12 hours ago
13ኛ ዙር የደም ልገሳ መርሃ ግብር
አዲስ ዓመትን በተስፋ እና በሕይወት እንቀበል
መስከረም 30 እና ጥቅምት 1, 2019 ዓ.ም.በኢትዮጵያ 20+ ከተሞች
አንድ የደም ልገሳ እስከ ሦስት ሰዎች ሕይወት ሊያድን ይችላል።
አዲስ ዓመት አዲስ ተስፋን ይዞ ይመጣል። በዚህ የበዓል ወቅት ለራሳችን ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ተስፋ እንሁን።
በየቀኑ በሆስፒታሎቻችን ውስጥ ለቀዶ ሕክምና፣ ለአደጋ ተጎጂዎች፣ ለካንሰር ሕክምና ላይ ላሉ ሕፃናት፣ ለእናቶች እና ለሌሎች በርካታ ሕሙማን ደም በአስቸኳይ ያስፈልጋል።
ይህ 13ኛው ዙር የደም ልገሳ መርሃ ግብር በአዲሱ ዓመት የሕይወት ስጦታን ለመጀመር የሚያስችለን የሰብዓዊነት ጥሪ ነው።
እርስዎ የሚለግሱት ደም...
ለአንድ ልጅ ነገን፣
ለአንድ ቤተሰብ ተስፋን፣
ለአንድ ታማሚ ሕይወትን፣
ለአንድ እናት ፈገግታን ሊሰጥ ይችላል።
በጎ ፈቃደኞች፣ ወጣቶች፣ ቤተሰቦች፣ ተቋማት እና መላው ማኅበረሰብ በዚህ ታላቅ የሕይወት ማዳን ተግባር እንዲሳተፉ በክብር እንጋብዛለን።
አዲስ አበባ ያላችሁ ስታዲየም አካባቢ በሚገኘው የቀይ መስቀል ጊቢ የደም ልገሳው የሚደረግ ሲሆን በየክልሎቹ በሚገኙ የደም ባንክ ቅርጫፎች በመሄድ ደም እንድትለግሱ ጥሪ እናስተላልፋለን
ደም መለገስ ሕይወት መስጠት ነው!
ኑ! በደማችን አዲስ ታሪክ እንፃፍ!

18 hours ago
ለ7 ዓመታት በህመም ስትሰቃይ ከነበረቸዉ እናት 25 ኪሎ ግራም እጢ በቀዶ ህክምና ተወገደ
የ52 ዓመት ዕድሜ ያላቸዉ እኚህ እናት ለሰባት ዓመታት ያህል በህመም ሲሰቃዩ የነበረ ሲሆን በደብረ ብርሃን አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም በተደረገላቸው ህክምና 25 ኪሎ ግራም ክብደት ያለዉ የማህፀን እጢ ተወግዶላቸዋል።
በሆስፒታሉ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት ሃኪም ዶክተር ሳሙኤል በዛብህ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት ታካሚዋ በሰባት ዓመታት ዉስጥ ሆዳቸዉ አከባቢ እየጨመረ የመጣዉን እብጠት የክብደት መጨመር ሊሆን ይችላል በሚል ትኩረት ሳይሰጡት ቆይተዋል።
የማህፀን እጢ በአፋጣኝ ህክምና ካላገኘ ወደ ካንሰር ተቀይሮ ለህይወት አስጊ የሚሆንበት አጋጣሚ ሊኖር እንደሚችል የሚገልፁት ዶክተር ሳሙኤል ለታካሚዋ እስካሁን በተደረገዉ ምርመራ እብጠቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከመጨመሩ ዉጪ የካንሰር ባህሪይ እንዳልተገኘበት ገልጸዋል ።
በሆድ አከባቢ ህመሞች እና እብጠቶች ሲኖሩ ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ ምርመራዎችን ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ከከፋ ስቃይና ህመም መዳን እንደሚቻል ተጠቁሟል፤ 1 ሰዓት ተኩል የፈጀ ቀዶ ህክምና የተደረገላቸዉ የ52 ዓመቷ እናት አሁን ላይ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ታውቋል።
በመባ ወርቅነህ
#ዳጉ_ጆርናል

24 hours ago
በደቂቃዎች ውስጥ የቆዳ ካንሰርን የሚለየው
አስገራሚው የኤ.አይ (AI) ሥርዓት!
በዩናይትድ ኪንግደም ብራድፎርድ በሚገኘው ሴንት ሉክስ ሆስፒታል የቆዳ ሕክምና ቡድን አጠራጣሪ የቆዳ እብጠቶችን እና የጤና መጓደሎችን በፍጥነት ለመመርመር አዲስ የኤ.አይ (AI) ሥርዓትን በሥራ ላይ ማዋሉ ተሰማ። «DERM» (Deep Ensemble for the Recognition of Malignancy) የተሰኘው ይህ ዘመናዊ ሥርዓት፣ አጠራጣሪ የቆዳ እብጠቶችን ሦስት ፎቶዎች ብቻ በመውሰድ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ውጤት ማቅረብ ያስችለዋል።
የሕክምና ባለሙያዎች ይህ ቴክኖሎጂ ታካሚዎች ረጅም ሰዓት በሰልፍ የሚጠብቁበትን ጊዜ በእጅጉ በመቀነስ ላይ ትልቅ ለውጥ እያመጣ መሆኑን ይናገራሉ። አልሚው አካል «ስኪን አናሊትክስ» (Skin Analytics) እንዳገለጸው ከሆነ፣ ቴክኖሎጂው ካንሰር እንዳልሆነ በመለየት ረገድ እስከ 99.9 በመቶ ትክክለኛነት አለው፤ ሆኖም በሂደቱ ውስጥ ሐኪሞች ሁልጊዜም በንቃት ይሳተፋሉ።
ይህ የጤና ዘርፍ ፈጠራ የካንሰር ምርመራን ፈጣን እና ቀለል በማድረግ በብዙዎች ሕይወት ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣል ተብሎ ይጠበቃል። ቴክኖሎጂው ከጊዜ ወደ ጊዜ በሕክምናው መስክ እየተጫወተ ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑንም ይህ ክስተት በግልጽ ያሳያል።
Seledadotio

1 day ago
በኢትዮጵያ የአፍና የጥርስ ህክምና ባለሙያዎች እጥረት መኖሩ ተገለፀ
በአገሪቱ የአፍና የጥርስ ጤና ችግሮች በስፋት የሚታዩ ቢሆንም በዘርፋ የህክምና ባለሙያዎች እጥረት መኖሩን የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ አስታውቋል።
በማህበረሰቡ ዘንድ ከሚስተዋሉ የጥርስ ጤና ችግሮች መካከል በዋናነት የህፃናትና የአዋቂዎች ጥርስ መበስበስ፣ የድድና የጥርስ አቃፊ አጥንት ሕመም፣ የጥርስ መርገፍ እንዲሁም የአፍና የከንፈር ካንሰር ይገኙበታል።
በሆስፒታሉ የጥርስና ማክሲሎፌሻል ትምህርት ክፍል ኃላፊ እንዲሁም የፊትና መንጋጋ ቀዶ ጥገና ማኅበር ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር አዲስ ካሳሁን ከብስራት ሬዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለፁት ጥርስን እስከ ማጣት ሊያደርስ የሚችለው የድድና የጥርስ አቃፊ አጥንት ህመም 18.7 በመቶ ስርጭት ሲኖረው የጥርስ መርገፍ ደግሞ 1.8 በመቶ ስርጭት እንዳለው ተናግረዋል።
የሕክምና ኮሌጁም ከመደበኛው የጥርስ ህክምና በተጨማሪ የአፍ፣ የመንጋጋና የፊት ቀዶ ጥገና ሕክምናን እንደሚሰጥ ገልጿል።ተቋሙም በየቀኑ ከ90 እስከ 140 የሚደርሱ ታካሚዎችን በማስተናገድ ሕክምናን እየሰጠ መሆኑን ዶክተር አዲስ ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል።
በፈረንጆቹ 2022 የታተመውና በ2018 አ/ም የተሰበሰበው መረጃን ያካተተው የዓለም ጤና ድርጅት ጥናት እንደሚያሳየው ከሆነ በኢትዮጵያ የሚገኙት 1 ሺህ 745 የጥርስ ህክምና ባለሙያዎች ብቻ ናቸው።በዘርፋ የተሰማሩ የባለሙያዎችን ቁጥር አስመልክቶ ወቅታዊና የተጠናቀረ መረጃ ባለመኖሩ በአሁኑ ወቅት ያለው ቁጥር ከዚህ የተለየ ሊሆን እንደሚችልም ዶክተር አዲስ ገልጸዋል።
በሰብል አበበ

2 days ago
የየካ አባዶ ምዕመናን እንኳን ደስ አላችሁ‼️
ከመስከረም 28- ጥቅምት 1 የትም አይኬድም🔴
ለየካ አባዶ ምዕመናን አገልግሎት ከሚሰጡ አብያተ ክርስቲያናት መካከል
የደብረ ልዕልና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን አንዷ ናት።ይህች ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ውጣ ውረድ ያሳለፈችና በተለያዩ ምክንያቶች 3ት ጊዜ ፈርሳ የተሰራች ቆራጥ በሆኑ የአካባቢው ምዕመናን ከታላቅ እስከ ታናሽ በእንባ፣ ጸሎት በአንድነትና በልዩ ተጋድሎ የጸናች የአካባቢው ልዩ መገለጫ ስትሆን ለምዕመኑን ከምትሰጠው የበረከት አገልግሎት ጎን ለጎን ልዩ የማስተሳሰሪያ ገመድ ሆና እያገለገለች ትገኛለች።
የየካ አባዶ ደ/ልዕልና ቅድስት አርሴማ ከምስረታዋ አንስቶ በብዙ ተዓማራት እና ጸሎትን በመስማት የምትታወቅ ቤተክርስቲያን ናት። ልዩ ልዩ ውስጣዊ እና ውጫዊ ደዌዎችን(የካንሰር፣ የኩላሊት፣ የአንጀት፣ የአጽም፣ የቆዳ፣ የደም ግፊት፣ የስኳር እና መሰል ህመሞች) እንዲሁም የሚጥል በሽታዎችበመፈወስ የሚታወቅ ሲሆን ለዚህም ከህመማቸውና ከደዌአቸው የተፈወሱ ልዩ ልዩ እርዳታዋን ያገኙ በርካታ ምዕመናን በየጊዜው ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። ጸበሏን በመጠጣት እምነቷን በመቀባት በሚገባ እምነትና ሕይወት የተመላለሱባት ብዙ ችግራቸው ተወግዷል፤ ልጅ ያጡ አግኝተውበታል፤ ሥራ ያጡ ሥራ ይዘውበታል፤ ሠላም ያጡ ሠላማቸው ተመልሶላቸዋል፤ በእምነት የጠየቀ የሚገባውንበየሚመለስለት ልዩ የበረከት አደባባይ ናት።
ይህች ቤተ ክርስቲያን ታዲያ ለዚህ ሁሉ የማኅበረሰብ ክፍል ይህንን ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የምትሰጠው ሦስት ጊዜ ፈርሶ በተሰራው የቆርቆሮ መቃኞ የነበረ ሲሆን ይህም፡-
1ኛ. የከበረ ታቦተ ሕጉ ያረፈበት ቤተ መቅደስ ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን ለአገልግሎት አመቺ ባለመሆኑ
2ኛ. የአካባቢው ምዕመናን የሚገባ ቤተ ክርስቲያን ይሰራለትና አገልግሎቱ ተደራሽ ይሆንለት ዘንድ ለብዙ ጊዜ የሚጠይቅና ለዚህም ሳያቋርጥ የሚተጋ ስለነበር
3ኛ. የአካባቢው ምዕመን ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ በመሆኑና ለዚሁ ምዕመን አገልግሎት ለመስጠት እጅግ ፈታኝ በመሆኑ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑን መገንባት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል
በአምላክችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምላካዊ ፈቃድ፣ በሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ረድኤት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እና በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ ቤተ ክህነት ፈቃድ
1ኛ. የቤተ ክርስቲያኗን የይዞታ ካርታ በሚመለከተው የመንግሥት አካል ሕጋዊ በማድረግና ሕጋዊ ካርታ በመያዝ
2ኛ. ከሚመለከተው የመንግሥት አካል የግንባታ ፈቃድ በማውጣት
3ኛ. በሀገረ ስብከቱ አሰራር መሠረት ሁሉንም ሕጋዊ ሁኔታዎችን በማሟላት
4ኛ. የተለያየ የሙያ ስብጥር ያለው ብቁ የሕንጻ አሰሪ ኮሚቴ በሚመለከተው ሕጋዊ አካል በማዋቀር
5ኛ. ደረጃውንና ሕጋዊነቱን የጠበቀ የኮንትራክተር እና የአማካሪ ድርጅት እንዲሁም ሁሉንም የምህንድስና ሞያዎች ያካተተ የቴክኒክ ኮሚቴ በማዋቀር
6ኛ. ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንንና የቦታ አቀማመጡን ያማከለሁለት ቤተ መቅደስ (ቤዝመንት ጨምሮ) ያለው የሕንጻ ቤተክርስቲያን ዲዛይን ለመስራት በሚመለከተው የቤተ ክርስቲያኗ አካል በማጸደቅ ወደ ሕንጻ ግንባታው ሥራ ተገብቷል
የየካ አባዶ ደ/ልዕልና ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን ሰበካመንፈሳዊ ጉባኤና የሕንጻ አሰሪ ኮሚቴው አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት የዛሬ አንድ ዓመት ከ3 ወር የቤተክርስቲያኗን ቁፋሮ፣ የፓድ መሙላትና ማዋቀር እንዲሁም እንዲሁም ኮለን ማቆም ሥራ የጀመረ ሲሆን የአካባቢው ምዕመናን፣ ማኅበረ ካህናት፣ በሃገር ውስጥም ውጭም ሃገርም ያሉ የሰማዕቷ ወዳጆች እና የሚዲያ ባለሞያዎች ባደረጉት ከፍተኛ ርብርብ እና እጅግ ቆራጥነት የታየበት ልዩ ድጋፍበአንድ ዓመት ከሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ተዓምራዊ በሆነ መልኩ
1ኛ. የታችኛው ቤተ መቅደስ (Basement)፡- የውጨኛው የድንጋይጥርብ ጌጥ ሥራና የበር ሥራ ጨምሮ ሙሉ በሙሉ ያለቀናለአንዳንድ አገልግሎቶች ዝግጁ ለማድረግ የቻክ እና የመብራትገጠማ ሥራ ብቻ የቀረው
2ኛ. የላይኛው ቤተ መቅደስ፡- (ዋናው) ሥራ structure” ሥራአልቆ የካንች ሥራ እየተገባደደ ሲሆን የጣራ ቆርቆሮለማልበስም የቆርቆሮ ማምረት (በፋብሪካ) ሥራ እየተሰራ ነው
3ኛ. የብሎኬት ሥራ የተገባደደ ሲሆን የውጩ የጥርብ ድንጋይጌጥ ሥራም በግማሽ አልቋል
4ኛ. አካባቢውን የማጽዳትና እና የቤተልሔም ሥራንምለመጀመር ቅድመ ሁኔታዎችን የጨረሰን በመሆኑ ይህ ጋዜጣዊመግለጫ ለሦስት ምክንያቶች አስፈልጓል።
1ኛ. በዚህ ደረጃ ለተሠራው ሥራ እግዚአብሔርን አምላካችንንእና ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማን እንዲሁም በከፍተኛመሰዋዕትነት ሥራውን ከዚህ ላደረሱት ለአካባቢው ምዕመናን፣ ማኅበር ካህናት፣ የሰማዕቷ ወዳጆችና የሚዲያ ባለሞያች ምስጋናለማቅረብ፣ የሥራውን ውጤት ያለበትን ደረጃ መግለጽ የሚገባበመሆኑ
2ኛ. በዋናነት በጥቅምት 01/2019 ዓ.ም እሁድ ዕለት (ከ05 ቀናትበኋላ) ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያንየአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና ወረዳ ቤተ ክህነት ኃላፊዎች፣ የቤተክህነት አስተዳዳሪዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው አካላት፣ ሙሉየአካባቢው ምዕመን፣ በርካርታ የሚዲያ አካላት እና የሰማዕቷወዳጆች በሚገኙበት የጉልላት መስቀል መርሐ ግብር የተዘጋጀበመሆኑ ሁሉም የሰማዕቷ ወዳጆች፣ የሚዲያ አካላት እና አጋርአካላት ከጠዋቱ 1 ሰዓት ጀምሮ በየካ አባዶ ደ/ልዕልና ቅድስትአርሴማ ቤተ ክርስቲያን በመገኘት አብራችሁ በመሆን የበረከቱእና የደስታችን ተከፋዮች እንዲሆኑ ጥሪ ለማስተላለፍ ነው
3ኛ. ቤተ ክርስቲያናችንን በአጭር ጊዜ አጠናቀን ለአገልግሎትምቹ ለማድረግና ለማሳወቅ በብዙ እንግልትና ፈተና ውስጥላለው ምዕመንም ለማስረከብ የሚከተሉትን ቀሪ ሥራዎች
1. የቤተልሔም ሥራ
2. የማርብል ሥራ
3. የቻክ ሥራ
4. የስዕል ሥራ
5. የቤተ መቅደስ በሮች
6. የዶም መስኮቶች ሥራ
7. የመብራት ሥራ
8. የሳውንድ ሲስተም ሥራ
9. ምንጣፍ እና የመሳሰሉት
እነዚህን ሥራዎች ሁሉም የሰማዕቷ ወዳጆች በተለመደውትብብርና ዕርብርብ አስተዋጽኦ እንድታደርጉልንበእግዚአብሔር ስም ለመጠየቅ ነው
በሀገር ውስጥም ሆነ ውጭ ያላችሁ ምዕመናን
1ኛ. በዕለቱ የጉልላት መስቀል መርሐ ግብር በጋራ በመስቀልበአካልና በተለያዩ የሚዲያ አውታሮች የበረከቱ ተሰታፊእንድትሆኑ
2ኛ በአካል መምጣት የምትችሉ የሰማዕቷ ወዳጆች በአካልበመምጣት የሥራውን ሁኔታ እንድታዩ የቦታውን በረከትንእንድትሳተፉ በማለት መንፈሳዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን
የደብሩ ሕንጻ አሰሪ ኮሚቴ ከሰበካ ጉባኤ ጋርበመተባበር
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

Sponsored by
Surafel
2 days ago
ወ/ሮ ለሊሴ ዱጋ ከስድስት ዓመታት አገልግሎት በኋላ የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን መሪነታቸውን አጠናቀቁ
#ethiopia | ለስድስት ዓመታት የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽንን በኮሚሽነርነት ሲመሩ የቆዩት ወይዘሮ ለሊሴ ዱጋ ከኃላፊነታቸው መሰናበታቸው ተገለጸ።
ወ/ሮ ለሊሴ በቆይታቸው በኢትዮጵያ የቱሪዝም እንቅስቃሴ ውስጥ ከፍተኛ አሻራ ያሳረፉ ሲሆን በተለይም «ቪዚት ኦሮሚያ» የተሰኘውን የቱሪዝም ብራንድ ከምንም በመነሳት በሀገር አቀፍ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ስሙ ከፍ ብሎ እንዲጠራና ለሌሎች ክልሎችም አርአያ እንዲሆን አስችለዋል።
የኦሮሚያን የቱሪዝም ሀብት በዓለም አቀፍ ደረጃ የማስተዋወቅ፣ አዳዲስ መዳረሻዎችን የማልማት፣ የሥራ አጋርነትን የማጠናከር፣ ዲጂታል ቱሪዝምን የማሳደግ፣ «የኦሮሚያ ቱሪዝም ሳምንት»ን ወደ ዓለም አቀፍ መድረክ የማሳደግ እንዲሁም ለኢንቨስትመንትና ለሥራ ዕድል ፈጠራ አዳዲስ መንገዶችን የመክፈት አበይት አሻራዎችን አሳርፈዋል።
በተጨማሪም የሀገሪቱንና የክልሉን የተፈጥሮና የባህል መስህቦች ዓለም በሚረዳው ቋንቋና መንገድ በማስተዋወቅ ረገድ ትልቅ ኢንሼቲቭ በመቅረፅና በመተግበር ረገድ የጎላ ሚና ተጫውተዋል።
ኮሚሽነሯ በሥራ አፈጻጸማቸው፣ በትህትናቸውና ሰዎችን ለመርዳት ባላቸው ዝግጁነት የሚታወቁ ሲሆንበሥራ አጋጣሚያቸው ወቅት ያጋጠማቸውን የካንሰር ሕመም በጽናት ታግለው በማሸነፍ ለሌሎችም የጽናት ማሳያ ሆነዋል።
''የኦሮሚያ ቱሪዝም ሳምንት'' በተከበረበት ወቅት በለተቋሙና ለዘርፉ ላበረከቱት ላቅ ያለ አስተዋጽኦና አገልግሎት ምስጋና የቀረበላቸው ሲሆን በሚቀጥለው አዲስ የሕይወትና የሥራ ምዕራፋቸውም መልካም ሁሉ እንመኛለን።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu

አጂባደም ኸልዝኬር ግሩፕ በአዲስ አበባ አዲስ የታካሚዎች መረጃ መስጫ ቢሮ ከፈተ።
በቱርኪዬ ከጤና አገልገሎት ሰጪ ተቋማት ስመጥር የሆነው አጂባደም ኸልዝኬር ግሩፕ በአዲስ አበባ አዲስ የታካሚዎች መረጃ ቢሮ መክፈቱን አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ታካሚዎች እና ቤተሰቦቻቸው በቱርክ ስለሚገኙ ልዩ የህክምና አገልግሎቶች እና የህክምና አማራጮች መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በሀገር ቤት ሆነው ከሀኪሞች ጋር በቀጥታ መረጃ ለመለዋወጥ የሚያስችል አገልግሎት ይሰጣልም ተብላል።
ማዕከሉ፤ የታካሚዎችን ነባር የህክምና መረጃዎችን ግምገማ ከማከናወን እና ተጨማሪ የባለሙያ ምክር ከመስጠት ጀምሮ እስከ ህክምና ዕቅድ ዝግጅት፣ የጉዞ ዝግጅት ማስተባበር እና ከህክምና በኋላ የሚደረግ ክትትል ድረስ ባሉት ሂደቶች ሁሉ ለታካሚዎች ድጋፍ እንደሚሰጥ የአጂባድም ኸልዝኬር ግሩፕ የአለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር የሆኑት ሚስተር ኢሊያስ ቤንቬኒስቴ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።
የጤና መረጃ መዓከሉ ትኩረት ከአደረገባቸው የጤና ዘርፎች ውስጥ የኒውሮሎጂ እና ኒውሮሰርጀሪ፣ የኩላሊትና ጉበት ንቅለ ተከላ ፣ የሜዲካልና ራዲዬሽን ኦንኮሎጂ ወይም ካንሰር፣ እና አይ.ቪ.ኤፍ እንዲሁም የፅንስና ማህፀን ህክምናዎች ይገኙበታል ተብሏል።
ቢሮው ለታካሚዎች አገልግሎት ከመስጠት ባለፈ በኢትዮጵያና በቱርክ ሀኪሞች መካከል የልምድ ልውውጥ፣ የስልጠናና የልዩ ሙያ እድሎችን በማመቻቸት የሁለቱን ሀገራት የጤና ትብብር ያጠናክራል ሲሉ ሚስተር ኢሊያስ ጨምረው ተናግረዋል።
አጂባደም በዓለም ዙሪያ 30 ሆስፒታሎችና 15 ክሊኒኮች ያሉት ሲሆን፣ ይህ የአዲስ አበባው ማዕከል በዓለም አቀፍ ደረጃ 52ኛው የመረጃ ቢሮው መሆኑም ተገልፃል።

ስለ ወተት የተደረገው ጥናት ምንድነው የሚለው ?
የጥሬ ወተት ጥራትና ደህንነትን በተመለከተ ከእርባታ ሼድ እስከ ሽያጭ ባለው ሂደት አንዳንድ ለጤና አስጊ ሁኔታዎች እንዳሉ በጥናት ማረጋገጡን የአዲስ አበባ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የኮሚሽኑ ም/ኮሚሽነር ፀጋ ለማ፣ በከተማዋ 11 ክፍለ ከተሞች ስለወተት ጥራት ደህንነትና የግብይት ስርዓት ጥናት መደረጉን ነግረውናል።
በዚህም " ከእንስሳት እርባታ ሼዶች ጀምሮ እስከ ምርት መሸጫ ድረስ ባለው ሂደት ለጤና ስጋት የሚሆኑ ሁኔታዎች እንዳሉ ጥናቱ ጠቁሞናል " ሲሉ ተናግረዋል።
ከውሃ ባሻገር ለጤና ጠንቅ የሆነ "ባዕድ ኬሚካል" ጥሬ ወተት ላይ እንደሚጨመር ስሞታ ይቀርባል፤ "ኬሚካል" እንደሚጨመር ጥናቱ አሳይቷል ? ብለን ስንጠይቃቸው፣ "በጥናት ያረጋገጥነው በዋናነት ከፍተኛ ውሃ የሚጨምሩ አንዳንድ ነጋዴዎችና አርቢዎች እንዳሉ ነው" ብለዋል።
በጥናቱ " ወተቱ ዋናውን ይዘቱን እንዲያጣ የሚያደርጉ ችግሮች እንዳሉ አይተናል። ከማህበረሰቡ በኩል ግን 'ባዕድ ኬሚካል' የሚጠቀሙ እንዳሉ ጥቆማዎች ይመጣሉ። ያንን በቀጣይ ጥናት መመለስ ያስፈልጋል " ሲሉም ተናግረዋል።
ጥናቱ " በተጨባጭ የወተት አያያዛችን ለጤና ስጋት የሚያስከትል ስለሆነ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል ፤ ቁጥጥር መደረግ አለበት " በሚል ኮሚሽኑ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ያጠናው ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ለ " ካንሰር " የሚያጋልጥ ንጥረ ነገር ወተት ላይ መገኘቱን ጥናቱ በተጨባጭ አሳይቷል ?
ም/ኮሚሽነሩ፣ " በተጨባጭ ጥናቱ ይሄን አመላክቷል ሳይሆን አሁን ላይ ያለው የወተት አያያዝ ስርዓታችን ከሚፈለገው ስታንዳርድ አንጻር ሙሉ አይደለም ፤ ጉዳት ሊደርስ ስለሚችል ቅድመ ጥንቃቄ መደረግ አለበት " የሚል ነው ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ይሁን እንጅ በዋነኛነት በየሱቁ የሚገዛው ወተት " በሁለት፣ ሦስት ቀንም አይረጋም፤ ችግሩ ምንድን ነው ? " በማለት ህብረተሰቡ ቢሮ ድረስ እየሄደ ጥቆማ እንደሚሰጥ አመልክተዋል።
" በጭምጭምታ ደረጃ ወተቱ ላይ ኬሚካል እንደሚጨመርበት ነው የምንሰማው " ሲሉ ተናግረዋል።
" ኬሚካሉ ደግሞ በጣም ከባድ ነው ወተቱን እንዳይረጋ ቢያደርግም በጊዜ ሂደት በጤና ላይ ጉዳት እንደሚያደርስ ሀኪሞች ያነሳሉ። በጊዜ ሂደት እነዚህ ነገሮች በከተማዋ በተጨባጭ ካሉ ካንሰር ሊያስከትል የሚችል ስጋት ሊያስከትል ይችላል " ብለዋል።
የተስተዋሉ ክፍተቶችን በተመለከተ ምን አሉ ?
የወተት አያያዝን በተመለከተ በእንስሳት እርባታ ሸዶች የሚደረጉ ጥንቃቄዎች ችግር ያለባቸው መሆኑንም ጥናቱ ማሳየቱን ገልጸዋል።
በእርባታ ቦታ ለላሞች የህክምና አሰጣጥ አንዲት ላም ህክምና ካገኘች ከስንት ጊዜ በኋላ ነው መታለብ ያለባት ? የሚለውን በሳይንሱ መሰረት አለመተግበር መስተዋሉን ገልጸዋል።
" የመድኃሃቱ ቅሪት እያለ አብሮ ወተቱን የማለብ እንቅስቃሴዎች እንዳሉ፣ የግንዛቤ ክፍተትም አለ " ሲሉ ተናግረዋል።
በመታለብ ላይ ያለች ላም በበሽታ ብትጠቃ መድኃኒት እንደሚሰጣት፣ መድኃኒቱ በላሚቷ ሰውነት ውስጥ ለምን ያክል ጊዜ እንደሚቆይ በሳይንስ የተረጋገጠ ነገር እንዳለ፣ የመድኃኒቱ ቅሪት የሚጠፋው ሀኪሞች በሚያስቀምጡት አግባብ በተለያዩ ጊዜ እንደሆነና የሀኪም ትዕዛዝ መተግበር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
" የመድኃኒቱ ቅሪት ከላሚቷ አካል ሙሉ ለሙሉ ሳይጠፋ ወተት ታልቦ ጥቅም ላይ የሚውል ከሆነ ግን የመድኃኒቱን ቅሪት ሰው እንዲመገበው እያደረግን ነው ማለት ነው " ብለው፣ ይህን በተመለከተ ዝርዝር ማዕቀፍ እየወጣ መሆኑን ገልጸዋል።
እንዲሁም፣ መኖ በተመለከተ በተለይ ከአቀማማጡ ጋር በተያያዘ "አፍላ ቶክሲን" የመፈጠር እድሉ ሰፊ መሆኑን ገልጸው፣ በዚህ ረገድ ክፍተቶች እንዳሉ ገልጸዋል።
" ከምንም በላይ የወተት ማለቢያ መሳሪያዎች ለምግብ ተስማሚ አለመሆናቸውን " የተናገሩት ፀጋ፣ በተለምዶ ወተት የሚገዛው በሃይላንድ፣ የሚጓጓዘውም ለማጽዳት አስቸጋሪ በሆኑ ጀርካዎች መሆኑን አንስተዋል።
በጊዜ ሂደት የፕላስቲኩ ፍቅፋቂ ከፀሐይ፣ ሙቀት ጋር ሲገናኝ የሚለቀቁ ነገሮች እንዳሉና ከፍተኛ የጤና ስጋት እንደሚያስትከሉ ሳይንሱ እንደሚያረጋግጥ ገልጸው፣ " እኛም በጥናታችን እነዚህ ነገሮች እየተተገበሩ እንደሆነ አይተናል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
(ተጨማሪ ይኖረናል)
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia

የማቴዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን መስራች አቶ ወንዱ በቀለ የዐይን ብሌናቸውን ለገሱ
የኢትዮጵያ ደምና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት ለአቶ ወንዱ በቀለ ቤተሰቦች የምስጋና የክብር ምስክር ወረቀት አበርክቷል።
የማቲዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወንዱ በቀለ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት መስከረም 24 ቀን 2019 ዓ.ም ረፋድ ነበር።
አቶ ወንዱ በቀለ በኢትዮጵያ በካንሰር በሽታ ቁጥጥር እና በሕፃናት ሕክምና ድጋፍ ዙሪያ የሚሰራው "ማቲዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን" (የቀድሞው ማቲዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ) መስራች እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ነበሩ።
በሙያቸው የቢዝነስ አስተዳደር ባለሙያ የሆኑት አቶ ወንዱ በቀለ፣ የበጎ አድራጎት ሥራቸውን እንዲጀምሩ ያደረጋቸው ልጃቸው ሕፃን ማቲዎስ ወንዱ በደም ካንሰር ሕመም ምክንያት በሕፃንነቱ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ነበር።
የልጃቸውን ሕልፈት መታሰቢያ በማድረግ ሚያዝያ 9 ቀን 1996 ዓ.ም (በ2004 እ.ኤ.አ) ድርጅቱን መሠረቱ።
ተቋሙ በካንሰር ለተያዙ አቅም የሌላቸው ሕፃናትና ወላጆቻቸው የምክር፣ የመጠለያ፣ የሕክምና ቁሳቁስ እና የፋይናንስ ድጋፍ ይሰጣል።
በተጨማሪም፤ የካንሰር ተጋላጭነትን ለመቀነስ ጥብቅ የትንባሆ ቁጥጥር ሕጎች በሀገሪቱ እንዲወጡ ከጤና ሚኒስቴር እና ከዓለም ጤና ድርጅት ጋር በመሆን ከፍተኛ የፖሊሲ ሙግት አድርገዋል።
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

3 days ago
በአዲስ አበባ ጥሬ ወተት ላይ ለካንሰር አጋላጭ መርዛማ ንጥረ-ነገሮች መገኘታቸው ተገለጸ
በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ሁሉም 11 ክፍለ ከተሞች በተካሄደ የዳሰሳ ጥናት፣ ለሽያጭ በሚቀርብ ጥሬ ወተት ላይ ከውኃ እስከ ለካንሰር አጋላጭ የሆኑ መርዛማ ባዕድ ንጥረ-ነገሮች ተጨምረው መገኘታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አርሶ አደር እና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን አስታወቀ።
የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ዶክተር ፀጋ ለማ እንደገለጹት፤ ጥናቱ ቁጥጥር ከሚያደርጉ ባለሙያዎች ጋር በመቀናጀት የተከናወነ ሲሆን፣ በየመንደሩ ለሽያጭ በሚቀርበው ወተት ላይ የሚጨመሩ ባዕድ ነገሮች መበራከታቸው ተረጋግጧል።
በወተቱ ላይ የሚጨመረው ውኃ አስፈላጊውን ንጥረ-ነገር የሚያሳጣ ሲሆን፤ ወተቱ ሳይበላሽ ከ4 እስከ 5 ቀናት እንዲቆይ ተብለው የሚጨመሩት ንጥረ-ነገሮች ደግሞ የኅብረተሰቡን ጤና ለከፍተኛ አደጋ እና እንደ ካንሰር ላሉ ከባድ በሽታዎች የሚያጋልጡ መርዛማ ነገሮች ናቸው።
ይህንን የጤና ስጋት ለመግታት እና የቁጥጥር ሥራውን ለማጠናከር ኮሚሽኑ አዲስ የሕግ ማዕቀፍ በማዘጋጀት ላይ እንደሚገኝ ዶክተር ፀጋ አስታውቀዋል።
@Yenetube Fikerassefa

በሁሉም ክፍለከተሞች በተካሔደ የዳሰሳ ጥናት ካንሰርን ጨምሮ ለተለያዩ በሽታዎች አጋላጭ ንጥረ-ነገሮች በጥሬ ወተት ላይ መገኘታቸው ተገለጸ።
በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ 11 ክፍለ ከተሞች በተካሄደ የዳሰሳ ጥናት በጥሬ ወተት ላይ ከውሀ እስከ ለካንሰር አጋላጭ መርዛማ ባእድ ንጥረ-ነገሮች ተጨምረው መገኘታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አርሶ አደር እና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን አስታውቋል።
የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ዶክተር ፀጋ ለማ፣ ጥናቱ በጥሬ ወተት ላይ ቁጥጥር ከሚያደርጉ ባለሙያዎች ጋር በመቀናጀት እንደተከናወነ ጠቅሰው፤ "በየመንደሩ ለሽያጭ የሚቀርበው ጥሬ ወተት ላይ የሚጨመሩ ባዕድ ነገሮች መበራከታቸው ተረጋግጧል" ብለዋል።
በወተት ላይ የሚጨመረው ውኃ ወተቱ ሊኖረው የሚገባውን አስፈላጊ ንጥረ ነገር እንዳይዝ እንደሚያደርግ ምክትል ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።
ከውኃ ባለፈ ወተቱ ሳይበላሽ የሚቆይበትን ጊዜ ከ4 እስከ 5 ቀናት ለማስረዘም ሲባል የሚጨመሩ ንጥረ-ነገሮች የሰዎች ጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትሉ እና መርዛማ እንደሆኑ ተናግረዋል።
የተደረጉ የቁጥጥር ሥራዎች እንደሚያሳዩት በወተት ላይ የሚጨመሩ ባዕድ ንጥረ-ነገሮች የማኅበረሰቡን ጤና ለከፍተኛ አደጋ የሚያጋልጡና እንደ ካንሰር ላሉ ከባድ የጤና ችግሮች የሚያጋልጡ ናቸው።
ይህንን ተከትሎ የቁጥጥር ሥራውን ለማጠናከር ኮሚሽኑ የሕግ ማዕቀፍ በማዘጋጀት ላይ እንደሚገኝ ዶክተር ፀጋ አስታውቀዋል።
#አሐዱ_ሬዲዮ

የቀድሞው " የማቲዎስ ወንዱ ካንሰር ሶሳይቲ " የአሁኑ " የማቲዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን " መስራች እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወንዱ በቀለ ስርዓተ ቀብር ዛሬ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም በቦሌ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስትያን ተፈጽሟል።
በ1996 ዓ/ም ህፃን ልጃቸውን በደም ካንሰር የተነጠቁት አቶ ወንዱ "ብዙ ማቲዎሶችን ማዳን እንችላለን" በሚል ለ22 ዓመት አገልግሎት የሰጠውን የማቲዎስ ወንዱ ፋውንዳሽንን መስርተው ለበርካቶች ወገኖቻቸው ደርሰዋል።
አቶ ወንዱ፣ ለአንድ አመት ከ10 ወር ከካንሰር ህመም ጋር ታግለው ህክምና ሲከታተሉ ቢቆዩም፣ መስከረም 24 ቀን 2019 ዓ/ም ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።
ኢትዮጵያን አልፎ ለአፍሪካ እና ዓለም ሀገራት መድረስ የሚችል ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች ችግር ለመፍታት ያለመ "ጤናማ አፍሪካ የልህቀት ማዕከል" የተሰኘ ፕሮጀክት ቀርጸው በመስራት ላይ ነበሩ። ይህንኑ ፕሮጀክት ከግብ ለማድረስ ፋውንዴሽኑ ጥሪ አቅርቧል።
አቶ ወንዱ በቀለ የ3 ልጆች አባት ነበሩ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia "ታሞ ሕክምና ሲከታተል ነበር። ባልጠበቅነው ሁኔታ በድንገት ነው ያረፈው" - የሟች ቤተሰብ ልጃቸው ህፃን ማቲዎስን የካንሰር በሽታ ሲነጥቃቸው በልጃቸው ስም የህክምና ተቋም ያቋቋሙት "የማቲዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን" መስራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ወንዱ በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ፋውንዴሽኑና ቤተሰባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ። አንድ ቤተሰባቸው በሰጡን ገለጻ፣ አቶ ወንዱ በቀለ ሕይወታቸው…

“ስምም ብርሃንም ከመቃብር በላይ ዋለ!”
«መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ፤ ሩጫውን ጨርሻለሁ፤ ሃይማኖቴንም ጠብቄያለሁ።»
#ethiopia | የማቲዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ፣ በኢትዮጵያ የካንሰር እና የተላላፊ ያልሆኑ ሕመሞች መከላከልና ቁጥጥር ላይ ለዓመታት የላቀ አስተዋጽኦ ያበረከቱት አቶ ወንዱ በቀለ ወ/ማርያም የቀብር ሥነ-ሥርዓታቸው ዛሬ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም. በቦሌ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ-ክርስቲያን ተፈጽሟል።
አቶ ወንዱ በቀለ ከተወለዱበት ከምሥራቅ ሐረርጌ ጀምሮ በትምህርት፣ በሥራ፣ በማኅበራዊ አገልግሎትና በበጎ አድራጎት የተሞላ ሕይወት ኖረዋል። በአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪነት፣ በፋብሪካ አስተዳደር፣ በትምህርት እና በተለያዩ የሥራ ኃላፊነቶች አገልግለዋል።
የሕይወታቸው ትልቁ የበጎ ሥራ ምዕራፍ ግን የልጃቸው ማቲዎስ በሕፃንነቱ በደም ካንሰር ምክንያት መሞት በኋላ ተጀመረ። ከግል ሐዘናቸው በመነሳት ለሌሎች ቤተሰቦች ተስፋ ለመሆን የወሰኑት አቶ ወንዱ፣ የማቲዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲን መሠረቱ፤ በኋላም ተቋሙ ወደ ማቲዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን ተለወጠ።
ላለፉት 22 ዓመታት ፋውንዴሽኑ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የካንሰርና ሌሎች ተላላፊ ያልሆኑ ሕመምተኞች በሕክምና ለመደገፍ፣ የኬሞቴራፒ መድኃኒቶችንና የላቦራቶሪ ምርመራ ወጪዎችን ለመሸፈን እንዲሁም ከሩቅ አካባቢዎች ለሕክምና የሚመጡ ሕመምተኞችንና አስታማሚዎቻቸውን ለመደገፍ ሰፊ ሥራ አከናውኗል።
አቶ ወንዱ በግል በጎ አድራጎታቸውም የሚታወቁ ነበሩ። በትውልድ አካባቢያቸውና በአዲስ አበባ ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ በማድረግ፣ ለአብያተ ክርስቲያናትና ለገዳማት እንዲሁም በትውልድ መንደራቸው ለመስጊዶች ድጋፍ በማድረግ ይታወቁ ነበር።
በካንሰር ቁጥጥር፣ በትምባሆ ቁጥጥርና በተላላፊ ያልሆኑ ሕመሞች ላይ በሀገር ደረጃ ለተደረጉ የፖሊሲ ለውጦች ያበረከቱት አስተዋጽኦም በስፋት ይጠቀሳል። ፋውንዴሽኑም ከ2017 እስከ 2024 ዓ.ም. ብቻ ስድስት ዓለም አቀፍና ሦስት አገር አቀፍ በድምሩ ዘጠኝ ሽልማቶችን ማግኘቱ ተገልጿል።
አቶ ወንዱ በበሽታ ላይ ሲሆኑም ከሥራቸው አልተለዩም። ለአንድ ዓመት ከ10 ወራት በላይ ከካንሰር ሕመም ጋር ትግል በማድረግ ሕክምናቸውን ሲከታተሉ እንኳን የፋውንዴሽኑን ሥራ በመምራት የታካሚዎችን ድምፅ ማሰማታቸውን ቀጥለው ነበር።
አቶ ወንዱ በቀለ ከወ/ሮ አምሳለ በየነ ጋር ከ42 ዓመታት በላይ በትዳር የቆዩ ሲሆን፣ የሦስት ልጆች አባትና የሁለት የልጅ ልጆች አያት ነበሩ። በደግነታቸውና በሰዎች ላይ በነበራቸው የማያቋርጥ ድጋፍ ግን ከቤተሰባቸው አልፈው ለብዙዎች “አባት” ሆነው ኖረዋል።
አቶ ወንዱ በቀለ የጀመሩት የጤናና የበጎ አድራጎት ሥራ እንዲቀጥል፣ የእሳቸውም ራዕይ በተግባር እንዲተረጎም ቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጆቻቸውና ባልደረቦቻቸው ጥሪ አቅርበዋል።
እጅግ የተከበሩ የሕዝብ ባለውለታ አቶ ወንዱ በቀለ ወ/ማርያም፣ በጎ ሥራዎት ይታወሳል፤ ለብዙዎች ያበሩት ብርሃንም ከመቃብር በላይ ይዘልቃል።
ለባለቤታቸው ወ/ሮ አምሳለ በየነ፣ ለልጆቻቸው ዮናስ ወንዱና ሚዛን ወንዱ፣ ለልጅ ልጆቻቸው፣ ለመላው ቤተሰብ፣ ወዳጅ ዘመድና የሥራ ባልደረቦቻቸው መጽናናትን እንመኛለን።
ነፍሳቸው በሰላም ትረፍ።

4 days ago
"ታሞ ሕክምና ሲከታተል ነበር። ባልጠበቅነው ሁኔታ በድንገት ነው ያረፈው" - የሟች ቤተሰብ
ልጃቸው ህፃን ማቲዎስን የካንሰር በሽታ ሲነጥቃቸው በልጃቸው ስም የህክምና ተቋም ያቋቋሙት "የማቲዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን" መስራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ወንዱ በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ፋውንዴሽኑና ቤተሰባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።
አንድ ቤተሰባቸው በሰጡን ገለጻ፣ አቶ ወንዱ በቀለ ሕይወታቸው ማለፉን ገልጸው፣ "ታሞ ሕክምና ሲከታተል ነበር። ከዚያም ወዲህ ወደ አይሲ (IC) ገብቶ ተመልሶ ወጥቷል፤ ባልጠበቅነው ሁኔታ በድንገት ነው ያረፈው" ብለዋል።
"ዝርዝሩን አሁን ባለሁበት ሁኔታ መግለጽ አልችልም" ያሉት እኚሁ ቤተሰብ፣ "ህመሙ ከጀመረው ከ1 አመት በላይ ሆኖታል። ህመሙ የጉበት ካንሰር ነው። ሃሌሉያ ሆስፒታል ክትትል ላይ ነበር" ሲሉም ተናግረዋል።
አቶ ወንዱ በቀለ የተወለዱት፣ ሕዳር 21ቀ ን 1947 ዓ/ም በሐረርጌ ክፍለ ሀገር በወበራ አውራጃ ደደር ከተማ በቡርቃ ገጠራማ ቀበሌ ከአባታቸው አቶ በቀለ ወ/ማርያምና ከእናታቸው ወ/ሮ ዘነበች ወ/ማርያም መሆኑን ፋውንዴሽናቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
በተወለዱ በ72 ዓመታቸው መስከረም 24/2019 ዓ/ም ባደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም ድካም ተለይተዋል ብሏል።
ሥርዓተ ቀብራቸው ነገ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም በቦሌ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ከቀኑ 6 ሰዓት እንደሚፈጸምም ጠቁሟል።
አቶ ወንዱ በቀለ ከአመታት በፊት የአራት ዓመት ልጃቸው ህፃን ማቲዎስ ወንዱ በደም ካንሰር በሽታ ተጠቅቶ በህክምና ማዳን አልተቻለም።
ታዳጊ ልጃቸውን ያጡት አቶ ወንዱ ሀዘናቸውን ዋጥ አድርገው "ማቲዎስን ማዳን ባይቻልም ብዙ ማቲዎሶችን ማዳን እንችላለን" በሚል "ማቲዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ" የሚል የህክምና ተቋም አቋቁመው ካለፉት 22 ዓመታት ጀምሮ በሺዎች ለሚቆጠሩ የካንሰር ህሙማን የህክምና አገልግሎት መስጠት ችለዋል።
ሶሳይቲው፣ ከዚህ ቀደም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ "የካንሰር ህመም እየመጨረ ነው" ሲል በመግለጽ ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጥ ማሳሰቡ ይታወሳል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
እሁድ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia " የካንሰር ህክምናዬን እየተከታተልኩ ነው ፤ በህክምና ቆይታዬ ህሙማን የሚሰማቸውን ስሜት ተረድቻለሁ " - አቶ ወንዱ በቀለ ማቲዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን 22ኛ የምስረታ በዓሉን አከበረ። በ4 ዓመቱ በደም ካንሰር ምክንያት ከዚህ ዓለም የተለየውን ህፃኑን ማቲዎስ ማዳን ባይቻልም ብዙ ማቲዎሶችን እናድናለን በሚል የተቋቋመው ማቲዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን ላለፉት 22 ዓመታት ህሙማንን በመርዳትና ተላላፊ ያልሆኑ…

5 days ago
የማቲዮስ ወንዱ ፋውንዴሽን መስራች ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
የማቲዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን መስራች እና ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ወንዱ በቀለ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ መስከረም 24 ቀን 2019 ዓ.ም. ረፋድ ከዚህ ዓለም ተለይተዋል።
አቶ ወንዱ በቀለ በኢትዮጵያ በካንሰር በሽታ ቁጥጥር እና በሕፃናት ሕክምና ድጋፍ ዙሪያ የሚሰራው "ማቲዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን" (የቀድሞው ማቲዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ) መስራች እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ነበሩ።
በሙያቸው የቢዝነስ አስተዳደር ባለሙያ የሆኑት አቶ ወንዱ በቀለ፣ የበጎ አድራጎት ሥራቸውን እንዲጀምሩ ያደረጋቸው ልጃቸው ሕፃን ማቲዎስ ወንዱ በደም ካንሰር (Leukemia) ሕመም ምክንያት በሕፃንነቱ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ነበር።
የልጃቸውን ሕልፈት መታሰቢያ በማድረግ ሚያዝያ 9 ቀን 1996 ዓ.ም (በ2004 እ.ኤ.አ) ድርጅቱን መሠረቱ።
ተቋሙ በካንሰር ለተያዙ አቅም የሌላቸው ሕፃናትና ወላጆቻቸው የምክር፣ የመጠለያ፣ የሕክምና ቁሳቁስ እና የፋይናንስ ድጋፍ ይሰጣል።
በተጨማሪም፤ የካንሰር ተጋላጭነትን ለመቀነስ ጥብቅ የትንባሆ ቁጥጥር ሕጎች በሀገሪቱ እንዲወጡ ከጤና ሚኒስቴር እና ከዓለም ጤና ድርጅት ጋር በመሆን ከፍተኛ የፖሊሲ ሙግት አድርገዋል።
አሐዱ ሬድዮ አቶ ወንዱ በቀለ ህልፈት የተሰማውን ሐዘን እየገለጸ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ቤተሰቦቻቸው መጽናናትን ይመኛል።

የማቲዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን መስራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ወንዱ በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
የማቲዎስ ወንዱ-የኢትዮጵያ ካንሰር ማህበር (የማቲዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን) መስራች እና ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ወንዱ በቀለ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ መስከረም 24 ቀን 2019 ዓ.ም ረፋድ ከዚህ ዓለም ተለይተዋል።
አቶ ወንዱ ወጣቱን ልጃቸውን ማቲዎስን በካንሰር በሽታ ካጡ በኋላ፣ ያጋጠማቸውን የግል ሃዘን ወደ ህይወት ዘመን አገር አቀፍ ተልዕኮ በመቀየር በኢትዮጵያ የካንሰር ህሙማን እንክብካቤ፣ ግንዛቤ ማስጨበጫ እና የህዝብ ጤና ፖሊሲ ተሟጋችነት ዘርፍ ታላቅ አሻራ ያኖሩ አንጋፋ ሰው ነበሩ።
በፋውንዴሽኑ ስር በመሆን በሺዎች የሚቆጠሩ የካንሰር ህሙማንን (በተለይ ሴቶችን እና ህፃናትን) የህክምና፣ የስነ-ልቦና እና የማህበራዊ ድጋፍ እንዲያገኙ አድርገዋል።
ህብረተሰቡ ስለ ካንሰር ያለው ግንዛቤ እንዲለወጥ እና በበሽታው ዙሪያ የነበረውን ስጋትና ማህበራዊ ጫና ለመቀነስ ሰፊ አገር አቀፍ ንቅናቄዎችን መርተዋል።
ከካንሰር እንክብካቤ ባለፈ በሀገሪቱ የህዝብ ጤና ፖሊሲዎች በተለይም የትንባኦ ቁጥጥር ስራዎች እና የህግ ማዕቀፎች እንዲጠናከሩ ግንባር ቀደም ሚና ተጫውተዋል።

7 days ago
እስከ 70% የሚደርሱ የጡት ካንሰር ህመምተኞች ወደ ህክምና የሚሔዱት በሽታው ከተባባሰ በኋላ እንደሆነ ተገለጸ
በኢትዮጵያ ከ65 እስከ 70 በመቶ የሚሆኑ የጡት ካንሰር ሕመምተኞች ወደ ሕክምና ተቋማት የሚሄዱት የበሽታው ደረጃ ከፍ ካለ በኋላ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ 700 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በዚሁ በሽታ እንደሚሞቱ ተገልጿል።
በጤና ሚኒስቴር የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሕይወት ሰለሞን፣ "የጡት ካንሰር በበለጸጉ ሀገራት ጭምር እየጨመረ መጥቷል" ብለዋል።
ከማህፀን በር ጫፍ ካንሰር እና ከሌሎች መሰል ሕመሞች መካከል የጡት ካንሰር በግንባር ቀደምነት እንደሚጠቀስም ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ በነሐሴ እና በኅዳር ወራት መካከል፣ በፈረንጆቹ ደግሞ በኦክቶበር ወር የጡት ካንሰር ቀንን በማሰብ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።
ዕለቱ ሲከበር ለማኅበረሰቡ ግንዛቤ ከመፍጠር ባለፈ የምርመራ ሥራ እንደሚከናወን ዶክተር ሕይወት ጠቁመዋል።
በሽታው ከፍ ያለ ደረጃ ላይ ደርሶ የሚመጡ አብዛኞቹ ሕመምተኞች ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጫና እንደሚደርስባቸውም ገልጸዋል።
በተመስገን ተጋፋው

8 days ago
በስህተት ጤናማ እግሯ የተቆረጠባት አሜሪካዊት ሁለቱንም እግሮቿን አጣች
በአሜሪካ ኦሃዮ ግዛት የምትገኝ ሻሮን ጃክስ የተባለች የካንሰር ታካሚ በሴልቢ ጄኔራል ሆስፒታል ለቀዶ ጥገና በገባችበት ወቅት በህክምና ቡድኑ በፈጸመው ከባድ ስህተት ህይወቷ ተለውጧል።
WBNS እንደዘገበው ታካሚዋ የታመመው የቀኝ እግሯ እንዲቆረጥ ወደ ሆስፒታል ብትገባም፡ ሀኪሞቹ በስህተት ጤናማውን የግራ እግሯን ቆርጠውታል።
ከቀዶ ጥገና በኋላ ከእንቅልፏ ስትነቃ ያልታመመው እግሯ መቆረጡን ያወቀችው ሻሮን፡ በኋላ ላይ የቀኝ እግሯም መቆረጥሁለቱንም እግሮቿን ለማጣት ተገዳለች።
የታካሚዋ ጠበቃ እንደገለፁት፡ ከቀዶ ጥገናው በፊት የቀኝ እግሯ በግልጽ የተቀመጠ መለያ ምልክት የነበረው ቢሆንም የህክምና ቡድኑ ግን ስህተቱን ፈፅሟል።
ሆስፒታሉ የሰራተኞቹን ጥፋት ያመነ ሲሆን፡ ከጉዳዩ ጋር እጃቸው ያለበት ሰራተኞች ከስራ መባረራቸውን አስታውቋል።
አሁን ላይ ተጎጂዋ በሆስፒታሉ እና በህክምና ቡድኑ ላይ የካሳ ክስ መስርታለች።

13 days ago
🚨 #እንድታውቁት
የኢትዮጵያ የምግብ እና መድኃኒት ባለሥልጣን /EFDA በካንሰር ሕክምና ላይ የሚውለው "Avastin 400 mg/16 mL" የተሰኘው መድኃኒት ሐሰተኛ ቅጅ በሀገሪቱ ገበያ ውስጥ መገኘቱን በማረጋገጥ ማስጠንቀቂያ አውጥቷል።
የካንሰር ሕክምና መድኃኒቱን ሕጋዊ አምራች ከሆነው «F. Hoffmann-La Roche Ltd» ከተገኘው መረጃና ከተደረገው የድህረ-ገበያ ቁጥጥር በተገኘው ግኝት መሠረት፤ የፓኬጁ ባች ቁጥር H1180A34 የሆነውና የምርት እንዲሁም የማብቂያ ቀኑ 01/2026 እና 05/2029 ተብሎ የተጻፈበት መድኃኒት ሐሰተኛ መሆኑ ተረጋግጧል ብሏል።
ትክክለኛው «Avastin 400 mg/16 mL» መድኃኒት በውስጡ «bevacizumab» የተሰኘውን ይዘት የያዘና የአንጀት፣ የጡት፣ የኦቫሪ እንዲሁም የኩላሊት ካንሰር ሕክምናዎች ላይ የሚውል ነው።
ይህንን የተጭበረበረ ምርት መጠቀም በሕሙማን ላይ ከፍተኛ የጤና አደጋና የሕይወት ስጋት የሚያስከትል በመሆኑ የሕክምና ተቋማት፣ የጤና ባለሙያዎችና ሕሙማን ከስርጭትና ጥቅም ላይ ከመዋል እንዲያግዱት ባለሥልጣኑ ጥሪ አቅርቧል።
ኅብረተሰቡ ወይም የጤና ባለሙያዎች ይህን ምርት ሲያገኙ ወይም ጉዳት ሲያጋጥማቸው በነፃ ስልክ መስመር 8482፣ በኢሜይል pharmacovigilanceefda.gov.et፣ በ«Med Safety» ሞባይል መተግበሪያ ወይም በባለሥልጣኑ ድረ-ገጽ (www.efda.gov.et) ጥቆማ መስጠት ይችላሉ ተብሏል።
@TikvahethMagazine

14 days ago
በኢትዮጵያ በአመት በጡት ካንሰር ህመም ከሚያዙ 80 ሺህ ሴቶች ውስጥ ግማሽ ያህሎቹ ለህልፈት ይዳረጋሉ።
የጡት ካንሰር በሽታ በኢትዮጵያ ለበርካታ ሴቶች ህልፈት ምክንያት እየሆነ መምጣቱን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በጤና ሚኒስቴር የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሕይወት ሰለሞን ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት የጡት ካንሰርን በተመለከተ ከ65 እስከ 70 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ወደ ህክምና ተቋም የሚመጡት የህመሙ ደረጃ ከፍ ካለ በኋላ ነው፤ ይህም ከሕክምና አንፃር አዳጋች የሚሆንበት ሁኔታ መኖሩን ጠቅሰው ለጉዳዮ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ ተናግረዋል።
በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የጡት ካንሰር እና የእንቅርት ሰብ ስፔሻሊስት ዶ/ር ተስፋዬ አጋ በበኩላቸው በኢትዮጵያ 80 ሺህ የሚሆኑ አዲስ የጡት ካንሰር ታካሚዎች በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ ይመዘገባሉ። ከእነዚህም መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ወይም 60 በመቶ ያህሎቹ ለህልፈት ይዳረጋሉ ብለዋል።
በኢትዮጵያ ከፍተኛ ለሆነ የጡት ካንሰር ሞት ምክንያት የሆኑ ጉዳዮች በርካታ ናቸው ያሉት የህክምና ባለሙያው የህብረተሰቡ የግንዛቤ እጥረት፣በቂ የህክምና ተቋማትና አገልግሎት ያለመኖር ተጠቃሽ መሆናቸውን አንስተዋል።በተጨማሪም የመድሀኒት እና የህክምና መሳሪያዎች እጥረትን ጨምሮ በቂ የሰለጠኑ የጤና ባለሙያዎች አለመኖር ሌሎች መንስኤዎች እንደሆኑ ጠቅሰዋል።
ሲጋራ ማጨስ፣አልኮልን አብዝቶ መጠቀም፣ከመጠን በላይ የሆነ ውፍረት፣ጤናማ የአመጋገብ ስርአት አለመኖር፣እንቅስቃሴ አለማድረግ፣የጡት ካንሰር የቤተሰብ ታሪክ መኖር፣ዘግይቶ ልጅን መውለድ እና የእድሜ መጨመር ለጡት ካንሰር ህመም አጋላጭ ከሆኑ መንስኤዎች መካከል ናቸው።ጡት ላይ ህመም የሌለው እባጭ፣ከጡት ጫፍ የሚወጣ ፈሳሽ፣የቆዳ ቀለም መለወጥና የጡት ቆዳ ወደ ውስጥ መሰርጎድ የበሽታው ምልክቶች ሊሆኑ እንደሚችሉ ተነግሯል።
በመሆኑም እድሜዋ 30 አመት የሞላት አንዲት ሴት አስቀድማ በሽታውን መከላከል እንድትችል በአመት አንዴ በጤና ባለሙያ ዘንድ ቀርባ የጡት ምርመራ ማድረግ ይኖርባታል ተብሏል።የጤና ሚኒስቴርም ለጉዳዮ መፍትሄ ለማምጣት የጡት ካንሰር ጋይድላይን ማዘጋጀቱን ገልጾ በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች የቅድመ ምርመራ እያደረገ እንደሚገኝ ተናግሯል።
ቅድስት ደጀኔ

ያለማዘዣ የሚሸጠው "ፎርማሊን" ለውስብስብ የጤና ችግሮች ስለሚያጋልጥ ቁጥጥር ሊደረግበት ይገባል ተባለ
መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬዲዮ) ያለ ሐኪም ማዘዣ በመድኃኒት መደብሮች የሚሸጠው "ፎርማሊን" ካንሰርን ጨምሮ ለተለያዩ ውስብስብ የጤና ችግሮች ስለሚያስከትል ጥብቅ ቁጥጥር ሊደረግበት እንደሚገባ ተገለጸ።
በአዲስ አበባ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን የመድኃኒት ተቋማት ቁጥጥር ባለሙያው አቶ ንጉሡ ብዙወርቅ መድኃኒቱ ያለማዘዣ ከሚሸጡ መድኃኒቶች መካከል አንዱ እንደሆነ ጠቅሰው ሰዎች ላልተፈለገ ጥቅም ሲያውሉት ለከፍተኛ የጤና ጉዳት እንደሚያጋልጥ አብራርተዋል።
ባለሙያው "አንዳንድ አካላት" ሲሉ የገለጿቸው ግለሰቦች ይህንን እና ሌሎች ያለማዘዣ የሚሸጡ መድኃኒቶችን በምግብ ነክ ቁሶች ላይ አለአግባብ እንደሚጠቀሙ መረጃዎች እንዳሉ ተናግረዋል።
ምግቦች ሳይበላሹ ለረጅም ጊዜ እንዲቆዩ ለማድረግ መድኃኒቱን መጠቀም ለጤና አደገኛ መሆኑ ተጠቅሷል።
የኢትዮጵያ ምግብ እና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ከሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመሆን ያዋቀረው የባለሙያዎች ቡድን የጉዳቱን መጠን እያጠና ሲሆን፣ ጥናቱ እንደተጠናቀቀ መድኃኒቱ በማዘዣ ብቻ እንዲሸጥ የሚያስገድድ መመሪያ ይወጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።
ቀደም ሲል እንደ "ትራማዶል" ያሉ መድኃኒቶች በጥናት መነሻነት በማዘዣ ብቻ እንዲሸጡ መደረጋቸውን ያስታወሱት ባለሙያው፣ የ"ፎርማሊን" ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ የመድኃኒት መደብሮች የማማከር አገልግሎት እንዲሰጡ መክረዋል።
በመሰረት ሙሉ
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ፌስቡክ ገጽ፡- https://web.facebook.com/a...
ቴሌግራም ገጽ፡- https://t.me/ahaduradi

ላንድማርክ ሆስፒታል የታካሚዎች ደህንነት ቀንን አከበረ
#ethiopia | ላንድማርክ አጠቃላይ ሆስፒታል የዓለም አቀፍ የታካሚዎች ደህንነት ቀንን ለ8ኛ ጊዜ አከበረ። የዘንድሮው መርሃ ግብር በተለይ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ለሚጠቁ ታካሚዎች ደህንነቱ የተጠበቀ ሕክምናና እንክብካቤ ማረጋገጥ ላይ አተኩሯል።
የላንድማርክ አጠቃላይ ሆስፒታል መስራች ፕሮፌሰር ከበደ ኦሊ በመርሃ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ከ11 ታካሚዎች አንዱ በሕክምና ሂደት ወቅት ከደህንነት ጉድለት ጋር በተያያዘ ለጉዳት ሊዳረግ እንደሚችል የዓለም አቀፍ መረጃዎች እንደሚያመለክቱ ገልጸዋል። በታዳጊ ሀገራት ደግሞ ችግሩ የበለጠ ሊስፋፋ እንደሚችል ጠቁመዋል።
ደህንነቱ የተጠበቀ ሕክምና ለማረጋገጥ የመድኃኒትና የሕክምና ቁሳቁሶች ጥራት፣ የሕክምና መሣሪያዎች ተገቢ አጠቃቀምና ጥገና፣ የጤና ባለሙያዎች ብቃትና ሥልጠና እንዲሁም የጤና ተቋማት የአሠራር ሥርዓት ወሳኝ መሆናቸውን ፕሮፌሰር ከበደ አስረድተዋል። የታካሚዎች ደህንነት እንዲረጋገጥም የጤና ባለሙያዎች፣ ታካሚዎች፣ ቤተሰቦች፣ ማህበረሰብና መንግሥት በጋራ መሥራት እንዳለባቸው ገልጸዋል።
በዘንድሮው የታካሚዎች ደህንነት ቀን ትኩረት የተሰጠው በተለይ የልብና የደም ቧንቧ በሽታ፣ ካንሰር፣ የስኳር በሽታና ሥር የሰደዱ የመተንፈሻ አካላት በሽታዎችን ጨምሮ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች የሚጠቁ ታካሚዎች የሚያገኙት ሕክምና አስተማማኝ እንዲሆን ነው። በጊዜ መመርመር፣ ተገቢ ሕክምና መስጠትና ቀጣይነት ያለው ክትትል ማድረግ በዚህ ረገድ ተጠቃሚ መሆኑ ተጠቁሟል።
የታካሚዎችና የቤተሰቦቻቸው ተወካይ ኢንጂነር ፈቲያ መሐመድ በበኩላቸው፣ ታካሚዎችና ቤተሰቦቻቸው ከታካሚው ጋር በቅርበት ስለሚገኙ በሕክምና ሂደት ውስጥ ቀድመው ሊያስተውሏቸው የሚችሉ ጉዳዮች እንዳሉ ገልጸዋል። የታካሚዎችንና የቤተሰቦችን ድምፅ መስማትና ማክበር የታካሚዎችን ደህንነት ለማሻሻል አስፈላጊ መሆኑንም አስገንዝበዋል።
በዕለቱ ላንድማርክ አጠቃላይ ሆስፒታል ከአጋር ድርጅቶችና ባለድርሻ አካላት ጋር በተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ላይ የሚደረገውን ሕክምና ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ የጋራ የትብብር ስምምነት ማዕቀፍ ይፋ አድርጓል።
የዓለም አቀፍ የታካሚዎች ደህንነት ቀን ከ2019 ዓ.ም. ጀምሮ በየዓመቱ የሚከበር ሲሆን፣ ዓላማው በሕክምና ሂደት የታካሚዎችን ደህንነት ስለማረጋገጥ ግንዛቤ ማሳደግና በዘርፉ ዓለም አቀፍ ትብብርን ማጠናከር ነው።
#patientsafety #safecare
#worldpatientsafetyday #safehealthcare #healthcaresafety #patientcare #healthcarequality #healthforall

16 days ago
የትኩስ ሻይ ቡና አፍቃሪዎች ማወቅ ያለባቸው እውነታ
በጣም ትኩስ ሻይ ወይም ቡና መጠጣት ለጉሮሮ ካንሰር ሊያጋልጥ እንደሚችል በቅርቡ የተደረገ ጥናት አረጋገጠ። ተመራማሪዎች እንዳሉት ከ10 ዓመታት በላይ ባደረጉት ክትትል፣ ትኩስ መጠጥ አዘውትረው የሚጠጡ ሰዎች ከቀዝቃዛ መጠጥ ተጠቃሚዎች ጋር ሲወዳደሩ እስከ ሦስት እጥፍ የሚደርስ የስጋት ደረጃ አላቸው። ከዚህም በላይ በቀን ከስድስት ሲኒ በላይ መጠጣት አደጋውን ይጨምረዋል።
ችግሩ ያለው ከሻይ ወይም ከቡና ዓይነት ሳይሆን ከመጠጡ ከፍተኛ ሙቀት የተነሳ ነው። መፍትሔው ቀላል ነው፤ ሙቅ መጠጦችን ትንሽ እስኪቀዘቅዙ መጠበቅ ከዚህ ስጋት ይጠብቃል።
ተመራማሪዎቹ 1 ሚሊዮን ገደማ በሚደርሱ አዋቂዎች ላይ ጥናቱን ማድረጋቸውን ዲስካቨር ማጋዚን ጠቁሟል፡፡

17 days ago
ናይጄሪያ በሮቦት የተደገፈ የመጀመሪያውን ቀዶ ሕክምና አከናወነች
የናይጄሪያ የሕክምና ባለሙያዎች በካንሰር የተጠቃን ኩላሊት በሩቅ ሆኖ በሮቦት እርዳታ በስኬት በማስወጣት አዲስ ታሪክ አስመዝግበዋል። ይህ እመርታ በሀገሪቱ የሕክምና እድገት ላይ ትልቅ ምዕራፍ ከፍቷል።
የሕክምና ባለሙያዎቹ እንደገለጹት፤ የቦታ ርቀት ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ ሕክምና የማግኘት መብታቸውን ሊከለክላቸው አይገባም። ይህ አዲስ ቴክኖሎጂ ህሙማን ጥራት ያለው ሕክምና ለማግኘት ወደ ውጭ ሀገር የሚያደርጉትን ጉዞ በእጅጉ ይቀንሰዋል።
ይህን ስኬት ለማስቀጠልም በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ 150 የሕክምና ባለሙያዎችን የሚያሰለጥን አዲስ የሮቦቲክ አካዳሚ እንደሚቋቋም ተነግሯል።

የ2 ወር እድሜ ተሰጥቶት የነበረው መምህር የ6 ዓመታት አስደናቂ ተአምር!
#ethiopia | በፈረንጆቹ 2020 ዶክተሮች ጆን ዳቤል በህይወት የሚቆየው ለሁለት ወራት ጊዜ ብቻ ነው አሉ።
ዛሬ ላይ ሆነን ስናየው ግን ጆን አሁንም በህይወት አለ በጽናትም እየኖረ ይገኛል።
የጆን የካንሰር ትግል የተጀመረው ከአስር ዓመታት በፊት በ2009 ነበር።
መምህር የነበረው ጆን የምላሱ ማበጥ አሳስቦት ወደ ህክምና ሲሄድ ከባድ የአንገትና የጭንቅላት ካንሰር እንደያዘው ተነገረው።
ከዚያ በኋላ የገጠመው ህክምና እጅግ አስጨናቂ ነበር።
ለ13 ሰዓታት በተደረገ ከባድ ቀዶ ጥገና ዕጢውና አብዛኛው የምላሱ ክፍል ተቆርጦ ተወገደ።
ከዛም የኬሞቴራፒ እና የራዲዮቴራፒ ህክምናዎችን አጠናቀቀ።
እኛ በየቀኑ የምናደርጋቸው መናገር መብላትና ምራቅን መዋጥ ለጆን በየቀኑ ትልቅ ፈተናዎች ሆኑበት።
ጆን ያንን ሁሉ ተወጥቶ በህይወት ተረፈ።
ነገር ግን በ2020 የኮቪድ ወረርሽኝ መግቢያ ላይ ካንሰሩ ዳግም ተመለሰ።
በዚህ ጊዜ ዶክተሮች በጉሮሮው ውስጥ ደረጃ 4 ላይ የደረሰና ሊድንም የማይችል ዕጢ አገኙበት።
ዶክተሮቹም የቀረው እድሜ የሁለት ወር ብቻ ሊሆን እንደሚችል ነገሩት።
ነገር ግን ሁለት ወሩ ወደ ሶስት ወር አደገ።
ሶስት ወሩ ወደ ስድስት ወር።
ከዚያም ወደ ዓመታት ተቀየረ።
ጆንም የተቀበለውን የጊዜ ገደብ በቁጭት በጥሩ ልብ ነበር።
ጆን በየቀኑ በእግር መጓዝን ልክ እንደ ህክምናው አንድ አካል አድርጎ ያየው ጀመር።
በየቀኑ እስከ 8 ኪሎ ሜትር ያህል ይጓዛል።
ህክምና በሚወስድባቸው ቀናት እና በአስከፊ የአየር ጠባይ ውስጥ እንኳ ሳይቀር ወደ ውጭ ወጥቶ ይራመዳል።
በእግር ጉዞው ወቅት ደግሞ አንድ እጅግ ተራ ግን አስደናቂ ተግባር ያከናውናል ሌሎች የጣሉትን ቆሻሻ ያነሳል።
በእጁ የቆሻሻ ማንሻ ቁሳቁስና ፌስታል ይዞ በየመንገዱ ላይ ያሉ ቆሻሻዎችን ያጽዳል።
በአንድ ወቅት ሲጽፍ “የቀኔ እጅግ ውብ አጋጣሚ ጠዋት ቆሻሻ ስለቅም የማያውቁኝ ሰዎች ቆመው ምስጋና ሲያቀርቡልኝ ነበር” ብሏል።
ሊድን የማይችል ካንሰር አለበት የተባለው ጆን ስለ መኖር ብቻ አይደለም የሚያወራው።
እርሱ የሚያወራው ስለ ህይወት አላማ፣ ስለ ተስፋ እና በእጃችን ላይ ባሉ ጥቂት ነገሮች ላይ እንዴት ቁጥጥር ማድረግ እንደምንችል ነው።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #johndabell #cancersurvivor #inspiration #hope #kindness

ሰላም፣ እንደምን አደራችሁ?
የሰው ሰራሽ አስተውሎት፡ ለኢትየጵያ ሁለንተናዊ እድገት መፋጠን
በቀደሙት ጊዜያት ሀገራት የጦርነት አቅምን የሚያጎለብቱ መሳሪያዎችን መታጠቅ የኃይል ምንጫቸው አድርገው የሚቆጥሩት ራስን ማስከበሪያ መንገድ ነበር፡፡
ዛሬ ላይ ግን በኢኮኖሚና በፖለቲካ ዘርፉ ተፅዕኖ መፍጠሪያ እንዲሁም የፉክክር ዋነኛው መንገድ በቴክኖሎጂ የበላይነትን መያዝ ሆኗል፡፡
ዓለም በቴክኖሎጂ እየተራቀቀች በምትገኝበት በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ ከዳር ተመልካችነት ወጥታ ወደ ዋና ተጋሪነት ለመቀላቀል የሚያስችል መንገድ ላይ እየተጓዘች ትገኛለች፤ ይህንንም በዘላቂነት ለማስቀጠልና የተሻለ ደረጃ ላይ ለማድረስ በወጣቶች ላይ በተግባር እየተሰራ ነው፡፡
በዚህም የራስን አቅም በራስ ለመገንባትና የራስን ችግር በራስ ለመፍታት የሚያስችል ከአፍሪካ ፈር ቀዳጅ የሆነውን የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ገንብታ ወጣቶቿ ክህሎታቸውን የሚያዳብሩበትን መንገድ አመቻችታለች፡፡
ኢትዮጵያ በርካታ በግብርናው ዘርፍ የተሰማሩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ያሏት እንደመሆኑ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ የአፈር ለምነትን፣ የአየር ንብረትና የተባይ በሽታዎችን ቀድሞ በመተንበይ ሀገሪቱ በምግብ ሉዓላዊነቷን ለማስከበር የምታደርገውን ጥረት የሚያግዝ ሆኗል፡፡
በሌላ በኩል በጤናው ዘርፍ የሕክምና ምስሎችን የሚተነትኑ፣ የጡት ካንሰር፣ ቲቢ፣ የሳንባ ሕመሞችን የሚለዩ ሶፍትዌሮች ተዘጋጅተዋል፡፡
የሰሌዳ ቁጥር ማሳወቂያ፣ የሰው ፊት ማሳወቂያ፣ በቪዲዮ የሚደረግ የትራፊክ ፍሰት መቆጣጠሪያ እንዲሁም ስማርት ፖሊስ ጣቢያዎች የመሳሰሉት ደህንነትን ከማስጠበቅ አንፃር ቴክኖሎጂውን ተከትለው የመጡ በረከቶች ናቸው፡፡
በኢትዮጵያ የተለያዩ የተቋማት አገልግሎቶች እንዲሁም የትምህርት መርጃዎች የሚሰጡት በውስን ቋንቋዎች እንደመሆኑ ሀገሪቷ ያላትን 130 ሚሊየን በላይ ሕዝብ ያማከሉ ባለመሆናቸው በዚህ ቴክኖሎጂ አማካኝነት ተጨማሪ ቁጥር ያላቸው ቋንቋዎች ወደ መተግበሪያ እንዲጨመሩ በመሆኑ ለዜጎች ቋንቋዎችን ተርጉሞ የመረዳት እድል አሳድጓል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በብሪክስ መሪዎች ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር የሰው ሰራሽ አስተውሎት በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ለውጥን እውን ለማድረግ ወሳኝ መሆኑን አጽንዖት ሰጥተዋል፡፡
በመሆኑም በዚህ ሰዓት ለኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ቅንጦት ሳይሆን ከልማትና እድገት አንፃር የሚቃኝ መሠረታዊ ከሚባሉት ነገሮች አንዱ ነው፡፡
ኢትዮጵያ በሻንጋይ በተካሄደ ስብሰባ 29 ከሚሆኑ ሀገራት ጋር በመጣመር የዓለም አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ትብብር ድርጅት መስራች አባል በመሆን ተፈራርማለች፡፡ በቻይናና አሜሪካ ካሉ የቴክኖሎጂ ተቋማት ጋር የዳታ ሴንተር ግንባታና የክላውድ መሠረተ ልማት ስምምነቶችንም አድርጋለች፡፡
የዓለም ሀገራት ዛሬ ያሉበት ላይ ለመድረስ ብዙ ጊዜያትን ፈጅተዋል፤ ኢትዮጵያ ግን ያንን ረጅም መንገድ መጓዝ አይጠበቅባትም፤ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘመን ላይ በመሆናችን በቀላል መንገድ ለልማት እንድንፈጥን የሚያስችለን ጊዜ ላይ ነን፡፡
ስለሆነም ዘርፉን ይበልጥ ለማዘመን እና የሚሰጠውን ዘርፈ ብዙ ጥቅም ለማሳደግ የተጀመሩ ሥራዎችን በቁርጠኝነት ማጠናከር ይገባል፡፡

22 days ago
በኢትዮጵያ በቀን 600 ሰዎች ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ህይወታቸው ያልፋል ተባለ።
በአለምአቀፍ ደረጃም ሆነ በኢትዮጵያ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፏ መምጣታቸው ተጠቁሟል።
ይህ የተባለው በዛሬው እለት በኢትዮጵያ ለ8ኛ ጊዜ የሚከበረውን የዓለም አቀፍ የሕሙማን ደህንነት ቀንን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው መድረክ ላይ ነው።የጤና ሚኒስቴር ከአለም ጤና ድርጅት ጋር በመተባበር አለም አቀፍ የሕሙማንን ደህንነት ቀንን አስመልክቶ መድረኩን ያዘጋጀ ሲሆን እለቱም‹‹ ደህንነቱ የተጠበቀ ክብካቤ ለጤናማ ህይወት በሚል መሪ ቃል ›› በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል በተለያዩ መርሃ-ግብሮች እየተከበረ ይገኛል።
የሪዞልቭ ቱ ሴቭ ላይቭ በኢትዮጵያ ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ግርማ አሰፋ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት በአለም አቀፍ ደረጃ አራት ህይወታቸው ከሚያልፉ ሰዎች ሶስቱ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች የተነሳ ህይወታቸውን ያጣሉ። ይህ ሁኔታ በኢትዮጵያም ጎልቶ እንደሚታይ ተናግረው በቀን 600 የሚሆኑ ሰዎች በዚህ በሽታ ህይወታቸው ያልፋል ነው ያሉት።ከጉዳዮ ጋር በተያያዘ የህክምና አገልግሎት ማዕቀፉ ተደራሽነትን ለማሳደግ ብዙ ስራ መስራት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።
ዶክተር ግርማ መረጃዎችን ጠቅሰው እንደተናገሩት በኢትዮጵያ በደማቸው ውስጥ የደም ግፊት አለባቸው ተብለው የሚጠበቁ አዋቂዎች ከ11 እስከ 12 ሚሊዮን ይገመታሉ።እንደ የደም ግፊት፣ የስኳር፣ የልብ፣ የደም ቧምባ በሽታ እና የካንሰር ህመም ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች መካከል በዋነኛነት ተጠቃሽ ሲሆኑ የሚፈለገውን የጤና ግብ ለማሳካት የታካሚ ደህንነት እና እንክብካቤ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ መሆኑ ተመላክቷል።
በመሆኑም በዘንድሮው የህሙማን ደህንነት ቀን ለጉዳዮ ትልቅ ትኩረት በመስጠት ውጤታማ ስራ ለመስራት ያግዛል ተብሏል።

"ገንዘቤ ባንክ ውስጥ ተቀምጦ ከምሞት የካንሰር ህመምተኞች ይታከሙበት!"
#ethiopia | በጡረታ የተገለሉት ህንዳዊቷ ዶክተር በህይወት ዘመናቸው የቆጠቡትን ገንዘብ ለካንሰር ታካሚዎች እንዲሆን ለግሰዋል።
የቀድሞ የህንድ የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት ሐኪም የነበሩት እኚህ አዛውንት አቅም የሌላቸው ሴቶች የካንሰር ህክምና ማግኘት እንዲችሉ የቆጠቡትን ሙሉ ገንዘባቸው ለግሰዋል።
በህክምና ሙያ ዘመናቸው የካንሰር ህክምና ከአቅማቸው በላይ በመሆኑ ምክንያት በርካታ ሴቶች ሲሰቃዩ መመልከታቸውን ተናግረዋል።
በመሆኑም ገንዘባቸው በባንክ አካውንት ውስጥ ከመቀመጥ ይልቅ እነዚህን ሴቶች መርዳቱ የበለጠ ጥቅም እንዳለው ወስነዋል።
ወደ 350,000 ዶላር የሚጠጋው ይህ የገንዘብ የገንዘብ ልገሳ በካንሰር ህክምና ላይ ለሚገኙና ለተቸገሩ ሴት ታካሚዎች ይውላል ነው የተባለው።
አዛውቷ ሰዎችን በመንከባከብ ሁለት አስርት ዓመታትን ካሳለፉ በኋላ በህይወታቸው የቆጠቡትን አብዛኛውን ገንዘብ ያንኑ ደግ ተግባራቸው ለማስቀጠል አውለውታል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #drlakshmibai #inspiration #womenhealth #generosity #cancercare #aiims #humanity #healthcarehero #philanthropy

26 days ago
አፍሪካ አሜሪካን የምታንበረክክበት የAI ዘመን
አፍሪካ የዓለምን የኃይል ሚዛን የምታፈራርስበት የAI ምሥጢር
የኔታ ሚዲያ
ለክፍለ ዘመናት፣ የዓለም ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ካርታ የተሳለው በጥቂት የምዕራባውያንና የምስራቅ እስያ ኃያላን ሀገራት ብዕር ነበር። አፍሪካ ደግሞ በዚህ ታላቅ የዓለም ድራማ ላይ የጥሬ ዕቃ አቅራቢ፣ የብድር ተቀባይ እና የታሪክ ተመልካች ሆና እንድትቀጥል ተፈርዶባት ኖራለች። የኢንዱስትሪ አብዮት ባቡር ሲያመልጣት፣ የፋብሪካዎች ጭስና የባቡር ሀዲዶች አውሮፓንና አሜሪካን ወደ ሀብት ማማ ሲያወጧቸው፣ አህጉሪቱ ግን በታሪክ የኋላቀርነት ሰንሰለት ታስራ ቀረች። ነገር ግን ታሪክ መስመራዊ አይደለም፤ አልፎ አልፎ ዓለምን ከመሠረቱ የሚያናውጡ እና የቀደመውን የኃይል ሚዛን ፍጹም አቧራ የሚያስቡ ታላላቅ ማዕበሎች ይመጣሉ።
ዛሬ፣ በሰው ሰራሽ አስተዋይነት (AI) አማካኝነት እየመጣ ያለው አብዮት ያንን የቆየ የኃይል ተዋረድ ለመደምሰስ የተዘጋጀ ታሪካዊ ማዕበል ነው። እስኪ አስበው፤ ቀደም ሲል (Before Computing) ዘመን አንዲት ሀገር ኃያል ለመሆን ግዙፍ የፋብሪካ ጭስ ማውጫዎች፣ የባቡር መስመሮች እና በቢሊዮን የሚቆጠር የካፒታል ሀብት ያስፈልጋት ነበር።
አሜሪካና ምዕራባውያን ይሄንን መሠረተ-ልማት ለመገንባት ሁለት መቶ ዓመታት ፈጅቶባቸዋል። አፍሪካ ያንን ሁሉ መንገድ ደረጃ በደረጃ መጓዝ አለባት ማለት ዘላለማዊ ጥገኝነትን መቀበል ነበር። ነገር ግን AI የታሪክን የጊዜ ሰሌዳ አጣጥፎታል። በይነመረብና የኮምፒውተር ኃይል በጂኦሜትሪ እድገት (Exponential Growth) በሚፈጥኑበት በዚህ ዘመን፣ አፍሪካ የመጨረሻዋ ተቀባይ ሳይሆን የቴክኖሎጂው ቀዳሚ ተጠቃሚ የሚትሆንበትና ከአሜሪካ ጋር እኩል የምትሰለፍበት መንገድ ተከፍቷል።
ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? ወደፊት ረቅቅ አድርገን እንመልከት።
በሕክምናው ዘርፍ፣ አሜሪካ ዘመናዊ ሆስፒታሎችንና የላቀ የሕክምና ተቋማትን ለመገንባት ትሪሊዮን ዶላሮችን አፍስሳለች። አፍሪካ ግን ለብዙ ዘመናት የዶክተሮች እጥረት ሰለባ ነበረች። አሁን ግን AI ይህንን ክፍተት በአንድ ጀምበር ያጠፋዋል። በሴራሊዮን ወይም በኢትዮጵያ ገጠራማ መንደር ያለች አንዲት ተንቀሳቃሽ ስልክ፣ በAI አምሳያ የተሰራንና በዓለም ላይ ያሉ ሁሉንም የሕክምና መጻሕፍት፣ የካንሰር ምርመራዎችንና የምስል ትንተናዎችን (MRI/CT Scans) ያጠና የሱፐር-ኮምፒውተር አእምሮ በኪሷ ይዛለች።
በአሜሪካ ታዋቂ ሆስፒታል ውስጥ የሚገኝ ስፔሻሊስት ዶክተር ሊደርስበት የማይችለውን ጥልቅ የሕክምና ምርመራ፣ የAI ረዳት በሴኮንዶች ውስጥ በማከናወን ሕይወት ይታደጋል። አፍሪካ ቢሊዮን ዶላር ወጥቶባቸው የሚገነቡ ሆስፒታሎችን ሳትጠብቅ፣ ቀጥታ ወደ "ዲጂታል ሕክምና" (Leapfrogging) በመሸጋገር የህዝቧን ጤና ከአሜሪካ የሕክምና ጥራት ጋር እኩል ታደርጋለች። በግብርናና በኢኮኖሚው ዘርፍ የሚከሰተው ተአምር ደግሞ ይበልጥ ያስገርማል።
አሜሪካ ሰፊውን የግብርና መሬቷን የምታርሰው በግዙፍ ትራክተሮችና በቢሊዮን ዶላር የሚገመቱ የቴክኖሎጂ አግሮ-ኢንዱስትሪዎች ነው። አፍሪካ ግን በAI የሚመሩ ርካሽ ድሮኖችንና አነስተኛ የሴንሰር መዋቅሮችን በመጠቀም፣ ሳይንሳዊ የአፈርና የውኃ አጠቃቀምን በአጭር ጊዜ ውስጥ ትተገብራለች።
በሳተላይት መረጃዎችና በAI ስልተ-ቀመሮች የሚመሩ አነስተኛ ድሮኖች፣ የትኛው መሬት ምን ዓይነት ንጥረ-ነገር እንደሚፈልግ፣ ዝናብ መቼ እንደሚጥል እና ተባዮች የት ጋር እንደተከሰቱ ከሰማይ ተንቢየው ይናገራሉ። በውጤቱም፣ እስካሁን ያልታረሱት የሰሃራ በታች የዓለም ግዙፍ ለም መሬቶችና የውኃ ሀብቶች በAI ጥበብ አማካኝነት ታርሰው አፍሪካን የዓለም ዋነኛ የምግብ ቅርጫት ያደርጓታል። አሜሪካ በግብርናው ዘርፍ ያላትን የበላይነት አፍሪካ በጥቂት ዓመታት ውስጥ ትረከበዋለች።
ይህ አብዮት በፖለቲካውና በወታደራዊው የኃይል ሚዛን ላይ የሚያመጣው ለውጥ ደግሞ እጅግ አስደንጋጭ ነው።
ቀደም ሲል አሜሪካ የዓለም ፖሊስ የሆነችው በቢሊዮን ዶላር የሚገመቱ የጦር መርከቦች፣ የአየር ኃይሎችና ግዙፍ ወታደራዊ በጀት ስላላት ነበር። በAI ዘመን ግን የጦርነትና የመከላከያ ትርጉም ተቀይሯል። ግዙፍ ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች ይዞ ከመንቀሳቀስ ይልቅ፣ በAI የሚመሩ እና በራሳቸው ውሳኔ የሚሰጡ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ አነስተኛና ርካሽ ድሮኖች (Swarm Drones) የጦር ሜዳውን ሙሉ በሙሉ ይቆጣጠሩታል።
አንዲት አነስተኛ የአፍሪካ ሀገር በAI የተቃኘ የሳይበር መከላከያና የድሮን ሰራዊት በመገንባት፣ የትኛውንም ግዙፍ የባህር ኃይል ወይም የጦር አውሮፕላን ማክሸፍ የምትችልበት አቅም ታገኛለች።
የወታደራዊ አቅም የበላይነት የሚለካው በሰው ኃይል ብዛት ወይም በብረት ክብደት ሳይሆን፣ በስልተ-ቀመሮች (Algorithms) ፍጥነትና ጥራት ይሆናል። ከሁሉም በላይ ደግሞ የአፍሪካ ትልቁ ሀብት የሕዝቧ ስነ-ሕዝብ (Demographics) ነው። አሜሪካ፣ አውሮፓ እና ምስራቅ እስያ በዕድሜ የገፉ ሰዎች ሀገር እየሆኑ ሲመጡ፣ አፍሪካ የዓለም ወጣቱና ንቁው የሰው ኃይል ማዕከል ነች። ይህ ወጣት ትውልድ የቀደመውን የኢንዱስትሪ ዘመን ቢሮክራሲ ሳይሸከም፣ ቀጥታ ከAI ጋር ተዋህዶ አዳዲስ የሶፍትዌር፣ የባዮ-ቴክኖሎጂ እና የሳይንስ ግኝቶችን መፍጠር ይጀምራል።
በአንድ ወቅት በድህነትና በረሃብ የምትታወቀው አህጉር፣ በAI ዘመን የዓለም የዲጂታል አእምሮ ማዕከል ሆና ትወጣለች።
ወይ ጉድ! AI እንዲህ ሊያደርገን ይችላል? አዎን! የዓለም ታሪክ በሚቀጥሉት ጥቂት አሥርተ ዓመታት ውስጥ የመጨረሻውን ታላቅ ሰርፕራይዝ ለማሳየት እየተዘጋጀ ነው። ቴክኖሎጂ ሀብታሞችን ብቻ ሳይሆን፣ ወደኋላ የቀሩትን ወደፊት የማስወንጨፍ ተፈጥሮአዊ ህግ አለው።
አፍሪካ የኢንዱስትሪውን ዘመን ታሪክ በሽንፈት አጠናቃ ይሆናል፤ የሰው ሰራሽ አስተዋይነትን (AI) ዘመን ግን በበላይነትና በንጉሥነት ለመምራት በታሪክ ደጅ ላይ ቆማለች።

Comments