በአዲስ አበባ አንዳንድ መንገዶች ላይ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ተከለከለ
የአዲስ አበባ ፖሊስ በከተማዋ እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማትና የመንገድ ግንባታ ስራ ለማፋጠን እንዲቻል፣ በተወሰኑ መስመሮች ላይ ተሽከርካሪዎችን አቁሞ መሄድ (Parking) ሙሉ በሙሉ መከልከሉን አስታውቋል።
📍 ክልከላው የተጣለባቸው ዋና ዋና መስመሮች፦
ከቅዱስ ኡራኤል — በአትላስ ሆቴል (ኤድሞል) በኩል እስከ ቦሌ ብራስ።
በአደይ አበባ ስታዲየም ዙሪያ ያሉ መንገዶች።
🚧 የክልከላው ምክንያት፦
በእነዚህ ቀጠናዎች የሚቆሙ ተሽከርካሪዎች በግንባታው ሂደት ላይ እንቅፋት እየፈጠሩ በመሆኑና የልማት ስራው የሚጠቀማቸው ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ እንዳይገደብ ለማድረግ ነው።
⚠️ ለአሽከርካሪዎች የተላለፈ ጥብቅ ማሳሰቢያ፦
ክልከላው ከዛሬ ጥር 04 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ሆኗል።
በስራው ላይ ከተሰማሩ ተሽከርካሪዎች ውጭ ማንኛውም የግልም ሆነ የህዝብ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት የተከለከለ ነው።
አሽከርካሪዎች አማራጭ የመኪና ማቆሚያ ቦታዎችን በመጠቀም ከአላስፈላጊ ቅጣትና እንግልት ራሳቸውን እንዲጠብቁ ፖሊስ አሳስቧል።
seledadotio

7 months ago