ብራዚል በሸንኮራ አገዳ ተረፈ ዘላቂና ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑ መንገዶችን እየገነባች መሆኑ ተገለጸ
📌ከባህላዊ የአስፋልት መንገዶች የበለጠ ጠንካራ እና ረጅም ጊዜ የሚቆዩ እንደሆነም ተገልጿል::
#ethiopia | ብራዚል፣ ዘላቂ ልማትንና የአካባቢ ጥበቃን የሚያስቀድም አዲስና አስደናቂ የቴክኖሎጂ ፈጠራ በማስተዋወቅ ላይ ትገኛለች ተብሏል። አገሪቱ ከሸንኮራ አገዳ ምርት ከሚገኘው ብክነት ጠንካራ፣ ዘላቂነት ያላቸው እና ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑ መንገዶችን በመገንባት ላይ መሆኗን አስታውቃለች።
ይህ አዲስ ዘዴ፣ በአብዛኛው ወደ ቆሻሻ የሚሄደውን የሸንኮራ አገዳ ተረፈ ምርት በመጠቀም፣ የመንገድ ግንባታ ወጪን ከመቀነስ ባለፈ፣ ለአካባቢ ጥበቃም ትልቅ አስተዋፅኦ ያደርጋል። አዲሶቹ መንገዶች ከባህላዊ የአስፋልት መንገዶች የበለጠ ጠንካራ እና ረጅም ጊዜ የሚቆዩ እንደሆኑ ተገልጿል። ይህም የመንገድ ጥገና ወጪን በእጅጉ የሚቀንስ ሲሆን፣ የአካባቢ ብክለትንም ይቀንሳል ነው የተባለው፡፡
የዚህ ፕሮጀክት ትግበራ ብራዚልን በመንገድ ግንባታ ቴክኖሎጂ ውስጥ ቀዳሚ ከሆኑት አገራት ተርታ እንድትሰለፍ ያስችላታል የተባለ ሲሆን ይህ ፈጠራ የግብርና ምርቶችን ተረፈ ምርት ወደ ጠቃሚ ሀብት በመቀየር፣ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ጥቅሞችን በማስገኘት ረገድ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ትልቅ ትምህርት ሊሆን ይችላል ነው የተባለው።
ሌሎች አገሮችም ይህን የመሰለ ዘላቂነት ያለው የመንገድ ግንባታ ዘዴን ለመተግበር ፍላጎት እያሳዩ መሆኑ ተመላክቷል። #menahriafm

11 months ago