4 months ago
ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2027 የሚካሄደውን የዓለም አቀፍ የፀረ-ዶፒንግ ትምህርት ጉባኤን እንድታስተናግድ በይፋ ተመረጠች
#ethiopia | ሀገራችን ኢትዮጵያ ለስፖርቱ ዘርፍ ዕድገት ለሰጠችው ልዩ ትኩረት ትልቅ ማሳያ የሚሆንና ከፍተኛ ፋይዳ ያለው ዓለም አቀፍ የባህልና የስፖርት ኩነትን የማዘጋጀት ዕድል አግኝታለች።
በዓለም አቀፉ የፀረ-ዶፒንግ ኤጀንሲ አስተናጋጅነት በየወቅቱ የሚካሄደው የዓለም አቀፍ የፀረ-ዶፒንግ ትምህርትና ሥልጠና ጉባኤ በፈረንጆቹ 2027 በኢትዮጵያ እንዲሰናዳ ተወስኗል።
ይህ ትልቅ መድረክ በፀረ-አበረታች ቅመሞች እንቅስቃሴ ላይ ሰፊ ተፅዕኖ ያለው ሲሆን ቀደም ሲል እ.ኤ.አ በ2018 በቻይና ቤጂንግ፣ በ2022 በአውስትራሊያ ሲድኒ እንዲሁም በ2024 በፈረንሳይ ፓሪስ መካሄዱ ይታወሳል።
ይህ የዓለም አቀፍ የፀረ-ዶፒንግ ትምህርት ጉባኤ በአፍሪካ አህጉር ሲካሄድ የአሁኑ የመጀመሪያው ነው። በመሆኑም መድረኩ ለሀገራችን መልካም ገጽታ ግንባታና ለስፖርት ቱሪዝም ዕድገት ከሚያበረክተው ዘርፈ ብዙ ጥቅም ባለፈ በአህጉር ደረጃ ንጹህ ስፖርትን ለማስፋፋትና የፀረ-አበረታች ቅመሞች ቁጥጥርን ይበልጥ ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።
ከምንም በላይ ደግሞ ኢትዮጵያ የአበረታች ቅመሞች ወይም የዶፒንግ መከላከል ሥራዎችን በመደበኛው የትምህርት ሥርዓት ውስጥ በማካተት፣ ጠንካራ የሕግ ማዕቀፎችን በማውጣት፣ እንዲሁም አስተማማኝ የምርመራና የቁጥጥር ሥርዓቶችን በመዘርጋት ረገድ ያስመዘገበቻቸውን በርካታ ስኬቶች ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በተግባር ለማሳየትና ለማስተዋወቅ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል።
#wada #globaleducationconference #cleansport #antidoping #sportstourism #africasports #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

የተከለከለ ንጥረ መድሃኒት በመጠቀሟ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለአራት ወራት ከውድድር ታገደች
የአትሌቲክስ ስነ ምግባር ክፍል (AIU) ባለ ሁለት ጊዜ የዓለም ሻምፒዮና እና የኦሎምፒክ ሜዳሊያ ባለቤቷ ኢትዮጵያዊት አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ላይ የ4 ወራት እገዳ መጣሉን ዛሬ ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ይፋ አደረገ።
ይህ እገዳ እስከ መስከረም 20 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ይቆያል።
የእገዳው መንስኤ ባለፈው ህዳር ወር መጨረሻ ከተወሰደባት የሽንት ናሙና ላይ ‘ሌትሮዞል’ የተባለ የተከለከለ ንጥረ ነገር በመገኘቱ ነው።
አትሌቷ ክሱ በደረሳት ማግስት ንጥረ ነገሩ ለታመመችው ህክምና በሀኪም የታዘዘላት መሆኑን የሚያሳይ ሙሉ የህክምና ሰነድ አቅርባለች።
የዓለም አትሌቲክስ የህክምና ኮሚቴ ጉዳፍ ህክምናው እንደሚያስፈልጋት ቢያረጋግጥም፣ ከዓለም ፀረ-ዶፒንግ ኤጀንሲ (WADA) አስቀድማ የህክምና ፈቃድ (TUE) ሳታስፈቅድ በመቅረቷ የላቀ ኃላፊነት ህግን ተላልፋለች ብሏል።
ይሁን እንጂ አትሌቷ ሆን ብላ ያደረገችው አለመሆኑ በመረጋገጡ እና ጥፋቱን በፍጥነት በመቀበሏ፣ ሊጣልባት ይችል የነበረው የሁለት ዓመት ቅጣት ወደ አራት ወራት ዝቅ እንዲል ተደርጓል።
Seledadotio

አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ እና አትሌት ዘመናይ አያና የፀረ-አበረታች ቅመሞች የህግ ጥሰት መፈፀማቸው በመረጋገጡ ቅጣት ተጣለባቸው።
አትሌት ጉዳፍ ፀጋየ እና አትሌት ዘመናይ አያና ቀደም ሲል በተደረጉ የአበረታች ቅመሞች (ዶፒንግ) ምርመራዎች የተከለከሉ አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግ በመጠቀም ተጠርጥረው ጉዳያቸው ሲጣራ ቆይቷል።
በዚህም መሰረት የአለም አትሌቲክስ ኢንተግሪቲ ዩኒት(AIU) እ.ኤ.አ ዲሴምበር 05 ቀን 2025 ዓ.ም ከውድድር ጊዜ ውጭ ባካሄደው ምርመራ አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ ‘ሌትሮዞል’ (Letrozole) የተባለውንና በማንኛውም ጊዜ እንዳይሰድ የተከለከለውን መድኃኒት ተጠቅማ መገኘቷ ተረጋግጧል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ባለፉት ጊዜያት ጉዳዩ ሲታይ የቆየ ሲሆን የአለም አቀፉ የፀረ-ዶፒንግ ኤጀንሲ (WADA) እና የአለም አትሌቲክስ ኢንተግሪቲ ዩኒት (AIU) ከአትሌቷ ጋር በተፈጠረ የጋራ ስምምነት (Case Resolution Agreement) በአትሌቷ ላይ እ.ኤ.አ ከሰኔ 01/2026 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 30/2026 ዓ.ም የአራት (4) ወር እገዳ (Period of Ineligibility) ቅጣት ተጥሏል፡፡ በተጨማሪም አትሌቷ እ.ኤ.አ ከዲሴምበር 5/2025 ዓ.ም ጀምሮ ያስመዘገበቻቸው የውድድር ውጤቶች በሙሉ እንዲሰረዙ፣ ሜዳሊያዎች እና የገንዘብና ሌሎችም ሽልማቶች እንዲመለሱ ተወስኗል። የህግ ጥሰቱ የተፈፀመው ከአትሌቷ ጤንነት ጋር በተያያዘ በተሰጠ የህክምና ፈቃድ አገልግሎት (Therapeutic Use Exemption) እንደሆነ የተመላከተ ሲሆን የተሰጠው ውሳኔም ይግባኝ የማይቀርብበትና የመጨረሻ ውሳኔ መሆኑ ታውቋል።
በተመሳሳይ መልኩ የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን (ETH-ADA) በአትሌት ዘመናይ አያና ላይ እ.ኤ.አ
ግንቦት 4/2025 ዓ.ም ከውድድር ጊዜ ውጪ ባካሄደው የአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ምርመራ አትሌቷ 'የአናቦሊክ አንድሮጄኒክ ስቴሮይድ’ (Testosterone) ንጥረ ነገር ተጠቅማ መገኘቷ ታውቋል፡፡ ይህንንም መነሻ በማድረግ ባለፉት ጊዜያት በጉዳዩ ላይ ጥልቅ ምርመራ ሲካሄድ የቆየ ሲሆን አትሌቷ ጥፋተኛ መሆኗ በመረጋገጡ ጊዜያዊ እገዳ ከተጣለበት እ.ኤ.አ ከጥር 21/2026 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥር 22/2030 ዓ.ም ድረስ ለአራት (4) ዓመታት በማንኛውም ስፖርታዊ ውድድሮች ላይ እንዳትሳተፍ እገዳ (Period of Ineligibility) ተጥሎባታል፡፡ በተጨማሪም አትሌት ዘመናይ ምርመራ ከተደረገበት እ.ኤ.አ ከግንቦት 4/2025 ዓ.ም ጀምሮ ያስመዘገበቻቸው ማንኛውም የውድድር ውጤቶች፣ ሜዳሊያዎች እና የገንዘብ ሽልማቶች በሙሉ እንዲሰረዙና ተመላሽ እንዲሆኑ ተወስኗል።
የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን (ETH-ADA) አትሌቶችም ይሁን ሌላ ማንኛውም አካል የስፖርቱን ደህንነትና የአገርን ገጽታ ከሚያበላሹ መሰል የአበረታች ቅመሞች (ዶፒንግ) ወንጀሎች እንዲታቀቡና የግል ኃላፊነት (Strict Liability) መርህን አክብረው እንዲንቀሳቀሱ በድጋሚ ያሳስባል። በየደረጃው የሚደረገው ክትትልና ቁጥጥርም ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን !!!

Comments