው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደሩ በመሆኑ ከዛሬ ጥር 04 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ በተጠቀሱት አካባቢዎች ላይ የግንባታ ስራውን ከሚያከናውኑት ተሽከርካሪዎች በስተቀር ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት ተሽከርካሪን አቁሞ መሄድ ፈፅሞ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ያሳስባል፡፡
Addis Ababa police

6 months ago
ባሕርዳር : ከተማዋን ከጣና ሀይቅ ጋር የሚያስተሳስር የመንገድ ግንባታ አየተገነባ ነው
#ethiopia | የባሕርዳር ከተማ አስተዳድር የኮሪደርና የጣናዳር ልማት አካል የሆነው ከአማራ ልማት ማህበር እስከ ዋተርፍሮንት ሆቴል አስፓልት የማንጠፍ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገለጸ።
የመንገድ ግንባታ ሂደቱ የከተማው የመንግስት አመራሮች በተጎበኘበት ወቅት እንደተገለጸው መንገዱ ለነዋሪዎች ዘመናዊ እና የተሳለጠ የትራንስፖርት አገልግሎት ከመስጠት በተጨማሪ ከተማዋን ከጣና ሀይቅ ጋር በማስተሳሰር ተጨማሪ ውበት እንደሚፈጥር ተገልጿል።
የባህርዳር ከተማ ከንቲባ አቶ እንዳላማው ጎሹ በጉብኝት መርሐግብሩ ላይ እንደገለጹት "የመንገዱ ግንባታው የመኪና፣ የእግረኛ፣ የብስክሌት፣ የግሪነሪ ልማቶችን ያካተተ ሲሆን የመብራት፣ የቴሌ፣ የውሀ መስመሮች በዘላቂነት በመሰረተ ልማት ስራው ተቀናጅተው መሠራቱን ገልጸዋል።
በሬማ ጀኔራል ቢዝነስና ኮንስትራክሽን አማካኝነት ከአልማ ዋተርፍሮንት ሆቴል እየተነባ የሚገኘው ዘመናዊ መንገድ በቅድመ ክፍያ ብቻ አስፓልት የማንጠፍ ስራ እየተከናወነ መሆኑን የሬማ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ማናጀር አቶ አቤኔዘር ማስረሻ ገልጸዋል።
ይህ መንገድ በመሠራቱ የአካባቢው ነዋሪ እጅግ ደስተኛ በመሆኑ የባህርዳር ከተማ አመራሮችንና ሬማ ኮንስትራክሽንን እያመሠገነ እንደሚገኝ አቶ አቤኔዘር ገልጸዋል።
የአስፓልት ስራው የ3 ወር እቅድ ቢሆንም በመሀል የነበረው የክረምት ሁኔታ ተጨማሪ ቀናቶችን ቢወስድም በአድቫንስ ብቻ በአጭር ጊዜ መንገዱን ሰርቶ ለማጠናቅቅ በሂደት ላይ መሆኑን ገልጸዋል።
የኮንክሪት አስፓልት መንገዱ 8 መቶ ሜትር ርዝመት እና 40 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ሲሆን ይህ አስፓልት በፍጥነትና በቅድመ ክፍያ ብቻ እየተሰራ መሆኑን የሬማ ኮንስትራክሽን ባለቤትና መሥራች አቶ ፍቅሬ አስፋው ተናግረዋል።
በጉብኝቱ መርሐግብር ላይ አቶ ጎሹ እንዳላማው የባሕርዳር ከተማ ከንቲባ፣ አቶ ሞላ ሁሴን የባሕርዳር ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ፣ አቶ አስሜ ብርሌ የባሕርዳር ከተማ ምክትል ከንቲባ በቦታው ተገኝተዋል።

በአዲስ አበባ የውስጥ ለውስጥ መንገድ አጥሮች እንዲነሱ ባለሥልጣኑ አስጠነቀቀ
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን፣ በከተማዋ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን አጥረው የዘጉ ግለሰቦች መንገዶቹን በሰባት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ክፍት እንዲያደርጉ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ አስተላልፏል።
ባለሥልጣኑ በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች የተገነቡ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች በሕገወጥ መንገድ በግለሰቦች ታጥረው የተዘጉ መሆናቸውን ጠቅሷል።
ይህ ሕገወጥ ድርጊት የሕብረተሰቡን በመንገድ ሀብት የመጠቀም መብት ከመጋፋቱም በላይ፣ የትራፊክ እንቅስቃሴው እንዲስተጓጎል አሉታዊ ተፅእኖ እያሳደረ መሆኑንም አክሎ አስታውቋል።
በመሆኑም፣ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በሁሉም የከተማዋ ክፍሎች የሚገኙ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን አጥረው የዘጉ አካላት በሙሉ፤ ከዛሬ ቅዳሜ ታኅሣሥ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ሰባት ተከታታይ ቀናት ውስጥ መንገድ የዘጉበትን አጥር እንዲያነሱ እና መንገዱን ለትራፊክ እንቅስቃሴ ክፍት እንዲያደርጉ በጥብቅ አሳስቧል።
በሁሉም የከተማዋ ማዕዘናት መጠነ-ሰፊ የመንገድ ግንባታና ጥገና ሥራዎች እያከናወነ እንደሚገኝ የገለጸው ባለስልጣኑ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ አጥር የማያነሱ አካላት በሕግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ ባለሥልጣኑ አስታውቋል።

ሁለተኛው ምዕራፍ የደቡብ ሱዳን -ኢትዮጵያ- ጂቡቲ የትራንስፖርት ኮሪደር
የአፍሪካ ልማት ባንክ ለሁለተኛው ምዕራፍ የደቡብ ሱዳን -ኢትዮጵያ- ጂቡቲ የትራንስፖርት ኮሪደር ግንባታ ማስጀመሪያ የ214 ነጥብ 47 ሚሊየን ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ አፀደቀ።
ባንኩ ባወጣው መግለጫ 181 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር በኢትዮጵያ በኩል ለሚካሄደው የፕሮጀክቱ አካል ድጋፍ ይውላል ብሏል።
ገንዘቡ ለ67 ኪሎ ሜትር የፍጥነት መንገድ ግንባታ እና የ50 ኪሎ ሜትር መጋቢ መንገዶች ማሻሻያ ይውላል።
የመንገድ ግንባታው የሀገራቱን ግንኙነት ለማጠናከር ብሎም ቀጠናዊ የንግድ ትስስር እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ እንደሚረዳ ባንኩ አስታውቋል።

7 months ago
ከቦሌ ኤርፖርት ወደ ጎሮ የሚወስደው መንገድ ከዛሬ ጀምሮ ለሦስት ቀን ያህል በከፊል ዝግ ነው ተባለ
#ethiopia | የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ከቦሌ ኤርፖርት ወደ ጎሮ የሚወስደው መንገድ የመጨረሻ ደረጃ ተደራራቢ አስፋልት የማልበስ ስራ እያከናወነ መሆኑን አስታውቋል፡፡
በዚህም ምክንያት ከህዳር 15 ጀምሮ ለሦስት ቀናት ያህል ከቦሌ አቅጣጫ ወደ ጎሮ ሚወስደው የመንገዱ ክፍል በከፊል ለትራፊክ ዝግ ይሆናል ሲሉ በአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ እያሱ ሰለሞን ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም የጥገና ስራው ሙሉ በሙሉ እስኪጠናቀቅ ድረስ መንገዱ ለትራፊክ እንቅስቃሴ ዝግ በመሆኑ አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን አሳስቧል።
የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱ በአጠቃላይ 4 ነጥብ 9 ኪሎ ሜትር ርዝመትና 60 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ነው፡፡

8 months ago
የዓለምገና - ቡታጅራ መንገድ ግንባታ እየተካሄደ ነው
ቡታጅራ፣ ጥቅምት 07፣ 2018 (ኢ መ አ):- የኦሮሚያ እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎችን ጨምሮ በርካታ አካባቢዎችን የሚያስተሳስረው የዓለምገና - ቡታጅራ መንገድ ፕሮጀክት እየተካሄደ ነው።
የመንገድ ፕሮጀክቱ ወደ አዳዲ ማርያም ገዳም የሚወስደውን የ12 ነጥብ 7 ኪሎሜትር መንገድ ጨምሮ በጥቅሉ 132 ነጥብ 7 ኪሎሜትር የሚሸፍን ሲኾን፥ በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ በመገንባት ላይ ይገኛል።
ከጥቂት ወራት በፊት የተጀመረው የመንገድ ግንባታው አሁን ላይ የአፈር ቆረጣ እና ሙሌት፣ የውኃ መፋሰሻ ቱቦ ቀበራ እንዲሁም የፉካ ሥራዎች በመከናወን ላይ ናቸው።
የመንገድ ፕሮጀክቱ በከተማ ክልል የብስክሌት እና የእግረኛ መንገድ፣ የአነስተኛ እና ከፍተኛ ከልቨርቶች እንዲሁም የ16 ድልድዮች ግንባታ አካትቷል።
የመንገድ ግንባታውን የሚያከናውናው ሀገር - በቀሉ የንኮማድ ኮንስትራክሽን በርካታ ማሽነሪዎችን ወደ ሥፍራው በማንቀሳቀስ ፕሮጀክቱን ለማፋጠን እየሠራ ይገኛል። የማማከር እና የቁጥጥር ሥራውን ኤ አይ ሲ ፕሮጀቲስፓ ከስትራይድ ኮንሰልቲንግ ኢንጅነርስ ጋር በጥምረት ያከናውናሉ። ለመንገድ ግንባታው የተመደበው 14 ቢሊዮን ብር በፌደራል መንግስት በጀት ይሸፈናል።
መንገዱ ከዚህ ቀደም ጠባብ እና በአገልግሎት ብዛት በእጅጉ የተገጎዳ ሲኾን፣ አሁን ላይ በየጊዜው እየጨመረ የመጣውን ከፍተኛ የትራፊክ ፍስሰት ማስተናገድ እንዲያስችል በዞን መቀመጫ የመንገድ አካፋይ፣ የእግረኛ እና የብስክሌት መንገድ ጨምሮ 26 ሜትር ስፋት ይኖረዋል። በወረዳ ከተማ 19 ሜትር፣ በቀበሌ ከተማ 12 ሜትር እንዲሁም በገጠር የመንገድ ትከሻን ጨምሮ 10 ሜትር የጎን ስፋት ይኖረዋል።
የመንገድ ግንባታው ሲጠናቀቅ በፊት ከዓለምገና ቡታጅራ ለመጓዝ የሚወስደውን ከ3 ሰዓት በላይ የጉዞ ጊዜ ወደ 1 ሰዓት ተኩል ያሳጥረዋል።
በአካባቢው የሚገኙትን የጥያ ትክል ድንጋይ መካነ-ቅርስ እንዲሁም የአዳዲ ማርያም ገዳም የቱሪስት መዳረሻዎችን ለጎብኘዎች ምቹ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል።
በመንገዱ የሚገኙትን ዓለምገና፣ ሌመን፣ ተሬ፣ ጥያ፣ ሱተን፣ ኬላ፣ ቡታጅራ እና መሰል ከተሞች ማኅበራዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ ትስስር ያጠናክራል።
በተጨማሪም የተለያዩ የግብርና ምርት ውጤቶችን በቀላሉ ወደ ማዕከላዊ ገበያ ለማድረስ ያስችላል።

9 months ago
ኢትዮጵያና ጅቡቲ አዲስ የትራንስፖርት መስመር ለመገንባት ተስማሙ
#ethiopia | ቀጣናዊ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኡጋንዳን የሚያገናኝ ነው፡፡
የትራንስፖርትና ሎጂቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ እና የጅቡቲ አቻቸው ሀሰን ሁመድ፤ የዲካሂል-ጋላፊን ፕሮጀክት ለማጠናቀቅ እና የደሱ ኮሪደርን ለማቋቋም እና ወደትግበራ ለመግባት የጋራ መግባባት ላይ ደርሰዋል።
የደሱ ኮሪደር የባሕር ባር ለሌላቸው ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን አማራጭ የንግድ መስመር ሆኖ ያገለግላል፡፡
የንግድ ፍሰቱን ማሳደግ፣ የሎጀሰቲክስ ወጪን መቀነስና ድንበር ተሻጋሪ ትስስርን ማስፋት የኮሪደሩ መገንባት ዋነኛ ግብ ነው፡፡
በዓመቱ አጋማሽ አራቱ ሀገራት የደሱ ኮሪደርን አስመልክቶ የመገባቢያ ስምምነት መፈራረማቸው የሚታወስ ነው ሲል ኢትዮ ኤፍ ኤም ዘግቧል፡፡

11 months ago
በበጀት ዓመቱ ከ1 ሺ 391 ኪሎ ሜትር በላይ የመንገድ ግንባታና ጥገና ስራ ተከናውኗል
#ethiopia | የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በ2017 በጀት ዓመት 1 ሺ 391.5 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚሸፍኑ ልዩ ልዩ የግንባታና የጥገና ስራዎችን በማከናወን የዕቅዱን 117 በመቶ አፈፃፀም አስመዝግቧል፡፡
የ2017 በጀት ዓመት ጥቅል የመንገድ ግንባታና ጥገና አፈፃፀም ከ2016 ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነፃፀርም የ25 በመቶ ብልጫ አሳይቷል፡፡
በበጀት ዓመቱ ከ 370 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት የሚሸፍኑ ልዩ ልዩ የመንገድ ግንባታ ስራዎች የተከናወኑ ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል በጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ የተገነቡትን መንገዶች ጨምሮ 69.3 ኪሎ ሜትር የአስፋልት፣ 16 ኪሎ ሜትር የጠጠር እና 95.2 ኪሎ ሜትር የኮብል ንጣፍ መንገድ ስራ ተከናውኗል፡፡
በሌላም በኩል 107 ኪሎ ሜትር የነባር እግረኛ መንገዶች መልሶ ግንባታ ከመከናወኑም በተጨማሪ ከ79 ኪሎ ሜትር በላይ የፔዳል ሳይክል መንገድ የግንባታ ስራ ተካሄዷል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከግንባታ ስራዎች ጎን ለጎን፤ 110 ኪሎ ሜትር የአስፋልት፣ 23 ከ.ሜ የጠጠር፣ 29 ኪሎ ሜትር የኮብል መንገድ ጥገና አካሂደዋል።
ከዚህም በተጨማሪ የጎርፍ አደጋ ስጋትን ለመከላከል 483 ኪሎ ሜትር የድሬኔጅ መስመር ፅዳትና ጥገና፣ እንዲሁም ከ19 ኪሎ ሜትር በላይ የእግረኛ መንገድ ጥገናና የከርቭ ስቶን ስራዎች በድምሩ 1021 ኪሎ ሜትር ልዩ ልዩ የጥገና ስራዎችን በበጀት ዓመቱ አጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ማድረጉን ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡

ብራዚል በሸንኮራ አገዳ ተረፈ ዘላቂና ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑ መንገዶችን እየገነባች መሆኑ ተገለጸ
📌ከባህላዊ የአስፋልት መንገዶች የበለጠ ጠንካራ እና ረጅም ጊዜ የሚቆዩ እንደሆነም ተገልጿል::
#ethiopia | ብራዚል፣ ዘላቂ ልማትንና የአካባቢ ጥበቃን የሚያስቀድም አዲስና አስደናቂ የቴክኖሎጂ ፈጠራ በማስተዋወቅ ላይ ትገኛለች ተብሏል። አገሪቱ ከሸንኮራ አገዳ ምርት ከሚገኘው ብክነት ጠንካራ፣ ዘላቂነት ያላቸው እና ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑ መንገዶችን በመገንባት ላይ መሆኗን አስታውቃለች።
ይህ አዲስ ዘዴ፣ በአብዛኛው ወደ ቆሻሻ የሚሄደውን የሸንኮራ አገዳ ተረፈ ምርት በመጠቀም፣ የመንገድ ግንባታ ወጪን ከመቀነስ ባለፈ፣ ለአካባቢ ጥበቃም ትልቅ አስተዋፅኦ ያደርጋል። አዲሶቹ መንገዶች ከባህላዊ የአስፋልት መንገዶች የበለጠ ጠንካራ እና ረጅም ጊዜ የሚቆዩ እንደሆኑ ተገልጿል። ይህም የመንገድ ጥገና ወጪን በእጅጉ የሚቀንስ ሲሆን፣ የአካባቢ ብክለትንም ይቀንሳል ነው የተባለው፡፡
የዚህ ፕሮጀክት ትግበራ ብራዚልን በመንገድ ግንባታ ቴክኖሎጂ ውስጥ ቀዳሚ ከሆኑት አገራት ተርታ እንድትሰለፍ ያስችላታል የተባለ ሲሆን ይህ ፈጠራ የግብርና ምርቶችን ተረፈ ምርት ወደ ጠቃሚ ሀብት በመቀየር፣ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ጥቅሞችን በማስገኘት ረገድ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ትልቅ ትምህርት ሊሆን ይችላል ነው የተባለው።
ሌሎች አገሮችም ይህን የመሰለ ዘላቂነት ያለው የመንገድ ግንባታ ዘዴን ለመተግበር ፍላጎት እያሳዩ መሆኑ ተመላክቷል። #menahriafm

ዘመናዊ የመንገድ ደህንነት ባለመኖሩ አካል ጉዳተኞች ለትራፊክ አደጋ እየተጋለጡ ነው ተባለ
#ethiopia | አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የክልል ከተሞች ዘመናዊ የመንገድ ግንባታ እየተሰራ ቢሆንም፣ አካል ጉዳተኞችን ያማከለ አለመሆኑን የአካል ጉዳተኛ ሴቶች ብሄራዊ ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ድባቤ ባጫ ገልጸዋል፡፡
ለአካል ጉዳተኞች በድምፅ፣ በምስል እና በተለያዩ አማራጮች የተደገፉ ስራዎች እንደማይሰሩ አክለዋል።
በበጀት ዓመቱ በተደረገው የ6 ወራት ጥናት በመዲናዋ 3 ሴት አካል ጉዳተኛ የብሔራዊ ማህበሩ አባላት በትራፊክ አደጋ ህይወታቸው ማለፉን ገልጸዋል፡፡
የዊልቸር ተጠቃሚዎችን ጨምሮ ለአይነ ስውራን በድምጽ፤ መስማት ለተሳናቸው ደግሞ በምስል የተደገፈ መረጃ በተለይ በዋና ዋና ማቋረጫ መንገዶች ላይ ባለመኖሩ ችግሩን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያባባሰው መሆኑንና ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡
ከመንገድ ደህንነት፤ ከመንገድ ትራንስፖርት ቢሮ እና ሌሎች ባለድርሻ ተቋማት ጋር በጋራ የመስራት ክፍተት እንዳለ ያመላከቱት ስራ አስፈፃሚዋ፣ የደጋውን መጠን ለመቀነስ ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ መስራት ይገባል ብለዋል።
የመንገድ ደህንነትና መድህን ፈንድ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አባሶ፣ አገልግሎቱ የትራፊክ አደጋ የሚበዛባቸው አካባቢዎችን በመለየት ከተለያዩ የመንግስትና የግል ተቋማት ጋር እንደሚሰራ ተናግረዋል።
አካል ጉዳተኞች በስፋት ለትራፊክ አደጋ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸው፣ ዘመናዊ አሰራርን ከመዘርጋት አንጻር በትብብር እንደሚሰሩ አስታውቀዋል፡፡
በሌላ በኩል በበጀት አመቱ በአዲስ አበባ ከተማ የትራፊክ አደጋን ለመቀነስና ፍሰቱን ለማሳለጥ በርካታ ስራዎች እንደተሰሩ የከተማ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ገልጿል፡፡
የቢሮው ሃላፊ ወ/ሮ እናታለም መለስ በበጀት አመቱ ሁሉንም የአካል ጉዳት አይነት ያማከለ 53 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን መንገድ መገንባቱን አስታውቀዋል።
ይህም የአካል ጉዳተኞችን የትራፊክ አደጋ ተጋላጭነት ለመቀነስ እንደሚረዳ ገልፀዋል፡፡
በሃገር አቀፍ ደረጃ በትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን የሚያጡ ዜጎች ቁጥር በአመት ከ3 ሺህ እስከ 4ሺህ እንደሚደርስና በልዩነት ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ መስራት እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡ #menahriafm

Comments