5 days ago
አሸንድዬ፣ ሻደይ፣ ሶለል እና የአገው ፈረሰኞች በዓላት በዩኔስኮ እንዲመዘገቡ በጥናት ተለይተው ለኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን መላካቸው ተገለጸ
የአማራ ክልል ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ የአሸንድዬ፣ ሻደይ እና ሶለል በዓላትን "የሰሜን ኢትዮጵያ የልጃገረዶች በዓላት" በሚል፣ የአገው ፈረሰኞች ባህልን ደግሞ "የአገው ፈረስ ባህል" በሚል ስያሜ በዩኔስኮ በማይዳሰሱ የዓለም ቅርሶች ዝርዝር ውስጥ ለማስመዝገብ በጥናት መለየቱን አስታውቋል።
ቢሮው ለጥናቱ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን አጠናቅቆ ለኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን ማስረከቡን ለአሐዱ ሬድዮ ገልጻል።
የክልሉ ቱሪዝም ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አበበ እምቢያለ ለአሐዱ ሬድዮ እንዳስታወቁት፣ ቅርሶቹ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሲታወቁ የውጭና የሀገር ውስጥ ቱሪስቶችን በመሳብ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ገቢ ያስገኛሉ።
ቅርሶቹ በዩኔስኮ እንዲመዘገቡ ጥረት የሚደረገው ጥንታዊ ይዘታቸውን ጠብቀው ለቀጣዩ ትውልድ እንዲተላለፉና ዓለም አቀፍ የጥበቃ ድጋፍ እንዲያገኙ ለማድረግ መሆኑንም አብራርተዋል።
አቶ አበበ አክለውም፤ "እነዚህ ባህሎች የአብሮነት እና የሰላም ውርስ በመሆናቸው በሕዝቦች መካከል ያለውን እርቅና ሰላማዊ አብሮነት ለዓለም የሚያሳዩ ናቸው" ብለዋል።
የአማራ ክልል በቱሪስት ሀብት የታደለ በመሆኑ፣ ቅርሶችን በማጉላትና የገቢ ምንጭ በማድረግ ረገድ በትኩረት እንደሚሠራም አጽንኦት ተሰጥቶበታል።
በደረጄ መንግስቱ
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

1 month ago
ልጃገረዶቸና ወጣቶች ባህላዊ ጨዋታዎችን በጋራ እያከበሩ ነው !
በአማራ ክልል ከክረምቱ መግባት ጋር ተያይዞ በተለያሉ አካባቢዎች ሲከበሩ የነበሩ እንደ ቡሄ :ሻደይ: አሸንድዬ : ሶለል : እንግጫ ነቀላ እና አሱሪቲ የተባሉ ባህላዊ ክብረበዓላት የማጠቃለያ ፕሮግራም በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው ።
እነዚህ ክብረ በዓላት በየ አካባቢያቸው ካለፈው ነሀሴ ወር ጀምሮ በተለይ በልጃገረዶች ዘንድ ሲከበሩ የቆዩ ሲሆን ዛሬ በጋራ በባህር ዳር ከተማ በክልል አቀፍ ደረጃ በጋራ እያከበሩ ይገኛሉ
1 month ago
ልጃገረዶችና ወጣቶች ባህላዊ ጨዋታዎችን በጋራ እያከበሩ ነው !
በአማራ ክልል ከክረምቱ መግባት ጋር ተያይዞ በተለያሉ አካባቢዎች ሲከበሩ የነበሩ እንደ ቡሄ :ሻደይ: አሸንድዬ : ሶለል : እንግጫ ነቀላ እና አሱሪቲ የተባሉ ባህላዊ ክብረበዓላት የማጠቃለያ ፕሮግራም በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው ።
እነዚህ ክብረ በዓላት በየ አካባቢያቸው ካለፈው ነሀሴ ወር ጀምሮ በተለይ በልጃገረዶች ዘንድ ሲከበሩ የቆዩ ሲሆን ዛሬ በጋራ በባህር ዳር ከተማ በክልል አቀፍ ደረጃ በጋራ እያከበሩ ይገኛሉ
1 month ago
ታላቅ የባህልና ጥበብ ድግስ በውቢቷ ባህርዳር
የአማራ ክልል የክረምት ክብረ በዓላት የማጠቃለያ ፕሮግራም በባህርዳር ከተማ በድምቀት ይካሄዳል።
በአማራ ክልል ከሚከበሩት 6 የክረምት ክብረ በዓላት የተውጣጡ ከ200 በላይ ልጃገረዶች ቱባ ባህላቸውን ይዘው ወደ ባህርዳር ገብተዋል።
✨ ቡሄ — ከደብረ ታቦር
✨ ሻደይ — ከዋግኽምራ
✨ አሸንድዬ — ከላስታ ላሊበላ፣ ወልድያና እብናት
✨ ሶለል — ከራያ ቆቦና ወልድያ
✨ እንግጫ ነቀላ — ከምስራቅ ጎጃም
✨ አሱሪቴ — ከአዊ
ከባህርዳር ከተማም ከ400 በላይ ወጣቶችና ልጃገረዶች ለታላቁ የባህል ድግስ ተዘጋጅተዋል።
ታዋቂ ድምፃውያን መድረኩን ያደምቃሉ።
የአማራ ባህልና ኪነ-ጥበብ፣ የጎንደሩ ፋሲለደስ እና የጎጃሙ ግሽ ዓባይ ቡድኖችም ትዕይንቱን ይገማሸራሉ።
ቦታ፦ አፄ ቴዎድሮስ ስታዲየም — ባህርዳር
ቀን፦ ጳጉሜ 1/2018 ዓ.ም — እሁድ
ሰዓት፦ ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ
የባህርዳር ህዝብ ሆይ!
የራሳችንን ባህል፣ ቅርስና ኪነ-ጥበብ በአንድነት እናክብር!
ኑ! በዚህ ድንቅ የባህልና ጥበብ ድግስ አብረን እንድመቅ!
#ባህርዳር #የአማራባህል #ቡሄ #ሻደይ #አሸንድዬ #ሶለል #እንግጫነቀላ #አሱሪቴ #ክረምትክብረበዓላት #ባህልናጥበብ

2 months ago
መልካም የእረፍት ቀን!
🎁 በልዩ ቅናሽ ያቀረብናቸው የአሸንዳ | ሻደይ | አሸንድዬ | ሶለል በዓል ጥቅሎች ቆይታ ዛሬ ሌሊት 6:00 ሰዓት ያበቃል!
#sunday #stayconnected #ethiotelecom #telebirr #digitalafrica #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia
Sponsored by
Surafel
2 months ago
«ዘመን ገበያ የአዲስ ዓመት ኤክስፖ» በይፋ ተከፈተ!
#fastmereja :-የመጪውን የ2019 አዲስ ዓመት አስመልክቶ በሴንቸሪ ፕሮሞሽን እና ኤቨንትስ አዘጋጅነት የሚከናወነው 35ኛው «ዘመን ገበያ የአዲስ ዓመት ኤክስፖ» በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ኤግዚብሽን ማዕከል በይፋ ተከፈተ።
ከዛሬ ነሐሴ 15 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለ21 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆየው ይህ ታላቅ የንግድ ትርኢትና ባዛር፤ ከ500 በላይ አምራቾችን፣ አስመጪና ላኪዎችን፣ የንግድ ወኪሎችን እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ያሳተፈ ነው።
በዚህ ኤክስፖ ህብረተሰቡ በቂ ጊዜ አግኝቶ በተረጋጋ ሁኔታ ግብይትና እረፍቱን እንዲያሳልፍ ሲባል የመጎበኛና የግዢ ሰዓቱ ከጠዋቱ 2:30 እስከ ምሽቱ 4:00 ሰዓት ድረስ እንዲራዘም የተደረገ ሲሆን ተሳታፊ አጋር ድርጅቶችም ለህብረተሰቡ ተመጣጣኝ ዋጋና ልዩ ቅናሽ ለማቅረብ መስማማታቸዉ ተገልጿል።
በዛሬው ዕለት የንግድ እንቅስቃሴው በይፋ የተጀመረ ሲሆን፤ ከነገ ነሐሴ 16 ቀን ጀምሮ እስከ ኤክስፖው ማጠናቀቂያ ድረስ በየቀኑ የሚካሄዱ የሙዚቃ ኮንሰርቶች ይጀምራሉ።
በተለይም እስከ ነሐሴ 21 ቀን ድረስ የአሸንዳ፣ አሸንድዬ እና ሶለል በዓላትን የሚያደምቁ ልዩ የባህል ጭፈራ መርሃ-ግብሮች ለታዳሚዎች የሚቀርቡ ይሆናል።
ታዳሚዎች የመግቢያ ትኬታቸውን በቴሌብር አማካኝነት በቀላሉ መቁረጥ የሚችሉ ሲሆን፤ በጳጉሜ 5 ቀን ምሽት በሚወጣው ዕጣ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ አውቶሞቢል፣ የBMW ኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል እና ብስክሌት በሽልማት የሚያገኙ ይሆናል።

💥🎁 አሸንዳ/ሻደይ/አሸንድዬ/ ሶለል የሞባይል ጥቅል!!
👉🏼 በዓሉን ምክንያት በማድረግ ልዩ ቅናሽ የተደረገባቸውን የበዓል ጥቅሎች በ*999#፣ በማይ ኢትዮቴል ወይም አርዲ ቻትቦት ለራስዎ ይግዙ፤ ለሚወዷቸው በስጦታ ያበርክቱ!
🔗 በቴሌብር ሱፐርአፕ https://bit.ly/telebirr_Su... ተጨማሪ 30% ስጦታ ያገኛሉ!
እስከ ነሐሴ 17/2018 ዓ.ም
🎉 መልካም በዓል!
#ethiotelecom #telebirr #telebirrsuperapp #digitalethiopian #realizingdigitalethiopia

የደብረ ታቦር በዓል ከኢትዮጵያ ውጭ በሌሎች አህጉራትእንደሚከበር ያውቃሉ ?
በቴዎድሮስ መኩሪያ
#ethiopia | ከኢትዮጵያ ውጭ ይህ በዓል በእንግሊዝኛው "Feast of the Transfiguration" (የጌታችን የብርሃን መገለጥ በዓል) በመባል ይታወቃል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ታቦር ተራራ ላይ ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን ይዞ ወጥቶ ፊቱ እንደ ፀሐይ ያበራበትንና ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ የሆነበትን (ማቴ 17፥1-8) ታሪክ መሠረት አድርጎ በመላው የክርስትና ዓለም ይከበራል።
በዓሉ መቼ መከበር ጀመረ? (ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ዳራ)
በምሥራቁ ዓለም (Early Eastern Church)፡ የደብረ ታቦር በዓልን ማክበር የተጀመረው በጣም ቀደም ብሎ ነው። በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን (በ326 ዓ.ም ገደማ) ንግሥት ዕሌኒ በእስራኤል በሚገኘው የደብረ ታቦር ተራራ ላይ ቤተ ክርስቲያን ካነጸች በኋላ፣ በዓሉን በተራራው ላይ ማክበር ተጀመረ። ከ5ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ደግሞ በምሥራቅ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ በስፋት መከበር ጀመረ።
በምዕራቡ ዓለም (Western Church)፡ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በዓሉ በተለያዩ አካባቢዎች ይከበር የነበረ ቢሆንም፣ ዓለም አቀፋዊ በዓል ሆኖ በይፋ እንዲከበር የታወጀው በ1456 ዓ.ም (15th Century) በሊቀ ጳጳሳት (Pope) ካሊክስተስ 3ኛ (Callixtus III) ነው። ይህም የክርስቲያን ሠራዊት በቤልግሬድ ጦርነት ኦቶማን ቱርኮችን ድል ያደረጉበትን መታሰቢያ ለማመስገን ነው።
አከባበሩ ምን ይመስላል?
ይህ በዓል በአውሮፓ፣ በእስያ፣ በሰሜንና ደቡብ አሜሪካ በሚገኙ የኦርቶዶክስ፣ የካቶሊክ እና የአንግሊካን አብያተ ክርስቲያናት ይከበራል። አከባበሩም የየራሱ የሆነ የተለየ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ገጽታ አለው።
ሀ) በእስያ አህጉር (በተለይ በእስራኤል/ፍልስጤም)
በተራራው ላይ የካቶሊክ (Franciscan Church of the Transfiguration) እና የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያናት ይገኛሉ። በበዓሉ ዋዜማ ከመላው ዓለም የመጡ ምዕመናን ድንኳን ተክለው፣ ሌሊቱን ሙሉ የጸሎት ትጋት (Night Vigil) በማድረግ ያሳልፋሉ። በዕለቱ ፀሐይ ስትወጣ ታላቅ ቅዳሴ ይቀደሳል። እንደኢትዮጵያውያን የችቦ መብራት ትውፊት ባይኖራቸውም፣ ሻማዎችን በማብራት የብርሃኑን መገለጥ ያስባሉ።
በአውሮፓ አህጉር (በተለይ በምሥራቅ ኦርቶዶክስ - ሩሲያ፣ ግሪክ፣ ሮማኒያ)
የበዓሉ ቀን፡ በነዚህ ሀገራት በዓሉ በግሪጎሪያን ካሌንደር ነሐሴ 6 (August 6) አሊያም እንደ ኢትዮጵያ ነሐሴ 13 (August 19) ይከበራል።
አከባበሩና የፍራፍሬ ቡራኬ ሥርዓት (Blessing of the First Fruits)፡ በግሪክ፣ ሩሲያ እና ሌሎች የባልካን ሀገራት በዓሉ እጅግ ደማቅ ነው። በኢትዮጵያ እናቶች "ሙልሙል ዳቦ" ጋግረው እንደሚያካፍሉት ሁሉ፣ በእነዚህ ሀገራት ደግሞ "የመጀመሪያ የፍራፍሬ ምርት" (በተለይም ወይን እና ፖም/Apple) ወደ ቤተ ክርስቲያን አምጥተው የማስባረክ ጥንታዊ ትውፊት አላቸው።
በዚህ ዕለት ካህናት ነጭ ወይም በወርቅ የተንቆጠቆጠ ልብሰ ተክህኖ ይለብሳሉ (የክርስቶስን የብርሃን ልብስ ለመወከል)። ምዕመናኑም ከተባረከው ፍራፍሬ እየተቋደሱ የክረምቱን ማለፍና የመከሩን መድረስ ያከብራሉ።
በሰሜን እና ደቡብ አሜሪካ (በካቶሊክ እና ፕሮቴስታንት/አንግሊካን አብያተ ክርስቲያናት)
በእነዚህ አህጉራት በዓሉ በካቶሊክ፣ ኤፒስኮፓል፣ አንግሊካን እና ሉተራን አብያተ ክርስቲያናት ይከበራል።
ንደ አውሮፓ እና እስያ አደባባይ በሚወጣ ታላቅ ትዕይንት ባይሆንም፣ በዕለቱ ልዩ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት (Mass/Liturgy) ይካሄዳል። ስብከቱ የሚያተኩረው ክርስቶስ መለኮታዊ ክብሩን ስላሳየበት ሁኔታ እና ምዕመናን በሕይወታቸው መንፈሳዊ ለውጥ (Spiritual Transfiguration) ስለማምጣታቸው ነው።
የኢትዮጵያ የደብረ ታቦር (ቡሄ) በዓል ከሌሎች በምን ይለያል?
ከላይ እንዳየነው ሃይማኖታዊ መሠረቱ (የክርስቶስ ብርሃን መሆን፣ የሙሴና የኤልያስ መገለጥ፣ የደመና መታየት) በመላው ዓለም አንድ ቢሆንም፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አከባበር ግን ሙሉ በሙሉ ልዩ እና እጅግ አስገራሚ ሀይማኖታዊና ባህላዊ ማንነት አለው።
ጅራፍ ማጮህ፡ የክርስቶስን ድምፅ፣ ወይም በደብረ ታቦር የተሰማውን የአብን ድምፅ ("ይህ የምወደው ልጄ ነው...") ለማሰብ። (ይህ በዓለም የትም የለም)
ሆያ ሆዬ / የልጆች ዝማሬ፡ ልጆች ሐዋርያትን ወክለው የምስራች ይዘው መንደር ለመንደር መዘመራቸውና መመረቃቸው።ሙልሙል ዳቦ፡ ምስጢሩን ለማየት ተራራ ላይ ለወጡት ሐዋርያት የተላከ ስንቅን ለማሰብ፣ እንዲሁም እንደ አውሮፓውያን የበኩር ፍሬ (ምስጋና) አቻ መሆኑ።
በደብረ ታቦር ከተማ (ፋርጣ)፣ ከአሸንድዬ (የልጃገረዶች ጨዋታ) እንዲሁም ከታላላቆቹ የሀገራችን መሪዎች የአፄ ምኒልክና የእቴጌ ጣይቱ ልደት ጋር ተቆራኝቶ መከበሩ በዓሉን የኢትዮጵያውያን የብሔራዊ ኩራት እና የኪነ-ጥበብ መገለጫ ያደርገዋል።
የደብረ ታቦር በዓል የሰው ልጅ ከተፈጥሮ (ክረምት ወጥቶ ብርሃን ሲፈነጥቅ) እና ከፈጣሪው ጋር የሚያደርገውን ግንኙነት የሚያሳይ ዓለም አቀፋዊ የክርስትና በዓል ነው።
ይሁን እንጂ ወደ ደብረ ታቦር ከተማ ተጉዞ፣ አሸንድዬን እያዩ፣ የጅራፉን ጩኸት እየሰሙ፣ ሙልሙል እየቀመሱ እና በታላቋ ርዕሰ አድባራት ደብረ ታቦር ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ማክበር የሚሰጠው ስሜት፣ ከማንኛውም የዓለም ክፍል የላቀና ኢትዮጵያዊ ለዛ ያለው
ውብ ሥርዓት ነው!
ያመት ሰው ይበለን!!

ሴንቸሪ ፕሮሞሽን የ35ኛውን “ዘመን ገበያ የአዲስ ዓመት ኤክስፖ 2019” ሊያካሂድ ነው!
#fastmereja :-ሴንቸሪ ፕሮሞሽን እና ኤቨንትስ 35ተኛዉን ታላቅ የአዲስ አመት የንግድ ትርኢት እና ባዛር ከነሐሴ 15 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. ለ21 ተከታታይ ቀናት በኤግዚቢሽን ማዕከል እና በመስቀል አደባባይ እንደሚያካሂድ በዛሬው ዕለት በሰጡት ይፋዊ ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቁ።
ባለፉት 27 ዓመታት ከ60 በላይ ታላላቅ ሁነቶችን እና 34 የንግድ ትርኢቶችን ያዘጋጀው ሴንቸሪ ፕሮሞሽን፤ የዘንድሮውን የ2019 ዓ.ም. የአዲስ ዓመት ኤክስፖ ለማዘጋጀት በኤግዚቢሽን ማዕከልና ገበያ ልማት ድርጅት የወጣውን ጨረታ በማሸነፍ ወደ ተለመደው ስራው መመለሱን አስታውቋል።
በዚህ የንግድ ትርኢት እና ባዛር ላይ ከ500 በላይ አምራቾች፣ አስመጪና ላኪዎች፣ የንግድ ወኪሎች እና ልዩ ልዩ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች እንደሚሳተፉ ተገልጿል።
በዚህ የንግድ ትርኢት እና ባዛር ላይ የተለያዩ እጣዎች የተዘጋጁ ሲሆን በዚህም ላቅ ያሉ ሽልማቶች ተዘጋጅተዋል 1ኛ ዕጣ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሠራ ዘመናዊ አውቶሞቢል (መኪና) 2ኛ ዕጣ የቢ.ኤም.ደብሊው (BMW) ኤሌክትሪክሞተር ሳይክል እንዲሁም 3ኛ ዕጣ የኤሌክትሪክ ብስክሌት እንደሆነም ነዉ የተገለፀዉ።
በተጨማሪም ከነሐሴ 16 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን ድረስ በየምሽቱ የተለያዩ የሙዚቃ ኮንሰርቶች የሚቀርቡ ሲሆን፤ ከነሐሴ 16 እስከ 21 ባሉት ቀናት ደግሞ ለአሸንዳ፣ አሸንድዬ እና ሶለል በዓላት የተዘጋጁ ልዩ የባህል ጭፈራዎችና የየዕለቱ የሽልማት ውድድሮች እንደሚካሄዱ ተገልጿል።
📷 ከበደ መክብብ

1 year ago
የህዝብ ክብረ በዓላትን ለማስተዋወቅ እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ
#ethiopia | የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የባህልና ቋንቋ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ነፊሳ አልማህዲ በኢትዮጵያ የሚከበሩ የህዝብ ክብረ በዓላትን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።
ሚኒስቴር ዴኤታዋ እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ ለዘመናት የዳበሩ እና በትውልድ ቅብብሎሽ የጎለበቱ እምቅ የባህል ሀብቶች ባለቤት ነች። እነዚህን ሀብቶች በመጠቀም ሀገራዊ አንድነትን ለማጠናከር እና ባህል ለማህበረ-ኢኮኖሚ እድገት ያለውን አስተዋጽኦ ለማሳደግ ሚኒስቴሩ በፖሊሲ ላይ የተመሰረተ ሰፊ ስራ እየሰራ ነው።
በመግለጫቸው፣ በመጪዎቹ ሶስት ወራት የተለያዩ የህዝብ በዓላት እንዲከበሩ የባህል ንቅናቄ መጀመሩን አስታውቀዋል። ይህ ንቅናቄ ከፌደራል እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ በቅንጅት የሚከናወን ሲሆን፣ የህዝብ ተሳትፎን በማሳደግ የጋራ እሴቶችን ለማጎልበት ያለመ ነው።
በ2018 በጀት ዓመት የአዲስ ዓመት አቀባበል እና የጳጉሜ ቀናት በኪነ-ጥበብ ስራዎችና የተጎዱ ዜጎችን በመርዳት የመተሳሰብ እና የአብሮነት ባህላችንን በማጎልበት መከበራቸውን ወ/ሮ ነፊሳ ገልጸዋል።
በተጨማሪም በተለያዩ ክልሎች የተከበሩ የባህል በዓላትን በመጥቀስ፣ በትግራይ አሸንዳ፣ በአማራ ሻደይ፣ አሸንድዬ፣ ሶለል፣ እንግጫ ለቀማና ቡሄ፣ በኦሮሚያ ጎቤ እና ሽኖዬ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ጉዋንዳ፣ እንዲሁም በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የዳውሮ ቶኢ-ቤኣ እና የኮንታ እንግጫ ክብረ በዓላት በደመቀ ሁኔታ መከበራቸውን አብራርተዋል።
በመስከረም ወር የሚከበሩ በዓላትን በተመለከተም መግለጫ የሰጡ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል በደቡብ ኢትዮጵያ የጊፋታ፣ የዮ መስቀላ እና የጋዜ መስቀላ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ የማሳላ፣ ያሆደ፣ መስቀል እና ሄቦ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ማሽቃሮ ባሮ፣ በኦሮሚያ ኢሬቻ እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ጋሪ ዎሮ ክብረ በዓላት በደመቀ ሁኔታ እንዲከበሩ ሰፊ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።
በመጨረሻም፣ እነዚህ በዓላት የህዝቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር የሚያጠናክሩ በመሆናቸው፣ ህዝብና መንግስት በጋራ ተቀናጅተው የተሳካ በዓል እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል። እንዲሁም፣ ሚዲያዎች እነዚህን በዓላት በአገር አቀፍ፣ በአህጉር አቀፍ እና በአለም አቀፍ ደረጃ በማስተዋወቅ አገራዊ ገፅታን በመገንባት ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው አሳስበዋል።

ላስታ በነሃሴ ካልመጣችሁ ብዙ ቀርቶባችኋል።
"አሸንድዬ-የነሃሴ ፀሐይ"
በተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም
#ethiopia | ".....ላስታ በዓመት ብዙ ጊዜ ብዙ ዓይነት ነው። ጥምቀት ተአምር ይታይበታል። እንደ ታኅሣሥ በነሐሴ ይደምቃል። ነሐሴን ያላየ በታኅሣሥ አውቀዋለሁ አይበል።
"ተወረወረች ኮከብ፤
ተወረወረች ኮከብ፣
በጊዮርጊስ ክበብ".... ኮከብ ስትወረወር ቤተ ጊዮርጊስ አፋፍ ላይ ቆሜ ያየሁበት፡፡ የምስጋና ኮከብ፣ የሆታ ኮከብ፣ የወጣቶች ኅብረ ዜማ ኮከብ፡፡
ነሐሴ ሲጋመስ ላስታ እንደ ታኅሣሥ በበዓል ይደምቃል፡፡ ተራሮች በጅራፍ ድምጽ ያስገመግማሉ፣ ከምትሰሙት ይልቅ በመካከላቸው ኾናችሁ የምመለከተውን መመልከት ብትችሉ ስሜቱን በተጋራችሁኝ።
አንድ ሰው "በሕይወት ዘመኔ ላስታ ስንቴ ልምጣ ቢለኝ?" ምን እመልሳለሁ። ምድሩም ሰውም የማይጠገብበት፣ ቅርሱም ባህሉም ሰርክ ብርቅ የሚኾንበት።
የቅድስቷን ማረግ በምሳሌ የሚያሳዩ ክብ ጨዋታዎች ያፈዛሉ። ከላስታ ምድር ላሊበላ የገቡት ደናግላን ከወርወር ቆነጃጅት ጋር ሆነው የሰው ቀልብ ያስራሉ።
በገና መጣሁ ያለ የአሸንድዬ ቀርቶ “ላስታን አውቀዋለሁ” የማይመስል ነው። የላስታ ተራሮች እንደ ልጃገረዶቹ ሳያጌጡ መድረስ ምን መምጣት ይባላል?
"እንደ ነአኩተለአብ እንደላልይበላ፤
ቤት ሠራች ይሉኛል ዲንጋዩን ፈልፍላ፤
ዲንጋዩን ፈልፍላ የሠራችው ቤት፤
አልባብ አልባብ ይላል ማርያም ገብታበት።” ይሄንን ላሊበላ ገብቶ መስማት ሌላ ስሜት አለው። በቤዛ ኩሉ የፈዘዘ በልጆቻቸው አጀብ ብሎ የሚቀርበት ቀን እንዲደርስ ነሐሴ አጋማሽ ቀጥሬዋለሁ።
ወንዶችም ሴቶችም ጠጉራቸው ልዩ ነው። ተኩለው ያጌጡት፣ ለብሰው ያማሩት ልጃገረዶች እንዲህ የኾኑት ለሚናፍቁት ቀን ነው። ጋሜና ቁንጮ፤ ቅልስና ግልብጭ፣ የጠጉር ስሪቱ ዕድሜን ይገልጣል። አሸንድዬ ብዙ የሚታይበት። አሸንድዬ ቅጠል ነው፤ ቄጤማ መሳይ ቅጠል።
"አሸንድዬ፣ አሸንዳ ሆይ
እሽ እርግፍ አትይም ወይ" ሲሉ ሰማኋቸው። ውብ ኅብረ ዝማሬው ልብ ያረግፋል። ፍቅር፣ ውበት፣ መረዋ ድምፅ አብረው ናቸው። እሴቱ በብዙ ይገለፃል። የደስታ ቀን ነው።
"አስገባኝ በረኛ...አስገባኝ ከልካይ እመቤቴን ላይ፣
ጌታዬ አሉ ወይ...
አሉ እንጅ አሉ እንጂ፤
ግቡ ይላሉ እንጅ፤
ተዘንብሏል ጠጅ..." ይኼንን መሳይ ግጥም በውብ ዜማ ሳርዛና መንደሮች ይደመጣል። ከአሸተን ቁልቁል ይወርዳል። ኩል መስክ ኩልል ይላል። የብልባላ ጆሮዎች ምነኛ የታደሉ ናቸው፤ ይሄንን ሲሰሙ ኖረዋልና።
ያለ ንግግር፣ ያለ ግርግር፣ ያለ ተጨማሪ ብዙ ነገር፤ ባህል ብቻ ስላየሁበት ከድግስ የሚበልጥ ዓለም ብዬዋለሁ፡፡ እሴት ብቻ በኾነው ድንቅ ኩነት ወጣቶቹ ሙሽራ ያጀቡ ሚዜዎች መስለው ቀኑን ልዩ ያደርጉታል፡፡ ቤተ ጊዮርጊስን ከበቡት፡፡ እንደ ቤዛ ኩሉ ካህናት አሸበሸቡ፡፡"
ከሄኖክ ስዩም "መንገድ ዓይኑ ይፍሰስ" መጽሐፍ የተወሰደ

የአሸንዳ፣ አሸንድዬ እና ሶለል በዓላት የቀደመውን ትውፊት በጠበቀ መልኩ እንዲከበሩ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ
በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በየዓመቱ ከነሐሴ ወር አጋማሽ ጀምሮ ለሚከበሩት አሸንዳ፣ አሸንድዬ እና ሶለል በዓላት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቃቸውን የአማራ እና የትግራይ ክልል ባህል እና ቱሪዝም ቢሮዎች አስታውቀዋል፡፡
ነጻነት እና ሰላምን የሚሰብከው፤ ሴቶች በዘፈን እና በጭፈራ የሚያከብሯቸው በዓላት ለብዙ ሺሕ ዓመታት በአካባቢዎቹ ሲከበሩ መቆየታቸውን ስለበዓላቱ የተጸፉ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
በዚህም በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ሻደይ፣ አሸንድዬ፣ ሶለልና እንግጫ ነቀላ በዓላት እንደየአካባቢው ወግና ልማድ በተለያዩ ባህላዊ አልባሳት እና ጌጣጌጦች አምረውና ደምቀው አደባባይ በሚወጡ ልጃገረዶች ባህላዊ ዜማዎች እና ውዝዋዜዎችን ታጅበው በድምቀት ይከበራሉ።
በተመሳሳይ በትግራይ ክልልም የአሸንዳ በዓል በልጃገረዶች ልዩ የጸጉር አሰራር፣ የተለየ አለባበስ፣ ህብረ ዝማሬ እና የተለየ የአጊያጊያጥ ስርዓት ደምቆ በተለይም በመቀለ ከተማ በልዩ ሁኔታ በድምቀት ይከበራል፡፡
በተለይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የአክባሪዎቻቸው ቁጥር እየጨመረ እና የቱሪዝም መስህብ እየሆኑ የሚገኙትን እነዚህን በዓላት፣ ባህላዊ ትውፊትን በጠበቀ መልኩ ለማክበር እና ለማስከበር ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ የክልሎቹ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮዎች ገልጸዋል
ለክብረ በዓሉ የሚመጡ እንግዶችን ምቾት እና ማረፊያ ለመጠበቅ ዝግጅት መደረጉንም ጨምረው አስታውቀዋል፡፡
የአማራ ክልል ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዓባይ መንግስቴ፤ "አሸንድዬ፣ ሻደይ እና ሶለል በተለየ ድምቀት ከሚከበሩባቸው የክልሉ አካባቢዎች መካከል ጎንደር፣ ሰሜን ወሎ እና ዋግህምራ ይጠቀሳሉ" ብለዋል።
አቶ ዓባይ የክብረ በዓሉን ሁኔታ አስመልክቶ ለአሐዱ እንደተናገሩት፤ በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር ተከብሮ እንዲያልፍ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በስፋት ተሰርተዋል፡፡
የትግራይ ክልል የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አፅብዓ ገብረእግዚአብሔር በበኩላቸው፤ በዓሉን ለመታደም ወደ ክልሉ የሚመጡ ኢትዮጵያዊንን እና የውጭ ዜጎችን በሰላም ተቀብሎ ለመሸኘት የፀጥታን ጨምሮ በሁሉም ረገድ የሚደረጉ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
ሻደይ፣ አሸንዳ፣ አሸንድዬ እና ሶለል በሁለቱ ክልሎች ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚከበሩና በአብዛኘው ሴቶች እና ልጃገረዶች የሚሳተፉባቸው ዓመታዊ ክብረ በዓላት ሲሆኑ፤ ነጻነት እና ሰላምን ከመስበካቸው በተጨማሪ የክረምቱን ወቅት ማብቃትና የወንዙን መጉደል እና የጸሐይን መውጣት ያበስራሉ፡፡
#አሐዱ

የሻደይ፣ አሸንድዬ እና ሶለል በዓላት
#ethiopia | የሻደይ፣ አሸንድዬ እና ሶለል በዓላትንጨምሮ በነሐሴ ወር የሚከበሩ በዓላትን በድምቀት ለማክበር አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የአማራ ክልል ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ።
በአማራ ክልል በየዓመቱ ከነሐሴ ወር አጋማሽ ጀምሮ የሻደይ፣ አሸንድዬ፣ ሶለል እና እንግጫ ነቀላ የአደባባይ በዓላት እንደሚከበሩ የክልሉ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ መልካሙ ፀጋዬ ለኢቢሲ ተናግረዋል።
“እነዚህ በዓላት በተለይ ልጃገረዶች አደባባይ በመውጣት በድምቀት የሚያከብሯቸው በመሆናቸው የልጃገረዶች የነፃነት በዓላት ናቸው ብሎ መውሰድ ይቻላል” ብለዋል።
በዓላቱ በልጃገረዶች ብቻ ሳይሆን በሌላውም የማኅበረሰብ ክፍል ጭምር ተናፋቂ እየሆኑ መምጣታቸውንም ተናግረዋል።
ከቀናት በኋላ በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች መከበር የሚጀምሩት እነዚህን በዓላትን የማኅበረሰቡን ማኅበራዊ ግንኙነትን እና መስተጋብርን የሚያጠናክሩ መሆናቸውንም አስረድተዋል።
ከነሐሴ 16 እስከ 21 ቀን 2017 ዓ.ም የሻደይ፣ አሸንድዬ እና ሶለል በዓላት በስፋት በሚታወቁባቸው በወሎ፣ በዋግ ኸምራ እና ሌሎች አካባቢዎች በድምቀት እንደሚከበሩ ነው የተናገሩት።
እንዲሁም እንግጫ ነቀላ በዓልን በጳጉሜን ወር የመጨረሻዎቹ ቀናት በምስራቅጎጃም አካባቢዎች በድምቀት ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የቢሮ ኃላፊው ገልፀዋል።
ከሻደይ፣ አሸንድዬ እና ሶለል በዓላት በተጨማሪም የቡሄ (የደብረ ታቦር) በዓልን በደብረ ታቦር ከተማ በድምቀት ለማክበር ዝግጅት መደረጉንም አንስተዋል ያለው አራዳ ነው።

አሸንድዬ የላስታ ላሊበላ ድንቅ ውበት
#ethiopia | ሕዝብ ማንነቱን የሚገልጽበት የራሱ የኾነ ባሕል እና ወግ ያለው ነው፡፡ የላስታ ላሊበላ ሕዝብ ማኅበራዊ ዕሴቱን ከሚገልጽባቸው ባሕላዊ እሴቶች መካከል በየዓመቱ የሚከወነው አሸንድዬ በዓል አንዱ የአካባቢው ማኅበረሰብ መገለጫ ክብረ በዓል ነው።
ይህ በዓል ሃይማኖታዊ መሠረት ያለው እንደኾነም ይነገርለታል፡፡ የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ ገዳም የአራቱ ጉባኤያት መምህር ሊቀ ሊቃውንት ሳሙኤል አስናቀ የአሸንድዬ በዓል በፍልሰታ ጾም ፋሲካ የድንግል ማርያምን በዓለ ዕርገት አስመልክቶ የሚከበር መኾኑን ተናግረዋል፡፡
በዓሉ በሔዋን የመጣውን ዕዳ በድንግል ማርያም አማካኝነት ሴቶች ያገኙትን ነጻነት የሚያወሳ መኾኑንም ገልጸዋል፡፡ አሸንድዬ ቅጠሉ የብሉይ ዘመን ጨለማ በድንግል ማርያም እንዳበቃ አሁንም የክረምቱን ዘመን አብቅቶ አዲስ ዓመት መምጣቱን የሚያበስሩበት እንደኾነ ነው ያስረዱት፡፡
ወይዘሮ ገነት አሰፋ የላሊበላ ከተማ ነዋሪ ናቸው። በልጅነታቸው ያሳለፉትን የአሸንድዬ ክብረ በዓል ትውስታቸውን አካፍለውናል። አሸንድዬ ብለው የሚጠሩት በበዓሉ ወቅት ልጃገረዶች በወገባቸው የሚያስሩት ረጅም እና ስሩ ነጭ ከላይ አረንጓዴ የኾነ ቅጠል ነው። በዓሉም ስያሜውን ያገኘው ከዚሁ ነው ብለውናል፡፡
በላስታ ላሊበላ የአሸንድዬ በዓል በየዓመቱ ከነሐሴ 16 ቀን ጀምሮ የሚከበር ነው። ቅድመ ዝግጅቱ ከሳምንት በፊት ይጀመራል ነው ያሉት። ልጃገረዶች በሰፈራቸው በመሠባሠብ በዓሉን አንዴት እንደሚያከብሩት ይወያያሉ። ቡድኑን የምትመራው አለቃ የመምራት እና የማሥተባበር ችሎታ ያላት፣ በአካል እና በዕድሜ ከፍ ያለች መኾን እንዳለባትም ገልጸውልናል። ኀላፊነቷም ቡድኑን ማሥተባበር፣ መምራት እና ገንዘብ መያዝ ነው ይላሉ፡፡
ከዚያም መርሐ ግብራቸውን የሚጀምሩበትን እና እንዴት እንደሚከውኑት ይነጋገራሉ ነው ያሉት፡፡
በዓሉ ሦስት ቀን ሲቀረው ደግሞ ጸጉራቸውን እንደሚሠሩ ነግረውናል። የጸጉር አሠራሩም ታዳጊዎች ጋሜ፣ ቁንጮ እና ሳዱላ ሢሠሩ ከፍ ያሉት ልጃገረዶች ደግሞ ሹርቤ እና አፈሳሶ የሚባል የጸጉር ስሬት እንደሚሠሩ ትናንታቸውን አውስተውናል።
ልጃገረዶች ለበዓሉ ከጥጥ የተሠራ ጥልፍ ቀሚስ፤ የልጆች ከሌላቸውም የእናቶቻቸውን በመቀነት አሳጥረው እንደሚለብሱ ነግረውናል፡፡ በዕለቱ በእጅጉ ለመዋብ የአንገት ጌጦችን አጭር መስቀል፣ ትልቅ መስቀል፣ ድሪ፣ ማርዳ እና ድባ ልጃገረዶች ያደርጋሉ ብለዋል፡፡
ታዳጊዎች ደግሞ ቁርጥ የሚባል የአንገት ጌጥ ያደርጋሉ ነው ያሉት፡፡ በበዓሉ ዋዜማ አሸንድዬ ቅጠሉን ከዱር በማምጣት ሁሉም ሴቶች በወገባቸው ልክ በገመድ በመጎንጎን ይሠራና እንዳይደርቅ ሙጃ ሳር ውስጥ እርጥበት ባለበት ያድራል ነው ያሉት።
ነሐሴ 16 በበዓሉ ዕለት በጠዋት ሁሉም ተነስተው በተቀጣጠሩበት ቦታ ተገናኝተው አሸንድዬውን ወገባቸው ላይ በማሰር፣ የባሕል ልብስ እና ጌጦቻቸውን ያስተካክላሉ ነው ያሉት። ከዚያም በመጀመሪያ በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ ቤተክርስቲያን በመሔድ እና ለፈጣሪያችን ምስጋና በማቅረብ ከሃይማኖት አባቶች ምርቃን ይቀበላሉ።በመቀጠል በየሁሉም ሰው መኖሪያ ቤት በመሔድ አሸንድዬ ጨዋታ የተለያዩ ስንኞችን በመግጠም እና በማዜም እንደሚጫወቱም አውስተውልናል።
አሸንድዬ አሸንዳ ሙሴ
ፈሰስ በይ በቀሚሴ
አበ ሙሴ ኧኸ ወርቅ አበሙሴ
ፈሰስ በይ በቀሚሴ....ከሚዜሙ እያሉ ያዜማሉ።
የቤቱ ባለቤቶችም ያላቸውን ብር እና ዳቦ ይሰጣሉ። ከሌለ ደግሞ ከዓመት እንዲያደርሰን ተመረቀን እንወጣለን ነው ያሉት፡፡
በዚህ ሂደት ለአንድ ቡድን ሁለት ወንዶች ጅራፍ የሚያጮኹ ይከተላሉ፡፡ እነዚህ ወንዶች የሴቶች አሸንድዬ በሌሎች ቡድኖች እንዳይበጥስ እና የሚፈልጋት ልጃገረድ ካለችም የመጠበቅ ዓላማ ያላቸው ናቸው።
አሸንድዬ እየተባለ የተሰበሰበው ገንዘብ ይቀመጣል።
አዲሱ ዓመት እንዳለፈ የቡድኑ አባላት በተሰበሰበው ገንዘብ ጠላና ዳቦ ያዘጋጃሉ፡፡ የመስቀል ዕለትም የአካባቢውን ሰዎች በመጥራት ደግሰው ያበላሉ፤ ያጣጣሉ። በአበውም ይመረቃሉ ነው ያሉን።
የዚህ ዘመን የአሸንድዬ ተጫዋቾች የኾነችው በላይነሽ ገብረ አምላክ ደግሞ ለክብረ በዓሉ የአሸንድዬ ግጥም እና ዜማውን በቡድን በመለማመድ እየተዘጋጁ መኾኑን ለአሚኮ ተናግራለች፡፡
ከበዓሉ ቀደም ብለው ስለ አልባሳት፣ ጌጣጌጦች፣ ስለሚያካሂዱት መርሐ ግብር በመመካከር እንደሚዘጋጁ ነው የገለጸችልን፡፡ ከነሐሴ14 ጀምረው ልጃገረዶች ጸጉራቸውን ይሠራሉ፤ እንደቀደመው ሁሉ ልጆች ጋሜና ቁንጮ ልጃገረዶች ደግሞ ሹሩባና አፈሳሶ ይሠራሉ ብላለች፡፡
ልጃገረዶች አራት ውርድ ጥልፍ ቀሚስ በመቀነት ተሸንሽኖ ይለብሳሉ፤ ሕጻናት ደግሞ ትፍትፍ ቀሚስ ይለብሳሉ። አንገታቸው ላይ ደግሞ ቁርጥ፣ መስቀል፣ ድሪ እና ማርዳ በማድረግ ይደምቃሉ ነው ያለችው፡፡
የላሊበላ ከተማ አሥተዳደር ባሕል እና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ዲያቆን አዲሴ ደምሴ የአሸንድዬ በዓል በላስታ ላሊበላ ሃይማኖታዊ እና ባሕላዊ ይዘቱን ጠብቆ የሚከበር በዓል ነው ብለዋል፡፡
በዓሉ የፍልሰታ ጾም ማብቂያ እና የድንግል ማርያምን የዕርገት በዓል አስመልክቶ በላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት በካህናት እና በሰንበት ተማሪዎች በመዝሙር እና በሃይመኖታዊ ክዋኔዎች ይከበራል ነው ያሉት፡፡
ይህንን መነሻ በማድረግ ማኅበረሰቡ ባሕላዊ እና ሃይማኖታዊ ይዘቱን ጠብቆ በየዓመቱ ከነሐሴ 16 ጀምሮ ልጃገረዶች አምረው እና ተውበው የአሸንድየ ቅጠል በወገባቸው በማሰር አደባባይ የሚወጡበት መኾኑን ገልጸዋል፡፡
በበዓሉ ላይ የሚሳተፉት ልጃገረዶች ሲኾኑ ባሕሉ እንዳይበረዝ እናቶች እገዛ እንደሚያደረጉላቸውም ገልጸውልናል፡፡ በዓሉ ሴቶች በነጻነት አደባባይ የሚወጡበት፣ አንድነታቸውን የሚያጠናክሩበት ማኅበራዊ መስተጋብራቸውን ለማጠናከር የሚጠቀሙበት እንደኾነም ተናግረዋል፡፡
በዚህ ዓመትም የአሸንድዬ በዓል ባሕላዊ እሴቱን ጠብቆ “ባሕላዊ ዕሴቶቻችን ለዘላቂ ሰላማችን” በሚል መሪ መልዕክት በድምቀት ለማክበር ዝግጅቱ ቀደም ብሎ መጀመሩን ተናግረዋል፡፡
ባሕሉን በማይዳሰስ ባሕላዊ ቅርስነት በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ከክልሉ ባሕል እና ቱሪዝም ቢሮ ጋር እየተሠራ መኾኑንም አንስተዋል፡፡ #አሚኮ

Comments